ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄና መልስ
Email this page to a friend Printer-friendly   Sunday, 24 September 2017
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

ማርያም በስጋ የወለደችው ልጅ አላት? መጽሐም ቅዱስ ላይ ካለ ጥቅሱን ቢቻል፡፡

ማርያም በስጋ የወለደችው ልጅ አላት? መጽሐም ቅዱስ ላይ ካለ ጥቅሱን ቢቻል፡፡መ
6 ዓመታት በፊት መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
ማርያም በስጋ የወለደችው ልጅ የላትም፡፡ በድንግልና እንደወለደችው ነው ያሰተምረነናል እንዲሁም አየሱስ ወንድሞቼ የሚላቸው በወቅቱ የነበሩትን ሰዎች ወይም ሀዋርያት ወድሞቼ እህቶቼ በማለት ነው
ምስራቅ

እንዴት ነው መጽሐፍ ቅዱስ እየጠቀስን እንጂ። እንዲያው በራሳችን ስልጣን ብቻ መጽሐፍ ቅዱስ ያላላውን መናገር ሰው ያስታል። ከታች መልስ የሰጠው ሰው ማርያም በሥጋ ልጅ እንዳላት ከመጽሐፍ ቅዱስ ከተለያየ ቦታዎች አውጥቶ ጠቅሶ ነው ያስረዳው። አንቺ ደግሞ አይ ተሳስቶአል ማርያም ልጅ የለታም ካልሽ ይሄንን ከመጽሐፍ ቅዱስ አውጥተሽ ማስረዳት ይኖርብሻል እንጂ እንደው ከራስሽ አይደለም። ሰው የሚፈልገው የእኛን አስተያየት ሳይሆን የእግዚአብሔር ቃል ምን እንደሚል ለማወቅ ነው።

"እኔ ራሴ መጽሐፍ ቅዱስ ነኝ" ወይም "እኔ ራሴ የእግዚአብሔር ቃል ነኝ" ካላልሽ በስተቀር ከቃሉ የአምላካችን ቃል በመጥቀስ መልስሽን መስጠት ይኖርብሻል። ያለዚያ የሰው አስተያየት ብቻውን ዋጋ የለውም፤ ያስታል።
እሺ ማርያም ሌላ በስጋ የወለደቻቸው እነማን ናቸው?
ቱቱ ከታች የተሰጠውን መልስ ብታነብቢ ስማቸው ተዘርዝሮ ታገኚአለሽ። ያንን ማንበብ ካልፈለግሽ ደግሞ የማቴዎስ ወንጌል 13፡55-56 አንብቢ
በዚህ አይነትማ እህቶችም አሉት እነማን ናቸው? እኅቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን? እንኪያስ ይህን ሁሉ ከወዴት አገኘው? ተሰናከሉበትም።
57 ኢየሱስ ግን፦ ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤቱ በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው።
58 በአለማመናቸውም ምክንያት በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም ነው የሚለው ማቴ.12 ቁ 46. ገናም ለሕዝቡ ሲናገር፥ እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋገሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር። 47 አንዱም። እነሆ፥ እናትህና ወንድሞችህ ሊነጋገሩህ ፈልገው በውጭ ቆመዋል አለው።
እርሱ ግን ለነገረው መልሶ፦ እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው? አለው።
49 እጁንም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘርግቶ። እነሆ እናቴና ወንድሞቼ፤
50 በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነውና አለ
ስለዚህ እናስተውል ዮሴፍ ማርያምን አወቃት ወለደችም አላለም መጽሐፍ ቅዱስ
አመሰግናለሁ።
የላትም ነው መልሱ በድጋሚ ከኛ የሚጠበቀው ማስተዋል ብቻ ነው
እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋገሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር። 47 አንዱም። እነሆ፥ እናትህና ወንድሞችህ ሊነጋገሩህ ፈልገው በውጭ ቆመዋል አለው። እርሱ ግን ለነገረው መልሶ፦ እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው? አለው።
49 እጁንም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘርግቶ። እነሆ እናቴና ወንድሞቼ፤
50 በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነውና አለ
ኦሪት ዘፍጥረት 4
1 አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች። እርስዋም፦ ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ አለች። 2 ደግሞም ወንድሙን አቤልን ወለደች እንዳለው ሁሉ ዮሴፍም ሚስቱን አወቃተት ልጆችንም ወለደች ብሎ ስማቸውን ይዘረዝር ነበረ
ስለዚህ እናስተውል ዮሴፍ ማርያምን አወቃት ወለደችም አላለም መጽሐፍ ቅዱስ
አየሱስ ወንድሞቼ የሚላቸው በወቅቱ የነበሩትን ሰዎች ወይም ሀዋርያት ወድሞቼ እህቶቼ በማለት ነው
ወገኔ የአንተ ሎጂክ የሚያስኬድ አይደለም

አንደኛ ማቴዎስም፣ ማርቆስም ሉቃም ሶስቱም የወንጌላቱ ጸሃፊዎች ኢየሱስን ሊያነጋግሩ የመጡትን ሰዎች "እናቱና ወንድሞቹ" እንደሆኑ ነው የሚጽፉት፤ እናቱና ወንድሞቹ እያሉም ነው የሚጠሯቸው። እነዚህ ሰዎች እናቱና ወንድሞቹ ካልሆኑ ለምንድነው የወንጌላቱ ጽሃፊዎቹ ራሳቸው እናቱና ወንድሞቹ ሊያነጋግሩት እንደፈለጉ የሚነግሩን?
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል
12፥46 ገናም ለሕዝቡ ሲናገር፥ እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋገሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር

የማርቆስ ወንጌል
3፥31 እናቱና ወንድሞቹም መጡ በውጭም ቆመው ወደ እርሱ ልከው አስጠሩት

የሉቃስ ወንጌል
8፥19 እናቱና ወንድሞቹም ወደ እርሱ መጡ፥ ከሕዝቡም ብዛት የተነሣ ሊያገኙት አልተቻላቸውም

ይህ ብቻ አይደለም፡ በዮሐንስ ወንጌል ላይ ደግሞ ሶስቱንም ለያይቶ ሲጠራቸው እንመለከታለን። ማለትም እናቱን፣ ወንድሞቹንና ደቀመዛሙርቱን። ይህም ሶስቱ የተለያዩ እንጂ አንተ እንዳልከው አንድ እንዳልሆኑ በማስረጃ ያሳየናል።
Quote:
የዮሐንስ ወንጌል
2፥12 ከዚህ በኋላ ከእናቱና ከወንድሞቹ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፥ በዚያም ጥቂት ቀን ኖሩ።

አንተ ያልከው ፈጽሞ እንዳልሆነ የሚያስረዱ ሌሎችም ማስረጃዎች መጨመር ይቻላል። ሆኖም በዚሁ አምድ ላይ ብዙ መልስ ስለተሰጠባቸው እነርሱን አንብብ። እኔ እንደገና መድገም አልፈልግም።

4 መልሶች

+2 ድምጾች
ማርያም ኢየሱስን በጸነሰች ጊዜ ዮሴፍ እጮኛዋ እንደነበርና ኢየሱስን ከወለደች በኋላ ግን አብረው በትዳር ኖረው ሌሎችን ልጆችም እንደወለዱ ነው መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው።
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል 11
24 ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቅቶ የጌታ መልአክ እንዳዘዘው አደረገ፤ እጮኛውንም ወሰደ፤
25 የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው የማርያም እጮኛ ዮሴፍ ማርያም "የበኩር ልጅዋን እስትወልድ ድረስ አላወቃትም" ነው የሚለው። ማለትም በሌላ አገላለጽ የበኩር ልጇን ከውለደች በኋላ ግን አውቆአታል። ኢየሱስ ከተወለደ በኋላ ዮሴፍና ማርያም እንደማንኛውም ሰው በትዳር እንደኖሩና ወንድና ሴቶች ልጆችም እንደወለዱ መጽሐፍ ቅዱስ ይናራል።
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል 13
53 ኢየሱስም እነዚህም ምሳሌዎች ከጨረሰ በኋላ ከዚያ ሄደ።
54 ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ እስኪገረሙ ድረስ በምኩራባቸው ያስተምራቸው ነበር፤ እንዲህም አሉ። ይህን ጥበብና ተአምራት ይህ ከወዴት አገኘው?
55 ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን?
56 እኅቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን? እንኪያስ ይህን ሁሉ ከወዴት አገኘው? ተሰናከሉበትም።
57 ኢየሱስ ግን፦ ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤቱ በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው።

ከላይ እንደምናየው በመጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ወዳደገበት ወደገዛ አገሩ በሄደበት ጊዜ እርሱንና ቤተሰቦቹን በሚገባ የሚያውቁት ሰዎች የተናገሩት ተጽፎአል። ምንድነው ያሉት? ይሄ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? ጸራቢ ማለት አናጺ ማለት ነው። ዮሴፍ አናጺ ስለነበር፡ የአናጺው የዮሴፍ ልጅ አይደለም እንዴ? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮስ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን? እቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ አይደሉምን? ብለው ነበር የተናገሩት። ይህ ክፍል ማርያምና ዮሴፍ በትዳር ብዙ አመታት አብረው እንደኖሩ ወንዶችንና ሴቶሽንም ልጆች እንደወለዱ ግልጽ ያደርጋል። በዚህ ክፍል የተጠቀሱት ያዕቆብና ይሁዳ የሚባሉት የኢየሱስ ወንድሞች ደግሞ በመጽሐፍ ቅድስ ውስጥ የሚገኙትን የያዕቆብንና የይሁዳን መልእክት የጻፉት እነርሱ እንድሆኑ የመጽሐፍ ቅድስ አዋቂዎች ይናገራሉ። ምንም እንኳን በመጀመሪያዎቹ የአገልግሎት ዘመኖቹ ወንድሞቹ በኢየሱስ ባያምኑም በተለይ ከሙታን ከተነሳ በኋላ የኢየሱስ ተከታዮች ሆነው አገልግለዋል።
Quote:
የዮሐንስ ወንጌል 7
1 ከዚህም በኋላ ኢየሱስ አይሁድ ሊገድሉት ይፈልጉ ስለ ነበር በይሁዳ ሊመላለስ አይወድም ነበርና በገሊላ ይመላለስ ነበር። 2 የአይሁድም የዳስ በዓል ቀርቦ ነበር። 3 እንግዲህ ወንድሞቹ፦ ደቀ መዛሙርትህ ደግሞ የምታደርገውን ሥራ እንዲያዩ ከዚህ ተነሣና ወደ ይሁዳ ሂድ፤ 4 ራሱ ሊገለጥ እየፈለገ በስውር የሚሠራ የለምና። እነዚህን ብታደርግ ራስህን ለዓለም ግለጥ አሉት። 5 ወንድሞቹ ስንኳ አላመኑበትም ነበርና

ወደ ገላትያ ሰዎች 1
18 ከዚህ ወዲያ ከሦስት ዓመት በኋላ ኬፋን ልጠይቅ ወደ ኢየሩሳሌም ወጥቼ ከእርሱ ጋር አሥራ አምስት ቀን ሰነበትሁ፤ 19 ነገር ግን ከጌታ ወንድም ከያዕቆብ በቀር ከሐዋርያት ሌላ አላየሁም።

