
የመልእክቱ
ጸሐፊ ጳውሎስ መሆኑን
ራሱ መልእክቱ
ይገልጻል (1፣1; 3፣1):: ጳውሎስ
የቆላስይስን
መልእክት በጻፈበት
ጊዜ፣ በ60 ዓ.ም. ገደማ
በሮም እስር ላይ
እያለ ይህን ደብዳቤ
እንደጻፈው ይታመናል
(3፣1 4፣1 6፣20 ሐዋ 28፣30):: ይህ
መልእክት ኤፌሶንን
ጨምሮ ወደ ሌሎች
ከተሞችም እንዲደርስ
የተጻፈ ዘዋሪ ደብዳቤ
ሳይሆን አይቀርም::
ምክንያቱም በጥንታዎ
ብራናዎች ላይ
“በኤፌሶን ላሉት” 1፣1
የሚለው ስንኝ አይገኝም::
ከዚህም በተጨማሪ
ጳውሎስ እንደ ሌሎቹ
መልእክቶች የስዎችን
ስም እየጠራ ሰላምታ
አያቀርብም፣ በዚያች
ቤ/ክ ብቻ ስለሚገኝ
የተለየ ችግር ወይም
ሁኔታ አያነሳም፣
በተጨማሪም ትምህርቱ
ሁሉ ሁሉንም አብያተ
ክርስቲያናት
እንዲመለከት ተደርጎ
የቀረበ ነው:: በዚህ
መልእክት “ቤተ
ክርስቲያን” የሚለው
ቃል የሚያመለክተው
የአጥቢያን ቤ/ክ
ሳይሆን አጠቃላይዋን
ቤ/ክ (universal church) ነው::
ሀ)ሰላምታ
ቁ. 1-3
·
በእግዚአብሔር
ፈቃድ ሐዋርያ መሆን
·
በሰው
ፈቃድ ወይም በቤ/ክ
ፈቃድ ወይም በራስ
ፈቃድ ሳይሆን፣
በእግዚአብሔር ፈቃድ
ብቻ (ገላ 1፣10-17)
·
ሐዋርያ:- በዚህ
ክፍል አላማችን ስለ
ሐዋርያት አገልግሎት
መሉ ጥናት ለማካሄድ
ሳይሆን የሐዋርያን
ምንነት ጳውሎስ
ሊያስተላልፈው ከፈለገው
ሃሳብ ጋር ለማገናዘብ
ነው:: የሐዋርያትን
አገልግሎት በምዕራፍ
4 በይበልጥ
እንመለከታለን::
·
የተላከ
መልእክተኛ ማለት
ነው::
·
ላኪው
የላከው እንጂ በራሱ
ተነሳሽነት የማይሄድ
·
ላኪው
መልእክት አደራ ብሎ
የሰጠው እንጂ የራሱ
መልእክት ያልሆነ
·
ላኪው
የሚያስፈልገውን
ትጥቅ፣ ብቃትና
ስልጣን የሰጠው እንጂ
በቂ ነገር ያልታጠቀ
ወይም በራሱ ወይም
በስዎች ስልጣንና
ትጥቅ የሚሄድ አይደለም
·
ሐዋርያነቱን
ማሳወቁ አብያተ
ክርስቲያናቱ
ሥልጣኑን አውቀው
የሚያስተላልፈውም
መልእክት
ከእግዚአብሔር
እንደሆነ ተረድተው
እንዲታዘዙ
ለማድረግም ነው:: መልእክቱን
ቢቃወሙ ሐዋርያን
ስለሚቃውሙና
ሐዋርያንም መቃወም
ጌታን መቃወም
ስለሆነ::
·
የኢየሱስ
ክርስቶስ ሐዋርያ
·
የክርስቶስ
አገልጋይና መልእተኛ
እንጂ የሰው
አገልጋይና መልእተኛ
ያልሆነ:: ጌታውን
እንጂ ሰውን ደስ
ለማሰኘት ያልቆመ::
·
ቅዱሳንና
ምእመናን
·
ቅዱስ:- በዚህ
ክፍል አላማችን ቅዱስ
የሚለውን ቃል ጠቅላላ
ትርጉም ለማጥናት
ሳይሆን የቃሉን
