ጳውሎስ
“ለተጠራችሁበት
መጠራት እንደሚገባ”
ብሎ የጠቀሰውን ሃሳብ
እንደሚከተሉት
በአራት ዋና ዋና
ክፍሎች ከፍለን
ማጥናት ጀምረናል::
1.
የጥሪው
ምንነት
2.
የመንፈስን
አንድነት ለመጠበቅ
መትጋት
3.
ሰባቱ
የአንድነት መሠረቶች
4.
የእግዚአብሔርን
ልጅ በማመንና በማውቅ
ወደሚገኝ አንድነት
ማደግ
በክፍል 1
ጥናታችን ላይ ቁጥር
አንድንና ሁለትን
የተመለከትን ሲሆን፣ በክፍል
2 እና 3 ጥናታችን ደግሞ
ቁጥር ሶስትን በሙሉና
አራትን ደግሞ እንደሚከተለው
ከፍለን በከፊል
ተመልክተናል::
4.የእግዚአብሔርን
ልጅ በማመንና በማውቅ
ወደሚገኝ አንድነት
ማደግ ቁ. 7-16
በዚህ
በቁጥር 4 ሥር፣
ማለትም በኤፌ 4፣7-16
ባለው ክፍል ውስጥ
ሐዋርያው ጳውሎስ
አገልግሎት ወይም
የአገልግሎት የጸጋ
ሥጦታዎች
በአንድነታችን ወይም
በሕብረታችን ላይ
ያላቸውን ሚና ያብራራል::
ይህንንም ሃሳብ
እንደሚከተሉት
ከፍለን ማጥናት
ጀምረናል:-
ህ)የጸጋ
ስጦታዎች ቁ. 7-10
ለ)የአምስቱ
ስጦታዎች ምንነት ቁ. 11
ሐ)አምስቱ ስጦታዎች የተሰጡበት ዓላማና በአካሉ ላይ የሚያስገኙት ውጤት ቁ. 12-16
በክፍል 2
ጥናታችን ላይ ከላይ
ከተጠቀሱት ውስጥ
ሀ)ን ተመልክተናል::
በክፍል 3 ጥናታችን
ደግሞ ለ)ን በከፊል
የተመለከትን ሲሆን፣
አምስቱ ስጦታዎችም
ውስጥ ባለፈው ጥናታችን
የሐዋርያትን ምንነት
የተመለከትን ሲሆን፣
በዚህ ጥናታችን ደግሞ
የነቢያትን፣
የወንጌላዊያንና
የእረኞችን ምንነት
እናያለን::
ለ)የአምስቱ
ስጦታዎች ምንነት ቁ. 11
·
ሐዋርያት
(ጥናት 13ን ይመልከቱ)
·
ነቢያት:-
የግሪኩ
ቃል ትርጉም one who speaks forth or openly
ወይም a proclaimer of a divine message ማለት
ነው:: ማለትም በግልጽ
የሚናገር ወይም
መለኮታዊ መልእክትን
የሚያውጅ ሰው ማለት
ነው::
·
ነቢያት
በአዲስ ኪዳን
ቤተክርስቲያን
ከሐዋርያት ቀጥሎ
በሁለተኛ ደረጃ
የሚጠቀሱ ናቸው 1ቆሮ
12፣28::
·
የተለያዩ
ሰዎች በአዲስ ኪዳን
ቤተክርስቲያንናት
ነቢያት ተብለው ተጠርተዋል
የሐዋ 13፣1 የሐዋ 15፣32
የሐዋ 21፣10::
·
ነቢያት
ከሌሎች በተለየ ሁኔታ
የሚገለጥላቸውን
ሰማያዊ መልእክት ለሕዝቡ
የሚናገሩና
የሚያስተምሩ ናቸው::
እንደ ሐዋርያት
የክርስቶስ የማዳኑና
የቤተክርስቲያን
ምስጢር በይበልጥ
የተገለጠላቸው ናቸው
ኤፌ 3፣5:: ስለዚህም
እንደ ሐዋርያት
በቤተክርስቲያን
ተከላና ምሥረታ ላይ
ዋና ሠራተኞች ናቸው
ኤፌ 2፣20::
·
ነቢያት
ምንም እንኳን ስለ
ወደፊቱም የሚናገሩ