የይሁዳ መልእክት 1
1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ፥ በእግዚአብሔር አብ ተወደው ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ፤ 2 ምሕረትና ሰላም ፍቅርም ይብዛላችሁ።

መጽሐፍ ቅዱስ እንግዲህ በግልጽና በማያሻማ ቃላት የሚነግረን፤ ማርያም ኢየሱስን እስከምትወልድ ድረስ ዮሴፍ እንዳላወቃት፤ ከዚያ በኋላ ግን እንደ ማንም ሰው መደበኛ ትዳር ለብዙ አመታት እንደመሩና ልጆችን እንደወለዱ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ አዋቂዎች ደግሞ ከልጆቻቸው ውስጥ በተለይ ያዕቆብና ይሁዳ ኢየሱስ ከሙታን ከተነሳ በኋላ በአገልጋይነት የሚታወቁና የያዕቆብና የይሁዳ መልእክት ተብለው በመጽሐፍ ቅዱስ የሚታወቁትን መልእክቶች የጻፉት እነርሱ እንደሆኑ ይናገራሉ።

ከዚህ ተጨባጭ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታ ውጪ ግን፡ ማርያም ልጅ ከወለደችም በኋላ ድንግልም ናት የሚል አስተሳሰብና እምነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የሌለውና ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ ካልሆነ በስተቀር መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማይገኝ ለመጽሐፍ ቅዱስ ጭርሶ ባእድ የሆነ አስተሳሰብ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሱትም ሐዋርያቱና ነብያቱ ጨርሰው እንዲህ ያለ ሃሳብ አልተናገሩም አላስተማሩምም።
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል 12
46 ገናም ለሕዝቡ ሲናገር፥ እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋገሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር
47 አንዱም፦ እነሆ፥ እናትህና ወንድሞችህ ሊነጋገሩህ ፈልገው በውጭ ቆመዋል አለው።
48 እርሱ ግን ለነገረው መልሶ፦ እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው? አለው።
49 እጁንም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘርግቶ፦ እነሆ እናቴና ወንድሞቼ፤
50 በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነውና አለ።
6 ዓመታት በፊት ስም-አልባ የተመለሰ
6 ዓመታት በፊት የታረመ ስም-አልባ
2ጵጥሮስ 3፤16 ''በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ፤ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ
ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ''
ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ይግባውና የጠራቢው የዮሴፍ ልጅ ነው ማለትህ እኮ ነው ።
''ተሰናከሉብት''.........''ተሰናከሉብት''................''ተሰናከሉብት
1 ውንድ 1 ሴት ነው ትዛዙ................... ማን ነው ያመነዘረው ባንተ ሀሳብ......................
አባት በገባበት ልጅ ይገባል..................its not logical......................
መውለድ ክብር ነው።ሴት ልጅ በመውለዶ ትድናለች....
ብዙ ማለት ይቻል ነበር ......... ፈጣሪ ማስተዋሉን ይስጣቹህ።
ሰይጣንም ይጠቅሳል። በዚህ way
ሰላም
አንደኛ የጠራቢው ልጅ የሚለው እኔ ሳልሆን መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ዮሴፍ አናጺ ስለነበረ ማለት ነው፡፡ ይሄ ግን የኢየሱስን ክብር አይቀንሰውም። ልክ በበረት መወለዱና ራሱን አዋርዶ ወደ ምድር መምጣቱ ክብሩን እንደማይቀንሰው ዮሴፍም አናጺ መሆኑ ምንም ክብሩን አይቀንሰውም። መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ብዙ ሃይማኖተኞች ፋናቲክ አይደለም። የሆነውን ሆነ፤ ያልሆነውንም አልሆነም በማለት እውነቱን በትህትና ይናገራል እንጂ።

በሁለተኛ ደረጃ ለምን ስለማመንዘር እንደምትናገር አልገባኝም። ማርያም ኢየሱስን እስከምትወልድ ድረስ ወንድ አታውቅም ነበር። ከዚያ በኋላ ደግሞ ዮሴፍን ብቻ ነው የምታውቀው፤ ማለትም ከዮሴፍ በስተቀር ማንንም ወንድ አታውቅም፤ ታዲያ ምኑ ላይ ማመንዘር የምትለው? ኢየሱስ ሌሎች ወንድሞችና እህቶች እንደነበሩት ከነስማቸው እየዘረዘረ የሚናገረው እኔ ሳልሆን መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ማርያም ከኢየሱስ ውጪ ሌላ ልጅ አልነበራትም፤ ኢየሱስም እህትና ወንድሞች አልነበሩትም የምትል ከሆነ አውጥተህ ከቃሉ ማሳየት ብቻ ነው።

የተለየ ሃሳብ ካለህ ከመጽሐፍ ቅዱስ አውጥተህ ብታስተምር የበለጠ ብዙዎችን ይጠቅማል እንጂ ሰይጣን ምናምን ማለቱ ብቻ ማንንም አይረዳም። ለማስታወስ ያህል ሰይጣን ብቻ ሳይሆን ኢየሱስም በጣም ብዙ ቦታ "የተጻፈውን አላነበባችሁምን" እያለ ከሰይጣን ይልቅ ብዙ ጠቅሶዋል። የተጻፈ ካለ ከቃሉ ማስተማር፤ ያለበለዚያ "ከተጻፈው አትለፍ" እንደሚል ቃሉ፤ ካልተጻፈ ዝም ማለቱ ይሻላል።
ይህንን በደንብ እዩት እባካችሁ!
ማት፤ 1፤25 እስክ ማለት በደንብ ተርጉሙት........
ትን ኢሳ 7፤14 ድንግል በድንግልና ትወልዳለች.......
ትን ህዝቂል 44፡1 'ይህ በር ተዘግቶ ነበር ተዘግቶም ይኖራል'
ማቴ 1፡25 ን በተለያዩ ትርጉሞች እዚህ ተመልከት
ቃሉ በቀጥታ የሚለው የበኩር ልጅዋን እስክትወልድ ድረስ "አላወቃትም" ወይም በትዳር ውስጥ በባልና በሚስት መካከል የሚደረገውን ግንኙነት የበኩር ልጁዋን እስክትወልድ ድረስ አላደረጉም
but he did not have marital relations with her until she gave birth to a son
but kept her a virgin until she gave birth to a Son
but did not have sexual relations ወዘተ ነው የሚለው።

ማለትም የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ ድንግል ነበረች፤ ዮሴፍም እስከዚያ ድረስ አላወቃትም ነው የሚለው። ከዚያ በኋላ ግን ድንግል ሆና አልኖረችም፤ ወይም ከዚያ በኋላ ግን ዮሴፍ አውቋታል ማለት ነው ባጭር ቃል።

ኢሳያስ 7፡14 የሚለው "ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች"

ይሄ በአዲስ ኪዳንም ስለ ኢየሱስ መወለድ የተነገረ መሆኑ የተረጋገጠ ጥቅስ ሲሆን፤ ማርያም በድንግልናዋ ኢየሱስን እንደጸነሰችው በአዲስ ኪዳንም ተጽፎአል። ምንም የሚያጠራጥር ነገር የለውም። ነገር ግን ይሄ ጥቅስ ኢየሱስን ከወለደችም በኋላ በትዳር ለብዙ ዓመታት እየኖረች፤ ድንግል ሆና ቀረች የሚል ነገር ጨርሶ አይናገርም።

ትንቢተ ሕዝቅኤል 44
1 ወደ ምሥራቅም ወደሚመለከተው በስተ ውጭ ወዳለው ወደ መቅደሱ በር አመጣኝ ተዘግቶም ነበር።
2 እግዚአብሔርም፦ ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፥ ሰውም አይገባበትም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል።

ከላይ በሕዝቅኤል 44፡1 ቁልጭ ብሎ እንደተጻፈው ይህ ክፍል የሚናገርው ወደፊት በእስራኤል ስለሚሰራው ቤተመቅደስ ነው። ሕዝቅኤል ከምዕራፍ 40 እስከ ምዕራፍ 48 በሙሉ የሚያወራውም ስለዚሁ ቤተመቅደስ ነው።

በብሉይ ኪዳንም ይሁን በአዲስ ኪዳን ይህ ክፍል ስለ ክርስቶስ ልደት ወይም ስለ ማርያም ነው የሚናገረው የሚል ምንም ዓይነት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የለም። ስለዚህ ስለ መቅደስ በር የተጻፈውን ሁሉ ስለ ማርያም ነው ለማለት በራሳችን ስልጣን የለንም። መጽሐፍ ቅዱስ ቢያንስ በአዲስ ኪዳን ይህ ክፍል ስለ ክርስቶስ ልደት መሆኑን መናገር ነበረበት። ነገር ግን ይህ ክፍል ስለ ክርስቶስ መወለድ ነው የሚል የትም ቦታ በመጽሐፍ ቅዱስ አልተጻፈም። እኛ ደግሞ ትንቢትን እንደፈለግነው መተርጎም አልተፈቀደልንም። እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፦

2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1
20 ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤
21 ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።

ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ አንድም ቦታ ሕዝቅኤል 44፡1-2 ያለው ክፍል ስለ መሲሁ መወለድ ወይም ስለ ማርያም ድንግልና ወዘተ ያወራል ስለማይልና እንደዛም ስለማይተረጉመው፤ ይልቁንም በእስራኤል ስለሚሠራው ስለ ቤተመቅደስ እንደሚያወራ ግልጽ ሆኖ ስለተጻፈ፤ ይህን ክፍል ለማርያም ድንግልና ወስደን መጠቀም አንችልም።
እንደዛ ማድረግ ከተጻፈው ማለፍ ነው።
የታረመ ተብሎ የተሰጠውን አስተያየት አልተቀበልኩትም ምክንያቱም ምንም ጥቅስ የሌለው ነው
ሰለዚህ ድፍረትሀ በፍርድ ቀን መልስ ትሰጥበታለሀ። ድሮስ ከእሶህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን?
በመሰረቱ የአይሁድ አነጋገር (ስድብ) መች ነው reference መሆን የጀመረው? ትክክለና ጸረ ማርያም መሆናችሁ ተደርሶበታል። ኣትልፉ።
መጥፎ ቃል መናገር ለሁላችንም አይጠቅምም ደግሞም የመቨነፍ ምልክት ነው ይህ የመማማሪያ መድረክ ነው እና ጥቅስ እያጣቀሱ መማማር እንጂ ሌላ ነገር አይጠቅመንም በነገራችን ላይ እኔ ጰንጤ ነኝ ግን እነዚህን ጥያቃዎችን የምጠይቀው ለምጠየቀው ጥያቄ ተጨባጭ መልስ ለመስጠት ነው እንጂ ለኔ አዲስ ነገሮች አይደሉም፡፡
ሰላም
የቱን ነው ስድብ ያልከው? ጸራጲ ወይም አናጢ እኮ ስድብ አይደለም። ኢየሱስ ያደገበት አገር የሚኖሩና ቤተሰቦቹን የሚያውቁ ሰዎች ናቸው፡ ይህ የአናጺው ልጅ አይደለም ወይ ያሉት፤ ምክንያቱም ዮሴፍ አናጺ ስለነበር ነው። ታዲያ አናጺ መሆን እኮ ስድብ አይደለም። የተከበረ ሙያ ነው።