መሠረታዊ ትርጉም
ለመያዝና አማኞች
በጌታ የተቀደሱ ወይም
ቅዱሳን እንደሆኑ
ለማየት ነው::
·
ከሌሎች
ሁሉ የተለየ (ልዩ)
·
ይሄውም
በክብሩና በግርማው፣
በኃያልነቱና
በታላቅነቱ ወዘተ
በነገር ሁሉ ተመሳሳይ
ወይም ተቀራራቢ
የሌለው እግዚአብሔር
ነው:: ራእይ 4፣8 ኢሳ 6፣3
·
ከእግዚአብሔር
የተነሳ አንዳንድ
ነገሮች ከእርሱ ጋር
ካላቸው የቅርብ
ግንኙነት የተነሳ
ቅዱስ ይባላሉ::
·
ቦታ ዘጸ
3፣5
·
ተራራ
2ጴጥ 1፣18
·
ቤተ
መቅደስ ሐዋ 6፣13 ዕብ
9፣1-3/9፣24-25
·
ኢየሩሳሌም
ከመቅደሱ የተነሳ ማቴ
4፣5/27፣53
·
ወዘተ
·
ንጹህ
መሆንና አለመቆሸሽን
(አለመርከስን)
ያመለክታል 1ጴጥ 1፣15-16
·
በኢየሱስ
ያመኑ ሁሉ
እንደተቀደሱ (ቅዱስን
እንደሆኑ) መጽሐፍ
ቅዱስ ያስተምራል ሮሜ
15፣16 1ቆሮ 1፣30-31/6፣11 2ተሰ 2፣13
ዕብ 10፣10 1ጴጥ 1፣2
·
ምእመናን
·
ምእመናን
ወይም በሌሎች
ትርጉሞች (ለታመኑ/faithful)
የሚለው እነዛኑ
አማኞች ለመጥራት
የተጠቀመበት አባባል
ነው::
·
ጸጋና
ሰላም
·
ጸጋና
ሰላም የሚለው እዚህ
ላይ በተለይ ለሰላምታ
የተጠቀመው እንጂ የጸጋን
መንፈሳዊ ትርጉም ሁሉ
ለማመልከት
አይደለም:: ጳውሎስ
ይህንን ሰላምታ
በሁሉም መልእቶቹ ላይ
ተጠቅሞባቸዋል:: ጸጋ
በግሪኮች ዘንድ የተለመደ
ሰላምታ ሲሆን፣ ሰላም
(shalom) ደግሞ የአይሁዶች
ሰላምታ ነው::
ለ)የመንፈስዊ
በረከቶች አይነት፣
ብዛትና ስፍራ ቁ. 3
ማሳሰቢያ
ለቁርጥ 3:- ይህንን
ስፍራ ስናጠና
አላማችን መጽሐፍ
ቅዱስ ውስጥ
የተጻፉትን በረከቶች
ሁሉ ለመዘርዘር
ሳይሆን በዚህ
በኤፌሶን መልእክት
ላይ የተዘረዘሩትን
መንፈስዊ በረከቶች
ለማየትና፣ ጸሐፊው
ሊያስተላልፍ
የፈለገውን ሃሳብ
በትክክል ለመረዳት
ነው:: እዚህ ክፍል ላይ
ልብ ማለት ያለብን፣
በረከቶቹ በአይነትና
በቦታ የተውሰኑ
መሆናቸውን ነው::
·
የበረከቱ
አይነትና ብዛት
·
መንፈሳዊ
·
መንፈሳዊ
የሚለው የሥጋዊ
ተቃራኒ ነው ወይም
ሥጋዊ ያልሆነ ማለት
ነው::
·
በቀድሞው
ኪዳን ሕግን በመጠበቅ
ከሚገኘው የእስራኤል
በረከት የተለየ ዘዳ
28፣1-6/28፣11
·
ሁሉ (every spiritual
blessing)
·
የቀረ
መንፈሳዊ በረከት
የለም ወይም መንፈሳዊ
በረከቶች በሙሉ ያለ
መቆጠብ (without reservation)
·
የበረከቱ
ቦታ/ስፍራ/ክልል/ወሰን/sphare