ቢሆኑም (የሐዋ 11፣27-28
የሐዋ 21፣10) የአዲስ
ኪዳንም ይሁን የብሉይ
ኪዳን ነቢያት
በዋናነት ደረጃ መገለጣቸው
የክርስቶስ የማዳኑ
ሥራ ነው ሉቃ 24፣25-27 ሉቃ
24፣44-46 ኤፌ 3፣5:: ስለዚህም
ነቢያት በመጀመሪያ
ደረጃ የክርስቶስ
ወንጌል አገልጋዮችና
አስተማሪዎች ናቸው ሐዋ
15፣32:: እንዲያውም ሲላስ
ነቢይ ተብሎ የተጠራ
ሰው ቢሆንም፣
ከጳውሎስ ጋር ልክ
እንደ ሐዋርያት
ወንጌልን
ሲያገለግልና
በአብያተ ቤተክርስቲያናት
ተከላ ላይ ሲሳተፍ
ነው የምንመለከተው::
·
ስለዚህ
ነቢያት የትንቢት
ስጦታ ብቻ ካላቸው ሰዎች
ወይም ከትንቢት
ተናጋሪዎች ይለያሉ::
አዲስ ኪዳን ትንቢት
ብቻ የሚናገሩትን
ሰዎች ነቢያት ብሎ
አይጠራቸውም
(የትንቢት ስጦታ ብቻ
የነበራቸውን አራቱ
የፊልጶስ ልጆችና
አጋቦስ እንዴት
እንደተጠሩ ተመልከት
ሐዋ 21፣8-10)::
·
የነቢያት
አዲስ መገለጥ ሁሉ
በቤተክርስቲያን
በመንፈስ ቅዱስ
እርዳታና የሐዋርያት
ትምህርትን መሠረት
በማድረግ ሊፈተን፣
ሊመረመርና ሊለይ (discern
ሊደረግ) ይገባዋል
1ቆሮ 14፣29 1ቆሮ 14፣37-38::
·
ቀደም
ብለን እንዳየነው
በአዲስ ኪዳን፣
የነቢያት ዋና መገለጥ
የክርስቶስ ምስጢር
መገለጥ ስለሆነና፣
በአዲስ ኪዳን
የእግዚአብሔር
መንፈስ በእያንዳንዱ
አማኝ ስለሚኖር፣
የእያንዳንዱን አማኝ
የግል ሕይወትና ኑሮ
መምራት የነቢያት ሥራ
አይደለም::
“በእግዚአብሔር
መንፈስ የሚመሩ ሁሉ
እነዚህ
የእግዚአብሔር ልጆች
ናቸውና::” ሮሜ 8፣14::
ተብሎ ተጽፎአል እንጂ
“በነቢያት የሚመሩ
የእግዚአብሔር ልጆች
ናቸው” ተብሎ
አልተጻፈም:: ስለዚህ
አማኞች ሕይወታቸው
የሚመራው በውስጣቸው
ባለው በእግዚአብሔር
መንፈስ ምስክርነትና
በእግዚአብሔር ቃል
ነው እንጂ በነቢያት
አይደለም ሮሜ 8፣16::
ነቢያትም ቢሆን
ከወንጌል አገልጋይነትና
ከክርስቶስ ምስጢር
አስተማሪነት፣
የእያንዳንዱን ሰው
ኑሮ መሪ ወደ መሆን
እንዳያዘነብሉ
መጠንቀቅ
ይገባቸዋል::
·
ወንጌላውያን
(ወንጌልን ሰባኪዎች):-
በግሪኩ euaggelistes
የሚለው ቃል ቀጥተኛ
ትርጉሙ a messenger of good
(የምሥራች የሚናገር
መልእክተኛ) ማለት
ሲሆን በአዲስ ኪዳን
ለወንጌል ሰባኪዎች
የተሰጠ ስም ነው:: ይህ
ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ
ከዚህ ክፍል ሌላ
በሁለት ሌሎች ክፍሎች
ብቻ የተጠቀሰ ነው
የሐዋ 21፣8 2ጢሞ 4፣5::
በመጽሐፍ ቅዱስ
ወንጌላዊ ተብሎ
የተጠራ ብቸኛ ሰው ፊልጶስ
ስለሆነ (የሐዋ 21፣8)፣
