እኔ እንደሚገባኝ የመንፈሳዊ ሕይወት መለኪያዎች በሕይወት የሚታዩ የመንፈስ ፍሬዎችና ክርስቶስን ማዕከላዊ ያደረገ ሕይወት ናቸው።
መንፈሳዊ ሕይወት፤ የምናከናውናቸው እቅስቃሴዎች
(activity) ብቻ ሳይሆኑ ሕይወት ነውና የሕይወት ለውጥን የሚመለከት ነው።
ከሁሉም በፊት ክርስቶስን በትክክልና በሙላት መረዳትና እርሱን ማዕከላዊ ያደረገ እምነት ነው። ሃዋርያቱን በአዲስ ኪዳን ስንመለከት የሚናገሩትና የሚጽፉት ሁሉ ክርስቶስን ማዕከላዊ ያደረገና ክርስቶስ ክርስቶስ የሚል ነው። ምክር እንኳን ሰዎችን ሲመክሩ ክርስቶስን ጠርተው ነው። ስብከታቸውም ይሁን ምክራቸው ወይም ደብዳቤያቸው በሙሉ ክርስቶስን የሚያከብርና እርሱን ማዕከላዊ ያደረገ ነው፤ እንጂ እንዳው በደፈናው ስለ እግዚአብሔር ብቻ አልነበረም።
ክርስቶስን ማዕከላዊ ያደረገ ሕይወት ደግሞ የመንፈስን ፍሬ ያፈራል። የመንፈስ ፍሬ የሕይወት ባህርያት መገለጫ ነው። ከሁሉም ባሕርያት የሚበልጠው ደግሞ ፍቅር ነው። እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።
Quote:
ወደ ገላትያ ሰዎች 5
22 የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13
13 እንዲህም ከሆነ፥ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው።