ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » መጽሐፍ ቅዱስ
Email this page to a friend Printer-friendly   Friday, 18 May 2012
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም።“
(ወደ ሮሜ ሰዎች 11:33)

rss

Today's verse

መጽሐፍ ቅዱስ

 


መዝሙረ ዳዊት  143
ልጁ ባሳደደው ጊዜ የዳዊት መዝሙር።
1 አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ በእውነትህ ልመናዬን አድምጥ፥ በጽድቅህም መልስልኝ።
2 ሕያው ሁሉ በፊትህ ጻድቅ አይደለምና ከባሪያህ ጋር ወደ ፍርድ አትግባ።
3 ጠላትህ ነፍሴን አሳድዶአታል፥ ሕይወቴንም በምድር ውስጥ አጐስቍሎአታል ቀድሞ እንደ ሞተ ሰው በጨለማ አኑሮኛል።
4 ነፍሴ በውስጤ አለቀችብኝ፥ ልቤም በውስጤ ደነገጠብኝ።
5 የቀድሞውን ዘመን አሰብሁ፥ ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ የእጅህንም ሥራ ተመለከትሁ።
6 እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች።
7 አቤቱ፥ ፈጥነህ ስማኝ ነፍሴ አልቃለች ፊትህን ከኔ አትመልስ፥ ወደ ጕድጓድም እንደሚወርዱ አልሁን።
8 አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አስታውቀኝ።
9 አቤቱ፥ ወደ አንተ ተማፅኛለሁና ከጠላቶቼ አድነኝ።
10 አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን ለማድረግ አስተምረኝ ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ።
11 አቤቱ፥ ስለ ስምህ ሕያው አድርገኝ በጽድቅህም ነፍሴን ከመከራዋ አውጣት።
12 በምሕረትህ ጠላቶቼን ደምስሳቸው፥ እኔ ባሪያህ ነኝና ነፍሴን የሚያስጨንቁአትን ሁሉ አጥፋቸው።



“በሳቅ ደግሞ ልብ ያዝናል፥ የደስታም ፍጻሜ ልቅሶ ነው።“
(መጽሐፈ ምሳሌ 14:13)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ The Amharic bible we are using for this website is the version of 1962 [የድሮው ትርጉም]. The Bible Society of Ethiopia is the owner of this bible. The electronic form of this bible was taken from bible.org and converted by iyesus.com from HTML to unicode character (UTF-8) for the purpose of the search functionality. You can find more information about the electronic form here. የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2012 by iyesus.com
Terms of use | Contact us