እንደ ሞዴል ወንጌላዊ
የምንወስደው እርሱን
ነው:: በየሐዋ 8፣5-40 ላይ
በተጠቀሰው
አገልግሎቱ የሚከተሉት
ዋና ዋና ነገሮች
ይታያሉ:-
·
ወንጌልን
ላላመኑት መስበክና
ወደ ድነት ማምጣት
የሐዋ 8፣5-13 (አገልግሎታቸው
ያላመኑትን እንጂ
ያመኑትን አይደለም)
·
ወንጌልን
በተዓምራትና በድንቅ
መስበክ የሐዋ 8፣6-7 1ቆሮ
2፣4-5
·
ጌታ
ወዳዘዘው በመዘዋወር
ወንጌልን መስበክ
የሐዋ 8፣40
·
ለብዙ
ሕዝብም ለአንድ ሰውም
በግል ወንጌልን መስበክ
የሐዋ 8፣26-39
·
ቤተክርስቲያንን
የመትከልና የማነጽ
ሥራ አይታይበትም
(ይሄንን ሥራ ለሐዋርያት
ነበር የሚተውላቸው)
የሐዋ 8፣14-17-25
·
እረኞች/ፓስተሮች
(pastors/shepherd):-
የግሪኩ
ቃል poimen ሲሆን፣
ትርጉሙም a shepherd, one who tends herds or flocks
ማለትም መንጋን
የሚያግድ ወይም
የሚጠብቅ እረኛ ማለት
ነው:: ጥሬ ቃሉ አንድ
የከብት ወይም የበግ
እረኛ ለመንጋው
የሚያደርገውን
እንክብካቤ ሁሉ
ያመለክታል:: ይሄውም መመገብን፣ ፊት ፊት በመሄድ መንገዱን እያሳየና እየቀደመ መምራትን፣ የደከመውን ማበርታትን፣ የታመመውን ማከምን፣ የተሰበረውን መጠገንን፣ የባዘነውንና ግራ የተጋባውን መመለስን፣ የጠፋውን መፈለግን፣ ከክፉ ነገርና ከአደጋ መንጋውን መጠበቅንና ለመንጋው ደህንነት የሚደረግን ማንኛውንም አይነት እንክብካቤና የሚከፈልን መስዋዕትን (ነፍስን እስከ መስጠት) ሁሉ የሚያጠቃልል ነው:: ይህ ቃል በአዲስ
ኪዳን በመጀመሪያ ደረጃ
የከብት ወይም የበግ
እረኞች መጠሪያ ሲሆን
(ለምሳሌ ሉቃ 2፣8)፣
ለጌታ ኢየሱስም
መጠሪያነት
አገልግሎአል (ዮሐ
10፣11)::
አሁን
እያጠናን ካለው ከዚህ
ከኤፌ 4፣11 ውጪ፣
እረኛ/ፓስተር ወይም pastor
የሚለው ቃል፣ በቤተክርስቲያን
ላለ አገልጋይ ወይም
አገልግሎት ወይም
የአገልግሎት ጸጋ
በአዲስ ኪዳን አንድም
ሌላ ቦታ አይጠቀስም::
ይህ ቃል
በቤተክርስቲያን እንዳለ
አገልጋይ ወይም
የአገልግሎት ጸጋ
ሲጠቀስ የምናየው
አንድ ጊዜ ብቻ ነው፣
ይሄውም አሁን በምናጠናው
በኤፌ 4፣11 ላይ ብቻ ነው::
ከምናጠው ከዚህ ከኤፌ
4፣11 ውጪ ለቤተክርስቲያን
አገልጋይ መጠሪያነት
አንድም ቦታ በአዲስ
ኪዳን ስላልተጠቀሰና
እረኛ/ፓስተር ወይም pastor
ተብሎም የተጠራ
አንድም አገልጋይ
በአዲስ ኪዳን
ስለሌለ፣
እረኞች/ፓስተሮች
ወይም pastors
በቤተክርስቲያን
የነበራቸውን
አገልግሎት በትክክል
ለመረዳት ከሌሎቹ
ከአራቱ ስጦታዎች ሁሉ
ይልቅ ይከብዳል::
ምክንያቱም አዲስ ኪዳን