ሌላው መጽሐፍ ቅዱስ ከዘፍጥረት ጀምሮ "አወቀ" የሚለውን ቃል ከወንድና ከሴት ጋር አያይዞ ሲናገር ስለ ግብረሥጋ ግንኙነት ነው የሚያወራው።

ኦሪት ዘፍጥረት
4፥1 አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች። እርስዋም፦ ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ አለች።
4፥17 ቃየንም ሚስቱን አወቀ ፀነሰችም፥ ሄኖሕንም ወለደች። ከተማም ሠራ፥ የከተማይቱንም ስም በልጁ ስም ሄኖሕ አላት።
4፥25 አዳም ደግሞ ሚስቱን አወቀ ወንድ ልጅንም ወለደች። ስሙንም፦ ቃየን በገደለው በአቤል ፋንታ እግዚአብሔር ሌላ ዘር ተክቶልኛል ስትል ሴት አለችው።

ኦሪት ዘፍጥረት
38፥26 ይሁዳም አወቀ። ከእኔ ይልቅ እርስዋ እውነተኛ ሆነች ልጄን ሴሎምን አልሰጠኋትምና አለ። ደግሞም አላወቃትም

የማቴዎስ ወንጌል
1፥25 የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው።

ግብረሥጋ ግንኙነት ደግሞ በትዳር ውስጥ እስከተደረገ ድረስ በመጽሐፍ ቅዱስ ንጽሕ ነው፤ ክፉ ነገር አይደለም ወይም ስድብ አይደለም።

ወደ ዕብራውያን
13፥4 መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።

ጸረ ማርያም የሚያስብለውና በእግዚአብሔር ፍርድ የሚያስቀጣውስ፤ ያልተጻፈውን በክቡር ቃሉ ላይ መጨመር ነው እንጂ የተጻፈውን ሳይጨምሩ ሳይቀንሱ መቀበል አያስቀጣም።
የክርስቶስ ተቃዋሚ ለሌላ ክብርሠጥ አያፍርም ክብርን የሚገባው አምልክ በቻነው ነቃ በሉ እንቢ አምላኬን ነው የማመልከው በሉ ነጻ ሁኑ።
ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ።
17 እንግዲህ ትውልድ ሁሉ ከአብርሃም እስከ ዳዊት አሥራ አራት ትውልድ፥ ከዳዊትም እስከ ባቢሎን ምርኮ አሥራ አራት ትውልድ፥ ከባቢሎንም ምርኮ እስከ ክርስቶስ አሥራ አራት ትውልድ ነው።
18 የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች።
19 እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ።
20 እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።
21 ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።
22 በነቢይ ከጌታ ዘንድ።
23 እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።
24 ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቅቶ የጌታ መልአክ እንዳዘዘው አደረገ፤ እጮኛውንም ወሰደ፤
25 የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው።
1/ ማቴ13፤55 ላይ ይህ የምናውቀው የጸራቢው ልጅ አይደለምን? የሚል ስለተጻፈ ኢየሱስ ከዮሴፍ እንደተወለደ ነው የምታምኑት ማለት ነው?
2/ አንዳንዶች የሚያቀርቡት ጭብጥ ማቴ 1፤25 ላይ ያለውን የበኩር ልጅዋን እስክትወልድ አላወቃትም፤ የሚለውን በመጥቀስ እስክትወልድ ድረስ እንጂ ከዚያ በኋላ ግን ከመውለድ መከልከሏን አያመለክትም ይላሉ። በ2ኛ ሳሙ 6፤23 ላይ እንደተመለከው የሳዖል ልጅ የሆነችውና የንጉሥ ዳዊት ሚስት የነበረችው ሜልኮል በታቦተ ጽዮን መመለስ ተደስቶ ክብሩን ትቶ በዘመረው በዳዊት ላይ በተናገረችው ምክንያት «እስከሞተችበት ጊዜ ድረስ ልጅ አልወለደችም ይላል» ይህን ማለቱ ሜልኮል ከሞተች በኋላ ነው ልጅ ለመውለድ የበቃችው ማለቱ ነው? የበኩር ልጅዋን እስክትወልድ...የሚለው ከወለደች በኋላ አወቃት ማለት ነው ማለት ከየት የተገኘ ትርጉም ነው? የመጽሐፍ ቅዱስ ወይስ የራሳችን እንደዚያ ቢሆን ነው እንጂ የሚል ስሜት?
3/ አይሁዳውያን ማርያም የዮሴፍ እጮኛ ስለነበረች ኢየሱስን ከዮሴፍ እንደተወለደ ስለሚያምኑ ያኔም ሆነ ዛሬ አዳኝነቱን አይቀበሉም። በእሱ ያመንንና የዳንን በድንግልና እንደወለደችው እናውቃለን። በኛ ዘንድ እነርሱ ስህተተኞች ናቸው።ምክንያቶች ማስተዋልን በተሰጠን የትንቢት ቃልና የፍጻሜው ምስራቹ የተነሳ። በእነርሱ ዘንድ ደግሞ እኛ ስህተተኞች ነን። ስህተተኞች የምንልባልበት ምክንያት የታጨላት ሰው ስለነበራት በእነርሱ ዘንድ በድንግልና ወለደች የምንለው ነገር ተቀባይነት የለውም ። በድንግልና ለመውለድ ለምን እጮኛ አስፈለጋት ቢሉ ምን ትመልሳላችሁ? በድንግልና ለምትወልድ ድንግል ሴት እጮኛ እንደማያስፈልጋት የእግዚአብሔር እውቀት አጭር ነበር? ስለኢየሱስ የዮሴፍ ልጅ የሚለውን የትውልድ ሀረግና በድንግልና መወለዱን እንዴት ያታያል?
3/ «የዮሴፍ ልጅ እንደመሰላቸው ሆኖ ....»እያለ የሉቃስ ወንጌል 3፤23 ሕዝቡ ኢየሱስን የዮሴፍ የስጋ ልጅ እንደሚመስላቸው በግልጽ እየተናገረ ካረጋገጠልን በማቴዎስ 12፤46 ላይ «አንድ ሰው እነሆ ወንድሞችህና እህቶችህ ....»ብሎ የተናገረው እንደመሰላቸው የማይሆንበት ምክንያት ምንድነው? አንድ ሰው «ወንድሞችህና እህቶችህ» ማለቱ ብቻ የሱ የስጋ ወንድሞችና እህቶች አንዳሉት በቂ ማረጋገጫ አድርገን የምንወስድ ከሆነ የዮሴፍ ልጅ ነው ማለታቸውም ትክክል ናቸው ማለት ነው? እኛ በድንግልና እንደወለደች የተጻፈውን አንብበን ተሳስተዋል ብንል ማርያም ተጨማሪ ልጆችን እንደወለደች በመጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ የተጻፈ ሳይኖር አይሁዳውያኑ ወንድሞችህና እህቶችህ ስላሉ ብቻ ማርያም ወለደች እንድንል የፈቀዱልን አይሁዳውያኑ ናቸው?
4/ በዮሐንስ ወንጌል 6፤42 ላይ እኔ ከሰማይ የወረድኩ እንጀራ ነኝ ሲል አይሁዳውያኑ«ይህ እናቱንና አባቱን የምናውቃቸው የዮሴፍ ልጅ አይደለምን» ብለዋል። የእነርሱን ምስክርነት የምንቀበል ከሆነ ከሰማይ የወረደ የሕይወት እንጀራ አይደለም ልንል ነው? በስጋ የዮሴፍ ልጅ ነው ብለው በራሳቸው እናውቃለን ማለታቸው ከእውነት በሆነ እውቀት ነበር? በማቴዎስ ወንጌል 13፤55 ላይ ያለውን «ወንድሞቹና እህቶቹ ከእኛው ጋር አይደሉምን» ብለው የዘረዘሩትን አምነን ተቀብለን የስጋ ወንድሞችና እህቶች አሉት ያሉትን ካጸደቅንና ወስደን የማርያም ልጆች ናቸው ብለን በማስታቀፍ ለእነሱ እውነተኛነት እኛ አሁን ምስክሮች ነን ማለት ነው?
4/ክርስቶስ በመስቀል ላይ እያለ ከመስቀሉ ስር ከነበሩት መካከል «እናቱን ማርያምንና የሚወደውን ደቀመዝሙር አጠገቧ ቆሞ ሲያያቸው እናቱን« አንቺ ሴት ሆይ ልጅሽ ይኸው አላት፤ ደቀመዝሙሩንም እናትህ ይህችው አለው»። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ይህ ደቀመዝሙር ወደቤቱ ወሰዳት። ይላል ዮሐንስ 19፤26-27 እዚህ ላይ በደረቅ ለሚሞግቱ ጥቂት ደረቅ ጥያቄዎችን ማቅረብ ተገቢ ይሆናል። ሀ/ እነሆ ልጅሽ ማለት ድሮ ያልወለደችው ያን ጊዜ መስቀሉ ስር ወለደችው ማለት ነው? ለ/ ጌታ ይወደው የነበረውን ደቀመዝሙር እነሆ ልጅሽ ሲላት ሌላ ልጅ እንዳልነበራት አምነን እንድንቀበል የጌታ ቃል በቂ ማረጋገጫችን አይሆንም? ወይስ ልጆችዋን ያገለለ ስለሆነ እንደዚያ መሆን አልነበረበትም፤ ጌታ ካደረገው ግን ምን ይደረግ መቀበል ብቻ ነው በማለት ፍትህ የጎደለው አሰራር ልንል ነው? ዮሴፍስ ወዴት ደርሶ ነበር? ሞቶ ነው እንዳንል ሞቷል የሚል ጽሑፍ አላነበብንም። በእርግጥ የዮሴፍን ታሪክ ጌታን ፈልገው ቤተመቅደስ ሲያስተምር ካገኙበት ጊዜ በኋላ በወንጌላት ውስጥ «የዮሴፍ ልጅ» እየተባለ ስሙ ከሚወሳ በስተቀር የምናነበው ነገር የለም። ዮሴፍ እስከመስቀሉ ጊዜ ድረስ በሕይወት ይኑር ፤አይኑር የተጻፈልን ነገር ስለሌለ ማርያም ለዮሐንስ እንደእናት የተሰጠችው ዮሴፍ ስለሞተ ነው ልንል አንችልም። ስለሞቱ አልተነገረምና።በህይወት እያለ ነው እንዳንል እንደአንዳንዶች አባባል ጌታ አፋትቶ ነው ከዮሴፍ እጅ አውጥቶ ለዮሐንስ የሰጠው ሊባል ነው?። ጌታ እንደዚያ ማድረጉን አላውቅም። የማውቀው ማርያም ከልጇ ሞት በኋላ እንደልጅ ለዮሐንስ መሰጠቷን ነው። ልጅ አላት የምትሉና ለምን ለልጆቿ እንዳልተሰጠችና ልጆቿም እናታቸውን «እናትህንና አባትህን አክብር»በሚለው ቃል መሰረት አክብረው ለመያዝ ለምን እንዳልቻሉ እስኪ ንገሩን!
ጽሁፌን ሳጠቃልል ከላይ ላቀረብኳቸው ጥያቄዎችና ማብራሪያ ያስፈልጋቸዋል ላልኳቸው ነጥቦች ምክንያት፤ መሸፈኛና ማድበስበሻ ሳይሰጣቸው በግልጽ እንድታስረዱኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ።
በግሌ የአይሁዳውያን የስሜት አባባሎች በቂ ማረጋገጫ ናቸው ብዬ አላምንም። መጽሐፍ ቅዱስ አንድም ቦታ ማርያም ልጆች ወለደች የሚል ቃል የለም። የጌታ ወንድሞችና እህቶች የሚለው ቃል ብቻውን የጌታ እናት እሷ ስለሆነች እሷ ስለወለደቻቸው ይሆናል እንደዚያ የተባለው እንድንል የግምት እምነትን አያበረታታም።የስጋ ወንድሞቹ ናቸው ፤አይደሉም እያልን ጌታም ሆነ ሐዋርያት ያጎደሉትን ማብራሪያ እኛ ለመሙላት የተሻልን የሆንን ያህል ለመታየት መጣር ከተጻፈው ወሰን ማለፍ ነው። ለእኛ የሚጠቅመውን በሰፊው ነግሮን ፤የሚያስፈልገንን ትቶት መሄዱ እኛ እንዲህ በመባሉ ነው፤ እንዲህ በመነገሩ ነው እያልን ወንጌልን እያረቅን ተራርቀን ቀርተናል። የጌታ ወንድሞችና እህቶች የጌታን ትዕዛዝና ቃል የሚጠብቁ እንጂ የስጋ ወንድሞችና እህቶች እንዳሉት አላውቅም። እሱም ያስተማረኝ እንደዚያ እንድል ነው። ጌታ ሰማያዊ አምላክ አይደለም የሚሉ ክርስቲያኖች አሉ፤ ጌታ የፍጥረት መጀመሪያ ነው የሚሉም አሉ፤ ማርያም የሰማይ ንግስት ናት የሚሉም አሉ፤ ያለማርያም ዓለም አይድንም የሚሉም አሉ፤ ማርያም ከጌታ ሌላ ወልዳለች የሚሉ አሉ፤ ማርያም በድንግልና ዕድሜዋን ሁሉ ኖራለች የሚሉም አሉ። ብዙ ብዙ ይባላል። ይህ ሁሉ የተጻፈውን እንዳለ ተቀብሎ በማመንና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የተጻፈውን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከማንበብ ይልቅ እውቀት በምትመስል ግን ልዩነትንና ስህተትን በምትዘራ የእንክርዳዱ ዘሪ ስራ የየራሱን ትርጉምና ስሜት እያስተጋባ ክርስትና ችግር ላይ ነው ።እንዲያ ባይሆን ኖሮ ስመ ክርስትና ሺህ ብጥስጥስ ባልሆነም ነበር። እኔስ የተሰቀለውን ብቻ እሰብካለሁ።የጌታ ኢየሱስን የስጋ ወንድሞችና እህቶች አላውቅም፤ የማውቀው ወንድሞቹና እህቶቹ በሰማይ ያሉ የአባቱን ፈቃድና ትእዛዝ የሚያደርጉትን ብቻ ነው።(ማቴ12፤50)
በቅድሚያ ማርያም የአምልኮ ወይም የእምነታችን ማእከል አይደለችም። በአዲስ ኪዳን የትም ቦታ የክርስቶስ ተከታዮች የማርያም ማንነት ላይ እንደ ወሳኝ ትምህርት ወይም የእምነታችን አንዱና ዋናው ክፍል እንደሆነ አድርገው አይተውት አያቁም።

