| መጽሐፈ ምሳሌ 11 |
| 16 | ሞገስ ያላት ሴት ክብርን ታገኛለች፥ ሀኬተኖችም ሀብትን ያገኛሉ። |
| 17 | ቸር ሰው ለራሱ መልካም ያደርጋል ጨካኝ ግን ሥጋውን ይጐዳል። |
| 18 | የኀጥእ ሰው ሞያ ሐሰተኛ ነው ጽድቅን የሚዘራ ግን የታመነ ዋጋ አለው። |
| 19 | በጽድቅ የሚጸና በሕይወት ይኖራል ክፋትን የሚከተል ግን ለሞቱ ነው። |
| 20 | ልበ ጠማሞች በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊዎች ናቸው በመንገዳቸው ፍጹማን የሆኑ ግን የተወደዱ ናቸው። |
| 21 | ክፉ ሰው እጅ በእጅ ሳይቀጣ አይቀርም የጻድቃን ዘር ግን ይድናል። |
| 22 | የወርቅ ቀለበት በእርያ አፍንጫ እንደ ሆነ፥ ከጥበብ የተለየች ቆንጆ ሴትም እንዲሁ ናት። |
| 23 | የጻድቃን ምኞት በጎ ብቻ ነው የኀጥኣን ተስፋ ግን መቅሠፍት ነው። |
| 24 | ያለውን የሚበትን ሰው አለ፥ ይጨመርለታልም ያለ ቅጥ የሚነፍግ ሰውም አለ፥ ይደኸያልም። |
| 25 | የምትባረክ ነፍስ ትጠግባለች፥ የረካም እርሱ ደግሞ ይረካል። |
| 26 | እህልን የሚያስቀር ሰው በሕዝብ ዘንድ ይረገማል በረከት ግን በሚሸጠው ራስ ላይ ነው። |
| 27 | መልካምን ተግቶ የሚሻ ደስታን ይፈልጋል ክፉን በሚፈልግ ግን ክፉ ይመጣበታል። |
| 28 | በባለጠግነቱ የሚተማመን ሰው ይወድቃል ጻድቃን ግን እንደ ቅጠል ይለመልማሉ። |
| 29 | ቤቱን የሚያውክ ሰው ነፋስን ይወርሳል፥ ሰነፍም ለጠቢብ ተገዥ ይሆናል። |
| 30 | የጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ናት፥ ነፍሶችንም የሚሰበስብ እርሱ ጠቢብ ነው። |