ጌታ ይባርክህ ደጄብርሃን
እኔ በተለያዩ ሚዲያዎች እግዚአብሔር በ7 ቀን ሰማይንና ምድርን ፈጠረ እያሉ በሚናገሩ ክርስቲያኖችም ይሁን በክርስቲያኖች ላይ ለማሾፍ የሚናገሩ የሚዲያ ሰዎች ሁል ጊዜ የሚያናድዱኝ ነገር ቢኖር መጽሃፍ ቅዱስ 7 ቀን ሲል ልክ የእኛ የሰዎች አይነት ማለትም በ24 ሰዓታት የተከፈለ ቀን ማለቱ እን
ዳልሆነ ክርስቲያኖችም ይሁኑ የሚዲያ ሰዎች አለመናገራቸው ነው። እንደው አንድም ሰው የለም ማለት ነው መጽሃፍ ቅዱሱን ራሱን የሚያነብብ
? መቼ ነው መጽሃፍ ቅዱስ በሰው በ24 ሰዓት በተከፈለ 7 ቀን ማለትም 24*7 ወይም ከሰኞ እስከ እሁድ ባለው ጊዜ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ የሚለው
? እንዲህ ያለ ነገር መጽሃፍ ቅዱስ ጨርሶ አይናገርም።
መጽሃፍ ቅዱስ ሰለ ሁለት ፈጽሞ የተለያዩ የቀን ወይም የጊዜ መቁጠሪያዎች ነው የሚናገረው። አንደኛውና የመጀመሪያው ብርሃን ብሎ የሚጠራው ነገር ግን ከጸሃይ የማይመነጭና ከየት እንደሚመነጭ ያልተገለጸው የእግዚአብሔር የቀን መቁጠሪያ ሲሆን፤ አንደኛው ደግሞ በእግዚአብሔር የቀን መቁጠሪያ በአራተኛው ቀን ላይ የተፈጠሩትና ለሰዎች በምድር ላይ ቀንና ዘመናት መቁጠሪያነት እንዲያገለግሉ የተባሉት ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት ናቸው።
Quote:
ኦሪት ዘፍጥረት 1
4 እግዚአብሔርም አለ፦ ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ
15 በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር ብርሃናት ይሁኑ እንዲሁም ሆነ
16 እግዚአብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ።
17 እግዚአብሔርም በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር አኖራቸው
18 በቀንም በሌሊትም እንዲሠለጥኑ፥ ብርሃንንና ጨለማንም እንዲለዩ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።
19 ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አራተኛ ቀን።
ስለዚህ እኛ የምናውቀው አይነት በፀሐይ መውጣትና መጥለቅ የሚቆጠረው ቀን የተጀመረው ራሱ በእግዚአብሔር ቀን መቁጠሪያ በአራተኛው ቀን ነው። ፀሐይ ከመፈጠሩም በፊት እግዚአብሔር ቀን እየቆጠረ ነበር። እናም እግዚአብሔር የሚቆጥርበት ቀን እኛ የምንቆጥርበት የ24 ሰዓት ቀን እንዳልሆነ መጽሃፍ ቅዱስ ላይ ግልጽ ነው።
ስለዚህ ይህ በፀሐይ ሳይሆን ከፀሐይ ውጪ ባለ ብርሃን በሚቆጠረው የእግዚአብሔር ቀን ተቆጥሮ ነው እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን በ7 ቀን ፈጠረ የሚለው መጽሃፍ ቅዱስ እንጂ በእኛ በፀሐይ መውጣትና መጥለቅ በሚቆጠር ቀን አይደለም።
ይህ 7 ቀን የተባለውና ፀሐይም ከመፈጠሩ በፊት እግዚአብሔር ይቆጥርበት የነበረው ቀን በእኛ በሰዎች አቆጣጠር ምን ያህል ቀን ወይም ወር ወይም ዓመት ይሁን ምንም የምናውቀው ነገር የለም። በእኛ አቆጣጠር 1000 ዓመት ሊሆን ይችላል ወይም ደግሞ 1 ቢሊዮን ወይም 100 ቢሊዮን ዓመታት ሊሆን ይችላል። በሰዎች የቀን መቁጠሪያ ምን አይነት ቀን እንደሆነ በፍጹም ስላልተጻፈ ይህን ያህል ጊዜ ነው የፈጀው ብለን መናገር አንችልም። ቢያንስ ቢያንስ ግን ከሰኞ እስከ እሁድ ወይም በሰው ቀን መቁጠሪያ 7 ቀን ብቻ ነው የፈጀው ይላል ብለን መጽሃፍ ቅዱስ ያላለውን ባናስተጋባና ያልተጻፈ እያነብብን መሳቂያ ባንሆን መልካም ነው።