ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Thursday, 3 December 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

የንጥቀት እና የዳግም ምጻት ልዩነት ምንድነው?

Mar 6, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

0 ድምጾች
መነጠቅና ዳግም ምጻት ተመሳሳይ ናቸው ሁለቱም ስለ ጌታ እየሱስ መመለስ ነው የሚናገሩት ግን የተለያዩ ሁለት ሁኔታዎች ናቸው። ብዙ ጊዜ አጠቃልለን እንጂ ለያይተን አንነገርባቸውም ግን በጣም ሰፊ ልዩነት አላችው። ይህ ልዩነት የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ስለ መጨረሻው ዘመን ለይተው የሚያጠኑ የእግዚአብሔር ሰዎች ያስተምሩታል።

ቤተ ክርስቲያን ብዙ ዓይነት አሳ የያዘ ትልቅ መርብን ትመስላለች። ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን የሚመላለስ ሁሉ እውነተኛ አማኝ ቅዱስ ነው ማለት አንችልም ግን እግዚአብሔር እንኳ ሰው አልሆነ እሱ ሁሉን ለይቶ አብጠርትሮ የሚያውቅ አምላክ ነው። ማቴ 24:36, 40 & 42 እና 1 ተሰ 4፡13 - 18 ሰለ መነጥቅ ያስተምሩናል። ይህ በድንገትና ሁሉ ሳያወቀው የሚሆን በጌታ የሚያምኑትንን ማለትም ቤተ ክርስቲያንን ከምድር ላይ ለመውሰድ የሚመለስብት ነው። ያንቀላፉት ተነስተው በሕይወት ያለነው ደግሞ አብረናቸው በቅጽበት ጌታን በማላእክቱ ታጅቦ ሲመለስ በአየር ላይ እንገናኛለን። እንዴት ያለ ቀን እንዴት ያለ ደንቅ የደስታ ጊዜ ይሆንልናል ምክንያቱም የትዕግሥቴን ቃል ስለ ጠበቅህ እኔ ደግሞ በምድር የሚኖሩትን ይፈትናቸው ዘንድ በዓለም ሁሉ ላይ ሊመጣ ካለው ከፈተናው ሰዓት እጠብቅሃልሁ (ራዕይ 3፡10) ያለውን የተስፋ ቃሉን የሚፈስምበት ነው።

ይህን የሚያገኙ ሁሌ በጸሎት እየተጉ ለእምነታቸው ቆርጠው የጽኑትን አማኞች ወደ አባቱ ለማቅረብ ቅልጥ ባለው ድግስ በበጉ ራት ላይ እንዲገኙ እግዚአብሔር ያዘጋጀው ታላቁ ዕድላችን ነው። በዚህ ራት ላይ ለመገኝት ክርስትና ውድና ከባድ ዋጋ ያስከፍላል። ስንሄድ ይዘነው ስለ ማንወስደው ደስ እያለን ጌታ አንተ የሰጠኽኝ ነውና እንሆ እንካ ውሰደው ብለን በውዴታ እንሰዋለት።

ዳግም ምጻቱ ደግሞ ክርስቶስ እየሱስ በሃይሉ በስልጣኑ በአምብላይ ፈረስ ሲመልስ ምድር የነገስታት ንጉሥ የጌታዎች ጌታ ሆኖ የምታውቅብት በአርሜጌዶን ጦር ጌትነቱን በተጻጻሪው መንፍስ ተመርተው የሚሰለፉቱን በምድር ላይ ይመጨረሻው ጦርነት ነው (ራዕይ 19፡11 - 16)። ከዚህ በኋላ ጌታ በምድር ላይ የሺው ዓመታት ይጀምራል።

ጌታ ይባርካችሁ
Mar 7, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Mar 10, 2011 ታርሟል
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...