ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Friday, 4 December 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ከዝህ ቀደም "አንድ ዘመዴ"

ጥያቄውን በመመለስ እየረዳችሁኝ ያላችሁ ወገኖች ጌታ ይባርካችሁ።ከዚህ ቀደም "አንድ ዘመዴ"ያልኩት አባቴ ነው።በ1999ዓ.ም ነው በዚህ ሁነታ የሞተው፤እኔ በ ግዜው የ10ኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩኝ፤እናቴ ደግሞ ገና በ ልጅነቴ በ19194 ዓ.ም ቀድማዋለች። እኔ ግን አሁን ቸር እግ/ር ረድቶኝ የአርባምንጭ ዩንቨርሲቲይ የጅኦግራፊና አከባቢ ጥናት ት/ት ክፍል የ3ኛ ዓመት ተማሪ ነኝ።ወገኖቼ ከሰው የተለየ ታሪክ አለኝ እያልኩ አይደለም፤ ነገር ግን የአባቴ ሞት ጥያቄ ስለፈጠረብኝ ነው። በዓለማችን በዝህ ዓይነት ሁነታ በየቀኑ በሺዎች ይሚቆጠሩ ሰዎች እንደሚሞቱ መረጃዎች ያሳያሉ። እባካችሁ እኔንና መሰል ችግሮች ውስጥ ያሉ ሰዎችን ከ እግ/ር ቃል እውነት ምከሩን እላችሁዋለው።የጌታን ቸርነት በዓይኔ ስላየሁ ባለኝ ስጦታ ሙሉ ጊዜዬን ሰጥቼ ማገልገል እፈልጋለውና ምን ትመክሩኛላችሁ?ስለ አገልግሎቴስ የእግ/ርን ፈቃድ እንደት መለየት እችላለው?
Mar 29, 2012 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

0 ድምጾች
ወንድሜ መጽናናትህ ለእኔ ደስታዬ ነው። ያለፈውን ለጌታ ሰጥተህ ያንተን ቀሪ ሕይወት ከጌታ ጋር ለማኖር በመቻልህም ከሁሉ የበለጠ ደስታ ነው። ከምንል ነገር በላይ አስቀድሞ ሁለንተናህን በእግዚአብሔር ላይ ጣል! እሱ ይተውህ ዘንድ እንደሰው አይደለም። ሰው ብትታመነው ይከዳሃል፣ ይተውሃል ፣ይለወጥብሃል፣ ባስቀመጥከው ላታገኘው ትችላለህና ጥንቃቄ ማድረግ ይገባሃል። ብዙዎች ባመኑት ወይም በቀረቡት ወይም የልቤ መልካም ምርጫ ባሉት ሰው ሲጎዱ በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን መታመን ሁሉ ሲጥሉ አይቻለሁ። ስለዚህ የሕይወትህ ባለቤት፣ የማይከዳ፤ የማይተው፤ የማይረሳ፤ የማይዘነጋ፤ የሚያዝንልህና የሚጋርድህን እግዚአብሔር በልብህ ሰሌዳ ላይ ጻፈው።
«መዝ 40፥17 እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ፥ ጌታ ግን ያስብልኛል አንተ ረዳቴና መድኃኒቴ ነህ አምላኬ ሆይ፥ አትዘግይ።
ከእሱ ወዲያ ላንተ የሚቀርብ የለም። ከእሱም ወዲያ ላንተ የሚፈጥን የለም!!

ይህንን ስንልንም ከሰዎች ጋር ያለንን ማኅበራዊና መንፈሳዊ ተግባቦቶች አንፈልግም ማለት እንዳልሆነ ይታወቃል። በክርስትናችን ውስጥ የቃሉን ብርሃን የሚረጩ የእግዚአብሔር ሰዎች አሉና ከእነሱም እንማር። ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ለፊልጶስ እንዳለው፤ «እርሱም፦ የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል? አለው። ወጥቶም ከእርሱ ጋር ይቀመጥ ዘንድ ፊልጶስን ለመነው» የሐዋ 8፣31 የሚያነበውን እንደተረጎመለት ሁሉ ቃሉን ለመማር ፈልግ።
«ሮሜ 10፥17
እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው»
አጥብቀህ ጸልይ! ጸሎት መልስ አለው። በሕይወቴ ያለኝ ልምምድ ያሳየኝ እሱን ነው።
«አምናችሁም በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ አላቸው» ማቴ 21፣22
በተረፈ እግዚአብሔር የልብህን መሻት ይሞላ ዘንድ ወንድማዊ ጸሎቴ ነው።
Mar 29, 2012 ብርሃን (1,840 ነጥቦች) የተመለሰ
ወንድሜ ለ መልስህ ጌታ ይባርክህ ። ስለአገልግሎት የጌታን ፍቃድ እንደት ማወቅ እንደሚችል ጠይቄ ነበር ለምን አልመልስክም? በተረፈ ኢመይልህን ብትሰጠኝ ብዙ ትረዳኝ ይሆናል የሚል ተስፋ አለኝ፤ደኅና ሁን።
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...