ስለዚህ ከሁሉም በፊት ማወቅ ያለብን ማርያም ኢየሱስን ከወለደች በኋላ ሌላ ልጅ ወለደች ወይም አልወለደች በዋናው የአዲስ ኪዳን አስተምህሮትና የደቀመዛሙርቱ እምነት ላይ የሚጨምረውም ይሁን የሚቀንሰው ነገር የለም። ኢየሱስ ከድንግል እንደተወለደ ሁላችን እናምናለን። ከዚያ ውጪ የደቀመዛርሙርቱ እምነትና ስብከት በአዲስ ኪዳን እንደተጻፈው የማርያምን ማንነትንና ሕይወትን አያጠቃልልም። የእምታችን ዋና እምብርት የሚለው ኢየሱስ ስለ ኃጢአታችንም ሲል በመስቀል ላይ ተሰቀለ፣ ተቀበረ፣ በሶስተኛውም ቀን ተነሳ የሚል ነው።
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15
1 ወንድሞች ሆይ፥ የሰበክሁላችሁን ደግሞም የተቀበላችሁትን በእርሱም ደግሞ የቆማችሁበትን በእርሱም ደግሞ የምትድኑበትን ወንጌል አሳስባችኋለሁ
2 በከንቱ ካላመናችሁ በቀር፥ ብታስቡት፥ በምን ቃል እንደ ሰበክሁላችሁ አሳስባችኋለሁ።
3 እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ። መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥
4 መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥[bgcolor]

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1
22 መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ፥
23 እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥
24 ለተጠሩት ግን፥ አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው።

እኛ የምንድነውም ኢየሱስ በመስቀል በሰራው ስራ ነው እንጂ ማርያም ከኢየሱስ ሌላ ልጅ ስላልወለደች ወይም ስለወለደች አይደለም። ከኢየሱስ ሌላ ልጅ ቢኖራትም ባይኖራትም በመስቀል ላይ ኢየሱስ የስራውን የማዳን ስራ የሚቀይረው ነገር የለም።

ስለዚህ ይህ ማርያም ሌላ ልጆች ነበሯት ወይም አልነበሯት የሚለው ጉዳይ በኢየሱስ የማዳን ስራ አንዳች የሚጨምረው ነገር የለም። አዲስ ኪዳንን በሚገባ ሙሉን ላነበበ ሰው ማርያም ከጠቅላላው የአዲስ ኪዳን ጽሑፍ የወሰደችው ቦታ በጣም በጣም ጥቂት ነው። ምናልባትም ከአንድ ፐርሰንት አይበልጥም። ከአራቱ ወንጌሎች ውስጥ ለምሳሌ ማርቆስና ዮሐንስ የኢየሱስን ከድንግል መወለድ እንደ ዋና ነገር ስላልቆጠሩት ጨርሶ አልጻፉትም። ስለ ኢየሱስ ሕይወት እየጻፉ እርሱ ከድንግል መወለዱን አልተናገሩም። አራቱም ወንጌሎች በአብዛኛው የሚያተኩሩት በሞቱና በትንሳኤው ላይ ነው (passion narrative)። በተለይም ለምን ኢየሱስ እንደሞተና መሞትም እንዳስፈለገው ነው ትልቁን የወንጌሉን ቦታ የያዘው። ይህ ብቻ አይደለም ከወንጌላቱ ሌላ ደግሞ የሃዋርያትን ስራ እንዲሁም ሁሉንም የሐዋርያትን መልእክቶችና የዮሃንስንም ራእይ ስንመለከት የማርያም በድንግልና ኢየሱስን መውለድ ጨርሶም አይጠቀስም።

ስለዚህ የማርያም ኢየሱስን ከወለደች በኋላ ድንግል ሆና መኖር ወይም አለመኖር በአዲስ ኪዳን ፈጽሞ ምንም ፋይዳ የሌለው ነገር ነው። ጸሓፊዎቹም ችላ ያሉት ጉዳይ ነው። ያንን ስላመንን አንድንም፤ ያንንም ባናምን አንጠፋም።

የማርያም ድንግል ሆና ለዘላለም መኖር የሚባለው ሃሳብ ትልቅ ስፍራ ማግኘት የጀመረው ማርያም ራሷ በአዲስ ኪዳን ካላት ቦታ በላይ እጅግ ከፍ ያለ ቦታ እየተሰጣትና እርሷም መመለክ ከጀመረች በኋላ ነው። እርሷን እጅግ ከመጠን በላይ ሰዎች ከፍ ማድረግ ሲጀምሩ ከዚያ በኋላ ነው ድንግል ሆና ለዘላለም ኖረች ወዘተ የሚል ያለ ቅጥ የተለጠጠና በአዲስ ኪዳን ጨርሶ የማይገኝ ከሃይማኖት ቅንዓት የተወለደ ነገር ሰዎች ማመን የጀመሩት።

አዲስ ኪዳን ግልጽ እንደሚያደርገው፤ ከሆነ ማለትም ያለ አይሁድ ምስክርነትም ቢሆን እንኳን ማርያም የዮሴፍ እጮኛ እንደነበረች ነው። ይባስ ብሎ የማቴዎስ ወንጌል ጸሃፊ የኢየሱስን የዘር ግንድ የሚቆጥረው በዮሴፍ በኩል ነው።
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል 1
16 ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ
17 እንግዲህ ትውልድ ሁሉ ከአብርሃም እስከ ዳዊት አሥራ አራት ትውልድ፥ ከዳዊትም እስከ ባቢሎን ምርኮ አሥራ አራት ትውልድ፥ ከባቢሎንም ምርኮ እስከ ክርስቶስ አሥራ አራት ትውልድ ነው።
18 የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች።
19 እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ።

የሉቃስ ወንጌል
1፥27 ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ

በዚያን ዘመን ደግሞ እጮኝነት ይደረግ እንደነበረው ማርያም ምናልባት የ15 እና የ16 ዓመት በሆነች ጊዜ ነው የታጨችውና ኢየሱስን የወለደችው። ማለትም አንድ ፍሬ ልጅ ናት እንጂ እኛ እንደምንስላት ትልቅ ሴትዮ አልነበረችም። ይህ ብቻ አይደለም በሁሉም የእንግሊዝኛ ትርጉሞች ብትመለከት ማቴ 1፡24 ላይ ዮሴፍ ማርያምን ሚስት አድርጎ እንደወሰዳት ተጽፎአል (እዚህ ተመልከት)። ይህ ትዳራቸው ደግሞ ቢያንስ ቢያንስ ለ12 ዓመታት ያህል እንደቆየ ደግሞ በሉቃስ ወንጌል እናገኛለን። ማለትም ኢየሱስ የ12 ዓመት ልጅ እያለ በመቅደስ ከቤተሰቦቹ ጠፍቶባቸው ማርያም ራሷ "አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን" ነው ያለችው።
Quote:
የሉቃስ ወንጌል 2
41 ወላጆቹም በያመቱ በፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ነበር።
42 የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ በሆነ ጊዜ፥ እንደ በዓሉ ሥርዓት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ፤
43 ቀኖቹንም ከፈጸሙ በኋላ፥ ሲመለሱ ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፥ ዮሴፍም እናቱም አላወቁም ነበር።
...
48 ባዩትም ጊዜ ተገረሙ፥ እናቱም:- ልጄ ሆይ፥ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ፥ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን አለችው።

እንግዲህ ዮሴፍና ማርያም በትዳር ቢያንስ ለ12 ዓመት እንደኖሩ ከተጻፈና ከ12 ዓመት በኋላ ማርያም ራሷ ዮሴፍን ልክ እንደ ኢየሱስ አባት አድርጋ የሚትጠራ ከሆነ፤ ይህ በእርግጥ ማርያም ዮሴፍን እንደ ባል እንደምታየው የሚያሳይ ነው።

