ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄና መልስ
Email this page to a friend Printer-friendly   Tuesday, 21 May 2013
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

መንፈስ ቅዱስ አምላክ ነው

መንፈስ ቅዱስ አምላክ ነው ካልን አየሱስም አምላክ ከሆነ አብ አምላክ ከሆነ ሱስት አምላክ አንበላቸው ወይስ አንድ አምላክ ከስላሴ አስተምህሮ ጋር አንዲት አናስታርቀዋለን?
1 ዓመት በፊት መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

3 መልሶች

+1 ድምጽ
ምንም እንኳን ልክ እንደ አዲስ ኪዳን በብሉይ ኪዳንም መንፈስ ቅዱስ በጣም የታወቀ ቢሆንም አይሁዳውያን በእብራይስጡ መንፈስ ቅዱስን የሚረዱበት መረዳት እኛ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ከምነረዳበት እጅግ የተለየ ስለሆነ እግዚአብሔርና መንፈስ ቅዱስ ሁለት persons የሆኑ ነገር ግን አንድ አምላክ ወደሚል መረዳት አልመጡም።

መንፈስ የሚለው ቃል በእብራይስጡ "Ruah" ሲሆን ትርጓሜውም እስትንፋስ ወይም ንፋስ ማለት ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ ተብሎ የተተረጎመው ቃል በእብራይስጡ "የእግዚአብሔር እስትንፋስ" የሚለው ሃሳብ ነው ያለው። እናም የእግዚአብሔር እስትንፋሱ በአንድ ቦታ አለ ማለት፤ እግዚአብሔር ፊቱን ወደዚያ አብርቶአል ወይም መገኘቱ (presence) በዚያ አለ ማለት ነው። በእግዚአብሔር presence መሆን ማለት በእብራይስጥ በእግዚአብሔር ፊት መሆን ማለት ነው። በዚያም እስትንፋሱ (መንፈሱ) አለ ማለት ነው። የእግዚአብሔር እስትንፋስ ተናገረ ማለትም እግዚአብሔር ተናገረ ማለት ነው። እግዚአብሔር ፊቱን ሰወረ ማለት ደግሞ እስትንፋሱ (መንፈሱ) በዚያ ቦታ የለም ማለት ነው።

በብሉይ ኪዳን "የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ" የሚለውንም ጥቅስ እብራውያን የሚረዱት "የእግዚአብሔር እስትንፋስ ፈጠረኝ" ብለው ነው። እናም ለእብራውያን የእግዚአብሔር እስትንፋስ ማለት ከእግዚአብሔር ከልቡ የሚወጣ እስትንፋሱና መገኘቱን የሚያመለክት የእግዚአብሔር አካል እንጂ፤ እኛ እንደምንረዳው ከእግዚአብሔር ተለይቶ ለብቻው ያለ ሌላ person አድረገው አይደለም የሚመለከቱት። በብሉይ ኪዳን "የእግዚአብሔር መንፈስ" ወይም "መንፈስህ" የሚሉትን ቦታዎች ሁሉ "የእግዚአብሔር እስትንፋስ" ወይም "እስትንፋስህ" እያልክ ብታነብበው ለምን አይሁዶች በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔርን መንፈስ ከእግዚአብሔር ለይተው እንደማያዩት ይገባሃል።

ጳውሎስም ተመሳሳይ ነገር በ1ኛ ቆሮ 2፡10-11 ይናገራል። "መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው። በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ በቀር ለሰው ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? እንዲሁም ደግሞ ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ለእግዚአብሔር ያለውን ማንም አያውቅም።"

ጳውሎስ በዚህ ክፍል የእግዚአብሔርን መንፈስ ከሰው መንፈስ ጋር ነው የሚያወዳድረው፡ እናም የእግዚአብሔር የውስጠኛው ማንነት እንደሆነ ነው የሚናገረው። የሰው መንፈስ የሰው አንዱ ክፍል እንጂ ከሰው የተለየ ሌላ person እንዳይደለ ሁሉ፤ ጳውሎስም እንዲሁ በዚህ ክፍል የእግዚአብሔር መንፈስ እንደ እግዚአብሔር የውስጥ አካል አድርጉ ነው የሚያየው።

