| ኦሪት ዘጸአት 40 |
| 1 | እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው። |
| 2 | ከመጀመሪያው ወር በፊተኛው ቀን የመገናኛውን ድንኳን ማደሪያ ትተክላለህ። |
| 3 | በእርሱም ውስጥ የምስክሩን ታቦት ታኖራለህ፥ ታቦቱንም በመጋረጃ ትጋርዳለህ። |
| 4 | ገበታውንም አግብተህ በእርሱ ላይ የሚኖረውን ዕቃ ታሰናዳለህ መቅረዙንም አግብተህ ቀንዲሎቹን ትለኵሳለህ። |
| 5 | ለዕጣንም የሚሆነውን የወርቅ መሠዊያ በምስክሩ ታቦት ፊት ታኖራለህ፥ በማደሪያውም ደጃፍ ፊት መጋረጃውን ትጋርዳለህ። |
| 6 | ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውንም መሠዊያ በመገናኛው ድንኳን በማደሪያው ደጅ ፊት ታኖረዋለህ። |
| 7 | የመታጠቢያውን ሰንም በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል አኑረህ ውኃ ትጨምርበታለህ። |
| 8 | በዙሪያውም አደባባዩን ትተክላለህ፥ የአደባባዩንም ደጃፍ መጋረጃ ትዘረጋለህ። |
| 9 | የቅብዓቱንም ዘይት ወስደህ ማደሪያውን በእርሱም ያለውን ሁሉ ትቀባለህ፥ እርሱንም ዕቃውንም ሁሉ ትቀድሳለህ ቅዱስም ይሆናል። |
| 10 | ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውንም መሠዊያ ዕቃውንም ሁሉ ትቀባዋለህ፥ መሠዊያውንም ትቀድሳለህ መሠዊያውም ቅድስተ ቅዱሳን ይሆናል። |
| 11 | የመታጠቢያውን ሰንና መቀመጫውን ቀብተህ ትቀድሳለህ። |
| 12 | አሮንንና ልጆቹንም ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አቅርበህ በውኃ ታጥባቸዋለህ። |
| 13 | የተቀደሰውንም ልብስ አሮንን ታለብሰዋለህ በክህነትም ያገለግለኝ ዘንድ ቀብተህ ትቀድሰዋለህ። |
| 14 | ልጆቹንም አቅርበህ ሸሚዞችን ታለብሳቸዋለህ |
| 15 | በክህነትም ያገለግሉኝ ዘንድ አባታቸውን እንደ ቀባህ ትቀባቸዋለህ መቀባታቸውም ለልጅ ልጃቸው ለዘላለም ክህነት ይሆንላቸዋል። |