ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
Email this page to a friend Printer-friendly   Friday, 18 May 2012
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም።“
(ወደ ሮሜ ሰዎች 11:33)

rss

Today's verse

የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ

 

 1 2 3 4 5 6 7 Next 

መጽሐፈ ኢዮብ 14፥1-17፥16

141 ከሴት የተወለደ ሰው
የሕይወቱ ዘመን ጥቂት ቀን ነው፥ መከራም ይሞላዋል።
142 እንደ አበባ ይወጣል፥ ይረግፋልም
እንደ ጥላም ይሸሻል፥ እርሱም አይጸናም።
143 እንደዚህስ ባለ ሰው ላይ ዓይኖችህን ትከፍታለህን?
ከአንተስ ጋር እኔን ወደ ፍርድ ታገባለህን?
144 ከርኩስ ነገር ንጹሕን ሊያወጣ ማን ይችላል?
አንድ እንኳ የሚችል የለም።
145 የሰው ዕድሜ የተወሰነ ነው፥
የወሩም ቍጥር በአንተ ዘንድ ነው፥
እርሱም ሊተላለፈው የማይችለውን ዳርቻ አደረግህለት።
146 እንደ ምንደኛ ዕድሜው እስኪፈጸም ድረስ
ያርፍ ዘንድ ከእርሱ ጥቂት ዘወር በል።
147 ዛፍ ቢቈረጥ ደግሞ ያቈጠቍጥ ዘንድ፥
ቅርንጫፉም እንዳያልቅ ተስፋ አለው።
148 ሥሩም በምድር ውስጥ ቢያረጅ፥
ግንዱም በመሬት ውስጥ ቢሞት፥
149 ከውኃ ሽታ የተነሣ ያቈጠቍጣል
እንደ አትክልት ቅርንጫፍ ያወጣል።
1410 ሰው ግን ይሞትና ይጋደማል
ሰውም ነፍሱን ይሰጣል፥ እርሱስ ወዴት አለ?
1411 ውኃ ከባሕር ውስጥ ያልቃል
ወንዙም ያንሳል ይደርቅማል።
1412 ሰውም ተኝቶ አይነሣም
ሰማይ እስኪያልፍ ድረስ አይነቃም፥
ከእንቅልፉም አይነሣም።
1413 በሲኦል ውስጥ ምነው በሰወርኸኝ ኖሮ!
ቍጣህ እስኪያልፍ ድረስ በሸሸግኸኝ ኖሮ!
ቀጠሮም አድርገህ ምነው ባሰብኸኝ ኖሮ!
1414 በውኑ ሰው ከሞተ ተመልሶ ሕያው ይሆናልን?
መለወጤ እስኪመጣ ድረስ፥
የሰልፌን ዘመን ሁሉ በትዕግሥት በተጠባበቅሁ ነበር።
1415 በጠራኸኝና በመለስሁልህ ነበር
የእጅህንም ሥራ በተመኘኸው ነበር።

 1 2 3 4 5 6 7 Next 


“በሳቅ ደግሞ ልብ ያዝናል፥ የደስታም ፍጻሜ ልቅሶ ነው።“
(መጽሐፈ ምሳሌ 14:13)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ The Amharic bible we are using for this website is the version of 1962 [የድሮው ትርጉም]. The Bible Society of Ethiopia is the owner of this bible. The electronic form of this bible was taken from bible.org and converted by iyesus.com from HTML to unicode character (UTF-8) for the purpose of the search functionality. You can find more information about the electronic form here. የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2012 by iyesus.com
Terms of use | Contact us