በቤተክርስቲያን
ስላሉና
እረኞች/ፓስተሮች
ወይም pastors ስለሚባሉ
አገልጋዮች ከዚህ
ከምናጠናው ክፍል ሌላ
ምንም ነገር
ስለማይናገር ነው:: በአሁኑ
ዘመን ከአምስቱ
ስጦታዎች ውስጥ ይህ
እረኛ/ፓስተር ወይም pastor
የሚለው መጠሪያ በጣም
ከተስፋፉት
የአገልጋይ መጠሪያ
ስሞች አንዱ ሆኖ
ሳለ፣ አዲስ ኪዳን
ግን እረኞች/ፓስተሮች
ወይም pastors ስለሚባሉ
አገልጋዮች አንድ ጊዜ
ብቻ መጥቀሱና ይህም መጠሪያ
በአዲስ ኪዳን
ከአምስቱ ስጦታዎች
ውስጥ ከሁሉ ይልቅ
እጅግ ያልተስፋፋ
መጠሪያ መሆኑ በጣም
ያስገርማል::
ስለዚህ
ይሄው ቃል እንደ ግሥ
ወይም verb
የተጠቀሱባቸውን
ቦታዎች በአዲስ ኪዳን
መመልከቱ፣ ይህንን
አገልግሎት በትንሹም
ቢሆን በትክክል ለመረዳት
ምናልባት ይረዳ
ይሆናል:: በቤተክርስቲያን
ያለ አገልግሎትን
ለመጥቀስ ይህ
እረኛ/ፓስተር ወይም pastor
የሚለው ቃል በግሥ (verb)
መልክ ሁለት ክፍሎች
ላይ በአዲስ ኪዳን
ተጠቅሶ እንገኛለን::
እነዚህም የሚከተሉት
ናቸው:- “በገዛ ደሙ
የዋጃትን
የእግዚአብሔርን
ቤተክርስቲያን ትጠብቁአት
ዘንድ መንፈስ ቅዱስ
እናንተን ጳጳሳት
አድርጎ ለሾመበት ለመንጋው
ሁሉና ለራሳችሁ
ተጠንቀቁ::” የሐዋ 20፣28::
በዚህ ክፍል
“ትጠብቁአት ዘንድ” ተብሎ
የተተረጎመው ቃል
የግሪኩ poimaino
የተባለው ቃል ነው::
ይህም በግሪኩ poimen
ወይም እረኛ/ፓስተር
ለሚለው ስም (noun)፣ ግሡ (verb)
ነው:: ማለትም poimen ወይም
እረኛ የሰውዬው
መጠሪያ ስም ሲሆን፣ poimaino
ወይም “መጠበቅ” ወይም
ማገድ ደግሞ የእረኛ
ሥራውና ተግባሩ ነው::
ስለዚህ ይህ
“ትጠብቁአት ዘንድ” ተብሎ
በአማርኛ
የተተረጎመው ቃል ቀጥተኛ
ትርጉሙ to act as a shepherd, to shepherd, to pastor
ወይም እንደ እረኛ
መሆን ወይም የእረኛን
ሥራ መሥራት ማለት
ነው:: ስለዚህም የAmplified
መጽሐፍ ቅዱስ ይህን
ክፍል እንደሚከተለው
ይተረጉመዋል:- “Take care and be on guard
for yourselves and the whole flock over which the Holy Spirit has
appointed you
bishops and guardians, to shepherd (tend and feed and guide)
the church
of the Lord or of God which He obtained for Himself [buying it and
saving it
for Himself] with His own blood. ስለዚህ
በዚህ ክፍል ጳውሎስ
