ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
Email this page to a friend Printer-friendly   Tuesday, 22 January 2019
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።“
(የማቴዎስ ወንጌል 7:7-8)

rss

Today's verse

የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ

 


መጽሐፈ ኢዮብ 11፥1-13፥28

111 ነዕማታዊውም ሶፋር መለሰ እንዲህም አለ፦
112 በውኑ ለቃል ብዛት መልስ መስጠት አይገባምን?
ወይስ ተናጋሪ ሰው እንደ ጻድቅ ይቈጠራልን?
113 ትምክህትህስ ሰዎችን ዝም ያሰኛቸዋልን?
ብትሳለቅስ የሚያሳፍርህ የለምን?
114 አንተ፦ ትምህርቴ የተጣራ ነው፥
በዓይንህም ፊት ንጹሕ ነኝ ትላለህ።
115 ምነው እግዚአብሔር ቢናገርህ!
በአንተም ላይ ከንፈሩን ቢከፍት!
116 የጥበቡን ምሥጢር ቢገልጥልህ!
ማስተዋሉ ብዙ ነውና።
እግዚአብሔር ለበደልህ ከሚገባው አሳንሶ እንደሚያስከፍልህ እወቅ።
117 የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ልትመረምር ትችላለህን?
ወይስ ሁሉን የሚችል አምላክ ፈጽመህ ልትመረምር ትችላለህን?
118 ከሰማይ ይልቅ ከፍ ይላል፤ ምን ልታደርግ ትችላለህ?
ከሲኦልም ይልቅ ይጠልቃል፤ ምን ልታውቅ ትችላለህ?
119 ርዝመቱ ከምድር ይልቅ ይረዝማል፥
ከባሕርም ይልቅ ይሰፋል።
1110 እርሱ ቢያልፍ፥ ቢዘጋም፥ ጉባኤንም ቢሰበስብ፥
የሚከለክለው ማን ነው?
1111 ምናምንቴዎችን ሰዎች ያውቃልና፥
በደልንም ሲያይ ዝም ብሎ አይመለከትም።
1112 የሜዳ አህያ ግልገል ሰው ሆኖ ቢወለድ፥
ያን ጊዜ ከንቱ ሰው ጥበብን ያገኛል።
1113-14 በእጅህ በደል ቢኖር አርቀው፤
በድንኳንህም ኃጢአት አይኑር፤
አንተ ልብህን ቅን ብታደርግ፥
እጅህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፥
1115 በዚያን ጊዜ በእውነት ፊትህን ያለ ነውር ታነሣለህ፤
ትበረታለህ፥ አትፈራምም።
1116 መከራህንም ትረሳለህ፤
እንዳለፈ ውኃ ታስበዋለህ።“ምሕረትና እውነት ከአንተ አይራቁ፤ በአንገትህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላት ጻፋቸው። በእግዚአብሔርና በሰው ፊትም ሞገስንና መልካም ዝናን ታገኛለህ።“
(መጽሐፈ ምሳሌ 3:3-4)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ The Amharic bible we are using for this website is the version of 1962 [የድሮው ትርጉም]. The Bible Society of Ethiopia is the owner of this bible. The electronic form of this bible was taken from bible.org and converted by iyesus.com from HTML to unicode character (UTF-8) for the purpose of the search functionality. You can find more information about the electronic form here.
Credits: We acknowledge and are grateful to the support we got from our sister Mehret Hailesilassie Woldekidan. She took the time to do the text and punctuation corrections of the entire Amharic bible. We would like to thank her in the name of all users for her dedicated service.
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2019 by iyesus.com
Terms of use | Contact us