
ማሳሰቢያ:-
በዚህ ክፍል ውስጥ
ለማየት
የምንሞክረው፣
በጥናታችን ክፍል
ውስጥ
የተጠቀሱትን
ስብዕት/persons እና
መንፈሳዊ በረከቶቹ
ወደ እኛ እንዲደርሱ
እነርሱ ያበረከቱትን
የሥራ ድርሻ ነው::
ይሄም ማለት ለማየት
የምንሞክረው በዚህ
በጥናታችን ክፍል
ውስጥ የተዘረዘሩትን
ሥራዎቻቸውን እንጂ፣
በመጽሐፍ ቅዱስ ሁሉ
የተጠቀሱትን
አይደለም::
በዚህ
በጥናታችን ክፍል
ውስጥ 4 አይነት
ስብዕት/persons እና
ለመንፈሳዊ በረከቶቹም
እውን መሆን፣ እነዚህ
ስብዕት/persons ያበረከቱት
ሥራ ተገልጾአል:-
1.
አብ
·
ሀ)የአብ
የሥራ ድርሻ
1.
መንፈሳዊ
በረከቶቹ ሁሉ ከእርሱ
ነው የመጡት ወይም
የመንፈሳዊ በረከቶቹ
ሁሉ ምንጭና ባራኪ
አብ ነው::
·
“...በመንፈሳዊ
በረከት ሁሉ
የባረከን የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ
አምላክና አባት
ይባረክ::” ኤፌ 1፣3
·
“...በክርስቶስ
መረጠን::” ኤፌ 1፣4
·
“...ለእርሱ
ልጆች ልንሆን
አስቀድሞ ወሰነን::”
ኤፌ 1፣5
·
“ጸጋውንም
በጥበብና በአእምሮ
ሁሉ አበዛልን::” ኤፌ 1፣8
·
“...የፈቃዱን
ምሥጢር
አስታውቆናልና...” ኤፌ
1፣9
2.
በክርስቶስ
ለተሠሩት ሥራዎች ሁሉ
እቅድና ፕላን አውጪ
አብ ነው:: የተጠቀሱትም
መንፈሳዊ በረከቶች
ሁሉ እውን የሆኑት
እንደ እርሱ አሳብና
ፈቃድ ነው::
·
“በክርስቶስ
ለማድረግ እንደወደደ
እንደ አሳቡ...” ኤፌ 1፣9
·
“...በዘመን
ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ
ያለው አሳቡም...” ኤፌ
1፣10
·
“እንደ
ፈቃዱ ምክር ሁሉን
የሚሠራ እንደ እርሱ
አሳብ...” ኤፌ 1፣11
·
ለ)አብ
ከላይ የተጠቀሱትን
ሥራዎች
እንዲያከናውን
ያነሳሳው ነገር (motive)
1.
ፍቅር
ኤፌ 1፣4:: በድሮው
የአማርኛ የመጽሐፍ
ቅዱስ ትርጉም
“በፍቅር” የሚለው ቃል
እኛ በፍቅር
እንድንሆን የሚለውን
ትርጉም የሚይዝ
ቢያስመስልም፣
በኦርጂናሉ መጽሐፍ
ቅዱስ ላይ ግን ይህ
ቃል የአብን ፍቅር
የሚያሳይ ነው::
ስለዚህም በአዲሱ
መደበኛ ትርጉም በቁጥር
4-5 ላይ አብ በፍቅር
እንደወሰነን ግልጽ
ያደርገዋል::
“...በፍቅር፣ በኢየሱስ
ክርስቶስ ልጆቹ
እንሆን ዘንድ፣ እንደ
በጎ ፈቃዱ አስቀድሞ
ወሰነን”:: ስለዚህ
እግዚአብሔር
በመንፈሳዊ በረከቶች
ሁሉ እንዲባርከን
ያነሳሳው ዋና ነገር
ፍቅር ነው::
2.
ይህን
ለማድረግ የአብ በጎ
ፈቃድ ስለሆነ ወይም
ይህንን ለማድረግ
ስለወደደ
·
“በበጎ
ፈቃዱ እንደወደደ...”