እናም አይሁድ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር መንፈስ ከመፍጠር ጀምሮ ሌሎችንም አምላካዊ ሥራዎች ሠራ ተብሎ ተጽፎም እያለ ቢሆን እንኳን እኛ ወደ ደረስንበት መደምደሚያ ማለትም እግዚአብሔርና መንፈስ ቅዱስ ሁለት persons ናቸው ወደሚለው መረዳት ያልመጡበት አንዱና ዋነኛው ምክንያት በእኔ ግምት ቋንቋቸው ይመስለኛል። የሰው እስትንፋስ የሰው አካል እንደመሆኑ መጠን የእግዚአብሔርም እስትንፋስ የእግዚአብሔር አካል ነው እንጂ የተለየ ሌላ person ነው ብለው አያምኑም ነበር። እኛም የእግዚአብሔር መንፈስ የሚለው ክፍል ሁሉ የእግዚአብሔር እስትንፋስ እየተባለ ቢተረጎምልን ኖሮ ወደ ተመሳሳይ መረዳት እንመጣ ይሆን ነበር።
1 ዓመት በፊት ስም-አልባ የተመለሰ
–1 ድምጽ
1 ሰው፤- መንፋስስጋ ፤ እና ነፍስ ነው ። እዲሁ ደግሞ 1 አምላክ ፤- አብ (ክርስቶስ አባት በሎ የጠራው)ወልድ (አብ የምወደው ልጂ ያለልት የነበር ያለ የሚመጣ በስጋ የተገለጠ)መንፈስ ቅዱስ(ምድር ስትበጅ በውሃው ላይ ሰፍኖ የነበረ፤ ጌታ ስለውነት ሁሉ የመሰክርላችሃል የተባለለት) ነው።
አንተ ነትህ ከስጋ አይላይም ወይም ከመንፈስህ ወይም ደግሞ ከነፍስህ። አንት አንድ አንተ ነህ ባንት ውስጥ ግን የስጋ ፈቃድ ዐለ ከመንፈስህ ፈቃድ የተለየ ፈቃድህ ግን ሰለ ተለያየ አንት ሁሉት ሰው ነህ ማለት ዐይደለም። እዲሁም አሰራራቸው ሰለ ተለያየ 1አምልክ አይደለም ማለት አይደልም።1 አምላክ እራሱን የተለያየ አሰራር እኛን ለማዳን ገልጾአል ለኛ ባይሆን ኖሮ ክርስቶስ መወልድም ባልስፈለገው ለኛ ባይሆን ኖሮ መንፈስ ቅዱስም ሊያጽናናን እና ወደ እውነት ሊመራን ባልመጣ ነበር። ፍቅር ግን ግድ ስላለው ለኛ በሎ እራሱን በ3 ገለፀው። መግለፁ ግን 3 አይደርገውም አንድ አምልክ ነው። ለኛ ሲል እንጂ እርሱ ለራሱ አይደልም።
1 ዓመት በፊት ስም አልባ (7,860 ነጥቦች) የተመለሰ
1 ዓመት በፊት የታረመ ስም አልባ
ታዲያ በዮርዳኖስ እንደ ርግብ የወረደው 3ኛ አካል ከየት መጣ?
መንፈስ የሚለው ቃል "Ruah" የሚለው የብሉዩ እብራይስጥ ቃልም ይሁን፤ "pneuma" የሚለው የአዲሱ ኪዳን ግሪክ ቃል፤ ሁሉም የሚናገሩት ስለ እስትንፋስ፣ አየርና ነፋስ ነው። መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር እስትንፋስና አየር ነው። ከእግዚአብሔር ወጥቶ የሚነፍስ ንፋስ ነው። ስለዚህም በነፋስ ወይም በአየር ላይ በምትበርር እርግብ ቢመሰል አይገርምም። ልክ እርግብ በርራ ሰው ላይ እንደምታርፍ፤ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንድ ሰው ሲያዞር እንዲሁ እስትንፋሱ እርሱ ላይ ያርፋል። ያ ሰውም በእግዚአብሔር መገኘት ፊት ይመላለሳል ማለት ነው። የእግዚአብሔር እስትንፋስ እንደ እርግብ አረፈበት ማለት ግን የእግዚአብሔር እስትንፋስ እርግብ ነው ማለት ግን አይደለም።
–1 ድምጽ
ስላም ወገኖች

እስኪ እነዚን እናንብብ።

የዮሐንስ ወንጌል 4፡24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡17 ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ።

በማቴዎስ ወንጌል ኢየሱስ ይሕን አለ

19-20 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።

ይሕን ቃል በ ግሪኩ (codexsinaiticus)ከበታች የተስጠውን ሊንኩን ተጭነን ብንመለከት ይሕን ይላል።

ሊንክ

19 Go, make disciples of all nations, baptizing them into the name of the Father and of the Son and of the Holy Spirit.

እናስተውል ፤ ኢየሱስ " name" በስም አለ እንጂ " names" በስሞች አላለም!! ይህን ከተረዳን አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ መሆኑን እናውቃለን።


የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።

ሄኖክ
1 ዓመት በፊት Henok (1,610 ነጥቦች) የተመለሰ
ስለ መንፈስ ቅዱስ ያልከው ጥሩ ቢሆንም፣ ኢየሱስና አብ አንድ person ናቸው የሚለው ሃሳብ ግን ፈጽሞ መጽሃፍ ቅዱሳዊ አይደለም። ኢየሱስና አብ ሁለት person ናቸው። መጽሃፍ ቅዱስ አንድ አምላክ ብሎ በሚናገርበት ክፍሎች ሁሉ የሚናገረው ስለ ሁለቱ ሳይሆን ስለ አብ ብቻ ነው። የአንተ አመለካከት የኦንሊ ጂሰሶችን ይመስላል። ይህ ደግሞ በፍጹም ልክ አይደለም። ኢየሱስና አብ ሁለት person መሆናቸውን የሚያሳዩ በብሉይም ይሁን በአዲስ ኪዳን በጣም በጣም በጣም ብዙ ጥቅሶች አሉና ሂዱና አህዛብን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቋቸው የሚለውን ጥቅስ ብቻ ይዘን በጣም በጣም ብዙ የሆኑትን ሌሎችን ጥቅሶች መሻር አንችልም።

በዚህ ጉዳይ ከዚህ በፊት የተደረጉ የሚከተለቱን ውይይቶች አንብብ።

ስለ ኦንሊ ጂሰስ

ስለ አንድ አምላክ

ጌታ ይባርክህ!
ስላም ላንተ ይሁን

እኔ የ እዝጊያብሄርን መንፈስ "መንፈስ ቅዱስን" ካድኩ ወይንስ ክርስቶስ አባቴ ያለውን "አብን" ካድኩ ኦንሊ ጂሰስ የምትለኝ። በርግጥ ኦንሊ ጂሰስ የሚባለው እምነት Christology እንዴት እንደሆነ አላውቅም።

እኔ የተገለጸውን አልክድም አብም አምላክ ነው ወልድም አምላክ ነው መንፈስ ቅዱሰም አምላክ ነው ግን ሶስት አምላክ የለም። በርግጥ እዚ ደር ገጽ ላይ በተደጋጋሚ ክርስቶስን ከአብ የተለየ አምላክ ከሱ ዝቅ ብሎ የሚመለክ ለማለት ብዙ ጥረት ይደረጋል ፤ ይጻፋል።

ክርስቶስ እራሱ መስከሮ በዮሃንስ 10፡30 እኔና አብ አንድ ነን ያለውን ቃል እንዴት ልትቀይረው ትወዳለሕ። በብሉይ ኪዳን አንድ አምላክ የተባለውን አምላክ ባይሆን ለምንስ 10፡31 አይሁድ ሊወግሩት ደግመው ድንጋይ አነሡ። ይላል ቃሉ?

እስኪ "person" ምን ማለት ነው? "a self-conscious being" ይህን ይዘሕ አንተ የምታምንበትን Christology ግለጽልን።

ሄኖክ።
ሰላም ወንድሜ ሄኖክ

"የአንተ አመለካከት የኦንሊ ጂሰሶችን ይመስላል" አልኩ እንጂ አንተ አብን ወይም ኢየሱስን ወይም መንፈስ ቅዱስን ካድክ አላልኩም። ካስቆጣሁህ ይቅርታ እጠይቃለሁ።

ወደ ተነሳንበት ነገር ስንመጣ፤ የሰጠሁህን የመጀመሪያ ሊንክ ብታነብብ ኖሮ "እኔና አብ አንድ ነን" ያለው ቃል ምን ማለት እንደሆነ በግልጽ ትረዳው ነበር። እባክህን እንደገና አንብበው። አንተ እንደምታስበው እኔም አብም አንድ person ነን ማለቱ አይደለም።

አንድ አምላክ ስለሚለውም እንዲሁ አዲስ ኪዳን በግልጽ ስለ አንድ አምላክ ሲናገር ሁል ጊዜም አብን ብቻ እንጂ ኢየሱስንና አብን በአንድ ላይ ጠቅልሎ እንዳልሆነ ሁለተኛ የሰጠሁህ ሊንክ ላይ ተብራርቶ ታገኛለህ። ከላይ ያሉትን ሁለቱን ጥቅሶች ሳታነብብ ግን እነዚያን ሃሳቦች እንደገና እዚህ መድገሙ ጥቅም የለውም።

በሚገባ ካነበብካቸው በኋላ ከወደድክ ውይይታችንን እዚህ መቀጠል እንችላለን።

person ለሚለው በአማርኛ ትክክለኛ ቃል ስለማላውቅ ነው የእንግሊዝኛውን የምጠቀመው። ለምሳሌ ቃሉ እንደሚለው ባልና ሚስት አንድ ናቸው ወይም አንድ አካል ናቸው። ሆኖም አንድ person ግን አይደሉም። ሁለት ራሳቸውን የቻሉ persons ናቸው እንጂ። ምንም እንኳን በእግዚአብሔር ፊት እንደ አንድ አካል ቢታዩም፤ ሁለት person መሆናቸው ግን ተለወጠ ማለት አይደለም። አንድ ናቸው የሚለው ቃል እንግዲህ የህብረታቸውንና የግንኙነታቸውን ጥልቀት ለመግለጽ እንጂ ሚስትዮዋም ራሷ ባል ናት ወይም ባልየውም ራሱ ነው ሚስት እናም ሁለት person የለም ማለት ግን አይደለም። ይሄ አንተ የጠቀስከው የዮሓንስ ወንጌል ክፍል ላይ ያለው የግሪኩ ቃል ራሱ፤ ለደቀመዛሙርትም አንድነት ተጠቅሷል። ለማናቸውም ከላይ የሰጠሁህን ሁለት ሊንኮች በሚገባ አንብባቸው።

ጌታ ይባርክህ።
ወንድም ስም-አልባ

ገጾቹን አነበብክኝ "ስም-አልባ" ስለሆንክ አንተ የትኛው እንደሆንክ በርግጥ ማውቅ ያስቸግራል። ልገምት ከሆነ ይህን ከበታች ያለውን ቃል ያልከው አንተ ትመስለኛለሕ።

ኢየሱስ ከአብ እንደሚያንስና አብ ኢየሱስን መብለጥ ብቻ ሳይሆን የኢየሱስ አምላክም እንደሆነ ተጽፎአል።

እዛው ደረ ገጽ ላይ በተብራራ በትክክል ሌላው "ስም አልባ" ገልጾልሕ ሊስረዳሕ ሞክሮ የ መጽሃፉን ቃል ስትለዋውጥበት ። ክ ሃይማኖትሕ ቃሉን እንድትውድ አሳስቦሕ ቆጭቶል።

እስኪ "person" ምን ማለት ይመስልሃል? "person" ስትል በሃሳብሕ ምን እየ ቀረጽክ ነው?

ይህ ቃል ለስው እንኮን ስንጠቀምበት ለዘመናት አከራካሪ ቃል እንደነበረስ ታቃለህ? አሁነስ በየ ፍርድ ቤቱ እንዴት እንደሚቶረጎም ታቃለህ? እስኪ ለስው እንኮን መግለጽ የሚከብደው "Personhood " ለፈጣሪ ስትጠቀምበት ምን እያልኽ እንደ ሆነ አብራራ?

እስኪ ይሕን አንብብ።

Hebrews 1፡3 who, being the effulgence of his glory and the exact image of his substance, bearing onward also all things by the word of his power, when he had through himself made a cleansing of sins sat down at the right hand of the majesty on high,

ስለ ክርስቶስ ስናወራ ስማይ እና ምድር ስለፈጠረውን አምላክ እያወራን መሆኑን አትሳት።

ሄኖክ


ሰላም ሐኖክ ሰላምህ ይብዛ ተባርክ በደንብ አቅርበሀዋል መልሱን ያልወደ - ደምጽ በሰጡ አይግራምህ።
ጌታ እግዚአብሄር የባርክህ።
ሰላም ወንድሜ ሄኖክ

በቅድሚያ የኢየሱስን አምላካዊ ባህርይ እየተቃወምኩ አይደለም። ብዙ ቦታ ቃሉ ስለሚናገር ያንን እቀበላለሁ። እኔ እያልኩ ያለሁት አንዱ አምላክ የሚባለው ግን አብን ብቻ ነው እያልኩ ነው። ልክ ነው እግዚአብሔር በኢየሱስ ዓለማትን ፈጥሮአል። ኢየሱስም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ነው፤ ሆኖም ኢየሱስ የማይሞተውና የማይታየው፣ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን የሚኖረው የአንዱ እግዚአብሔር ነጸብራቅና image ነው እንጂ ራሱ ያ አንዱ እግዚአብሔር ወይም Yahweh አይደለም።
Quote:
1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ
6፥16 እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን።