·
በሰማያዊ
ስፍራ (heavenly places)
·
የቃሉ
ትርጉም
·
ይህ
ስንኝ በዚህ መልእክት
ውስጥ 5 ጊዜ ተጠቅሷል
1፣3/ 1፣20-21/ 2፣6-7/ 3፣10/ 6፣12:: እነዚህን
ቦታዎች በጥንቃቄ
ስንመረምር
የሚከተሉትን ሃሳቦች
እናገኛለን:-
·
ክርስቶስን
እግዚአብሔር
በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ
እንዳስቀመጠው 1፣20-21
·
እኛንም
እግዚአብሔር
ከክርስቶስ ጋር በሰማያዊ
ስፍራ እንዳስቀመጠን
2፣6-7
·
በመንፈሳዊ
ስፍራ አለቆችና
ስልጣናት እንዳሉ 3፣10
·
በመንፈሳዊ
ስፍራ የክፋት
መንፍሳዊ ሠራዊቶች
እንዳሉ 6፣12
·
ከነዚህ
ጥቅሶች የምንረዳው
እንግዲህ ጳውሎስ
“መንፈሳዊ ስፍራ” ብሎ
የሚናገረው
የማይታየውን አለም
በሙሉ
(የእግዚአብሔርን
ማድሪያንም የክፉ
መናፍስት መኖሪያንም)
ሁሉ መሆኑን ነው::
·
በብሉይ
ኪዳን የሚገኘው ሥጋዊ
በረከት የሚሰጥበት
ቦታ የከነዓን ምድር እንደሆነ
(ዘዳ 28፣11)፣ በዚህ ክፍል
ደግሞ መንፍሳዊ
በረከት የሚገኘው
በሰማያዊ ስፍራ ነው::
·
“እኛ
አገራችን በሰማይ
ነውና...” ፊል 3፣20
·
“...ለእናንተ
በሰማይ መዝገብ
ሰብስቡ...” ማቴ 6፣19-21
·
“...በላይ
ያለውን እሹ፣ በላይ
ያለውን አስቡ...” ቆላ
3፣1-2
·
“...ሕይወታችሁም
በእግዚአብሔር
ከክርስቶስ ጋር
ተሰውሮአልና...” ቆላ
3፣3-4
·
“...በሰማይ
ከተዘጋጀላችሁ ተስፋ
የተነሳ...” ቆላ 1፣3-5
·
“...ይህ
ርስት...ለእናንተ
በሰማይ
ቀርቶላችኋል::” 1ጴጥ
1፣3-5
·
አምላክና
አባት
·
ኢየሱስ
ሙሉ ሰው የሆነው
አምላክነቱን ትቶ ነው
(ፈል 2፣6-8):: እንደ ሙሉ
ሰውነቱ አብ አምላኩ
ነው:: ክርስቶስ ሙሉ
ሰው፣ ሙሉም አምላክ
ነውና::
·
በብሉይ
ኪዳን እውነተኛውን
የሰማይና የምድር
ፈጣሪ አምላክ ከሌሎች
አማልክት ለይቶ
ለመጥራት የአብርሃም
አምላክ ወይም
የእስራኤል አምላክ ወዘተ
ተብሎ እንደሚጠራ
ጳውሎስም
እውነተኛውን አምላክ
ለማመልከት
የተጠቀመበት ነው::
·
ምስጋና
·
የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ
አምላክና አባት ይባረክ
·
እግዚአብሔር
ከታላቅ ፍቅሩ የተነሳ
ምንም ሳያስቀር
በመንፈሳዊ በረከት
ሁሉ ስለባረከን
ጳውሎስ ይህንን ክፍል
ሲጽፍ በምስጋና ልብ
ሆኖ ነው::