ኤፌ 1፣5
·
“በክርስቶስም
ለማድረግ
እንደወደደ...” ኤፌ 1፣9
·
“እንደ
ፈቃዱ ምክር ሁሉን
የሚሠራ እንደ እርሱ
አሳብ...” ኤፌ 1፣11
·
ሐ)አብ
መንፈሳዊ በረከቶቹን
የባረከበት ሁኔታ
·
ከእኛ
በጎ ሥራ ወይም
መልካምነት ሳይሆን
ከጸጋው ብዛት ነው
·
“ዓለም
ሳይፈጠር...” ኤፌ 1፣4
·
“...አስቀድሞ
ወሰነን::” ኤፌ 1፣5
·
“...እንዲያው
የሰጠን የጸጋው
ክብር...” ኤፌ 1፣6
·
“...እንደ
ጸጋው ባለጠግነት
መጠን...” ኤፌ 1፣7
·
“ጸጋውንም
... አበዛልን::” ኤፌ 1፣8
·
መ)አብ
መንፈሳዊ በረከቶቹን
ሁሉ የባረከበት
ምክንያት
·
“...እንዲያው
የሰጠን የጸጋው ክብር
ይመሰገን ዘንድ ይህን
አደረገ::” ኤፌ 1፣6
·
በዚህ
ክፍል ክብር የሚለው
ጥሬ ቃል ትርጉሙ:-
በሌሎች ዘንድ
መመስገንን፣
መከበርን፣
መወደስን፣
መሞገስን፣ መደነቅን
ወዘተ የሚያነሳሳ
ማናቸውም መልካም
ነገር ወይም የተለየ
ነገር ወዘተ ነው::
·
ጸጋው
የሚያድን ወይም
የሚምር መሆኑ ራሱ
አንዱ የጸጋው ክብር
ነው:: ጸጋው ግን
ከምህረትና ከይቅርታ
ያለፈ የተትረፈረፈ፣
የልጅነት ስልጣን የሚሰጥ፣
ርስትን የሚያወርስ፣
ጥበብንና ማስተዋልን
የሚሰጥ ወዘተ ነው::
እነዚም ነገሮች
የጸጋው ክብር ናቸው::
·
“...እኛ
ለክብሩ ምስጋና
እንሆን ዘንድ ነው::”
ኤፌ 1፣12
·
እዚህ ላይ
የተጠቀሰውን አባባል
በተለያየ ሁኔታ
ልንረዳው
እንችላለን:: በተለይ
ግን በእኛ በሠራው
ሥራ እግዚአብሔር
በእኛም፣
በመላእክትም በፍጥረትም
ሁሉ ክብሩ
እንዲመሰገን ነው::
ይሄም እኛ ራሳችን
የምስጋና ምክንያት
እንድንሆን:: ራእይ 5፣8-14
·
“...ይህም
ለክብሩ ምስጋና
ይሆናል::” ኤፌ 1፣14
·
እግዚአብሔር
በሠራው ሥራ ፍጥረት
ሁሉ የእርሱን ጸጋ፣
መልካምነት፣ ምሕረት
ወዘተ ወይም ክብር
እንዲያመሰግኑ ነው::
ማጠቃለያ:-
አብ የመንፈሳዊ
በረከቶች ሁሉ ምንጭ
እንዲሁም እቅድ አውጪ
ነው:: ይህንን ሁሉ
ያደረገውም ከፍቅሩና
ከበጎ ፈቃዱ የተነሳ
ነው:: በጎነቱ
ስላነሳሳው፣ ጸጋው
ብዙ ስለሆነ እንጂ
ከእኛ ማንነትና
መልካምነት አይደለም::
ስለዚህም እንዲያው
ባደረገው ሥራ ሁሉ
ክብሩንና ምስጋናውን ሊወስድ
የሚገባው እርሱ ነው::
2.