አንድ እግዚአብሔር አለና፤ ኢየሱስ ደግሞ በዚህ በአንዱ እግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለ መካከለኛ ነው እንጂ ራሱ ያ አንዱ እግዚአብሔር አይደለም።
Quote:
1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ
2፥5 አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
8፥6 ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፥ ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።

ስለዚህ እያልኩ ያለሁት አዲስ ኪዳን ስለ አንዱ እግዚአብሔር ወይም ስለ አንዱ አምላክ ሲናገር ሁልጊዜም ስለ አብ እንጂ የሚናገረው አብንና ወልድን ጠቅልሎ በአንድ ላይ አንድ እግዚአብሔር ወይም በአንድ ላይ አንድ አምላክ ብሎ አይደለም እያልኩ ነው። ይህ ደግሞ ከብሉይ ኪዳኑ ጋር የሚስማማ ነው።

ጌታ ይባርክህ!
ሰላም ወንድም

አዎን የ ጆሆቫ ዊትነስ ተከታይ እንደሆንክ ተረድቻለሁ የ ዋች ታወርንም "Christology" አምብቢያለሁ በርግጥ "This Means Everlasting Life" የሚለው የ ዋች ታወር መጽሃፍ ላይ ጆሆቫ ዊትነሶች ክርስቶስ መላኩ ሚካኤል እንደሆነ እንደሚያምኑ ያስተምራል።

እኔ የምመክርህ " the New World Translation" የሚለውን ዋች ታወር የሚሳትመውን መጽሃፍ ቅዱስ በግራሕ እጅ ይዘህ ከዘመናት የነበሩተን ኮዴክሶች እንደነ "codexsinaiticus" ያሉት ጋር እያዛመድክ አንብበው።

ግዜ ከሌለህ እንዚን ከበታች የተጻፉተን እንኮን አንብብ እንዴት አድርጎ የ ዋች ታወር ሶሳይቲ ቃሉን እንደሚያጣምም ታስተውል ይሆናል።

1] John 1:1 In the beginning was the Word, and the Word was with God, and the Word was God. 2 He was in the beginning with God.

ምንም እንኮን God የሚለውን ለመግለጽ ሁልም ላይ አንድ አይነት የግሪክ ቃል ቢገኝ ፤ ዋች ታወር ይህ ቃል ክርስቶስ አምላክ መሆኑን ስለሚገልጽ እንደዚ አድርገው ቀይረውታል።

John 1:1 In [the] beginning the Word was, and the Word was with God, and the Word was a god
. 2 This one was in [the] beginning with God

2] Acts 20: 28 reads "...the church of God which He purchased with His own blood"

ዋች ታወር ይህ ቃል ክርስቶስ አምላክ መሆኑን ስለሚገልጽ የ መጨረሻውን ቃል `with the blood of His own'. ብለው ቀይረውታል።

3)Luke 23: 43, "Assuredly I say to you: `today you will be with Me in Paradise'"

ዋች ታወር ይህ ቃል ስው ከሞት በሆላ በመንፈስ እንደሚኖር ስለሚገልጽ ጆሆቫ ዊትነስ ኣስተያየት ጋር ስለሚጋጭ የክስቶስን ቃል ቀይረው እንደዚ ብለውታል።

"I say unto you today: `you shall be with me in Paradise...'


4) ዋች ታወር እንደሚያስተምረው ክርስቶስ በስጋ አላረገም ስጋው በመላኢእክት ተደብቆ በመንፈስ ቅዱስ በመንፈስ ነው ያረገው። ይህ ደሞ በጭራሽ የተሳሳተ ነው።

በ ሉቃስ ወንጌል 24፡ክርስቶስ ይሀን አለ ... 39 እኔ ራሴ እንደ ሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት፥ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ዳስሳችሁ እዩ አላቸው። 40 ይህንም ብሎ እጆቹንና እግሮቹን አሳያቸው። 41 እነርሱም ከደስታ የተነሣ ገና ስላላመኑ ሲደነቁ ሳሉ። በዚህ አንዳች የሚበላ አላችሁን? አላቸው።42 እነርሱም ከተጠበሰ ዓሣ አንድ ቁራጭ፥ ከማር ወለላም ሰጡት፤ 43 ተቀብሎም በፊታቸው በላ።

ሌላም ሌላም አለ ግን ግዜው ካለሕ እራስሕ አነጻጽረው።

ሄኖክ
አዬ ወንድሜ ሄኖክ፤ ምነው ምነው ጠቅላላ ውይይቱን ወደ ተዛባ መስመር ወሰድከው። እኔ ፈጽሞ የጆቫ እምነት ተከታይ አይደለሁም። እንዲያውም አጥብቄ ከምሞግታቸው ሰዎች አንዱ ነኝ። እኔ እኮ አንተን ኦንሊ ጂሰስ ተከታይ ነህ ሳልልህ፤ ገና ለገና ሃሳብህ ኦንሊ ጂሰስ እምነት ይመስላል ስላልኩህ እንዴት እንደተሰማህ ረሳኸው እንዴ? ታዲያ በራስህ ሲያደርጉብህ የማትወደውን እንዴት በሙሉ ልብ ሆነህ የጆቫ ዊትነስ ተከታይ ነህ ትለኛለህ። እኔስ እንዲህ ያልሆንኩትን ስትለኝ አልከፋም እንዴ?