የሚናገረው ስለ
እረኝነት ሥራ ነው::
በዚህ ክፍል
እረኝነትን
የሚያመለክተው ሌላው
ቃል “ለመንጋው
ሁሉና ለራሳችሁ
ተጠንቀቁ” የሚለው
ስንኝ ነው:: ስለ
እረኝነት ሥራ ስለሆነ
የሚናገረው
የእግዚአብሔር ሕዝብ
መንጋ ብሎ ይጠራዋል::
ይህም በዚህ ክፍል
ጳውሎስ የሚናገረው
ስለ እረኞች ሥራ
መሆኑን በተጨማሪ
ያረጋግጣል:: በዚህ
ክፍል የእረኞችን ሥራ
እንዲሠሩና መንጋውን
እንዲጠብቁ ወይም
ለመንጋው እንደ
እረኞች እንዲሆኑለት
የተነገራቸው፣ በየሐዋ
20፣17 ላይ
እንደተጠቀሰው
የቤተክርስቲያን
ሽማግሌዎችን ነው::
ይህ
እረኛ/ፓስተር ወይም pastor
የሚለው ቃል በግሥ (verb)
መልክ የተጠቀሰበት
ሌላው ክፍል 1ጴጥ 5 ላይ
ነው:: “እንግዲህ እኔ፣
ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ
የክርስቶስም መከራ
ምስክር ደግሞም
ሊገለጥ ካለው ክብር
ተካፋይ የሆንሁ፣
በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች
እመክራቸዋለሁ፣
በእናንተ ዘንድ
ያለውን የእግዚአብሔርን
መንጋ ጠብቁ፣ እንደ
እግዚአብሔር ፈቃድ
በውድ እንጂ በግድ
ሳይሆን፣ በበጎ ፈቃድ
እንጂ መጥፎውን ረብ
በመመኘት ሳይሆን
ጎብኙት፣ ለመንጋው
ምሳሌ ሁኑ እንጂ
ማኅበሮቻችሁን
በኃይል አትግዙ፣ የእረኞችም
አለቃ በሚገለጥበት
ጊዜ የማያልፈውን
የክብርን አክሊል
ትቀበላላቸሁ::” 1ጴጥ
5፣1-4:: በዚህም ክፍል
ጴጥሮስ መልእክቱን
የሚያስተላልፈው
ለቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች
ነው:: “በመካከላቸው
ያሉትን ሽማግሌዎች
እመክራቸዋለሁ”
ይላልና::
በመጀመሪያውም ክፍል
እንዳየነው፣ በዚህም ክፍል
የእግዚአብሔርን
ሕዝብ እንደ መንጋ
ነው የሚጠራው
“በእናንተ ዘንድ
ያለውን የእግዚአብሔርን
መንጋ ጠብቁ” ይላል::
ልክ እንደ ባለፈው ክፍል፣
በዚህም ክፍል “ጠብቁ”
የሚለው ቃል በግሪኩ poimaino
የሚባለው ቃል ነው::
ይህም በግሪኩ poimen
ወይም እረኛ/ፓስተር
ለሚለው ስም (noun)፣ ግሡ (verb)
እንደሆነና
የእረኞችን ሥራ
የሚያመለክት
እንደሆነ
ተመልክተናል::
ካለፈው ክፍል
በተጨማሪ በዚህ ክፍል
ስለ እረኞች አለቃም
ተጠቅሷል “የእረኞችም
አለቃ በሚገለጥበት
ጊዜ የማያልፈውን
የክብርን አክሊል
ትቀበላላቸሁ” ይላል::
ጴጥሮስ እንግዲህ ስለ
እረኝነትና መንጋን
ስለመጠበቅ ገልጾ፣
እንደገና ደግሞ የእረኞች
አለቃን አያይዞ በዚህ
ክፍል መጥቀሱ፣
ሽማግሌዎች
የእረኝነትን ሥራ
እንዲሠሩ
እያበረታታቸውና
