ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Monday, 23 July 2018
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

መንፈሳዊ ህይወት ማለት ምን ማለት ነው?ስዎች ለምንስ መንፈሳዊ ህይወትን መኖር አልቻሉም?

Mar 14, 2012 መንፈሳዊ ሲሳይ (120 ነጥቦች) የተጠየቀ

2 መልሶች

0 ድምጾች
መንፈሳዊ ህይወት ማለት እንደራስ ፈቃድ ሳይ ሆን እንደአምላክህ ፈቃድ በመንፈስ መመላለስ ማለት ነው ፡፡ እንደው እንደዘመኑ ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ነን እያሉ በአፍ መንፈሳዊ በልብ ግን ሰዋዊ ሆነው እንደሚመላለሱት አይደለም፡፡ ውድ ጠያቂ ሰዎች ለምን በመንፈሳዊ ህይወት መመላለስ አልቻሉም ላልከው ጥያቄ ትክክለኛ መንፈስን ተረድተው አምላካቸውን የሚያከብሩ ከ100 ቢያንስ 10 ፐርሰንት ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ሌሎቹ ግን መንፈሳዊ ነን ብለው በአልባሌ ነገር ላይ ጊዜያቸውን በማባከን አስመሳይ መንፈሳዊያን ናቸው፡፡ እነዛ ሰዎች ደግሞ መንፈስን አልተረዱትም ወይም ለምደውታል ስልክ በመንፈስ መመላለስ ማለት ለእነርሱ ቤተክርስቲያ መመላለስ ማለት ነው ፡፡ ይህ ማለት ድግሞ አንድ ሰው ቤተክርስቲያን ሄዶ አምልኮ ሲመለስ የነበረው መንፈስ ተቀይሮ መንፈሳዊ ሆኖ ሲመጣ አነዛ ሰዎች ግን እንደነበሩት ወይም ብሰው ይወጣሉ ምክንያቱም የሚሄዱት በራሳቸው ሃሳብና መንፈስ ስለሆነ፡፡ ስለዚህ ሰዎች መንፈስን ወይም የመንፈሳዊነትን ኑሮ በትክክል እስካልተረዱት ድረስ በዛውስጥ መኖር ወይም መመላለስ አይችሉም፡፡ እንዲሁ መንፈሳዊ ነን በማለት በማጭበርበር ይኖራሉ፡፡ ለምሳሌ አሁን ክምናየው መንፈሳዊ ነኝ እያሉ በተለያዩ ማህበራዊ ድህረገጽ ውስጥ ገብቶ መንፈሳዊ ሥራን ለመስራት የሚታትሩ አትራክሽን የሚፈጥሩ ቀርበክ ስታያቸው መንፈሳዊ ወይም ….ብለህ የምትላቸውም አሉ፡፡
Mar 14, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
+1 ድምጽ
ለጥያቄው ምላሽ ለመስጠት ጥቂት ለአረዳድ እንዲመች ስለነፍስ፣ ስጋና መንፈስ፣

ሰዎች የተፈጠርነው ከሥጋ፣ ከነፍስና ከመንፈስ ባህርይ ነው።የመጀመሪያውን ሰው ከምድር አፈር አበጀው ሲል «ሥጋችን» የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ሲል «ነፍሳችን» ነው።
ብዙ ተባዙ ሲባል ሰው ዝርያውን ከነፍስና ከስጋው ሌላ ሰዋዊ አካል ይተካል ማለት ነው። መንፈሳዊው ባህርይ ግን ነፍስና ስጋን ከፈጠረው ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ግንኙነት አጥብቆ በመያዝ ወይም በመጣል ላይ ይመሰረታል።
ነፍስና ሥጋውን በፈጠረው ላይ ሲያደርግ መንፈሳዊ ኃይልን ያገኛል። ይህንን ግንኙነት ሲያቋርጥ በውድቀቱ ለወደቀ መንፈስ ይገዛል ማለት ነው። ነፍስና ስጋ በተፈጠረበት ማንነት ላይ ለሁሉም (ይመንም፣አይመን) የጋራ ባህርይ ሆኖ መንፈሳዊ ተፈጥሮ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው። ሰው ብርድ ሲበርደው ወይም ሙቀት ሲያቃጥለው ስሜቱን የሚገልጸው በስጋና ነፍስ ባህርያቱ ሲሆን መንፈሳዊነቱ ግን በስሜት ህዋሳት አይታወቅም። ይልቁንም በእምነት እንጂ!
አዳም በበደለ ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር የነበረውን የመንፈስ ግንኙነት እንዲቋረጥ አድርጓል። የመንፈሳዊ ማንነቱ መጥፋት በስጋው ላይ አሜከላና እሾህን አተረፈ። በነፍሱም ለራሱም ሆነ ለብዙዎች ሞትን ተቀበለ።(ሮሜ 5፣15)
ክርስቶስም ይህንን የመንፈስ፣የነፍስና የሥጋ ሞትን ሊሽር መጣ፣ ያኔም ተቀደስን።

«የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ» 1ኛ ተሰሎ 5፣23
ለድነት ማንም ቢሆን ዳግም መወለድ አለበት የምንለው የነፍስና የስጋ ልደትን የሚያድሰውን መንፈሳዊ ተፈጥሮውን ከእግዚአብሔር እንዲቀበል ነው። ኢየሱስም የነገረን ይህንኑ ነው።
«ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው» ዮሐ 6፣63
ለኒቆዲሞስም ሲነገረው የሰማነው «ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው» ዮሐ3፣6

ሰው በስጋው ኃጢአትን ሲሰራ መንፈስን ይቃወማል። ነፍስን ስጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን ፍሩ የተባለው ከመንፈስ ሞት እንድንድን ነው። የመንፈስ ሞት ደግሞ ከእግዚአብሔር አንድነት መለየት ነው።
«ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ» ገላ 5፣16
ነፍስ በስጋና በመንፈሳችን መካከል ያለች የሕያው ማንነት አካል ነች። በስጋችን ኃጢአትን ስንፈጽም ነፍሳችን መንፈሳዊ ኃይሏን ታጣለች። ያኔም ዘላለማዊ ሞት ሆነ ማለት ነው።
ማቴ10፥28
ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ። በማለት የስጋና የነፍስ ሞት ዘለዓለማዊ የሚሆነው መግደልና ማዳን ከሚቻለው ከእግዚአብሔር ጋር ባለው ግንኙነት እንጂ በሚታየው ሞት እንዳልሆነ ተናግሯል።
እንግዲህ እንደጥያቄው የዳነ ሰው መንፈሳዊ ማንነት ማለት በስጋው፣በነፍሱና በመንፈሱ ሁሉ ለእግዚአብሔር ፈቃድ ሲታዘዝ ማለት ሲሆን ከዚህ ውጪ ከሆነ ማለት ለዘላለማዊ ሞት ራሱን አዘጋጀቷል ማለት ነው።
«የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ» 1ኛ ተሰ 5፣23
ለምን መንፈሳዊ ሕይወትን መኖር አልተቻለም? ለሚለው ጥያቄ አጭር መልስ ነፍስና ስጋችን ለመዋጥ የሚፈልግ መንፈስ ስላለ ነው። ሕይወትን ከሚሰጥ ማንነት ውጪ መሆን ማለት ሞትን ከሚያመጣው ማንነት ጋር መስማማት ማለት ነው። ይህም አውሬ የሚባለውን ለማግኘት ሌሊትና ቀን ይዞራል።
«በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና» 1ኛ ጴጥ 5፣8
የዳነ ሰው በዳነ ማንነቱ ከዚህ አንበሳ መከላከል የሚያስችለውን ትጥቅ ካልያዘ መንፈሳዊ ሕይወቱን ጠብቆ መከላከል አይችልም።

«የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ» ኤፌ 6፣11-13
ይለናል። ሰው ይህ የጦር እቃውን በኃጢአቱ ጥሎ ሲያበቃ የታጠቀ መስሎ ለመታየት ሊሞክር ይችላል።
እነዚህ በሕይወቱ ውስጥ ሲጠፉ ማንነቱ ይገለጻል።
«የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው» ገላ 5፣22
Mar 14, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2018 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...