ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Thursday, 3 December 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ግብረስጋግንኙነት እና ከጋብቻ በፊት ስለሚደረግ ጾታዊ ግንኙነት ምን ይላል?

የሴት ጓደኛዬ በተደጋጋሚ ጾታ ግንኙነት እንድናደርግ አምርራ ትጠይቀኝ ጀምራልች ምን ማድርግ እንደምችል እርዱኝ
Mar 4, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
Mar 4, 2011 ተመልካች ታርሟል
ትግስቱን ይስትልክ የኔ ወንድም
ለፓስተርህ አማክር ወይን የጋብቻ ትምህርት መውሰድ ይኖርችባችዋል።ለማንኛውም ነገሩን ሳታንዛዛ ለማግባት ትጋ። ጌታ ጸጋውን ያብዛልህ።
አሜን!የሰርግ ወጪያችንን ለመሸፈን ያብቃህ
ከጋብቻ በፊት የሚሆን ነገር ሁሉ እጊዛብህር አይከብርበትም በሃላም መከራ ያመታል ወደፈተናም እንዳትገቡ ተግታችሁ ሰልዩ እንደሚል ሰለይ ከመሪህ ጋር ተነጋገር ዝም አትበል.
ከጋብቻ በፊት ለየትኛውም ነገር መቸኮል ኋላ ላይ ፀፀት ያመጣል!! ለምሳሌ የሴት ጓደኛህ በዚህ ግንኙት ወቅት ብታረግዝ ጥሩ የሆነ ነገር ላይፈጠር ይችላል!! እናም ራስን መግዛትና ጥንቃቄ ማድረግ በተለይ እንደወንድ ከአንተ የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው፡፡ ምናልባት የሴት ጓደኛህ እንዲህ ደፍራ እንድትጠይቅ ያደረጋት ያላስተዋልከው ስሜትን የሚቀሰቅስ ነገር ተፈጥሮ ይሆናል፡፡ ስለዚህ በተቻለ መጠን ከጋብቻ በፊት ይህን ነገር ላለማድረግ ለዚህ ያነሳሱኛል ከምትላቸው ሁኔታዎች ራቅ (ብቻችሁን ከሰው ተሰውራችሁ አትሁኑ) እርሷንም ስሜቷና እንዳይጎዳ ይህን አለማድረጋችሁ ጥቅሙ ለወደፊት ደስታችሁ እንደሆነ ንገራት

4 መልሶች

0 ድምጾች
ችጝር ዬሌም አሰረዳት
መንፈሳዊ ቦታ ውሰዳት
ክዝያም ትረዳሃለች
Mar 4, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
+4 ድምጾች
በቅድሚያ ቃሉ የሚለውን እንመልከት፦
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል
5፥28 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል።

ካላገባሃት ሴት ጋር ግብረሥጋ ግንኙነት ማድረግ ይቅርና መመኘትም ኃጢአት ነው። ምንም የሚመቻመች ነገር የለውም፤ ግልጽና ቁልጭ ያለ የእግዚአብሔር ቃል ነው።

ሌላው ግን ይህቺን ሴት ለትዳር አስበሃት ነው እጮነት የጀመራችሁት ብዬ አስባለሁ። ታዲያ ይህቺ ሴት አሁን ባለችበት ሁኔታ፤ እግዚአብሔር ሳይቀይራት ትርዳ ውስጥ ገብታ ደስተኛ ታደርገኛለች ብለህ ታስባለህ? ይሄንን ለምን አልክ በለኝ።

በድንገት ሳያስቡት ሁለት ፍቅረኛሞች በዝሙት ኃጢአት ሊወድቁ ይችሉ ይሆናል። ነገር ግን አስባና አውቃ አንተ እንዳልከው በተደጋጋሚ በዚህ ኃጢአት እንድትወድቁ የምትጠይቅ ሴት፤ እግዚአብሔር ዓይንህን ከከፈተው፤ ይህ ድርጊቷ ስለ እርሷ ትልቅ የሚናገረውና አንተንም የሚያስጠነቅቅህ ማስጠንቀቂያ አለው።

