ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Thursday, 3 December 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ማቴዎስ 24:4-14 የሚናገረው ስለ እስራኤል ነው ወይስ ስለ ቤተ ክርስቲያን ነው?

ስለ ቤተክርስቲያነ ከሆነ በእግዚኣብሔር ቃል ኣስደግፋቹሁ ብታስረዱን
ስለ እስራኤል ከሆነ በእግዚኣብሔር ቃል ኣስደግፋቹሁ ብታስረዱኝ
Mar 7, 2011 መንፈሳዊ መዳንበየሱስ (150 ነጥቦች) የተጠየቀ
Mar 9, 2011 iyesus ታርሟል

2 መልሶች

–2 ድምጾች
ይህ ጥያቄ በሓሳብና በአስተያዬት ልዩነት ብዙ ሰዎችን የከፋፈል ክፍል ነው። ጌታ ከወደ ፊቱ በኢየሩሳሌም የሚጠብቀውን በሌሎች ምዕራፋት ቀደም ብሎ ትንሽ በትንሽ እየነገረ ሲያዘጋጃቸው ልብ ብለናል። በሽተኞች ሲፈውስ ርኩሳት መንፍስትን ሲያውጣ ሲያስተምር የሰሙት ህዝቡ ሁሉ ይደነቁ ነበር። በስልጣን ያስተምራል ከየት ያመጣው ነው ይሀ የጸራቢው የዮሴፍ ልጅ አይደልም እንዴ ይሉ ይንቁት ነበር። ልጅ ሆኖ ስለ ሚያውቁት በእርሱ አላመኑም የእግዚአብሔር መንግስት ከናንተ ትወሰዳለች ለአህዛብ ትሰጣለችም ይላቸው ነብር

እንድ ምዕራፍ ላይ ስጋዬን ያልበላ ደሜን ያልጠጣ እያለ ሲያስተምራቸው እንዴ ይህ ግራ የሚያጋብ አባባል ምን ማለት ነው ብለው እርስ በርሳቸው ይጠያየቁ ነበር። ብዙ ጊዜ ከእርሱ ጋር በቆዩበት ብዙ ድንቅ ስራ አይተዋል ብዙ እውነት የሆነ ምስጥር ድንቅ ሰምቶዋል ጥሎ መመለስ የማችሉብት (Point of no return) ሁኔታ ላይ የደርሱ ይመስለኛል ምክንያቱም ወድያውኑ የሚከናውን በሕይወታቸው ዘመን የሚፈጸም ጉዳይ አድርገው የሚያይት የነበረ ለዚህ ይመስለኛል፡: ለዚህም ይመስለኛል ይህ መቸ ይሆናል እያሉ የሚጠይቁት የነበር።

በዚህ ምዕራፍ 24፡1 ላይ በመደንቅ በገረም ያዩት የቤተ መቅደሱን ድንጋዮችን ሊያሳዩት የሚሞክሩ ይመስላሉ ጌታ ግን በዚህ ነው የምትገረሙ እላችሁልሁ ድንጋይ በድንጋይ ላይ የማይቀርበት ጊዜ ይመጣል እንዳልነበረ ይሆናል ሲላችው መቸም የልባቸው ትርታ እጅግ ክፈ ሳይል እንድማይቀር እርግጠኛ ነኝ የተፈጠርባቸውንም ጥያቄ ማሰብ መገመት እንኳን አልፈልግም። ይህን ጥያቄ ያቀረቡት ደቀ መዛሙርቱ አሁን የሉም በዚህ ጊዜ ያልነው እኛ ነን። በእድሜያችን ስንቱ ናቸው እየሱስ ክርቶስ እኔ ነኝ ብለው የተነሱት? ስለዚህ ይህ ጌታ ያለው እውነት ሆኖ የምንመራበት ቃል ለናም ጭምር ነው። አሬዲ ቢቢሲ ሲነኤንኤን ዘዲኤፍ ያውሩ ቢያውሩ አንት ግን አንቺ ግን ቤተ ክርስቲያን ግን መናወጥ የለባትም።
Mar 8, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Mar 10, 2011 ታርሟል
0 ድምጾች
የማቴዎስ ወንጌል 24፥4-14 የሚናገረው በመጨረሻው ዘመን ሊሆን ሳለውና ታላቁ መከራ በመባል ስለሚታወቀው የመጀመሪያ ክፍል ነው። ይህም ማለት የሚመለከተው በአንደኛ ደረጃ እስራኤልን እንጂ ቤተክርስቲያንን አይደለም። ይህንን ደግሞ እንደሚከተለው ከመጽሐፍ ቅዱስ ለማስረዳት እሞክራለሁ።

በማቴዎስ ወንጌል 24፥1-3 ባለው ክፍል ደቀመዛሙርቱ የቤተመቅደሱን ግንቦች ለኢየሱስ ሲያሳዩት፤ ጌታ ግን ቤተመቅደሱ እንደሚፈርስ ይነግራቸዋል።
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል 24
1 ኢየሱስም ከመቅደስ ወጥቶ ሄደ፥ ደቀ መዛሙርቱም የመቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ቀረቡ።
2 እርሱ ግን መልሶ፦ ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አላቸው።
3 እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው። ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።

ይሄን የጌታን ንግግር ተመርኩዘው ነው እንግዲህ ደቀመዛሙርቱ ሁለት ጥያቄዎችን የጠየቁት። አንደኛ "ይህ መቼ ይሆናል?" ማለትም የመቅደሱ መፍረስ መቼ ይሆናል? የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድነው?" የሚል ነው።

