ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Friday, 7 August 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

አምልኮ ምንድን ነው?

ሰላም ለናንተ ይሁን!

አንድ ጥያቄ አለኝ፡፡

ከቤተ ክርስቲያን ፕሮግራም በኋላ በተለይም በእሁድ ፕሮግራም ጊዜ "ጥሩ የአምልኮ ጊዜ ነበር...." ሲባል እሰማለሁ፡፡ እንደዚሁም ደግሞ የቃል ጊዜን ወይም የፀሎጥ ጊዜን ለየብቻው ለይቶ "ጥሩ የቃል ጊዜ ወይም ጥሩ የፀሎት ጊዜ ነበር....." ይባላል፡፡ ሁን ማወቅ የፈለግሁት ለመሆኑ አምልኮ ምንድን ነው? ማምለክ ሲል መፅሐፍ ቅዱስ ምን ማለቱ ነው? መፅሐፍ ቅዱስ "ኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ" ሲል በዚህ ክፍል ውስጥ ያለው ማምለክና የእሁድ አምልኮን የምንገልፅበት አምልኮ አንድ ዓይነት ናቸው?

እባካችሁን መልሱን በቶሎ............በመፅሐፍ ቅዱስ እይታ ሲታይ፡፡

ካሳቸው ከአዳማ፡፡
Aug 31, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

3 መልሶች

0 ድምጾች
ሰላም ሰላማችሁ ይብዛ።

"ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤
እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።"ዮሃን4፡23-24
"But the hour cometh, and now is, when the true worshippers shall worship the Father in spirit and in truth: for the Father seeketh such to worship him. God is a Spirit: and they that worship him must worship him in spirit and in truth."
አምልኮ እራሳችን አዋርደን በፊቱ በመንፋስ እና በእውነት መስገድ ነው ። ሌላው እኛ አምለኮ በለን የምንለው የዘማሬ አይነት 1 ክፍል ብቻ ነው ቃሉንም ማጥናት፤ መጸለይም፤ ኑሮአችንም ሁሉ በመንፋስ ስንመላለስ እሱን ከፍ አድርገን እኛ ዝቅ ብለን መገዛት አምልኮነው
Sep 1, 2011 YaelD (8,160 ነጥቦች) የተመለሰ
0 ድምጾች
መሰረታዊው የአምልኮ ትርጉም በተለይ በእብራይስጡ ማገልገል ወይም ታዛኝ መሆን ማለት ነው። ሃሳቡም በጥንት ዘመን ሁሉም ህዝብ የራሱ አምላክ ነበረው። እናም የአንዱ ሕዝብ ኑሮ ከሌላው እንደአምላኩ አይነትም ይለይ ነበር። ለምሳሌ የእስራኤልን ህዝብ ስንመለከት ከአህዛብ ከአበላላቸው ጀምሮ ከአህዛብ ይለይ ነበር። ለምን ቢባል ኑሮአቸው ማን አምላካቸው እንደሆነ ያመለክት ነበር። ስለዚህ አንድ ሰው እግዚአብሔርን አመለከ ወይም በቀጥተኛ ቃሉ አገለገለ ማለት እግዚአብሔር ያዘዘውን ትእዛዛት እያከበረ እንደ ትእዛዙ መሰረት ይኖራል ማለት ነው። እግዚአብሔርን አያመልክም ሌሎችን አማልክት ነው የሚያመልከው ማለት ደግሞ ለእነርሱ ይዘምራል ማለት አይደለም። ነገር ግን እግዚአብሔር ያዘዘውን ትእዛዛት ችላ ይላል ወይም ለዛ አይታዘዘም ይልቁኑ ግን ሌሎች አማልክት የሚፈልጉትንና ያዘዙትን ነገሮች በሕይወቱ ያደርጋል ማለት ነው።

ስለዚህ ኢያሱ "እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን" እናመልካለን ሲል ወይም ሰለሞን ሌሎችን አማልክት አመለከ ወዘተ ሲል መጽሐፍ ቅዱስ መዝሙር ዘመሩ ወይም እኛ በአሁኑ ዘመን እንደሚገባን "የአምልኮ ፕሮግራም" ያካሂዱ ነበር ማለት አይደለም። ነገር ግን አምላካችን ነው የሚሉት አምላክ ያዘዛቸውን ያደርጉና ይታዘዙ ነበር ማለት ነው።