በዚህ ኃጢአት ብትወድቁ እርሷን ይቅርና የአንተን መንፈሳዊ ሕይወትና ሕሊና ምን ያህል ጨለማ ውስጥ ሊከት እንደሚችል አስባዋለች? ለአመታትስ የሕሊና ጸጸት ሆኖብህ በጨለመ መንፈስ ዘመንህን ልትገፋ እንደምትችል፤ በንጹሕ ህሊና ወደ ጌታ እንዳትቀርብ ሊያደርግህ እንደምትችልስ አስባዋለች? እንደሚገባኝ አላሰበችውም።

ይህ ደግሞ ልጅቷ አንደኛ እግዚአብሔርን ጨርሶ የማትፈራና ለአንተም መንፈሳዊ ሕይወት ምንም ግድ የማይሰጣት፤ ባጠቃላይ እርሷ ልታገኘው ከምትፈልገው ምድራዊ ነገር ውጪ ለእግዚአብሔርም ይሁን ለሰው ፈጽሞ ደንታ የሌላት ራስ ወዳድ እንደሆነች ነው የምገምተው።

ተሳስቼ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ይሄን የምልህ አስባበት ደጋግማ አውቃ የምታደርገው እንጂ በመታለል ድንገት ሊሆን ስለሚችል ኃጢአት ስላልሆነ ነው የምንነጋገረው።

ታዲያ እንደዚህች አይነቱን ለእግዚአብሔርም ይሁን ለሰው ሕይወት ደንታ የማይሰጣትን ሴት አግብተህ እንዴት ሆነህ ነው ደስተኛ የምትሆነው? በአንተና በእርሷስ መካከል በትዳር ላይ ችግር ቢፈጠር ምን አይነት እርምጃ የምትወስድ ይመስልሃል? "አይ ይሄን አላደርግበትም ሊጎዳ ይችላል እግዚአብሔርም አይወደውም" ብላ የምትመለስ ይመስልሃል? እንደማንም ጌታን እንደማያውቅ ሰው የመሰላትንና እንደ ራስ ወዳድነቷ በፊቷ ደስ ያላትን ታደርጋለች እንጂ ለአንተም ይሆን ለሰው አትራራም፤ እግዚአብሔርንም ፈርታ አትመለሰም።

እንደ እኔ እንደ እኔ እግዚአብሔር ግልጽ በሆነ ሁኔታ ቀይ መብራት እያሳየህ ነው። ቢያንስ የጌታ ነገር እስኪገባት ጨክነህ ከእርሷ ተለይ ነው ምክሬ። አይ እንደዚህ አይደለም ምናምን ብለህ ተታልለህ ወደ ትዳር ከገባህ ግን፤ መንፈሳዊው ሕይወትህ ብቻ ሳይሆን የትዳርህም ሕይወት የጨለመ ነው የሚሆነው። አምልጥ ሽሽ! እግዚአብሔር እርሱን የምትፈራ፤ ለሰውም የምትራራ ይሰጥሃል። ለሴት ፍቅር ብለህ የጌታን ነገር አትሰዋ!
Quote:
መጽሐፈ መሣፍንት 16
15 እርስዋም፦ አንተ። እወድድሻለሁ እንዴት ትለኛለህ፥ ልብህ ከእኔ ጋር አይደለም? ስታታልለኝ ይህ ሦስተኛ ጊዜህ ነው፥ ታላቅ ኃይልህም በምን እንደ ሆነ አልነገርኸኝም አለችው።
16 ዕለት ዕለትም በቃልዋ ነዘነዘችው አስቸገረችውም፥ ነፍሱም እስከ ሞት ድረስ ተጨነቀች
17 እርሱም፦ ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ ለእግዚአብሔር የተለየሁ ነኝና በራሴ ላይ ምላጭ አልደረሰም የራሴንም ጠጕር ብላጭ ኃይሌ ከእኔ ይሄዳል፥ እደክማለሁም፥ እንደ ሌላም ሰው እሆናለሁ ብሎ የልቡን ሁሉ ገለጠላት።
18 ደሊላም የልቡን ሁሉ እንደ ገለጠላት ባየች ጊዜ። የልቡን ሁሉ ገልጦልኛልና ይህን ጊዜ ደግሞ ኑ ብላ ላከችና የፍልስጥኤማውያንን መኳንንት ጠራች። የፍልስጥኤማውያን መኳንንትም ብሩን በእጃቸው ይዘው ወደ እርስዋ መጡ።
19 እርስዋም በጕልበትዋ ላይ አስተኛችው አንድ ሰውም ጠራች፥ እርሱም ሰባቱን የራሱን ጕንጕን ላጨው። ልታዋርደውም ጀመረች፥ ኃይሉም ከእርሱ ሄደ።
20 እርስዋም፦ ሶምሶን ሆይ፥ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ አለችው። ከእንቅልፉም ነቅቶ። እወጣለሁ እንደ ወትሮውም ጊዜ አደርጋለሁ አለ። ነገር ግን እግዚአብሔር ከእርሱ እንደ ተለየው አላወቀም።