በል ወንድሜ የጆቫን እምነት እኔ መጽሃፍ ቅዱስን መሰረት አድርጌ ብዙ የምቃወምበት ምክንያቶች አሉ። ከእምነቱ አልፎ የድርጁትንም አሰራር ሳይቀር ነው የማልቀበለው። ስለዚህ እጅግ ስተሃል በዚህ ጉዳይ። ያቀረብኩልህን የመጽሃፍ ቅዱስ መረጃዎች ከማንበብ ይልቅ ወደሌላ ነገር ውስጥ ገባህ።

እኔ ወደዚህ መረዳት የደረስኩት እውነቱን ለመናገር የቱንም ሃይማኖት በመከተል ሳይሆን፤ በራሴ ቃሉን በመመርመር ነው። ለማናቸውም፤ የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ እውነት ሁሉ ሁላችንንም ይምራን።
ስላም ላንተ ይሁን

እኔ ያልኩትን ብል አይድነቅህ እኔም እንዳንተ ጭቃ ነኝ እና።

የምታምንበትን ስነ ክርስቶስ " Christology" በተደጋጋሚ እንድታብራራልኝ ጠየኩ ወደሌላ ገልጾች አመላከትከኝ እነዜያን ገልጾችን በተደጋጋሚ አንብቤ አንተ የጻፍከው የመስለኝን ይሕን ብልሃል ወይ ብልሕ መልስ ሳትስጥ ሌላ ማብራርያ ቀጠልክ። ገልጹ ላይ ተመልሼ የ ጻፍከውን እያዛመድክ አነበብኩ ፤ አንብቤም አንተ ሁለት አምላክ " polytheism " እንደምታምን ተረዳሁ።

እና አሁንም እለዋለሁ ከርስቶስ ከአብ ዝቅ ብሎ የሚመለክ አምላክ የሚል አስተያየት የ ጆሆቫ ዊትን መስረት ነውና አንተም ይሕን ስለምታምን ብታቀውም ባታቀውም የወች ታወር የተሳሳተ ትምርት ነው በየ ገልጹ የምትነድፈው።

በርግጥ እዚ ድረ ገጽ ላይ የ ሃይማኖት ድኖምኔሽን ሳንከፍል መጽሃፉን ይዘን እንድንማር የሚል አስተያየት ቢኖረም ፤ የትኛውን መጽሃፍ መመርኮዝ እንዳለብን ማወቕ ያስፈልጋል።

ሄኖክ
አዬ ወንድሜ ሄኖክ

ውይይትን መጽሃፍ ቅዱስን ተመርኩዞ ከማስረዳት ይልቅ ወደ ስም ማጥፋት (libeling, allegations, defamation) ውስጥ ገባህ። ይህ ለሃበሻ አማኞች በጣም የተለመደ ነገር ነው። የተነገረውን ሃሳብ ከመጽሃፍ ቅዱስ ከማሳመን ይልቅ ቶሎ ወደ ስም ማጥፋት የመሄድ ዝንባሌ አለን። የፕሮቴስታንት እምነት ሲጀመር እስከ አሁንም ድረስ አንዳንድ የኦርቶዶክስ አማኞች እንደሚያድረጉት፤ እምነቱን ከመጽሃፍ ቅዱስ ሞግተውና ቻሌንጅ አድርገው በቃሉ ከማሸነፍ ይልቅ፤ ብዙ ብዙ ስም መስጠትና ስም የማጥፋት ዘመቻ ነው የጀመሩት። ፕሮቴስታንቶችም በአብዛኛው ከዚያ አይለዩም። ከለመዱት የተለየ ነገር ሲመጣ ፈጥነው ስም ማጥፋት ይቀናቸዋል።

ግን ጆቫ ነህ ብትለኝ ወይም አሪዎስ፤ ከተገለጠለኝና ከገባኝ ነገር ፍቅቅ አልልም። በቃሉ አሳምነህ ካልረታኸኝ በቀር። እዚህ ላይ ከአንተ ጋር ያለኝን ውይይት አቆማለሁ፤ ፍሬያማ መማማሪያ ይሆናል የሚል ተስፋ ስለሌለኝ።

እግዚአብሔር ይባርክህ ወንድሜ!
ወንድም ቅር ካስኝሁሕ ይቅርታ።

ጽህፍትህን በስምሕ ስለማትጨርሰው እርግጠኛ ሆኜ እንኮን ሁሉም ላይ አንተነህ ባልልም ፤ልክ የአንተ አስተያየት ያላቸው ጽሃፊዎችን ብዙ የዚ ገጽ ደምበኞች በተደጋጋሚ ሊያስረዱህ ሞክረዋል።

እኔ እንደተረዳሁት ኣጠር አድርጌ ሶስት አንተ የምታምንባቸውን ልጥቅስና ባጭሩ ልቆጭ።

1) ኣብ እግዝያብሔር አምላክ መሆኑን ታምናለሕ
2) ክርስቶስ እግዝያብሔር አምላክ መሆኑን ታምናለሕ
3) ሁለቱ የተለያዩ እግዝያብሔር አምላኾች መሆናቸውን ታምናለሕ


እና እኔ የምለው በ ትንቢተ ኢሳይያስ 43፡10-11 ይህን ከበታች ያለውን አምላክ እንዴትስ ሁለት ታደርገዋለሕ?

ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ፥ እናንተ የመረጥሁትም ባሪያዬ ምስክሮቼ ናችሁ ይላል እግዚአብሔር፤ ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኋላ አይሆንም። እኔ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም።

ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው!! ይሕን አምብብ።

የማቴዎስ ወንጌል 1፡23 እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።

በ ትንቢተ ኢሳይያስ 7፡14 የተባለው ደሞ ይሕ ነበር።

ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።

ሄኖክ

ወንድሜ ሄኖክ

አንዳንድ የቃላት ችግር ያለ ይመስለኛል። አንደኛ አምላክ ወይም በእንግሊዝኛው God የሚለው ቃል ብቻውን ብዙም እግዚአብሔርን ብቻ የሚያሳይ ቃል አይደለም። በመጽሃፍ ቅዱስ ሰዎች አምላክ ወይም አምላኮች ተብለው ተጠርተዋል። ሰይጣን የዚህ ዓለም አምላክ ተብሏል። እንዲሁም አህዛብ የሚያመልኳቸው አጋንንቶች በሙሉ አማልክት ማለትም በብዙ ቁጥር ነው፤ አምላኮች ተብለው ተጠርተዋል።

ኢየሱስም አምላክ (God) ተበሎ ተጠርቶዋል። ጥያቄው ያለው ግን መጽሃፍ ቅዱስ ስለ አንዱና ብቸኛው አምላክ ሲናገር በዕብራይስጡ Yahweh የሚለውን ቃል ነው የሚጠቀመው። ይሄ አንዱና ብቸኛው አምላክ የሚባለው፤ የሁሉ ጌታና አለቃ፤ የአማልክት አምላክ ወይም የአምላኮች አምላክ የሚባለው ነው።

ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ Yahweh አንድ ብቻ እንደሆነና አንድ እግዚአብሔር ብለን የምንጠራው እርሱ እንደሆነ ነው መጽሃፍ ቅዱስ የሚነገረን። ለምሳሌ መዝሙረ ዳዊት 110፥1 ላይ "110፥1 እግዚአብሔር (Yahweh) ጌታዬን፦ ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው።" ይላል። እዚህ ክፍል ላይ ያ እንዱ እግዚአብሔር Yahweh ዳዊት ጌታዬ ብሎ ለሚጠራው ለመሲሁ የገባለትን ቃል ነው የሚነግረን። እዚህ ላይ ግልጽ እንደሚያደርገው መሲሁ Yahweh አይደለም። Yahweh የመሲሁ ማለትም የክርስቶስም አምላክና ጌታ እንጂ። ኢየሱስ ራሱ ነው በምድርም እያለም ይሁን ካረገም በኋላ Yahweh አምላኩና አባቱ እንደሆነ የሚናገረው።

በብሉይም ይሁን በአዲስ ኪዳን አንድ እግዚአብሔር የሚባለው የአማልክት አምላክና የኢየሱስም አምላክ የሆነው Yahweh ብቻ ነው። አንድም የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል አውጠተህ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ወይም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ እግዚአብሔር ወዘተ የሚል ጥቅስ ልታሳየኝ አትችልም። አንድም ቦታ በመጽሃፍ ቅዱስ አብና ወልድን ወይም አብን ወልድንና መንፈስ ቅዱስን በአንድ ላይ አጠቃልሎ አንድ አምላክ ያለበት አንድም ጥቅስ የለም። እግዚአብሔር አብ፣ እግዚአብሔር ወልድ ወዘተ የሚባል አባባል መጽሃፍ ቅዱስ ጨርሶ አያውቀውም።

ሁል ጊዜም ስለ አንዱ እግዚአብሔር ወይም ስለ ብቸኛው አምላክ ወዘተ ብሉይም ይሁን አዲስ ኪዳን ሲናገር አብን ወይም Yahwehን ብቻ ነው። የኢየሱስም የራሱ መረዳት ይህ ነበር።
Quote:
የማርቆስ ወንጌል
10፥18 ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም።

የዮሐንስ ወንጌል
17፥3 እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።

የራሱ የኢየሱስን መረዳት ብንመለከት፤ ስለ አንዱ እግዚአብሔር ወይም ስለ ብቸኛው እውነተኛ አምላክ ሲናገር ሁልጊዜም አብን ነው የሚለው። አዲስ ኪዳንንም በሙሉ ብታነብብ ሁልጊዜም አንዱን እግዚአብሔርንና ኢየሱስን ጎን ለጎን አድርጎ እንጂ አንድ ላይ እግዚአብሔር አብ እግዚአብሔር ወልድ እያለ የጠራበት ስፍራ የለም። እግዚአብሔርና ኢየሱስ ነው የሚለው እንጂ፤ የትም ቦታ እግዚአብሔር አብና እግዚአብሔር ወልድ አይልም።

ኢየሱስ ሁሉጊዜም ቢሆን ራሱን ከአብ እንደሚያንስና ለአብም እንደሚገዛ ነው የሚያቀርበው። አብ የሚያውቀው ኢየሱስ ደግሞ የማያውቀው ነገር እንዳለም ይናገራል። ያለ አንዱ አምላክ አብ ከራሱ ምንም ማድረግ እንደማይችል ነው የሚናገረው። የዮሃንስን ራእይ ቁጥር 1፡1 ብታነብብ ስለ መጨረሻው ዘመን ዮሃንስ ያየው ራእይ ያ አንዱ እግዚአብሔር ለኢየሱስ የሰጠውና የገለጠለት ራእይ ነው።

ምንም እንኳን እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ስላደረገው ኢየሱስ ሁሉን የሚገዛ ይሁን እንጂ፤ ስልጣኑ ሁልጊዜም ቢሆን ከእግዚአብሔር በታች እንጂ የትም ቦታ እግዚአብሔር ለኢየሱስ ይገዛል የሚል ነገር የለም። ወደፊትም በመጨረሻም ዘመን ቢሆን ኢየሱስ ራሱ ለዘላለም ለአንዱ እግዚአብሔር እንደሚገዛ ነው መጽሃፍ ቅዱስ የሚያስተምረን።
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15
27 ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቶአልና። ነገር ግን፦ ሁሉ ተገዝቶአል ሲል፥ ሁሉን ካስገዛለት በቀር መሆኑ ግልጥ ነው
28 ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል

ሐዋርያቱም ሁሉ ያስተማሩት አንዱ እግዚአብሔር የኢየሱስ አባትና አምላክ ነው፤ ኢየሱስ ደግሞ በአንዱ እግዚአብሔር በYahweh እና በሰው መካከል ያለ መካከለኛ ነው አሉ እንጂ አንድም ቦታ ኢየሱስ ራሱ አንዱ እግዚአብሔር ነው አላሉም። እስቲ ጳውሎስ ስለ አንዱ እግዚአብሔር ያለውን መረዳት በጥሞና ተመልከት፤ ኢየሱስ ከነበረው መረዳት ጋ አንድ አይነት ነው።
Quote:
1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ
2፥5 አንድ እግዚአብሔር አለናበእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው

ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
8፥6 ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፥ ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4
4 በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤
5 አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤
6 ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ

አማኑኤል ወይም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚለውም ቃል ቢሆን፤ ልክ ኢየሱስን አንዱ እግዚአብሔር ያደረገው የሚመስለን በስላሴ ትምህርት መነጽር ለምናየው ለእኛ ነው እንጂ፤ በመጀመሪያ በራሳቸው ቋንቋ ለተጻፈላቸው ለአይሁዶች ይሄ ምንም ማለት አይደለም። እግዚአብሔር በህዝቡ መሃል መኖሩና ማደሩ በመጀመሪያ በመገናኛው ድንኳን አማካኝነት በኋላም በቤተመቀደስ አማካኝነት አይሁዶች የሚያውቁት ነገር ነው። ሆኖም ግን እግዚአብሔር በርሱ ሆኖ በሰዎች መካከል የሚኖርበት የመገናኛው ድንኳኑ ራሱ ያ አንዱ እግዚአብሔር ነው ብለው አያውቁም። ቤተመቅደሱም እግዚአብሔር በህዝቡ መካከል የሚኖርበት የእግዚአብሔር ማደሪያ እንጂ መቅደሱ ራሱ እግዚአብሔር አይደለም።

ልክ ነው ኢየሱስ በሚያደርጋቸው ነገሮችና ቃሉም የሚመሰክረው፤ አሁን የአዲስ ኪዳን ማደሪያና እግዚአብሔር ሰዎችን የሚገናኝበት ስፍራ ኢየሱስ ራሱ ነው። ስለዚህ ነገር በጣም ብዙ ማለት እችል ነበር፤ ሆኖም አንድ ምሳሌ ብቻ ልጥቀስና ልጨርስ። ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ መጥቶ ያደረጋቸውን ድርጊቶች በጥንቃቄ በማርቆስ 11 እና ማርቆስ 12 ላይ ስናነብብ፤ በድሮው ቤተመቅደስ ላይ እግዚአብሔር እንደሚፈርድበትና እንደሚፈርስ ብቻ ሳይሆን፤ ስለ አዲሱም ቤተመቅደስ ተናግሮአል።

በመጀመሪያ በመቅደስ የሚነግዱትን ካስወጣ በኋላ ከነብዩ ኤርምያስ በመጥቀስ "ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ትባላለች ... እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት..." በማለት እግዚአብሔር በዚህ ቤተመቅደስ ላይ እንደሚፈርድበትና እንደሚያፈርሰው ተናግሮአል። ይህ ቃል በትንቢተ ኤርምያስ 7 የተነገረበትን ቦታ ሄደን ስናየው የሚያወራው የእግዚአብሄር ማደሪያ የነበረችውን ሴሎን እግዚአብሔር እንደተዋትና እንደፈረች፤ ቤተመቅደሱም እንደሚፈርስና በቤተመቅደስ ላይ እግዚአብሔር እንደሚፈርድ ነው።

ከዚያም በመቀጠል የወይኑን ስፍራ አከራቶ ስለሄደውና ገበሬዎቹ ግን በጊዜው ፍሬ ከመስጠት ይልቅ የባለቤቱን መልእክተኞችና ልጁንም ጭምር የሚገድሉበት ምሳሌና በምሳሌውም መደምደሚያ ላይ ያለው፤ የወይኑ አትክልት ጌታ ገበሬዎችን መጥቶ እንደሚያጠፋቸው የተናገረውም እንዲህ ስለ ፍርድ ነው። የድሮው ቤተመቅደስና መሪዎችም ጭምር ላይ እግዚአብሔር እንደሚፈርድ ነው።

በመጨረሻ ግን አዲስ ቤተመቅደስ እግዚአብሔር እንደሚሰራ የዛም ቤተመቅደስ የመሠረት ድንጋይ ወይም የማዕዘን ራስ፤ ራሱ ክርስቶስ እንደሆነ ነበር የተናገረው። ስለዚህ ኢየሱስ በሰዎች ክፋት የረከሰውን በተመቅደስ የሚተካው የአዲሱ ቤተመቅደስ የመሰረት ድንጋይ እንደሆነ ግልጽ ነገር ነው።
Quote:
የማርቆስ ወንጌል
12፥10-11 ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፥ ለዓይኖቻችንም ድንቅ ነው። የሚለውን ይህን መጽሐፍ አላነበባችሁምን?

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2
19 እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም።
20 በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ (የመሰረት ድንጋይ) ክርስቶስ ኢየሱስ ነው
21 በእርሱም ሕንጻ ሁሉ እየተጋጠመ በጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንዲሆን ያድጋል
22 በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ።

ስለዚህ አማኑኤል የሚለው ቃል ለእኛ በስላሴ መነጽር እንደምናየው ሳይሆን ያለ ስላሴ መነጽር ለሚያዩት አይሁዶች ሃዋርያትና ነብያት፤ ስለ አዲሱ ኪዳን የሚያበስር፡ የአዲስ ኪዳን የእግዚአብሔር በተመቅደስ የመሰረት ድንጋይ ክርስቶስ እንደሆነ የሚያሳይ ነገር ነው እንጂ ኢየሱስ አንዱ እግዚአብሔር Yahweh ሆነ ማለት አይደለም።