ይህ ብቻ አይደለም አሁንም የአይሁድን ምስክር ሳንጨምር ከደቀመዛሙርቱ ውጪ ኢየሱስ ወንድሞች እንደነበሩት የሚከተሉት ክፍሎች ያሳያሉ (እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለብን እነዚህ የኢየሱስ ወንድሞች እንደሆኑ የሚናገሩት የወንጌላቱ ጸሃፊዎች ናቸው እንጂ ከሳሽ አይሁዶች አይደሉም)
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል 12
46 ገናም ለሕዝቡ ሲናገር፥ እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋገሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር።
47 አንዱም፦ እነሆ፥ እናትህና ወንድሞችህ ሊነጋገሩህ ፈልገው በውጭ ቆመዋል አለው።
48 እርሱ ግን ለነገረው መልሶ፦ እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው? አለው።
49 እጁንም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘርግቶ። እነሆ እናቴና ወንድሞቼ፤
50 በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነውና አለ።

በዚህ ክፍል ምንም እንኳን ኢየሱስ ሊያስተምራቸው፤ እውነተኛ እናቴ ወይም እውነተኛ ወንድሞቼ ማርያምና የስጋ ወንድሞቼ ብቻ ሳይሆኑ፤ የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ ነው ብሎ ቢያርማቸውም፤ እርሱን ሊያነጋግሩት የመጡት ግን የኢየሱስ እናት ማርያምና የስጋ ወንድሞቹ እንደሆኑ ግልጽ የሆነ ጉዳይ ነው ምክንያቱም ማቴዎስ ራሱ ነው እየነገረን ያለው።
Quote:
የዮሐንስ ወንጌል
7፥5 ወንድሞቹ ስንኳ አላመኑበትም ነበርና።

በዚህ ክፍል ደግሞ የወንጌሉ ጸሃፊ ዮሐንስ ራሱ ነው የኢየሱስ የስጋ ወንድሞች ራሳቸው እንኳን እንዳላመኑበት የሚናገረው። እነዚህ መቼም ደቀመዛሙርቱ ሊሆኑ አይችሉም። ምክንያቱም በኢየሱስ የማያምን ደቀመዛሙርት የኢየሱስ መንፈሳዊ ወንድም ሊሆን አይችልምና። በኢየሱስ ምንም ባያምኑም እንኳን ነገር ግን ወንድሞቹ ተብለው ሊጠሩ የሚችሉት የስጋ ወንድሞቹ ብቻ ናቸውና።

በገላትያ መልእክቱ ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ ኢየሩሳሌም ጉዞው ሲናገር፤ ያዕቆብ የጌታ ወንድም እንደሆነ ይመሰክራል።
Quote:
ወደ ገላትያ ሰዎች 1
19 ነገር ግን ከጌታ ወንድም ከያዕቆብ በቀር ከሐዋርያት ሌላ አላየሁም።

ሁሉም ደቀመዛሙርት እንደ ጌታ ወንድም የሚታዮ ቢሆን ኖሮ ያዕቆብ የጌታ ወንድም እንደሆነ ጳውሎስ ለይቶ መጻፍ አያስፈልገውም ነበር። ነገር ግን የጌታ የስጋ ወንድም የሆነውን ያዕቆብ ጳውሎስ እንዳገኘ ለመግለጽ ነው። እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለብን ያዕቆብ በኢየሱስ ያመነው ከትንሳኤ በኋላ ኢየሱስ ራሱ ከተገለጠለት ነው (1ቆሮ 15፡7)

ይህ ብቻ አይደለም፤ በናዝሬት አይሁዶች የኢየሱስ ወንድሞች እንደሆኑ ከዘረዘሯቸው ስሞች ውስጥ ያዕቆብና ይሁዳ ይገኙበታል። የይሁዳን መልእክት የጻፈው ይሁዳ ደግሞ ስለ ራሱ ሲናገር፤ የያዕቆብ ወንድም እንደሆነ ይመሰክራል።
Quote:
የይሁዳ መልእክት
1፥1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ፥ በእግዚአብሔር አብ ተወደው ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ፤

የአይሁዶችን ሁሉ ምስክሮች እውጥተን የወንጌላቱ ጸሃፊዎች፣ ሃዋርያው ጳውሎስ እንዲሁም ሌሎቹ ደቀመዛርሙርት የሚመሰክሩትን ምስክርነት ብቻ እንኳን ብንወስድ የሚከተሉትን እናገኛለን፦

1- ሁሉም የሚመሰክሩት ኢየሱስ የስጋ ወንድሞች እንደነበሩት ነው
2- ወንጌላቱ የመሰክሩት ማርያምና ዮሴፍ በትዳር እንደ ባልና ሚስት ቢያንስ ለ12 ዓመታት ያህል መኖራቸውን ነው። ማርያምም ዮሴፍን እንደ ባልዋ እንደምታየው ነው።
3- ማርያምና ዮሴፍ ግብረ ስጋ ግንኚነት ያልነበራቸው ማርያም ኢየሱስ እስክትወልድ ድረስ ነው። (ማቴ 1፡25)

በእርግጥ ነው በስጋ የኢየሱስ ወንድሞች የማርያም ልጆች ናቸው ወይም የዮሴፍ ልጆች ብቻ ናቸው የሚለውን መጽሐፍ ቅዱስ አይመልስም። ሆኖም የማርያም አይደሉም ለማለትም የሚያመለክት ምንም አይነት ፍንጭ የለም። ፍንጮቹ ሁሉ የሚያመለክቱት ዮሴፍና ማርያም ባልና ሚስት ነበሩ ልጆችም ነበሯቸው ወደሚል ነው። በትዳርም ዓለም ኖራ ድንግል ናት ወዘተ ወደሚል የተለየና እጅግ የበሬ ወለደ አይነት አመለካከት ለመዞር የሚያሳይ ምንም ፍንጭ የለም። ፍንጮቹ በሙሉ ማርያምና ዮሴፍ በተዓምር ኢየሱስ ከተወለደ በኋላ እንደ ማንኛውም ሰው በትዳር ኖረው ልጆች ወልደው እንደኖሩ እንጂ፤ ሌላ የድንግልና ኑሮ፤ ሌላ ለዘላለም ድንግል የመሆን፤ የኢየሱስ ወንድሞች የማርያምና የዮሴፍ ላለመሆናቸው ወዘተ የሚያሳይ ቅንጣት ታህል እንኳን ፍንጭ የለም።