2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ
2፥22 ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ፥ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል።
Mar 4, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Mar 4, 2011 ታርሟል
+2 ድምጾች
ጌታ ይመስገን በድፍረት አደባባይ ውጥተህ ምክር እንድትፈልግ የረዳህ። ጌታ ለትልቅ ጉዳይ ይፈልግሃል ጠላት ግን ስጋህን የምታስደስትበት ገበታ አዘጋጅቶልሃል። ወንድሜ ሆይ በዚህ ጉዳይ እጅግ ተጠንቀቅ የአጭር ጊዜ ስጋዊ ድስታ ለዘመናት ጸጸት እንዳይሆንበህ በፍቅር ጉዳይህን አስረዳት ካልተቀበለችህ በትህትና ዞር ማለቱ ነው የሚብጅሀ። እንድገና ብወለድ ካደረኩዋቸው ወስጥ በዙ የማላደርጋቸውን ነገር አሉ። ባለህበት በኩል አልፌላሁ። ይቅርብህ!!! ይቅርብህ!!! ይቅርብህ!!!

ጌታ ይባርክህ
Mar 5, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Mar 5, 2011 ታርሟል
የሴት ጓደኛዬ የሆነ ቀን ምን እንዳልቺኝ አልዘነጋውም ‹‹ፍቅሬ መኪና ሳይሞከር አይገዛም
ልጅቱ ከዚህ በፊት ብዙ ያየች ከሆነ addiction ሊኖር ስለሚችል መራቁ ጥሩ ነው ካለበለዚያ የሆነ ቀን ትሳሳታለህ።
ወዳጄ...መኪናን ሰው ስለሰራው ሰው ይሞክረዋል... የሰው ልጅ ግን በእግዚአብሄር አምሳል የተፈጠረ ነውና ሙከራ አያስፈልገውም በልና አስረዳት። ከሁሉም በላይ ግን በትህትናና በፍቅር የእግዚአብሄርን ቃል አስረዳት...አልቀበልም ካለችህ...ሽሽ!!
"ወዳጄ...መኪናን ሰው ስለሰራው ሰው ይሞክረዋል... የሰው ልጅ ግን በእግዚአብሄር አምሳል የተፈጠረ ነውና ሙከራ አያስፈልገውም በልና አስረዳት። ከሁሉም በላይ ግን በትህትናና በፍቅር የእግዚአብሄርን ቃል አስረዳት...አልቀበልም ካለችህ...ሽሽ!!" እንዲህ በልህ የጻፍከውን ሰው ጌታ ይባርክህ ማለት እፈልጋለሁ። ትልቅ ማስተዋል ነው። ሰው ማንን የመስላል በሉ ዉሎውን አሉ እውነት ነው እድህ አይነትዋ ሴት ለትዳር የሚመርጥ እሳት ውስጥ አውቆ የምግባት ያህል ነው ነገ አልጠገብኩም እና ጎረቤት ልሂድ ተላለች ወንድሜ የሰው መክር ስማ መለስ በል።
