ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Thursday, 29 July 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

2 ቆሮ5፡21 ኃጢአትን የሚጸየፍ ጻድቅ አምላክ ኃጢአትን የማያውቀውን ልጁን ያደረገው?

ትያቄውን ሳቀርብ እንዳልኩት ኃጢአትን የሚጸየፍ ጻድቅ አምላክ ከኃጢአተኛው አመጸኛ ሰው ጋር ራሱን ሊያስታርቅ ወዶ የሚወዳደረው ሌላ የሌለበት አንድያና ብቸኛ መንገድ እውነት ሕይወት የሆነውን እንዴት ቢጨክን ነው እርሱ ራሱ ሦስት ጊዜ "በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ..." ብሎ የመሰከረለት የሚወደውን አንድያ ልጁን እንዴት ነው ኃጢአት እንዲሆን ያደረገው????

ይህ አባባል ሲተረጎም የቃላት ጥረት ስለአጋጠማቸው ነው እንዳልል በሁለት ሦስት አራት ቁውቅንቃ ነው ያየሁት ያው ነው። ያልገባኝ ነገር እንዴት ኃጢአት እንዳደረገው ልረዳው ቀርቶ ለመገምትም ፈጽሞ አልቻልኩም።

ስለምትሰጡኝ ማብራሪያና ስለ ውድ ጊዜያቸሁ ጌታ አብዝቶ ይባርካችሁ።
Mar 3, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
Mar 4, 2011 ታርሟል

3 መልሶች

+2 ድምጾች
ጳውሎስ በዚህ ክፍል ሊናገር የፈለገው ልክ በገላትያ 3፥13 "ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ" እንደሚለው አይነት አባባል ይመስለኛል። ክርስቶስ እኛን ለመዋጀት የእኛን ኃጢአት መሸከም ነበረበት። በመስቀል ላይ የተሸከመው ኃጢአት ግን እርሱ ራሱ የሠራው አይደለም። ኃጢአትን የሚያደርግ ኃጢአተኛ ነው፤ የሌሎችን ኃጢአትን ግን የሚሸከም ምን ይባላል። ጳውሎስ እንግዲህ እግዚአብሔር ክርስቶስን ኃጢአተኛ አደረገው ሊል ስለማይችል ኃጢአት እንዳላደረገ ነገር ግን የእኛን ኃጢአት እንደተሸከመ ለማሳየት የተጠቀመበት አገላለጽ ነው።

በተመሳሳይ ሁኔታ ክርስቶስ እኛን ከህግ እርግማን ሊዋጀን እርግማን እንደሆነ ገላትያ 3፥13 ላይ ይናገራል። በራሱ ሥራ ርግማን የሚገባው ሰው የተረገመ ነው። ክርስቶስ ግን የሰዎችን እርግማን ተሸከመ እንጂ የተረገመ ግን አይደለም። ስለዚህም በተመሳሳይ ሁኔታ ጳውሎስ ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆነ ነው የሚለው።
Quote:
3፥13 በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤

