| መዝሙረ ዳዊት 119 |
| 61 | የኃጥኣን ገመዶች ተተበተቡብኝ ሕግህን ግን አልረሳሁም። |
| 62 | ስለ ጽድቅህ ፍርድ፥ በእኩለ ሌሊት አመሰግንህ ዘንድ እነሣለሁ። |
| 63 | እኔ ለሚፈሩህ ሁሉ፥ ትእዛዝህንም ለሚጠብቁ ባልንጀራ ነኝ። |
| 64 | አቤቱ፥ ምሕረትህ በምድር ሁሉ ሞላች ሥርዓትህን አስተምረኝ። |
| 65 | አቤቱ፥ እንደ ቃልህ ለባሪያህ መልካም አደረግህ። |
| 66 | በትእዛዛትህ ታምኛለሁና መልካም ምክርና እውቀትን አስተምረኝ። |
| 67 | እኔ ሳልጨነቅ ሳትሁ አሁን ግን ቃልህን ጠበቅሁ። |
| 68 | አቤቱ፥ አንተ ቸር ነህ፥ በቸርነትህም ሥርዓትህን አስተምረኝ። |
| 69 | የትዕቢተኞች ዓመፅ በላዬ በዛ እኔ ግን በፍጹም ልቤ ትእዛዛትህን እፈልጋለሁ። |
| 70 | ልባቸው እንደ ወተት ረጋ እኔ ግን በሕግህ ደስ ይለኛል። |
| 71 | ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ። |
| 72 | ከአእላፋት ወርቅና ብር ይልቅ የአፍህ ሕግ ይሻለኛል። |
| 73 | እጆችህ ሠሩኝ አበጃጁኝም እንዳስተውል አድርገኝ፥ ትእዛዛትህንም እማራለሁ። |
| 74 | በቃልህ ታምኛለሁና የሚፈሩህ እኔን አይተው ደስ ይላቸዋል። |
| 75 | አቤቱ፥ ፍርድህ ጽድቅ እንደ ሆነች፥ በእውነትህም እንዳስቸገርኸኝ አወቅሁ። |