| መጽሐፈ ምሳሌ 14 |
| 1 | ብልሃተኛ ሴት ቤትዋን ትሠራለች ሰነፍ ሴት ግን በእጅዋ ታፈርሰዋለች። |
| 2 | በቅን የሚሄድ ሰው እግዚአብሔርን ይፈራል መንገዱን የሚያጣምም ግን ይንቀዋል። |
| 3 | በሰነፍ አፍ የትዕቢት በትር አለ የጠቢባን ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች። |
| 4 | በሬ በሌለበት ስፍራ እህል አይገኝም ብዙ ሲሳይ ግን በበሬዎች ኃይል ነው። |
| 5 | የታመነ ምስክር አይዋሽም የሐሰት ምስክር ግን በሐሰት ይናገራል። |
| 6 | ፌዘኛ ሰው ጥበብን ይፈልጋል አያገኛትም ለአስተዋይ ግን እውቀትን ማግኘት አያስቸግረውም። |
| 7 | ከሰነፍ ሰው ፊት ራቅ፥ በእርሱ ዘንድ የእውቀትን ከንፈር አታገኝምና። |
| 8 | የብልህ ሰው ጥበብ መንገዱን ያስተውል ዘንድ ነው የሰነፎች ስንፍና ግን ሽንገላ ነው። |
| 9 | ሰነፉ በኃጢአት ያፌዛል በቅኖች መካከል ግን ቸርነት አለች። |
| 10 | የራሱን ኀዘን ልብ ያውቃል ከደስታውም ጋር ሌላ ሰው አይገናኝም። |
| 11 | የኅጥኣን ቤት ይፈርሳል የቅኖች ማደሪያ ግን ያብባል። |
| 12 | ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች ፍጻሜዋ ግን የሞት መንገድ ነው። |
| 13 | በሳቅ ደግሞ ልብ ያዝናል፥ የደስታም ፍጻሜ ልቅሶ ነው። |
| 14 | ልቡን ከጽድቅ የሚመልስ ሰው ከመንገዱ ፍሬ ይጠግባል፥ ጻድቅም ሰው ደግሞ በራሱ። |
| 15 | የዋህ ቃልን ሁሉ ያምናል ብልህ ግን አካሄዱን ይመለከታል። |