ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Thursday, 29 July 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

የመንፈሳዊ አድግተ መለያዎቸ ምንምን ናችው?

Mar 3, 2011 መንፈሳዊ የህይወት ዛፍ (130 ነጥቦች) የተጠየቀ
Mar 3, 2011 ተመልካች ታርሟል

2 መልሶች

–1 ድምጽ
የመንፈሳዊ እድገት መለኪያ ነው ብዬ የምለው አንድና አንድ ብቻ ነው። ይኸውም አንተው ራስህ ለዚህ ጥያቄ የምትሰጠው መልስ ነው።
ምን ያህል ዕለት ዕለት ጌታ ኢየሱስን እየመሰልክ ነው?
እንደኔ አመለካከት ጌታ ኢየሱስን እየመሰልን በኖርን ቁጥር ሌሎች ነገሮች በሙሉ ስፍራቸውንና መልሳቸውን ያገኛሉ። እኛ ሊያሳስበን የሚያስፈልገን ጉዳይ ቢኖር ክርስቶስ ኢየሱስን የመምሰላችን ጉዳይ ነው። ሌሎች ሙከራዎች በሙሉ ጌታን ከመምሰላችን ስር የሚጠቃለሉ ናቸው ብዬ አስባለሁ።
በተጨማሪ ገላትያ 5 ስንመለከት ነፍሳችን የምትመገበው ከሥጋ የሆነ ወይስ ከመንፈስ የሆነ? ውሎአችንን የምንውልብት አዋዋል ትልቅ መመዘኛም ሊሆንን ይችላል። በሕይወታችን አሸናፊው ማን መሆኑን (ሥጋ ወይስ መንፈስ) ካወቅን ዕድገታችንም የትኛውን እንደሚመስል ማወቁ ያን ያህል ከባድ አይሆንም።

ጌታ ይባርክህ!

ተሾመ መለስ
ኢየሩሳሌም፣ እስራኤል
Mar 3, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ 1 ሪፖርት
+1 ድምጽ
እኔ እንደሚገባኝ የመንፈሳዊ ሕይወት መለኪያዎች በሕይወት የሚታዩ የመንፈስ ፍሬዎችና ክርስቶስን ማዕከላዊ ያደረገ ሕይወት ናቸው።

መንፈሳዊ ሕይወት፤ የምናከናውናቸው እቅስቃሴዎች (activity) ብቻ ሳይሆኑ ሕይወት ነውና የሕይወት ለውጥን የሚመለከት ነው።

ከሁሉም በፊት ክርስቶስን በትክክልና በሙላት መረዳትና እርሱን ማዕከላዊ ያደረገ እምነት ነው። ሃዋርያቱን በአዲስ ኪዳን ስንመለከት የሚናገሩትና የሚጽፉት ሁሉ ክርስቶስን ማዕከላዊ ያደረገና ክርስቶስ ክርስቶስ የሚል ነው። ምክር እንኳን ሰዎችን ሲመክሩ ክርስቶስን ጠርተው ነው። ስብከታቸውም ይሁን ምክራቸው ወይም ደብዳቤያቸው በሙሉ ክርስቶስን የሚያከብርና እርሱን ማዕከላዊ ያደረገ ነው፤ እንጂ እንዳው በደፈናው ስለ እግዚአብሔር ብቻ አልነበረም።

ክርስቶስን ማዕከላዊ ያደረገ ሕይወት ደግሞ የመንፈስን ፍሬ ያፈራል። የመንፈስ ፍሬ የሕይወት ባህርያት መገለጫ ነው። ከሁሉም ባሕርያት የሚበልጠው ደግሞ ፍቅር ነው። እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።
Quote:
ወደ ገላትያ ሰዎች 5
22 የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13
13 እንዲህም ከሆነ፥ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው።
Mar 3, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ 1 ሪፖርት
ጌታ ይባርክህ ! ይህን የገልፀልህ በውስጥህ ያለው በጌታ ያለህ እምነትህ ነው።
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...