ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Thursday, 3 December 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ገነት እና መንግስተ ሰማያት ልዩነት አላቸውን?

Mar 10, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

+1 ድምጽ
ገነት ወይም Garden ቦታ ሲሆን መንግሥተ ሰማያት ማለት ግን የሰማያት መንግስት ማለት ነው። የሰማያት ወይም የሰማይ መንግስት ማለት ደግሞ የእግዚአብሔር መንግስት ማለት ነው፡፡

በአብዛኛው በማርቆስ ወንጌል "የእግዚአብሔር መንግስት" የሚለው ቃል ነው በማቴዎስ ወንጌል "መንግስተ ሰማያት" የተባለው። ትርጉሙም የሰማይ መንግስት ወይም የእግዚአብሔር መንግስት ማለት ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ አዋቂዎች እንደሚናገሩት፤ ማቴዎስ "የእግዚአብሔር መንግስት" ከማለት ይልቅ "የሰማይ መንግስት" ወይም በግዕዙ "መንግስተ ሰማያት" ብሎ የጻፈበት ምክንያት የማቴዎስ ወንጌል የተጻፈው ለአይሁዶች ስለነበርና አይሁዶች ደግሞ "እግዚአብሔር" የሚለውን ስም ደጋግመው መጥራት ያስቀስፋል ብለው ስለሚይምኑ እንደነበር ይናገራሉ (ምክንያቱም በህግ የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ ይላልና)
Quote:
የማርቆስ ወንጌል
1፥14-15 ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና። ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ።

የማቴዎስ ወንጌል 4
17 የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ። ከዚያ ዘመን ጀምሮ ኢየሱስ፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ ጀመር።

የእግዚአብሔር መንግስት ደግሞ በአንደኛ ደረጃ ቦታ አይደለችም። ነገር ግን የእግዚአብሔር አገዛዝ ወይም አስተዳደር ናት። ለዚህ ነው በአባታችን ሆይ ጸሎት ጌታ "መንግስትህ ትምጣ" ካለ በኋላ ወዲያው "ፈቃድህ በሰማይ እደሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን" የሚለው።
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል
6፥10 ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤

ስለዚህ መንግስተ ሰማያት ወይም የእግዚአብሔር መንግስት ማለትም የእግዚአብሔር አገዛዝና ፈቃድ በሰማይ እንደሆነ ሁሉ በምድርም እንዲሆን ነው ጸሎቱ የሚያስተምረን።

የእግዚአብሔር ፈቃድ በሚፈጸምበትና የእርሱ ሥልጣን ተግባራዊ በሚሆንበት ሁሉ በዚያ የእግዚአብሔር መንግስት ወይም መንግስተ ሰማያት አለች።
Quote:
ቃስ ወንጌል 17
20 ፈሪሳውያንም፦ የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች ብለው ቢጠይቁት፥ መልሶ፦ የእግዚአብሔር መንግሥት በመጠባበቅ አትመጣም፤
21 ደግሞም፦ እንኋት በዚህ ወይም፤ እንኋት በዚያ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው።

ኢየሱስ በምድር በተመላለሰበት ጊዜ የእግዚአብሔር አገዛዝ ወይም መንግስት በእርሱ ይሠራ ስለነበር ኢየሱስ የእግዚአብሔር መንግስት በመካከላችሁ ናትና ብሎ ፈሪሳውያንን ሲነግራቸው እንመለከታለን። በመካከላችሁ የሚለው በልባችሁ ማለት እንዳይደለ ልብ ልንል ይገባል፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ ይህን መልስ የመለሰው ለፈሪሳውያን ነው። በመካከላችሁ ናትና የሚለው ኢየሱስ ራሱን ነው። ምንክንያቱም የእግዚአብሔር ሥልጣን አጋንንትን በማውጣት፣ በሽተኞችን በመፈወስ፣ ሙታንን በማስነሳት፣ ኃጢአተኞችን ይቅር በማለት በክርስቶስ አማካኝነት በመካከላቸው እየተገለጠች ነበርና።
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል 12
28 እኔ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች።

ባጭሩ ጥያቄውን ለመመስ፤ ገነት አንድ የተወሰነ ሥፍራ ወይም ቦታ ነው። መንግስተ ሰማያት የሚለው ቃል ትርጉም ግን የእግዚአብሔር መንግስት ወይም የእግዚአብሔር ፈቃድ የሚፈጸምበት አገዛዝ ማለት ነው። በሰማይም ይሁን በምድር የእግዚአብሔር ፈቃድ በሚፈጸምበትና የመንግስቱ ሥልጣን በሚገለጥበት ቦታ ሁሉ በዚያ የእግዚአብሔር መንግስት አለች።
Mar 11, 2011 በምሕረቱ (1,510 ነጥቦች) የተመለሰ
Apr 12, 2011 በምሕረቱ ታርሟል
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...