ክርስቶስ/ወልድ
·
ሀ)መንፈሳዊ
በረከቶች ሁሉ
(በዚህ ክፍል
የተጠቀሱት ስድስቱም በረከቶች
በሙሉ) የተባረክነው
በክርስቶስ
(በክርስቶስ ውስጥ፣
በክርስቶስ
አማካኝነት፣
በክርስቶስ ሥራ፣
በክርስቶስ በኩል
ወዘተ) ነው::
·
“በክርስቶስ
በሰማያዊ ስፍራ
በመንፈሳዊ በረከት
ሁሉ የባረከን...” ኤፌ 1፣3
·
“...በክርስቶስ
መረጠን::” ኤፌ 1፣4
·
“...በኢየሱስ
ክርስቶስ...ለእርሱ
ልጆች ልንሆን
አስቀድሞ ወሰነን::”
ኤፌ 1፣5
·
“በውድ
ልጁም እንዲያው
የሰጠን ጸጋ...” ኤፌ 1፣6
·
“በውድ
ልጁም...በደሙ
የተደረገ
ቤዛነታችንን አገኘን
እርሱም የበደላችን
ስርየት::” ኤፌ 1፣7
·
“...በክርስቶስ
ደግሞ ርስትን
ተቀበልን::” ኤፌ 1፣11
·
“...በክርስቶስ
አምናችሁ፣ በተስፋው
መንፈስ በመንፈስ
ቅዱስ ታተማችሁ...” ኤፌ
1፣13
·
ለ)ክርስቶስ
የእግዚአብሔር
ዘላለማዊ እቅድና
ፕላን መፈጸሚያ ነው::
·
“በዘመን
ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ
ያለው አሳቡም፣
በሰማይና በምድር
ያለውን ሁሉ
በክርስቶስ
ለመጠቅለል ነው::” ኤፌ
1፣10
ማጠቃለያ:-
ይህ በክርስቶስ ወይም
በልጁ ወዘተ የሚለው
ቃል ከ10 ጊዜ በላይ በዚህ
ክፍል ውስጥ
ተጠቅሷል:: በዚህም፣
ምንም አይነት
የእግዚአብሔር በረከት
ከክርስቶስ ውጪ
እንደሌለ ጸሐፊው
ለማሳየት እንደፈለገ
እንገነዘባለን::
እውነተኛው የወይን
ግንድ ክርስቶስ ነውና
(ዮሐ 15፣1-11):: በረከቱ ወደ
ሰዎች እንዲመጣ ዋናው
ቅድመ ሁኔታ
የክርስቶስ የመስቀሉ
ሥራ ነው:: እግዚአብሔር
የአለምን ሩጫና
የዘላለም ሃሳቡን
የሚቋጨው በክርስቶስ
ነው:: ይሄውም ሁሉም
ከክርስቶስ ራስነት
ስር ሲገዙ:: በዚህ ሁሉ
ልንረዳ የሚገባን፣ አብ
ለሰው ልጆች
መፍትሔንና በረከትን
ለማምጣት ያቀደውንና
ያሰበውን ሁሉ
የፈጸመው በክርስቶስ
ነው:: እግዚአብሔር
ጥንትም ቢሆን፣
አለማትንና
ፍጥረታትን ለመፍጠር
ሲያቅድ ይህን እቅዱን
የፈጸመው ወይም
ተግባራዊ ያደረገው
በክርስቶስ ነበር
(ዮሐ 1፣1-2 ዕብ 1፣1-2 ቆላ
1፣13-17):: ስለዚህ
ክርስቶስ ማናቸውንም
እቅዱን የሚፈጽምበት
የእግዚአብሔር
ጥበብና ዘዴ ነው::
ለዚህም ነው
የእስራኤል ልጆች
በበረሃ ጉዞአቸው
በገጠማቸው ማናቸውም
ችግር እንደ
መፍትሄነት
እግዚአብሔር የሚያመለክታቸው
የነበረው ክርስቶስን
ነበር (ዮሐ 3፣14-15 1ቆሮ 10፣4
ዮሐ 6፣31-35)::
3.