እየመከራቸው
እንደሆነ እንገነዘባለን::
ከላይ
ካየናቸው ከሁለቱ
ክፍሎች እንግዲህ
የምንረዳው፣
እረኝነት ወይም
ፓስተርነት
ሽማግሌዎች
ሊከናውኑት የሚገባ
ዋና ሥራቸው እንደሆነ
ነው:: ስለዚህም ደግሞ
ሽማግሌዎች
የእረኝነት ወይም
የፓስተርነት ጸጋ
ሊኖራቸውም ይገባል
ማለት ነው:: እረኝነት
የአገልግሎት ጸጋ
ነው:: የእረኝነት ጸጋ
የሌለው ሰው ሽማግሌ
ሆኖ ስለተሾመ ብቻ
የእረኝነትን ሥራ
መሥራት አይችልም::
በተቃራኒው ደግሞ፣
የእረኝነት ጸጋ ያለው
ነገር ግን ሽማግሌ
ሆኖ ያልተሾመ ሰውም
መንጋውን
ከመንከባከብና
ለመንጋው ከማሰብ ወደ
ኋላ አይልም:: ስለዚህ ሽምግልና የእረኝነት ጸጋ ላለቸው እረኞች/ፓስተሮች የሚሰጥ እውቅና
ሳይሆን
አይቀርም:: እንደ
ሌሎቹ አራቱ ስጦታዎች
ሁሉ የእረኝነትንም
ጸጋ አስታጥቆ እረኛ/ፓስተር
የሚያደርግ ጌታ
ኢየሱስ ብቻ ነው::
እረኝነት ወይም
ፓስተርነት በቤተክርስቲያን
ያለ office አይደለምና::
ጌታ እረኞች
ያደረጋቸውና ይህንን ጸጋ
ያስታጠቃቸው ሰዎች
በቤተክርስቲያን የሚሰጣቸው እውቅና ሽምግልና
ሳይሆን አይቀርም::
ከዚህ ውጪ
ግን፣ በአሁኑ ዘመን
በብዛት እንደሚታየው፣
ከተወሰነ የምእመናን
ቁጥር በኋላ
በእያንዳንዱ አብያተ
ክርስቲያን ላይ፣
ከሽማግሌዎች ሌላ፣
የበላይ የሆነ የሹመት
ወይም የፓስተርነት
ቦታ የሚባል ነገር
በመጽሐፍ ቅዱስ
አንድም ቦታ
አይገኝም:: በየአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የምንመለከተው የቤተክርስቲያን አመራር
በብዙ
ቁጥር የሆነ
ሽምግልና ብቻ ነው
የሐዋ 14፣23:: በአሁኑ
ዘመን በብዛት
የሚሠራበት የፓስተርነት
አሠራርና (system) ታሪካዊ
እንጂ መጽሐፍ ቅዱሳዊ
መሠረት የለውም:: ብዙ
ጊዜም ለዚህ አሠራር
እንደ ምሳሌነት የሚጠቀሱት
ጢሞቴዎስና ቲቶም፣
ከሐዋርያው ጳውሎስ
ጋር የሐዋርያትን ሥራ
ማለትም ወንጌልን
መስበክንና
ቤተክርስቲያንን
የማደረጃት ሥራን በብዙ
ቦታዎች እየተዘዋወሩ
የሠሩ እንጂ በአንድ
ቤተክርስቲያን
ፓስተር ሆነው የተሾሙ
እንዳልሆኑ፣ መጽሐፍ
ቅዱስን በጥንቃቄ
ስናጠና እናገኛለን::
ከዚህም በተጨማሪ እነዚህ
አገልጋዮች በመጽሐፍ
ቅዱስ አንድም ቦታ
ፓስተር የሚል ስያሜ
ሲሰጣቸው
አንመለከትም:: ነገር
ግን በተለያዩ ቦታዎች
ወንጌልን በመስበክና
አብያተ
ቤተክርስቲያናት
ራሳቸውን እንዲችሉ
በማደራጀት ሥራ
ለተወሰነ ጉዳይ
በጳውሎስ እየተላኩና
እየተዘዋወሩ
የሚያገለግሉ ነበሩ
2ቆሮ 1፣19 1ጢሞ 1፣3-4 ቲቶ 1፣5
1ተስ 3፣2 ፊልጵ 2፣19-24 1ቆሮ
16፣10::