ስለዚህ ማርያም ኢየሱስን ከወለደች በኋላ ድንግል ሆና ስለመኖሯ ቅንጣት ታህል ፍንጭ ስለሌለና ይልቁንም መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው ፍንጭ በተቃራኒው ማርያምና ዮሴፍ በትዳር ዓለም እንደ ባልና ሚስት ለብዙ ዓመታት መኖራቸውን ስለሆነ፤ ማመን የሚገባን ያንን ነው እንጂ፤ እንዲያው ማርያምን ከፍ ለማድረግ ብቻ የማይሆን ፋንታዚ ውስጥ መግባት የለብንም። በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተጽፈ ወይም ቃሉ ቅንጣት ታክል ፍንጭ የማይሰጠው ተዓምር ማለትም ልጅ ከወለዱ በኋላና በትዳር ከኖሩ በኋላ ድንግል ሆኖ መኖር የሚባል ነገር መፍጠር አያስፈልገንም።
ለጥያቄዬና እስካሁን በተደረጉ ውይይቶች አንጻር ብዙ ተብሎ ሳለ ላውቃቸው የምፈልጋቸው ነገሮችን ማንሳት በወደድኩት መጠን የሰጠኸን ነገር የለም። ቀደም ባሉ ክርክሮች ልትመልሳቸው ይገባ የነበረው «የርሷ ልጆች የመውለድና ያለመውለድ ጉዳይ የእምነታችን ማእከል አይደለም» የሚለው አባባልህ ለጥያቄዎቼና ማብራሪያ የፈለኩበትን ነጥብ በዚያ አስታከህ ለማለፍ መፈለግህ የውይይቱን መነሻ ሃሳብ ረስተህ ወደዋናው ሕይወት ቃል ጉዳይ ብቻ ግባ እያለ ጽሁፍህ ሲገፋኝ ይታየኛል። የክርስትና አንኳሩ ነገር የማርያም በድንግልና መኖር ፤አለመኖር ጉዳይ አይደለም ማለትህን ግን ሳላመሰግን አላልፍም። ጥሩ ብለሃል። ዋናውና የሕይወት ማጠንጠኛው የአዳኙ ቃል ነው። ብዙ ባልተጻፈ ነገር ላይ የየራስን ስሜት በፍልስፍና ዘይቤ እንዲህ ቢሆን ነው፤ወይም እንዲያ እንድንል የሚመራን ትምህርት አይጠቅመንም ከተባለ፤ አዎ እቀበላለሁ።ግን በድንግልና ኖረች የሚሉትን ለመቃወም ተብሎ የሚፈጠር የልጅ አላት ተቃውሞና በድንግልና ኖረች የሚሉ ሰዎች ከሁኔታዎች በላይ ለሰቀሉት ሃሳብ ማስረጃ አቅርቡ ከማለት በዘለለ እንዲሁም፤እንደዚያ የሚል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ የለም በማለት ምላሽ መስጠት፤የተሳሳተውንም መመለስ ሲገባ፤ እንደዚያ ማለት እንደዚህ ቢሆን ነው እያልን ጠንካራ መካቾች ሆነን ለመገኘት እውቀት አጠር የግምት ፍቺዎች ተጨባጭ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልሶች ላይሆኑ ወይ ያንን መተውና ወደ የሕይወታችን ራስ ጉዳይ መግባት አለያም በነካካው እጅ መጨረስ ይገባል ባይ ነኝ። ወንድሜም፤ «የእርሷ ልጆችን መውለድ አለመውለድ በሕይወታችን ላይ የሚጨምረው አንዳች ነገር የለም» ያልከውን እንዳለ የምቀበለው ሃሳብ ሆኖ ነገር ግን «አንዳች ምንጠቀምበት ነገር የለውም» ባልከው ጉዳይ ግን የሃሳብ ፍጭቶችህን የምንጠቀምበት እውነታ እንዳለው ያህል በመቁጠር መቀጠልህና አስረጂዬ ናቸው የምትላቸውን ጥቅሶች ለግምቶችህ ማጠናከሪያ ስትጠቀም እንደመነሻው አባባሉ የህይወት ቃል ባልሆነ ጉዳይ ላይ ምን አደከመው ታዲያ እንድል አድርጎኛል። ፋንታዚ በሆነ የልብ ሰቀላ የድንግልና ጉዳይ የህይወታቸው መመሪያ ላደረጉ ሰዎች የሚሰጡ መልሶች ለእኔ ደግሞ ያንን ለማፍረስ የሚፈጠር ሌላ ፋንታዚ መልስ እየተሰጠኝ እንዳይሆን እሰጋለሁ። አንተም እንዳልከውና እኔም እንደተቀበልኩት ጌታም ሆነ ሐዋርያት ያልነገሩን ለሰው ልጅ የተገባው የሕይወት ምህዋሩ ያ ስላልነበር ነው። ይሁን እንጂ ጽሁፉ ላቀረብኩት ሎጂካል ፋላሲ መልስ ሲጠፋው እስካሁን እንደመረጃ ስትጠቅሱት የቆያችሁትን ጥቅስ ሁሉ እንኳን ትተን የሐዋርያቱን ብንጠቅስ....ወደ ሚል ውሃ የማያነሳ ጥቅስ ፍለጋ መውረድ ተገቢ አይደለም። ማስረጃዬ በምትሉት ጥቅስ ሁሉ ለሚቀርቡ ጥያቄዎችና ማብራሪያ አስፈላጊ ነጥቦች ላይ በነበረው የእምነት አቋም ጸንቶ መመለስ ተገቢ ነው። ኢየሱስ ጠፍቶባቸው ቤተመቅደስ ባገኘችው ጊዜ «እኔና አባትህ ተጨንቀን ስንፈልግህ ነበር» በማለት የተናገረችውን በመጥቀስ የዮሴፍ ሚስት ስለሆነች የልጆች ወልዳለችን ሞገት ለማረጋገጥ በመረጃነት የተጠቀሰውን ተከትዬ ያልተመለሱልኝ እንዳሉ ሆነው አሁንም ከሕይወት ቃል መማማር ይልቅ....ምላሽ ለመስጠት በተሞከረው አካሄድ የማይመለሱልኝ እንደሚኖሩ ግንዛቤ ይዤ ጥቂት ልል ወደድሁ።።
በዚህ ምንባብ ከዮሴፍ ጋር መሆኗን ትናገራለች እንጂ ልጆች መውለዷን የገለጸችው ነገር እንዳለ አለማንበቤ የተጻፈውን ስቼ ይሆን? ወይ ደግሞ እኔ ጋር ያለው ወዲያ ካለው ይለይ ይሆን? ከዮሴፍ ጋር ከነበረች መቼም ልጆች መውለዷ አይቀርም ከተባለ አዎ ጥሩ ግምት ነው። ግምት ግን እውነተኛ አስረጂ ሊሆን ግን አይችልም። በቃ ከዮሴፍ ጋር ካለች ልትወልድ ትችላቻ!!! ግምቱ ግን ላትወልድም ትችላለች የሚል አጸፋ ይከተለዋልና መቶ በመቶ ስለማያረጋግጥ ግምቱ ግምት ሆኖ ይቀራል። እነያእቆብ እነዮሳ የጌታ ወንድሞች የሚል ጥቅስ ብዙ ቦታ ስላለ ከማርያም የተወለዱ ቢሆን ነው እንጂ እንደዚያ የተባለው የሚል አስረጂ ስላለ ማርያም ልጆችን ወልዳለች የሚለው ሃሳባችን በዚህ ይጠናከራል ቢባል አዎ ያስኬዳል። ግን ማርያም ሌሎች ልጆችን ወለደች የሚል ጽሑፍ በትክክል ተጽፎ የተቀመጠ ስለሌለ የማርያም ልጆች ሊሆኑ ይችላሉ ወይም መሆናቸው የበለጠ ተዓማኒ ነው ቢባል ጥሩ ግምት ነው። ግምቱ ከእውነታ ጋር የሚመሳሰል ሊሆን ይችላል። ያ ማለት ግን በትክክል የእርሷ ልጆች ናቸው እንድንል የመጽሐፍ ቅዱስ አስረጂ ስለሌለን የኛ ግምት ይሆናል። ግምታችንን እውነታውን ያንጸባርቃል ብንል፤ ያ ማለት ግን መጽሐፍ ቅዱስ ለጎደለው ግልጽነት አዎ የርሷ ናቸው የሚል የእውነታው ምትክ ጥቅስ ከእኛ ይሆናል ማለት አይደለም። የቱንም ያህል ካሉት ነባራዊ ሁኔታዎች ተነስተን ብንናገር መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያላስቀመጠውን ነገር ሁሉ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነታ ይተካል ማለት ልንል አንችልም። ዮሴፍ ከማርያም በፊት ልጆች ኖረውት ቢሆንስ? የሚል አጸፋ ቢነሳ እንደዚህ ዓለም የሰው ልጅ አኗኗር የተነሳ ቢገመት አዎ ይሄም ያስኬዳል። ይህም ከእውነታ ጋር የሚቀራረብ ግምት ነው። ግምት ግን ከግምት ባለፈ መጽሐፍ ቅዱስን አይተካምና ሚዛኑ የጎደለ ይሆናል። ከማርያም በፊት የወለዳቸው ቢኖሩ ከማርያም ጋር ሲኖር ልጆቹ የጌታ ወንድሞች ተብለው ሊጠሩ አይችሉም? የሚል ግምት ቢነሳ ይህም ያስኬዳል። ግምቱ ከግምት አልፎ እውነታውን አያስረዳም።ወንድሞች ስለተባሉ ማርያም ወለደቻቸው የሚል ካልተቀመጠ በምናልባታዊነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምላሽ አይሰጥም። በእርግጠኝነት ደግሞ እሷ አልወለደችም በሚል የተነገረን ነገር የለም። ግምታችን የቱንም ያህል እውነቱን ሊመስል ቢችል እንድናውቀው ባልተቀመጠው ነገር እኛ ስጋዊ ገማቾች ነን እንጂ በዘመኑ የነበርን የዓይን እማኞች አይደለንም። ደግሞ «እኔና አባትህ...»ስትል ዮሴፍ የኢየሱስ አባት ነው ብላለችና ዮሴፍ ወልዶታል የሚል ሰው ማነው? በአባትነት ስላሳደገው ነው «አባትህ » ያለችው የሚል ምላሽ የምናመጣው ከግምት የተነሳ ሳይሆን እቅጩን አረጋጋጭ ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ስለነገረን ነው።«ከአንቺ የሚወለደው በመንፈስ ቅዱስ ነው» የሚል ስለተቀመጠልን። «እነሆ ልጅሽ፤ እነኋት እናትህ» ያለው ክርስቶስ ዮሐ19-26 ልጅ ስላልነበራት ዮሐንስ እንደእናት ያኖራት ዘንድ ነው ቢባል ስህተት ይሆን? ከዮሴፍስ ለምን እንዲለያዩ ተደረገ ቢባልስ መልሱ ምን ይሆን? መልሶቹ ሁሉ ከግምት አያልፉም። እውነታው እውነት ሆኖ ያለቢሆንም ያ ለእኛ አስፈላጊ ስላይደለ አልተዘረዘረልንም። እኛ መዘርዘር ከፈለግን መዘርዘር እንችላለን። ዝርዝራችን ግን መጽሐፍ ቅዱስ ያልሰበሰበው ዝርዝር ሆኖ ከመቅረት አያልፍም። በጥቅሉ ያልተጻፈውን በመተርጎም ግምት ማስቀመጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስላልሆነ የትኛውም ወገን በድንግልና ስለመኖር የሚከራከሩም ሆነ ማርያም ልጆች ወልዳለች ባዮች ይደግፈናል በሚሉት ጥቅስ ላይ ተለጥፈው እውነት ሊመስል ከሚችል ግምት በዘለለ በዚህ ጉዳይ ላይ ግልጽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ አይደሉም።እኔ እዚህ ላይ እየተባለ ያለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም ከሚል መነሻ ሃሳብ እንጂ ኃይል አርያማዊት ነች፤ ዓለም የተፈጠረ ለማርያም ነው፤ ዓለም ያለማርያም አማላጅነት አይድንም ባዮችን ለመከላከል(defend)አይደለም። አባባሉን ስለማልቀበል። እንደዚሁ ሁሉ ማርያም ልጅ መውለዷን ስለክርስቶስ በግልጽ ከተቀመጠልን ውጪ ባልተነገረ ነጥብ ላይ የጌታ ወንድሞች የተባሉት ማርያም ብትወልዳቸው ነው ብዬ ባልታጻፈ ነገር ግምት አላስቀምጥም። ግምት ከሆነ መገመት ከምችላቸው የዚህ ዓለም አሰራሮች አንጻር በማሰብ ሌሎች ጽንፈኞችን ለመሞገት አላስብም።
«እስክትወልድ አላወቃትም....» የሚለው ጥቅስ ከወለደች በኋላ ግን አወቃት የሚል ተከታይ ጥቅስ እኛ ነን መሙላት ያለብን? እንደዚያ ያለው ከወለደች በኋላ እንዳወቃት ቢገልጽ ነው እንጂ....ማለት አንድም እንደዚህ ማለት ነው፤ አንድም እንደዚህ ሲል ነው እያሉ በአንድምታ የሚያሰለቹንን ሰዎች ደግመን እዚህ ላይ ልናገኛቸው ከምንገደድ በስተቀር ተከታይ ቃል ልንጨምር ከማቴዎስ ውክልና የተሰጠው የለም።
ዮሴፍን አንደአባቱ ቆጥራ በመናገሯ የሥጋ አባቱ እንደሆነ መናገሯ ነው ብዬ የማላየው በድንግልና እንደወለደችው፤ እሷም እንደቃልህ ይደረግልኝ ያለችውን ማስረጃ ይዤነው። አብረው ከዮሴፍ ጋር ሲኖሩ ስላለው ሁኔታ እንደማንኛውም ሰው ሊገመቱ የሚችሉ የዚህ ዓለም ኑሮ ግምቶች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ያ ሊሆን የሚችል ነገር ነው ተብሎ የሚገመቱ ግምቶች ግን ለእኔ እንደመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ ሊቆጠሩ አይችሉም። ማርያም ከሌሎች ሴቶች በተለየ ያለምንም የምጥ ጭንቅ ነው የወለደችው የሚሉ አሉ፤ ያለጭንቅ ስለመውለዷ የተጻፈ ስለሌለ ያ አባባል ከግምት ያለፈ ሊሆን አይችልም። እንደምናውቀውና እንደምንሰማው ልጅ ሲወለድ ከዚህ ተነስተን ስለማርያም አወላለድ የምንሰጠው ነገር ከነባራዊ ሁኔታ ተነስተን ብንገምት ግምት ያለጣር እንድንል በመጽሐፍ ቅዱስ የተቀመጠ አድርገን ልንወስድ እንዴት?
በጥቅሉ ማርያም ልጆች ወልዳለች የሚሉ ሞጋቾች ይህ እስከሆነ ድረስ እንዲህ ሊሆን የግድ ነው፤ያ ባይሆንማ እንዲህ ሊሆን አይችልም የሚሉ ግምቶችን አፍልቀው ራሳቸው ለመሰላቸው ሃሳብ ራሳቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ደጋፊ ማስረጃ በመጥቀስ ከሚናገሩ በስተቀር አንድም ቦታ ማርያም ተጨማሪ ልጆችን ወልዳለች ወይም ነበሯት የሚል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ከመረጃ ያለፈ ማስረጃ ጥቅስ ሊያቀርቡ አይችሉም። ይልቁንም ምክንያትና ጥቅስ ለግምት ማጠናከሪያ በማቅረብ በድንግልና ኖራለች ለሚሉ አንጀኞች እንደማፍረሻ ለመጠቀም የመሞከር መንፈስ ያይል ዘንድ የሚነገሩ ናቸው። በድንግልና ኖራለች ባዮችም ከግምት ያለፈ ከዮሴፍ ጋር ስትኖር በድንግልናዋ ነው ብለው ለሚከራከሩበት የተሰቀለ ሃሳብ ማሳመኛ አንድም ጥቅስ እንደዚያው በድንግልና ኖረች የሚል ጥቅስ ማቅረብ አይችሉም። ሁሉም የሚለያዩት የየራሳቸው ስነሞገት በማቅረብ ሲሆን ሁሉም አንድ የሚሆኑት በግምትና ሊሆን የሚችለው ሚዛን የኛው ትክክል ይሆናል በማለት አንድ ናቸው።
እንድናውቀው ባለማስፈለጉ ተብራርቶ ባልተቀመጠና ባልተጻፈ ነገር ላይ የሁለት ጎራ የየራስን ስሜት የኔው የበለጠ ተዓማኒነት ያለው ትርጉም ይሰጣል ከሚል ፈጠራና ግምት ላይ ተቸክለን ከመቅረት ከተጻፈው ሳንቀንስና ሳንጨምር የየራሳችንን የቢሆን ነው ትርጉም ትተን የማዳን ዋጋን በከፈለው በኢየሱስ ክርስቶስ ቃሎች ላይ አይኖቻችንን እናሳርፍ። ጉንጭ አልፋዎች ከመሆን እንራቅ። ሊላይ ነኝ።
ሰላም ወገኔ

