ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Thursday, 3 December 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

የፈሪሳውያን እና የስዱቃዊያን ልዩነት ምንድን ነው?

Mar 4, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

+3 ድምጾች
ሰዱቃውያን
በኢየሱስ ዘመን በአይሁድ መካከል ከሚገኙት ትልልቅ ቡድኖች መካከል አንዱ ሰዱቃውያን ናቸው፡፡ ጌታ በምድር በነበረበት ዘመን ተቀባይነታቸውና ክብራቸው እየቀነሰ በመሔድ ላይ ነበር፡፡
ቀደም ሲል በፖለቲካው ውስጥ ከፍ ያለ ስፍራን መያዝ በመቻላቸው ሰዱቃውያን ሐብታም ከሆኑት የመሬት ባላባቶች ሊሆኑ ችለዋል፡፡ በአይሁድ ሸንጎ ውስጥ ከፈሪሳውያን ያልተናነሰ ወንበር ነበራቸው፡፡ ሐዋ.ሥ 23፡6-10 አብዛኛዎቹ ዋና ዋና ካህናትም ሰዱቃውያን ነበሩ፡፡

እምነታቸው-
አፈ ታሪክ አይቀበሉም፣ ትንሳኤ ሙታንና ፍርድ መኖሩን አያምኑም፣ የመላዕክትን ሥልጣን ተዋረድ አያምኑም /አይቀበሉም/፣ የኦሪትን መጽሐፍት ብቻ ይቀበላሉ እንዲሁም ቀጥታ ትርጉምን ይከተላሉ፡፡
ፈሪሳውያን
ፈሪሳውያን ከክርስቶስ ልደት በፊት በሁለተኛው ክፍለ ዘመን ላይ ይኖሩ ከነበሩ ሐሲድም ከተባሉ ሰዎች ውስጥ የወጡ ናቸው፡፡ ጅማሬያቸው በግሪኮች ዘመን ለእምነታቸው ከነበራቸው ከፍተኛ ቅናት የመነጨ ነበር፡፡ ሕጉንና ወጉን እጅግ ዝርዝር በሆነ መንገድ አጥብቀው ለመጠበቅ የሚጣጣሩ ሰዎች ነበሩ፡፡
ብዙዎች ጸሐፍት ከፈሪሳውያን ወገን ናቸው፡፡ ከሌሎች ሰዎች እስኪርቁ ድረስ እራሳቸውን ይጠብቁ ነበር፡፡ ይህ አመለካከታቸው ነበር እራሳቸውን ከሌሎች የተለዩና ጻድቅ አድርገው የመቁጠር ፈተና ውስጥ የጣላቸው ፈሪሳውያን ከሰዶቃውያን ጋር የማይስማሙ ናቸው፡፡ ካህን ሳይሆኑ ተራ ሰዎች ናቸው፡፡
[u]እምነታቸው[/u][size=][/size]:-
ከአባቶች የተላለፈውን ወግ ይጠብቃሉ፣ ትንሳኤ ሙታንና የፍርድም ቀን እንዳለ ያምናሉ፣ የኦሪትን፣ የታሪክ መጻሕፍትንና የነቢያትንም መጽሐፍት 39ኙንም መጽሐፍት በእኩልነት ሥልጣን ይቀበላሉ፤ ከቅዱስ ስፍራ /ከመቅደስ/ በላይ በቅዱስ ሕዝብ ላይ ያተኩራሉ ማለትም ቅዱሳንን ይከታተላሉ፣የመሢሑን መምጣት ያምናሉ በ70 ዓ.ም መቅደስ ቢፈርስም እስከ ሁለተኛው 100 ክፍለ ዘመን ቀጣይነት ነበራቸው፡፡
Mar 4, 2011 ዞላ (270 ነጥቦች) የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...