ጥሩ ነው እግዚአብሀር ይባርክህ ወንድሜ! ምን አለ መሰለህ! አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ.. አንድ ተማሪ ዩኒቨርስቲ ወይም ኮለጀ አንደገባ ወዲያው የመመርቂያ ቆብ ቢጭን ምን ያህል ደስ ይለዋል? ትክክልስ ነው? ከጋብቻ በፊት ወሲብም ልክ እንደዚሁ ነው..!!! ስለዚህ ወንድሜ በጣም ኢወድሃለሁ ኢንደዚህ አይነት አስተሳሳብ ይቅርብህ!!! ይቅርብህ!!! ይቅርብህ!!! ይቅርብህ!!! ይቅርብህ!!! ይቅርብህ!!! ይቅርብህ!!! ይቅርብህ!!!
+1 ድምጽ
ጥቅሙ ብቻ ሳይሆን ጉዳቱ ለራሷ ነው ኃጢያቱም ለራሷ ነው ግን
ምክንያቷ ምንድን ነው ?
1 ካንተ ጋር በፍቅር ለመርካት ነው

2 በሆነ ምክንያት እንለያያለን የሚል ስጋት ስላደረባትና በጣም ስለምትወድህ ድንግልናዋን ላንተ ለትሰጥ ፈልጋ ይሆን
3 ከፍተኛ የሆነ የወሲብ ሱስ ስላለባት ይሆን
4 ካንተ ጋር ቤተሰብ መመስረት (ማርገዝ) ፈልጋ ይሆ
5 አንተ ማድረግ ያልፈለከው ከሌላ ሴት ጋር እያደረክ ስለመሰላትና በዚህ ምክንያት እንዳታጣህ ስለፈራች ይሆን

የምትወዳት ከሆነ መፍትሄው
1 ጋብቻ መፈጸም ነው፡፡ በምስክርና በመረጃ አስተደግፋችሁ አንድነታችሁን ገልጻችሁ ከዛ በኃላ እንደ ፈለገች ታስደስታታለህ፣ ትወልዳላችሁ ላንተም ለሷም በጣም ጠሩው መንገድ ይሄነው፡፡ ይሄ ደግሞ በሰርግ ወይም ያለሰርግ መሆን ይችላል፡፡

2 በድንገት ወይም በስህተት በስውር አንድነት ከፈጠራችሁ ማለትም ከሰው ተደብቃችሁ በእግዚአብሄር ፊት ብቻ አንድነት ከፈጠራችሁ መለያየት መፋታት የለባችሁም ደግሞ ወደፊት በሰው ፊት በሰርግ ጋብቻ መፈጸም ትቻላላችሁ ወናው አንድነታችሁን ጠብቃችሁ መኖራችሁ ነው፡፡ ከባዱ ኃጢያት መፋታቱ ነው፡፡

ማሳሰቢያ
1 መሞካከር የሚባለው ነገር አይመቸኝም፡፡ ድንግልናን እየወሰድክ መሞከር ብሎ ነገር አይሰራም፡፡ ያኔ በብሉይ ኪዳን ዘመን እሞክራለሁ ብትል በድንጋይ ተወግረህ ትሞታለህ ወይ ደግሞ በግድ ታገባታለህ፡፡ የደፈረና የሞከረ አንድነው ምን ልዩነት አለው ፡፡
2 በምኞት ከምትቃጠሉ በቀላሉ ተጋቡ፡፡
Apr 21, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...