ብዙውን የአንተን መከራከሪያ ነጥብ ወድጄዋለሁ። ምክንያቱም በማስረጃ የተመሰረተ መረጃን ስለምትፈልግ ማለት ነው። ሆኖም አዲስ ኪዳን በሚጻፍበት ጊዜ ማርያም ለዘላለም ድንግል ሆና ትኖራለች የሚል አስተሳሰብ ስላልነበረ፤ ለዚህ አስተሳሰብ መቃወሚያ የሚሆን ግልጽ ያለ ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ መፈለግ የለብንም። ማለትም ማርያም ዮሴፍን አግብታ በትዳር ድንግልናውን አጥታ ሌሎች ልጆችን ከዮሴፍ ወልዳ ኖራለች ብሎ እንዲጽፍልን መፈለግ የለብንም። እንዳልኩት የማርያም ከዚያ በኋላ ያለው ኑሮ ለወንጌል ጸሃፊዎቹ ዋና ነገር ስላልነበረ በቀጥታ አልጻፉትም። በተዘዋዋሪ ግን አንዳንድ የሰጡን ጠንካራ ፍንጮች አሉ ነው ያልኩት።

እነዚህ ፍንጮችም የሚከተለውን ያሳያሉ። አንደኛ ማርያምና ዮሴፍ ኢየሱስ ከተወለደ በኋላ እንደማንኛውም ባለትዳር በትዳር እንደኖሩ ያሳያሉ፡፡ ሚስት እንድትሆነው ወሰዳት ካለ እና እንዲሁም ደግሞ ያላወቃት ኢየሱስን እስክትወልድ ድረስ ከሆነ፤ በተጨማሪም ከ12 ዓመት በኋላም ዮሴፍና ማርያም አብረው ካሉና ማርያም ዮሴፍን እንደ ኢየሱስ አባት የምትጠራው ከሆነ ወዘተ እነዚህ ፍንጮች ማርያም ኢየሱስን ከወለደች በኋላ እንደማናቸውም ሰው በትዳር ኑሮ ከዮሴፍ ጋር እንደኖረች የሚጠቁሙ ናቸው።

ይህ እንዲህ ከሆነ ደግሞ ኢየሱስ ወንድሞች እንዳሉት ደግሞ የሚያሳዩ ብዙ ማስረጃዎች አሉ። ከላይ አንዳንዶቹን ጠቅሼአለሁ። ከዚህ በታች ደግሞ በተለይ ደቀመዛሙርቱንና ወንድሞቹን ለያይቶ የሚጠራበት አንድ ክፍል ልጨምር፦
Quote:
የዮሐንስ ወንጌል
2፥12 ከዚህ በኋላ ከእናቱና ከወንድሞቹ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፥ በዚያም ጥቂት ቀን ኖሩ።

NIV ©
After this he went down to Capernaum with his mother and brothers and his disciples. There they stayed for a few days.

ይህ እና ሌሎችም ከዚህ በፊት ያስቀመጥኳቸው ጥቅሶች ሁሉ ኢየሱስ ወንድሞች እንዳሉት በግልጽ ያለ ምንም ጥርጥር የሚያረጋግጡ ናቸው። ግምቶች አይደሉም።

ባጠቃላይ እንግዲህ ኢየሱስን ከወለደች በኋላ ማርያም ድንግል ነበረች ወይም አልነበረችም የሚለውን ጥያቄ አቅጣጫ ለማስያዝ ሁለት ተጨባጭ ፍንጮች አሉን ማለት ነው። አንደኛ ማርያምና ዮሴፍ ለብዙ ዓመታት በትዳር እንደኖሩን ማርያም የዮሴፍ ሚስት እንደሆነች፤ የግብረ ስጋ ግንኙነትም ያላደረጉት ኢየሱስ እስኪወለድ ጊዜ ድረስ እንደሆነ። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ኢየሱስ ወንድሞች እንደነበሩት።

ከእነዚህ ተጨባጭ ፍንጮች ስንነሳ እንግዲህ ፍንጮቹ ማርያም በትዳር የኖረችና ልጆችም የወለደች ነበረች ወደሚለው በእጅጉ የሚያሳዩና የሚያዘነብሉ ናቸው።

የሚገርመው ግን ተቃራኒውን ለማመን አንዳች እንኳን ትንሽዬ ፍንጭ አለመኖሩ ነው። ማለትም ማርያም ኢየሱስን ከወለደች በኋላ ድንግል ሆና ኖረች ለማለት የሚያስችል አንዳች እንኳን ፍንጭ የለም። ምንም አይነት ማስረጃም ይሁን ወደዚህ አስተሳሰብ የሚጠቁም አንዳችም ፍንጭ የለም። ማርያም ልጆች አልወለደችም ብንል እንኳን በትዳር የኖረች ሴትና ኢየሱስን ከወለደች በኋላ ግብረ ስጋ ግንኙነት እንዳላደረገች ያልተመሰከረላት ሴት እንዴት ሆና ነው ድንግል ናት ብለን ለማለት የምችለው? በምን መሰረትና ፍንጭ ላይ ተመስርተን ነው?

ስለዚህ እንዲያውም ማስረጃ ማቅረብ ያለበቸው ሰዎች፤ ማርያም ኢየሱስ ከወለደች በኋላ ድንግል ሆና ኖራለች የሚሉ ሰዎች ናቸው። እነርሱ ናቸው አንድ ተዓምር እየተናገሩ ያሉት እናም ይህንን ተዓምር ከመጽሐፍ ቅዱስ አውጥተው የማሳየት ግዴታ አለባቸው እላለሁ። ማርያም ኢየሱስን ከወለደች በኋላ ድንግል አልነበረችም የምንል ሰዎች እኮ እየተጠየቅን ያለነው፤ በትዳር የኖረች ሴትና መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ግብረ ስጋ ግንኙነት ኢየሱስን እስክትወልድ ድረስ ብቻ እዳላደረገች የሚናገራትን ሴት፤ በትዳር ውስጥ ኖራ ግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረጓን ማረጋገጫ አምጡ እየተባልን እኮ ነው። እንዴ፤ ሚስት እንድትሆነው ወሰዳት እያለ፤ ግብረ ስጋ ግንኙነት እዳደረጉ ማስረጃ አምጡ ማለት ምን ማለት ነው። ይልቁኑ ማስረጃ ማምጣት ያለባቸው ዮሴፍ ሚስት እንድትሆነው ከወሰዳት በኋላና ኢየሱስን ከወለደች በኋላ ለዘላለም ድንግል ናት ብለው ልዩ ተዓምር የሚናገሩት ናቸው። እንዲህ ያለ ለየት ያለ ተዓምር በመጽሐፍ ቅዱስ እንደ ፍንጭም እንኳን አይጠቅስምና።

የወንድሞቹም ጉዳይ ተመሳሳይ ነው። ማርያምም ይሁን ስለ ዮሴፍ የተጻፈው አንድ ትዳር እንደነበራቸው ነው፤ ኢየሱስም ወንድሞች እንደነበሩት ነው። ከዚህ ውጪ ግን ማርያምና ዮሴፍ እንደተፋቱ ወይም የኢየሱስ ወንድሞች ዮሴፍ ከማርያም ሳይሆን ከሌላ የወለዳቸው ናቸው ወዘተ ለማለት የሚያስችል አንዳችም ቅንጣት ታህል ፍንጭ የለም። ይህንንም የሚሉ ሰዎች ቢያንስ ቢያንስ አንድ ፍንጭ የሚሆን ነገር መስጠት አለባቸው።