ብዙ የስላሴ አይነት የተምታታና የሚያምታታ፤ "አንድ እግዚአብሔር ነገር ግን ሶስት person" ወይም ደግሞ "ኢየሱስም አብ ነው አብም ኢየሱስ ነው" ወዘተ ወደሚል ግራ ወደገባው መረዳት የምንመጣው የብሉዩን የአይሁድን እምነት እንደሚገባው የማናውቅ እኛ እንጂ በብሉይም ይሁን በአዲስ ኪዳን የነበሩ አይሁድ ነብያትና ሃዋርያት እንዲህ የተምታታ ነገር አልነበራቸው። አንዱ እግዚአብሔር ማለትም Yahweh እርሱ የኢየሱስ አምላክና አባት የሆነው እንደሆነና አንድ ሲባል አንድ እንጂ ሌላ ሶስቱ አንድ ወይም አንዱ ሶስት ወዘተ የሚል የተምታታ ፎርሙላ እንደማያስፈልገው ግልጽ ነበር ለእነርሱ። ቃሉ መጀመሪያ በተጻፈበት በዕብራይስጡ የአይሁድ አውድ context ስናየው ሁሉም በጣም ግልጽና ቀላል ነው። አንዱ ሶስት፤ ሶስቱ አንድ ወዘተ የሚል ትምህርት በተከታዮቹም እንደሚታየው፤ እንቆቅልሹን ከመፍታት ይልቅ በአብዛኛው ግራ መጋባት ነው ያተረፈው።
ስላም

ሙሉውን ገልጽ ላናነበበ መጀመርያ የጻፍካቸው ሃሳቦችን አንብቦ ፤ እኔ አንተ የምታምነው ብዬ እንደ ቁጥር ሁለት ያስቀመጥኩትን " ክርስቶስ እግዝያብሔር አምላክ መሆኑን ታምናለሕ" የሚለውን ለመቃወም ያቀረብከው ይመስላል።

ግን አይደለም ምክንያቱም ክርስቶስ አምላክ መሆኑን ታምናለሕ ፤ ቁጥር ሶስት ላይ ያስቀመጥኩትንም "ሁለቱ የተለያዩ እግዝያብሔር አምላኾች መሆናቸውን ታምናለሕ" እና እንዴት ሁለት አምላክ ብልሕ መልስሕ ባጨሩ ምን ይሆናል?


ቶማስስ መስክሮ በ ዮሐንስ ወንጌል 20፡28 ቶማስም። ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት። ክርስቶስ እሱ ጌታና አምላክ ባይሆን ተው ተሳሳታሃል አይለውምን? ግን ለነገሩ ክርስቶስ አምላክ መሆኑን ብገልጽ አይ መለኮታውነቱን አምናለሁ ትላላህ ፤ ታዲያ ሁለት አምላክ ታምናላሕ ብልሕ ምን ትላላሕ?

አንተ ሃሳብ ላይ ገብቼ እግዚአብሔር እንዴት አድርገህ እንደምትቀርጸው ባይ ለመግባባት በጣም ይቀለን ነበር። አማኑኤል ወይም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚለውም ቃል ለምንድን ነው እግዚአብሔር በ ክርስቶስ መገለጽን የማያሳይሕ ፤ በገሊላስ የተረማማደው እሱ በስጋ የተገለጠ እግዚአብሔር መሆኑስ እንዴት ግር ይልሃል?

እስኪ አንተ ያመላከትከውን የመገናኛው ድንኳኑ እንመልከት በ ኦሪት ዘጸአት 40፡

34፤ ደመናውም የመገናኛውን ድንኳን ከደነ፥ የእግዚአብሔርም ክብር ማደሪያውን ሞላ።
35፤ ደመናውም በላዩ ስለ ነበረ የእግዚአብሔርም ክብር ማደሪያውን ስለ ሞላ ሙሴ ወደ መገናኛው ድንኳን ይገባ ዘንድ አልቻለም።
36፤ ደመናውም ከማደሪያው በተነሣ ጊዜ የእስራኤል ልጆች በመንገዳቸው ሁሉ ይጓዙ ነበር።
37፤ ደመናው ባይነሣ እስከሚነሣበት ቀን ድረስ አይጓዙም ነበር።
38፤ በመንገዳቸውም ሁሉ በእስራኤል ቤት ሁሉ ፊት የእግዚአብሔር ደመና በማደሪያው ላይ በቀን ነበረና፥ እሳትም በሌሊት በዚያ ላይ ነበረና።


እና ምን ትላላሕ ይህ በቀን ደመና በሌሊት እሳት የነበረው አይ ይሄ እግዚአብሔር አይለም ትላለሕን ? በገሊላ የተመላላስው ክርስቶስም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር አማኑኤል ተብሎል እና በስጋ የተገለጠ እግዚአብሔር ነው ብልህስ አይ አይደለም ይሕ በቤት መቅደሱ የነበረው በቀን ደመና በሌሊት እሳት ይመስላል እንጂ አንድ እግዚአብሔር አይደለም ትላላህን? እግዚአብሔር እንዴት ሊገለጽ ትወዳለሕ?

እስኪ እግዚአብሔር በ ብሉይ ኪዳን የተገለጽባቸውን እንጥቀስ

9፤ ሙሴም አሮንም ናዳብም አብዩድም ከእስራኤልም ሰባ ሽማግሌዎች ወጡ፤
10፤ የእስራኤልንም አምላክ አዩ፤ ከእግሩም በታች እንደ ሰማይ መልክ የሚያበራ እንደ ብሩህ ሰንፔር ድንጋይ የሚመስል ወለል ነበረ።


እና እዚ ላይ የተገለጸው ትእይንት አይ ይሕ ትእይንት ነው እንጂ እግዚአብሔር አይደለም ትላላሕ።

እና ባጭሩ በአዲስ ኪዳን አማኑኤል ወይም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሲል በትክክል ያ አንዱ እግዚአብሔር በስው መልኩ ከእኛ ጋር ማላት ነው።

ሄኖክ

የተዛመዱ ጥያቄዎች

3 መልሶች
1 መልስ
4 መልሶች
1 ዓመት በፊት መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
2 መልሶች
የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2013 by iyesus.com
Terms of use | Contact us