እነዚህ ሁሉ የቃላት አገላለጾች እንጂ ዋናው መልእክቱ ያው በመጽሐፍ ቅዱስ ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ ሲነገር የነበረው የክርስቶስ በእኛ ፈንታ የተቀበለው የእኛን በደልና ኃጢአት፤ እግማንና ቅጣትን የሚያሳይ ነው። እርሱ ባልሠራው ኃጢአት የእኛን ኃጢአት እንደተሸከመ፤ እኛም እንደዚሁ ባልሠራነው ጽድቅ የእርሱን ጽድቅ ተቀብለናል።
Mar 3, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
ክላይ፡ መልስ፡የሰጠው፡ ሰው፡ በአጭርና፡ በጥሩ፡ ሁነታ መልሶታል-ለመጨመር፡ ያህል፡ መልክቱ ፡የሚገኘዉ፡ በ2ኛቆሮ 5፡21 ላይ ነው። እኛ፡ በርሱ፡ ሆነን፡ የእግዚአብሔርን፡ ጽድቕ፡ እንሆን፡ ዘንድ፡ ሃጥያት፡ ያላወቀዉን ፡እርሱን፡ ስለእኛ፡ ሃጢያት፡ አደረገው ። ጳውሎስ፡ ማስረዳት፡ የፈለገው፡ መድሃኒታችን፡ እየሱስ፡ ክርስቶስ፡ እጅግ፡ ታላቅ፡ ዋጋን፡ ከፊሎ፡ሃጥያታችንን፡ እንደወሰደልንና፡ ቀድሞ፡ እንኮነንበት፡ የነበረዉን፡ መተላለፍ፡ እንደተወገደልን፡ ነው። በአይሁድ፡ ስርዓት፡ በእንጬት፡ የሚሰቀለው፡ እጅግ፡ የተጠላ፡ በጣም፡ ከፍተኛ፡ ወንጀል፡ ያደረገ፡ እንዲሁም፡ የተረገመ፡ሰዉ፡ነው።ክርስቶስ፡ ግን ፡ንጹሕ፡ የእግዚአብሔር፡ ልጅ፡ ሆኖ፡ ሳለ፡ በመስቀሉ፡ ሞት፡ ከአባቱ፡ ጋር፡ አስታረቀን።ክብር ለግዚአብሔር ይሁን፡፡ ኤሳ 53 በጠቅላላ ማንኛዉም ሃጢያተኛ መክፈል ከሚገባዉ በላይ የከፈለዉን ዋጋ በደንብ ያብራራል ቁ2 "እንወደዉ፡ ዘንድ ፡ደም፡ ግባት፤ የለዉም.." ቁ3 "የተናቀ፡ከሰዉም፡የተጠላ..."ቁ4"በእግዚአብሔርም፡እንደተቀሰፈ፡እንደተቸገረም፡ቆጠርነው።"ቁ7"ተጨነቀ፡ተሰቃየ፡አፉንም፡አልከፈተም"ቁ10"እግአብሔር፡ በደዌ ፡ያደቀው፡ ዘንድ፡ፈቀደ።"እያለ መከራዉን ያብራራል።ቁ5ላይ"ደግሞ፡"በመገረፉ፡ ቁስል፡ተፈወስን"ይላል፡እግዚአብሔር፡ይባረክ። ኤየሱስ፡ክርስቶስ፡ትላንትናም፡ዛረም፡ለዘላለም ሕያዉ ነው። አብ፡ወልድ፡መንፈስ፡ቅዱስ፡አንድ፡አምላክ፡ አሜን!!!
Mar 4, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
እግዚአብሔር በአንድያ ልጁ ያደረገልን የጎልጎታ መሰቀል ፍቅሩ እጅግ ድንቅ ከሃሳባችን በላይ ሊገባን የማይችል እጹብ ድንቅ ፍቅር ነው። 2 ቆሮ 5 በጣም ብዙ ምስጢር ያካተተ ምዕራፍ ነው።

ጥያቄው ውስጥ ያለው ይህ ቃል ጠያቂው እንዳለው ምናልባት የአገላለጽ ጉድለት ሊሆን ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ ተርጉመው ያዘጋጁልን አባቶች ጌታን በሙሉ ልብ ያገለገሉ እንደ ሆኑ አልጠራጠርም። ቃሉ በጣም ግሩምና ድንቅ የሆነ ከሰው አስተሳሰብ በላይ ስለ ሆነው ፍቅር ነው የሚነገረን።

እየሱስ ኃጢአታችን ተሸከሞ ነው ኤሌሄ ኤሌሄ ለማሰበቅታኒ ብሎ የጮኸው አብም በሁዋላ ብዙ ወንድሞችና እህቶች ይኖርሃልና ያለው ይመስልኛል ፊቱን ዞር ሲያደርግበት። በይበልጥ ለመረዳት ዘሌዋውያን ሜራፍ 16 ጊዜ ወሰደን እናንብበው። በተረፈው ጌታ መንፈስ ቅዱስ ሁሌ ቃሉን ያስተምረን ይግለጽልን።
Mar 4, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...