በማቴዎስ 24 ላይ ኢየሱስ የመጀመሪያውን ጥያቄ፤ ማለትም ስለ ቤተመቅደሱ መፍረስ ለተጠየቀው ጥያቄ የሰጠው መልስ አልተጻፈም። ነገር ግን ሉቃስ 21፥20-24 ላይ ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ70 ዓ/ም ስለተከሰው ስለ ኢየሩሳሌም መፍረስ ጌታ የሰጠው መልስና ትንቢት ተጽፎአል።

በማቴዎስ 24 ላይ የተጻፈው እንግዲህ ስለ ሁለተኛው ጥያቄ፤ ማለትም ስለ ዓለም ፍጻሜ ምልክት ኢየሱስ የሰጠው መልስ ነው። ይሄ ጌታ የሰጠው መልስ በዮሐንስ ራእይ 6 ላይ ከተጻፈውና የታላቁ መከራ ዘመን መጀመሪያ ላይ ይከሰታል ተብሎ ከተተነበየው ትንቢት ጋር ቅደም ተከተሉ ጭምር በጣም ይመሳሰላል።

ይሄንን ለማየት ጌታ የተናገረውንና በራእይ 6 ላይ የተጻፉትን ጎን ለጎን ማየቱ የበለጠ ይረዳል።
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል 24
4 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።
5 ብዙዎች። እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።
Quote:
የዮሐንስ ራእይ 6
1 በጉም ከሰባቱ ማኅተም አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ከአራቱም እንስሶች አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ። መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።
2 አየሁም፥ እነሆም፥ አምባላይ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፥ አክሊልም ተሰጠው፥ ድልም እየነሣ ወጣ ድል ለመንሣት።
ኢየሱስ በነጭ (አምባላይ) ፈረስ እንደሚቀመጥና ድል እንደሚናሳ በራእይ 19፥11-15 ላይ ተጽፎአል። ከላይ ባለው ክፍል፤ የመጀመሪያው ማኅተም ሲከፈት ግን ኢየሱስ ሳይሆን ልክ እንደ ኢየሱስ አይነት በነጭ (አምባላይ) ፈረስ ላይ ተቀምጦ ድል የሚነሣ ተጽፎአል። ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ አዋቂዎች ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ እንደሆነ ይስማሙበታል። ኢየሱስም በመጀመሪያ ያስጠነቀቀው ስለ ሀሰተኞች መሲሖች ነው።

Quote:
የማቴዎስ ወንጌል 24
6 ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።
7 ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ...
Quote:
የዮሐንስ ራእይ 6
3 ሁለተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሁለተኛው እንስሳ። መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ። 4 ሌላም ዳማ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ ለተቀመጠው ሰላምን ከምድር ይወስድ ዘንድ ሰዎችም እርስ በርሳቸው እንዲተራረዱ ሥልጣን ተሰጠው፥ ታላቅም ሰይፍ ተሰጠው።

Quote:
የማቴዎስ ወንጌል 24
7 ... ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤
8 እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።
Quote:
የዮሐንስ ራእይ 6
5 ሦስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ። መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ። አየሁም፥ እነሆም፥ ጕራቻ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ያዘ። 6 በአራቱም እንስሶች መካከል ድምፅ። አንድ እርቦ ስንዴ በዲናር ሦስት እርቦ ገብስም በዲናር፥ ዘይትንና ወይንንም አትጕዳ ሲል ሰማሁ።
7 አራተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ የአራተኛው እንስሳ ድምፅ። መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።
8 አየሁም፥ እነሆም፥ ሐመር ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበረ። ሲኦልም ተከተለው፤ በሰይፍና በራብም በሞትም በምድርም አራዊት ይገድሉ ዘንድ ከምድር በአራተኛዋ እጅ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።

Quote:
የማቴዎስ ወንጌል 24
9 በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።
Quote:
የዮሐንስ ራእይ 6
9 አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ። 10 በታላቅ ድምፅም እየጮኹ። ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ። 11 ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፥ እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተባለላቸው።

ከላይ ለማብራራት እንደሞከርኩት፤ የጠየክኸው ክፍል የሚናገረው ስለ ታላቁ መከራ ስለሆነ፤ ይህ ክፍል በዋነኝነት የሚመለከተው እስራኤልን ነው። ታላቁ መከራ በዳንኤል መጽሐፍ ለእስራኤል ሕዝብ ከተወሰነለት 70 ሱባዔ (1ሱባዔ=7ዓመት) መካከል የመጨረሻው ነው። ታላቁ መከራ ለእስራኤል ሕዝብ ከተቀጠረው 70 ሱባዔ ውስጥ ስለሆነ፤ የሚመለከተውም እስራኤልን እንጂ ቤተክርስቲያንን አይደለም።
Quote:
ትንቢተ ዳንኤል 9
24 ዓመፃን ይጨርስ፥ ኃጢአትንም ይፈጽም፥ በደልንም ያስተሰርይ፥ የዘላለምን ጽድቅ ያገባ፥ ራእይንና ትንቢትን ያትም፥ ቅዱሰ ቅዱሳኑንም ይቀባ ዘንድ በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል

ትንቢተ ዳንኤል 9
26 ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ መሢሕ ይገደላል፥ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም የሚመጣውም አለቃ ሕዝብ ከተማይቱንና መቅደሱን ያጠፋሉ ፍጻሜውም በጐርፍ ይሆናል፥ እስከ መጨረሻም ድረስ ጦርነት ይሆናል ጥፋትም ተቀጥሮአል።
27 እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል በርኵሰትም ጫፍ ላይ አጥፊው ይመጣል እስከ ተቈረጠውም ፍጻሜ ድረስ መቅሠፍት በአጥፊው ላይ ይፈስሳል።
Mar 9, 2011 በምሕረቱ (1,510 ነጥቦች) የተመለሰ
Mar 9, 2011 በምሕረቱ ታርሟል
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...