ስለዚህም ነው አንድ ሰው እግዚአብሔርን አምላኪ (ተከታይ ወይም የእግዚአብሔር ታዛዥ) መሆኑና አለመሆኑ በኑሮው ነው የሚታወቀው። በእስራኤል ንጉሶች እግዚአብሔርን ያመልኩ ወይም አያመልኩ እንደነበር ስለ እያንዳንዱ ማለት ይችላል በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ እናገኛለን። አመለኩ የሚባሉት ንጉሶች ወይም ሰዎች ለምሳሌ እግዚአብሔር ያዘዘውን ሰንበትን ማክበር፣ አትብሉ ያለውን አለመብላት፣ እርሱ እንደፈለገ ጽድቅ ፍትህንና ፍርድን ማድረግ፣ እርሱ ያዘዛቸውን በዓላትን ማክበር፣ መስዋእቶችን ወዘተ ማድረግ፣ ለሌሎች አማልክት አለመሰዋት ወዘተ የሚባሉት ነገሮች በኑሮአቸው ስለሚታዩ ሰዎች ከኑሮአቸው አይተው እግዚአብሔርን ያመልኩ (ይከተሉ) እንደሆነና እንዳልሆነ ያውቁ ነበር።

በአንጻሩ ደግሞ እንደዚህንና የመሳሰሉትን በብሉይ ኪዳን እስራኤላውያን ያደርጉት ዘንድ እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ነገሮች የማያደርጉ በተቃራኒው ግን ክፋትን የሚያደርጉ፣ ድሆችን የሚያስጨንቁ፣ ፍትህን የማይወዱ፣ ለሌሎች አማልክት የሚሰው ወዘተ ደግሞ እግዚአብሔርን እንደማያመልኩ ነበር የሚቆጠሩት።

ስለዚህ አምልኮ የሚለው ቃል አንተ የማነህ የሚለውን የሚያመለክት ነው። ማንን ታመልካለህ ማለት የማንን ፈቃድ ነው በህይወትህ እየታዘዝክ ያለኸው ማለት ነው።