መንፈስ
ቅዱስ
እግዚአብሔር
ለእኛ ርስት
እንዳዘጋጀልን
የሚያረጋግጥ፣
የሚመሰክርና
በረከቱን በሕይወታችን
እውን እንዲሆን ወይም
ለእኛ ሕይወት ትርጉም
እንዲሰጥ ከሕይወታችን
ጋር የሚያዛምድ ነው::
በዚህም ለእኛ ተስፋ
የሚሰጠን ነው::
·
“...በተስፋው
መንፈስ በመንፈስ
ቅዱስ ታተማችሁ፣
እርሱም የርስታችን መያዣ
ነው...” ኤፌ 1፣13-14
·
“የእግዚአብሔር
ልጆች መሆናችንን ያ
መንፈስ ራሱ
ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል::”
ሮሜ 8፣16
ማጠቃለያ:-
ያለ መንፈስ ቅዱስ
ሥራ አብ በክርስቶስ
የሠራው ሥራ ከእኛ
ጋር አይዛመድም 1ቆሮ
12፣3:: የእግዚአብሔር
ሥራ ከሕይወታችን ጋር
ተዋሕዶ ለእኛ ትርጉም
እንዲኖረው
የሚያደርገው መንፈስ
ቅዱስ ነው:: እርሱ ነው
እግዚአብሔር
የሠራልንንና
ሊያደርግልን
ያሰበውን ሥራ
በሕይወታችን እውን
በማድረግ እውነተኛ
ተስፋ የሚሰጠን:: ያለ
እርሱ እግዚአብሔር ያደረገልን
ነገር ሁሉ ለእኛ
ምንም ትርጉም
አይሰጠንም::
4.
አማኞች
እግዚአብሔር
የባረከን በረከት ወደ
አማኞች እንዲመጣ
የአማኞች ድርሻ፣
በክርስቶስ ማመን
ወይም በእርሱ ተስፋ
ማድረግ በቻ ነው::
·
“...በክርስቶስ...ተስፋ
ያደረግን እኛ...” ኤፌ
1፣12
·
“እናንተም
ደግሞ የእውነትን
ቃል፣ ይኸውም
የመዳናችሁን
ወንጌል፣ ሰምታችሁ
ደግሞም በክርስቶስ
አምናችሁ...” ኤፌ 1፣13
እዚህ
ላይ ልብ ልንል
የሚገባው የአማኞች
ዋና ድርሻ በክርስቶስ
ማመን ነው:: እምነት
ደግሞ ሥራ አይደለም
ሮሜ 4፣1-5:: ይህ
የጥናታችን ክፍል
እንግዲህ በሥራና
በእምነት ወይም
በሠራተኞችና
በአማኞች የተከፈለ ነው::
መንፈሳዊ በረከቶቹ
ሁሉ ወደ እኛ
እንዲደርሱ
የሚያስፈልጉትን ሥራዎች
ሁሉ አብ፣ ወልድና
መንፈስ ቅዱስ
ተከፋፍለውት
እንመለከታለን:: ለአማኞች
የቀረላቸው ድርሻ
ቢኖር ሥራ ሳይሆን
በክርስቶስ ላይ ያለ
እምነት ነው:: ስለዚህ
ጸሐፊው ደጋግሞ አብ
ከበጎ ፈቃዱ፣
ከፍቅሩና ከማንነቱ የተነሳ
ለክብሩ በክርስቶስ
እንደባረከን በሰፊው
ሲገልጽ የአማኞችን
ድርሻ ግን በእምነት
ላይ ብቻ ወስኖታል::
ይህም መንፈሳዊ በረከቶችን
የተባረክነው ከእኛ
ማንነትና ከመልካም
ሥራችን ሳይሆን ከእግዚአብሔር
ማንነትና ጸጋ የተነሳ
መሆኑን
ያስገነዝበናል::
አማኝ ሁሉ ከሁሉም
በፊት በእግዚአብሔር
ሥራ ላይ ማረፍ
አለበት::
እግዚአብሔር ያለ እኛ
ሥራና ያለ እኛ
ማንነት
እንደተቀበለንና
እንደወደደን አምነን
በእርሱ መልካምነት
ላይ ልንደገፍ
ይገባናል::
እግዚአብሔር እንዲቀበለን
ከክርስቶስ መስዋዕት
ሌላ ተጨማሪ
መሥዋዕት፣
እግዚአብሔር ራሱ
ከምህረቱ ከሠራልን
ሥራ ሌላ ተጨማሪ
የእኛ ሥራ
አያስፈልግም:: በጌታ
ከምንሮጠው
ከማናቸውም ሩጫ በፊት
ይህ ለሕይወታችን
መሠረት ሊሆን ይገባል::
ክርስትና ከማረፍ፣
ከመወደድ እንዲሁም
ከበረከት ነው የሚጀምረው::