ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Monday, 18 January 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

የተለያዩ የቃላትና የስርአተ ነጥብ እርማቶች

ሰላም ፡
ከዚህ በታች አንዳንድ እርማቶችን ለመጠቆም ሞክሬአለሁ። አንዳንዶቹ የቃላት ግድፈት ሲሆኑ አብዛኞቹ ግን የስርአት ነጥብ ናቸው። በእርግጥ ስርአተ ነጥቦቹ አስመልክቶ በብዙ ቦታ ባስተውላቸውም አሁን ልጠቁም የቻልኩት ከአንድ ክፍል ላይ ያሉትን ብቻ ነው። ስህተቶቹ በዙ የትርጉም ለውጥ ባያመጡም በንባብ ጊዜ ግር ሊይሰኙ ስለሚችሉ ቢታረሙ መልካም ነው።

የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ


Daniel 5:2 ብልጣሶርም የወይን ጠጅ በቀመሰ ጊዜ ንጉሡና መኳንንቶቹ ሚስቶቹና ቁባቶቹ ይጠጡባቸው ዘንድ አባቴ ናቡከደነፆር በኢየሩሳሌም ከነበረው መቅደስ ያመጣቸውን የወርቁንና የብሩን ዕቃዎች አምጡ ብሎ አዘዘ።
KJV Daniel 5:25 And this is the writing that was written, MENE, MENE, TEKEL, UPHARSIN.


Acts 12:15 እርሱም፦ አብደሻል አሉአት። እርስዋ ግን እንዲሁ እንደ ሆነ ታስረግጥ ነበር። እርሱም፦ መልአኩ ነው አሉ።

Judges 13:13 የእግዚአብሔርም መልአክ ማኑሄን፦ ሴቲቱ ከነገርኋፅት ሁሉ ትጠንቀቅ።

Judges 15:2-3አባትዋም ፈጽመህ የጠላሃት መስሎኝ ለሚዜህ አጋባኋፅት ታናሽ እኅትዋ ከርስዋ ይልቅ የተዋበች አይደለችምን? እባክህ፥ በእርስዋ ፋንታ አግባት አለው።ሶምሶንም ከእንግዲህ ወዲህ በፍልስጥኤማውያን ላይ ክፉ ባደርግ እኔ ንጹሕ ነኝ አላቸው።


Judges 15:12 እርሱም፦ አስረን በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፈን ልንሰጥህ መጥተናል አሉት። ሶምሶንም እናንተ እንዳትገድሉኝ ማሉልኝ አላቸው።

Judges 15:16 ሶምሶንም በአህያ መንጋጋ ክምር በክምር ላይ አድርጌአቸዋለሁ በአህያ መንጋጋ አንድ ሺህ ሰው ገድያለሁ አለ።

Judges 16:7 ሶምሶንም ከእንግዲህ ወዲህ በፍልስጥኤማውያን ላይ ክፉ ባደርግ እኔ ንጹሕ ነኝ አላቸው።

Judges 16:15 እርስዋም፦ አንተ እወድድሻለሁ እንዴት ትለኛለህ፥ ልብህ ከእኔ ጋር አይደለም? ስታታልለኝ ይህ ሦስተኛ ጊዜህ ነው፥ ታላቅ ኃይልህም በምን እንደ ሆነ አልነገርኸኝም አለችው።

Judges 16:18 ደሊላም የልቡን ሁሉ እንደ ገለጠላት ባየች ጊዜ የልቡን ሁሉ ገልጦልኛልና ይህን ጊዜ ደግሞ ኑ ብላ ላከችና የፍልስጥኤማውያንን መኳንንት ጠራች። የፍልስጥኤማውያን መኳንንትም ብሩን በእጃቸው ይዘው ወደ እርስዋ መጡ።

Judges 16:20 እርስዋም፦ ሶምሶን ሆይ፥ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ አለችው ከእንቅልፉም ነቅቶ እወጣለሁ እንደ ወትሮውም ጊዜ አደርጋለሁ አለ። ነገር ግን እግዚአብሔር ከእርሱ እንደ ተለየው አላወቀም።

Judges 16:23 የፍልስጥኤምም መኳንንት አምላካችን ጠላታችንን ሶምሶንን በእጃችን አሳልፎ ሰጠን እያሉ ለአምላካቸው ለዳጎን ታላቅ መሥዋዕት ይሠዉ ዘንድ ደስም ይላቸው ዘንድ ተሰበሰቡ።

24 ሕዝቡም ሁሉ ባዩት ጊዜ ምድራችንን ያጠፋውን፥ ከእኛም ብዙ ሰው የገደለውን ጠላታችንን አምላካችን በእጃችን አሳልፎ ሰጠን እያሉ አምላካቸውን አመሰገኑ።
25 ልባቸውንም ደስ ባለው ጊዜ በፊታችን እንዲጫወት ሶምሶንን ጥሩት አሉ ሶምሶንንም ከግዞት ቤት ጠሩት፥ በፊታቸውም ተጫወተ ተዘባበቱበትም፥ በምሰሶና በምሰሶም መካከል አቆሙት።
26 ሶምሶንም እጁን የያዘውን ብላቴና ቤቱን የደገፉትን ምሰሶች እጠጋባቸው ዘንድ፥ እባክህ፥ አስይዘኝ አለው።
30 ሶምሶንም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ልሙት አለ ተጎንብሶም ምሰሶቹን በሙሉ ኅይሉ ገፋ፥ ቤቱም በውስጡ በነበሩት በመኳንንቱም በሕዝቡም ሁሉ ላይ ወደቀ በሞቱም የገደላቸው ሙታን በሕይወት ሳለ ከገደላቸው በዙ።
Sep 24, 2011 ቴክኒክ ነክ ነመ (350 ነጥቦች) የተጠየቀ
Sep 24, 2011 ነመ ታርሟል

1 መልስ

0 ድምጾች
ሰላም ነመ

ስለ ጥቆማህ/ሽ በጣም እናመሰግናለን።

የቃላት ስህተቶቹ አሁን ታርመዋል። የስርዓተ ነጥብ ችግሩ ግን የታወቀና ብዙ ስለሆነ በቀላሉ የሚታረም አይደለም። አንድ መሠረታዊ መፍትሔ እስከምናገኝለት ድረስ እንድትታገሱን በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን።

የጌታ ጸጋ ይብዛህ/ሽ!

iyesus.com
Sep 25, 2011 iyesus (7,430 ነጥቦች) የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...