ስለዚህ አምልኮ በመሰረቱ ከዝማሬ ወይም በቤተመቅደስና በጉባኤ ከሚደረጉ ሃማኖታዊ ስርዓቶች ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። በእርግጥ ነው እግዚአብሔርን በኑሮአቸው የሚታዘዙ ሰዎች የከንፈሮቻቸውን መስዋእት በዝማሬ ቢያቀርቡ መልካም ነው። ሆኖም ግን በቤተመቅደስና በጉባዬ የሚደረጉ አምልኮዎች እግዚአብሔርን በህይወት መታዘዝ ከሌለበት እግዚአብሔር እጅግ የሚጸየፈውና የማይቀበለው ነገር እንደሆነ ብዙ ጊዜ በነብያቱ ተነግሮአል። እንዲያውም በብሉይ ኪዳን ቤተመቅደሱ በእንዲህ ያሉት ሰዎች ሲሞላ መጽሐፍ ቅዱስ በኤርምያስ 7 ላይም ይሁን በጌታ በኢየሱስ እንደሚናገረው ቤተመቅደሱን "የወንበዴዎች ወይም የሌቦች ዋሻ አደረጋችሁት" ነው የሚለው። የወንበዴዎች ዋሻ የሚባለው በዛን ዘመን ወንበዴዎች ወይም ወንጀለኞች ከገደሉና ሕገ ወጥ ድርጊት ካደረጉ በኋላ መንግስት እንዳይቀጣቸው የሚደበቁባቸው በተራሮች ወገብ ላይ የሚቆፈሩ ከፍርድ ማምለጫና መሸሸጊያ ቦታዎች ናቸው። ስለዚህ በህይወታቸው ክፉ እያደረጉና እግዚአብሔርን የማይታዘዝ ህይወት እየኖሩ በቤተመቅደስና በጉባኤ በሚደረግ "አምልኮ" ሊሸሸጉና ሊታመኑ ለሚፈልጉ በኤርምያስ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ ነው። ኤርምያስም እንዳስጠነቀቀው የታመኑበት መሸሸጊያ ቤተመቅደስ በባቢሎን ተቃጠለ፣ ተዘረፈና ፈረሰ። ስለዚህ አምልኮ በዋናነት በፕሮግራም ወይም በጉባኤ የሚደረግ ነገር አይደለም።
Quote:
ትንቢተ ኤርምያስ 7
1 ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው።
2 በእግዚአብሔር ቤት በር ቁም፥ ይህንም ቃል እንዲህ ብለህ ተናገር። እግዚአብሔርን ልታመልኩ በእነዚህ በሮች የምትገቡ ከይሁዳ ያላችሁ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
3 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መንገዳችሁንና ሥራችሁን አሳምሩ በዚህም ስፍራ አሳድራችኋለሁ።
4 የእግዚአብሔር መቅደስ፥ የእግዚአብሔር መቅደስ፥ የእግዚአብሔር መቅደስ ይህ ነው እያላችሁ በሐሰት ቃል አትታመኑ።
5 መንገዳችሁንና ሥራችሁን ፈጽማችሁ ብታሳምሩ፥ በሰውና በጎረቤቱ መካከል ቅን ፍርድ ብትፈርዱ፥
6 መጻተኛውንና ድሀ አደጉን መበለቲቱንም ባትገፉ፥ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን ባታፈስሱ፥ ክፉም ሊሆንባችሁ እንግዶችን አማልክት ባትከተሉ፥
7 ከዘላለም እስከ ዘላለም ለአባቶቻችሁ በሰጠኋቸው ምድር በዚህ ስፍራ አሳድራችኋለሁ።
8 እነሆ፥ በማትረቡበት በሐሰት ቃል ታምናችኋል።
9 ትሰርቃላችሁ፥ ትገድላላችሁ፥ ታመነዝራላችሁ፥ በሐሰትም ትምላላችሁ፥ ለበኣልም ታጥናላችሁ፥ የማታውቋቸውንም እንግዶች አማልክት ትከተላላችሁ
10 መጣችሁም፥ ስሜም በተጠራበት በዚህ ቤት በፊቴ ቆማችሁ። ይህን አስጸያፊ የሆነ ነገርን ሁሉ አላደረግንም አላችሁ።
11 ይህስ ስሜ የተጠራበት ቤት በዓይናችሁ የሌቦች ዋሻ ሆኖአልን? እነሆ፥ እኔ አይቻለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፦
12 ነገር ግን በቀድሞ ዘመን ስሜን ወዳሳደርሁበት በሴሎ ወደ ነበረው ስፍራዬ ሂዱ፥ ከሕዝቤም ከእስራኤል ክፋት የተነሣ ያደረግሁበትን እዩ
13 አሁንም ይህን ነገር ሁሉ ስላደረጋችሁ፥ በማለዳም ተነሥቼ በተናገርኋችሁ ጊዜ ስላልሰማችሁ፥ በጠራኋችሁም ጊዜ ስላልመለሳችሁ፥
14 ስለዚህ በሴሎ እንዳደረግሁ እንዲሁ ስሜ በተጠራበት በምትታመኑበት ቤት ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠኋችሁ ስፍራ አደርጋለሁ።

የያዕቆብ መልእክት 1
26 አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው።
27 ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው
Sep 2, 2011 በቃሉ (2,230 ነጥቦች) የተመለሰ
Sep 2, 2011 በቃሉ ታርሟል
0 ድምጾች
ውድ የጌታ ልጅ
አምልኮ ማለት ይህ ነው።
ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።
በተጨማሪ ጳውሎስ እንዳለው
አምልኮ ማለት ራስን ሰውነትን ቅዱስ መስዋት አድረጎ ማቅረብ ነው(ነውርና ነቀፋ የሌለበት)
Sep 4, 2011 Biniam Tehelku (220 ነጥቦች) የተመለሰ
የእ/ር ሕዝብ ራሱን ለአምላኩ መስዋእት አድርጎ በማቀረብ በቃልም ሆነ በምግባር የሚያክናዉነዉ ማንኛዉም እንቅስቃሲ ወይንም አገልግሎት ሁሉ ለእግዝያብሒር እንደሆነ በመረዳት በቅድስና ከአምላኩ ጋር የሚያደርገው ሁለንተናዊና የማያቁዋርጥ ግንኙነት ነዉ፡፡
ይሁን እንጅ አምልኮ ክዚህም ብላይ ነው....
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...