ለማጠቃለል ያህል ማርያም ኢየሱስን ከወለደች በኋላ ድንግል አልነበረችም የሚሉት ብዙ ብዙ ተጨባጭ ፍንጮች ከመጽሐፍ ቅዱስ አሏቸው። በተቃራኒው ግን ማርያም ኢየሱስንም ከወለደች በኋላም ድንግል ሆና ኖራለች የሚሉ እንዲሁ ከያዙት እምነት በስተቀር ፈጽሞ ምንም አይነት መረጃም ይሁን ፍንጭ የላቸውም።
እስካሁን ስል ከቆየሁት አንጻር አሁንም አስረግጬ ጥቂት እላለሁ። ስለፍንጮች የሰጠኸውን እቀበላለሁ። ፍንጮቹ ከምናነባቸው የወቅቱ ነባራዊ ሁኔታ የተመሰረቱ ስለሆነ ጥሩ ፍንጮች ናቸው። ፍንጭ ግን የምንፈልገውን ነገር ለማጠናከር የሚያገለግል የመረጃ ደርዝ እንጂ በራሱ ውጤት አይደለም። የምናገኛቸው ፍንጮች ወደእውነታው ሊመራን ይችላል። ፍንጮቻችን የቱንም ያህል እውነታውን ሊመስሉ ቢችሉ እውነታው እነዚህ ናቸው የሚል አስረጋጭ ነገር እስካልተቀመጠ ድረስ ያገኘናቸውን ፍንጮች እውነታውን ይወክላሉ ልንል ፈጽሞ ተገቢ አይደለም። ማርያምና ዮሴፍ አብረው መኖራቸው አይካድም። ከዚህም የተነሳ እብራውያን ክርስቶስ ከዮሴፍ እንደተወለደ ለማመን ተገደዋል። ግምታቸው ሴትና ወንድ አብረው እስካሉ ሊታሰብ የሚችል ነገር ነው። ይህ ግን ሴትና ወንድ በአንድ ቤት ጥላ እስካሉ ሊሆን ከሚችል ከዓለሙ የኑሮ ጭብጥ በመነሳት የሚታሰብ እንጂ ከዘለዓለማዊው የእግዚአብሔር ዓላማ አንጻር አስተሳሰባቸው ውድቅ ነው። በኢሳ7፤14 ላይ ድንግል እንደምትወልድ ተቀምጧልና ነው። ዮሴፍ ማርያምን ወደ ቤቱ መውሰዱ እርግጥ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ነግሮናልና። ማርያም እጮኛው ነበረች? አዎ! ነበረች ሲል ይህንን አረጋግጧል። እጮኛውን ወደቤቱ መውሰድና አብረው መኖር ሊመጣው የሚችል ነባራዊ ሁኔታዎች ሊኖሩ አይችሉም? ሊኖሩ ይችላሉ፤ ግን በግልጽ የተቀመጠ ነገር ስለሌለ የኑሮ ውጤቶችን ተነስተን በራሳችን መናገር እንገደዳለን ። ያ ማለት ግን መጽሐፍ ቅዱስ ማርያም ከዮሴፍ ተጨማሪ ልጆችን ስለመውለዷ እስካልተናገረ ድረስ እንደዚህ ዓይነት ነገሮችን በዝርዝር ሊናገር አይችልም ከሚል ደካማ አስተሳሰብ የተነሳ እኛ የተሟላ ለማድረግ ፍንጮቹን ወደ ተለጠጠ የነባራዊ ዓለም ህይወት ጎትተን ልናመጣቸው መብቱ የለንም። እያልኩ ያለሁት መጽሐፍ ቅዱስ ሙላት የጎደለው አድርገን እንዲህ ያለው እንዲህ ለማለት ነው፤ ይህ ደግሞ እንዲህ ቢሆን ነው አንበል ነው።እግዚአብሔር ነገሩን በግልጽ በቃሉ መጽሐፍ መናገር ያልፈለገው የኋላ ትውልድ (እኛ) የተሟላና ስሜት የሚሰጥ አድርገን እንድንጠቀምበት ወይም በግልጽ አብራርቶ ማስቀመጥ የሚገባው ሆኖ ሳለ አሁን እኛ ይሄን ነው፤ያ ነው እያልን እንድንፋጭበት ፈልጎ እንዳልሆነ ልንረዳ ይገባል።
የሙሴ መቃብር እንዳይታወቅ ያደረገበትን ምስጢር የሚያውቀው እርሱ ብቻ ነው። እንደዚሁ ሁሉ በግልጽ ማርያምን በድንግልና ኖረች ወይም ብዙ ልጆችን ወለደች ያላለበትን ምክንያት የሚያውቀው እርሱ ብቻ ነው። ግምቶቻችን የእግዚአብሔር ሃሳብ ምትኮች ሊሆኑ በፍጹም አይችሉም።
ሌላው ወገን «በድንጋሌ ኅሊና፤በድንጋሌ ሥጋ የጸናች ክብርት እመቤታችን»የሚለው ክፍልም ቢሆን እንደዚያ የሚል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ይዞ ሳይሆን ልቡ ያፈለቀውንና ኅሊናው ቢሆን ሲል የሚመኘውን ብቻ ይዞ ነው። ብዙ ጊዜ እጮኛ ማለት ጠባቂ ማለት ነው የሚል የጅል ክርክር ያቀርባሉ። ይሁን እንጂ እጮኛን እብራይስጡ የሚናገረው(ארוס)ኧሮስ-ማለትም እጮኛ እንጂ ጠባቂ የሚለውን(שומר)ሾሜር ባለመሆኑ ይህንን ከየት እንዳመጡት አይታወቅም። እንዲሁም እብራይስጡ መጽሐፍ ቅዱስ(אשתי)ኢሽቲ-ማለትም «ሚስቱን» ሲል በግልጽ አስቀምጦት ይገኛል።γυναίκα ግሪኩም ጊኔይካ ይለዋል። ከዚህ የተነሳ በኛ የሚሳልና የሚጻፍ ዘላለማዊ የሚባል ድንግል ወይም በኛ የሚሟላ የልጆች እናትነት የመጽሐፍ ቅዱስ እርማት ሊኖር አይችልም።
ፍንጮችን ወደ ተጨባጭ የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ ለውጠንና የጎደለውን አሟልተን የኛው ከዚያኛው የተሻለ ድጋፍ የሚሰጡ ጥቅሶች ስላለን በዚያ መነሻ የዘላለማዊ ድንግልና ሙግት ባለቤቶችን እንሽራለን ማለት ከከንቱነት አያልፍም። ለየትኛውም ወገን መልሱን በቀጥታ መስጠት ያለበት መጽሐፍ ቅዱስ እንጂ እኛ አይደለንም። መጽሐፍ ቅዱስ ያልተናገረውን እኛ መጽሐፍ ቅዱስን አንተካምና ለምንናገረውና ለምናምንበት ነገር ጥንቃቄ ልናደርግበት ይገባል። ማስተዋልን ወደ ረቺነት መንፈስና የጥቅስ ፍንጭ ፍለጋ ከቀየርነው ጭንቁር ሃሳብ አራማጆች የመሆን ፍርሃት ይኖረኛል።
ወገኔ ማርያምማ ኢየሱስን ከወለደች በኋላ ድንግል ሆና እንዳልቆየች በቂ ማስረጃዎች አሉ። ቃሉ የሚያወራው አንተ እንዳልከው ሴትና ወንድ በአንድ ቤት ስለ መኖር ብቻ አይደለም። ቃሉ በቀጥታ የሚያወራው ባልና ሚስት ሆኖ ስለመኖር ነው። ይሄንን ከዚህ በታች በማስረጃ አብራራለሁ፤ ሆኖም በቅድሚያ ግን የዮሴፍንና የማርያምን ግንኙነት በተመለከተ አንድ መሰረታዎ ነገር መረዳት ያለብን ይመስለኛል።

በማርያምና በዮሴፍ እጮኝነትና ትዳር ሕይወት እኮ መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ነገር ብቻ ነው በዘመኑ ከነበረው ከሌሎች እጮኝነትና ትዳር የተለየ እንደሆነ የሚናገረው። ይሄውም በእጮኝነታቸው ጊዜ ማርያም አርግዛ መገኘቷ ነው። ይህንን ነው ማቴዎስም ይሁን ሉቃስ የተለየ ነገር እንደሆነ የሚናገሩትና ምክንያቱን የሚያብራሩት። ይህ በእጮንነት ጊዜዋ ማርያም ማርገዟ ባይኖር እኮ የዮሴፍና የማርያም የእጮኝነትና የትዳር ታሪክ ምንም የተለየ ነገር የለውም። ማርያምና ዮሴፍ የተጫጩትም እኮ አብረው ተጋብተው በትዳር ሊኖሩ ነው እንጂ ለሌላ አይደለም። ማርያም በመሃል አረገዘች ብሎ ይሄንን የመጀመሪያ እቅዳቸውን ዮሴፍ እንዳይተው እኮ ነው መልአኩ ለዮሴፍ የተገለጠለት። መጀመሪያም ሊጋቡና ትዳር ሊመሰርቱ ነው የተጫጩት፤ ማርያም ስታረግዝ ግን ዮሴፍ ጋብቻውን ሁሉ ሊተው ፈለገ፤ መልአክም ተገለጠለትና እንዳይተዋት አስረዳው፤ ከዚያም ዮሴፍ ልክ መጀመሪያ እንዳቀዱት ሁሉ ሚስት አድርጎ ወሰዳት። የተለየውን ነገር ብቻ ነው መጽሐፍ ቅዱስ የሚያብራርልን እንጂ ማንም የሚያደርገውንና የሚያውቀውን መደበኛውን አይደለም። ለዛ ማብራሪያ አያስፈልግም።

አሁን የሁለቱን የባልና ሚስት ግንኙነት ወደሚያረጋግጥልን ክፍል ልምጣ።
Quote:
Matthew 1:24-25

NASB
And Joseph awoke from his sleep and did as the angel of the Lord commanded him, and took Mary as his wife, but kept her a virgin until she gave birth to a Son; and he called His name Jesus.

NRSV
When Joseph awoke from sleep, he did as the angel of the Lord commanded him; he took her as his wife, but had no marital relations with her until she had borne a son; and he named him Jesus.

NIV
When Joseph woke up, he did what the angel of the Lord had commanded him and took Mary home as his wife. But he had no union with her until she gave birth to a son. And he gave him the name Jesus.

እስቲ ከላይ ያስቀመጥኩትን ማቴዎስ 1፡124-25 ያለውን ታሪክ ተመልከት። ዮሴፍ እጮኛውን ማርያምን ሚስት አድርጎ ወሰዳት ይላል በቁጥር 24። ይሄንን ሲጽፍ ማንም ይህንን የሚያነብብ ሰው ሌላ ማብራሪያ ካልተጨመረለት በስተቀር መደበኛ የትዳር ኑሮ እንደኖሩ ነው የሚረዳው። ዮሴፍ ማርያምን ሚስት አድርጎ ወሰዳት ብሎ ጽፎ፤ አንባቢዎች ግን ግብረ ስጋ የሌለው ትዳር ብለው እንዲያነብቡለት አይጠብቅም። ማንም የዛ ዘመንም ይሁን የአሁን ዘመን አንባቢ፤ ዮሴፍ ማርያምን ሚስት አድርጎ ወሰዳት ካለ፤ ትዳር እንደመሆኑ የግብረ ስጋ ግንኙነትንም ትዳራቸው ያጠቃልላል ብሎ ነው የሚገነዘበው። ጸሃፊው ሌላ ማብራሪያ ካልሰጠ በስተቀር። ከመደበኛ ትዳር የተለየ ነገር ካለ ጸሃፊው ሊጽፈው ይገባል። ለዚህ ነው ማቴዎስ ወዲያው በቁጥር 25 "የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም" ብሎ ለየት ያለውን ነገር የሚጽፍልን።

ዮሴፍ ማርያምን ሚስት አድርጎ ወሰዳት። ይሄ ማንም እንደሚያነብብው ግብረ ስጋ ግንኙነትን የሚያጠቃልል ነው። ሆኖም በማርያምና በዮሴፍ ትዳር ውስጥ ግን አንድ ለየት ያለ ነገር (exception) ነበር። ይሄውም ኢየሱስ እስኪወለድ ድረስ በትዳራቸው ውስጥ የግብረ ስጋ ግንኙነት አልመኖሩ ነው። በትዳር ውስጥ ግብረ ስጋ ግንኙነት አለመኖሩ ነው ልዩ የሆነው ነገር እንጂ የግብረ ስጋ ግንኙነት መኖሩ በጣም ግልጽና ማንም ሊጽፍው የሚያስፈልገው ነገር አይደለም። አንድ ጸሃፊ "በትዳር ኖሩ" ወይም "ሚስት አድርጎ አገባት" ወዘተ ካለ፤ አንባቢዎች ግብረ ስጋ ግንኙነትን አብረው እንደሚያስቡ በጣም ግልጽ ነገር ነው። "የግብረ ስጋ ግንኙነት እያደረጉ በትዳር ኖሩ" ወይም "ግብረ ስጋ ግንኙነትን የሚያጠቃልል ትዳር ነበራቸው" ወዘተ ብሎ የሚጽፍ ጸሃፊ በዚያን ዘመንም ይሁን አሁን የለም። እንዲህ አይነት አጻጻፍ ጨርሶ የለም። ምክንያቱም ትዳር በውስጡ የግብረ ስጋ ግንኙነትን እንደሚያቅፍ ለማንም ግልጽ ነውና። ከሌሎችም የሰዎች ግንኙነቶች ለየት የሚያደርገውም አንዱ ነገር እኮ የግብረ ስጋ ግንኙነቱ ነው።

ስለዚህ ማቴዎስ ሲጽፍ፤ ዮሴፍ ማርያምን ሚስት አድርጎ ወሰዳት ሆኖም የበኩል ልጇን እስክትወልድ ድረስ ግብረ ስጋ ግንኙነት አላደረጉም ካለ ይሄ ለማንም አንባቢ ግልጽ ነገር ነው። ከሌሎች ትዳሮች ልዩ የሚያደርገው ወይም exception የሆነው ነገር ተገልጿል፤ እርሱም ኢየሱስ እስኪወለድ ግብረ ስጋ ግንኙነት አለማድረጋቸው። ከዚያ ውጪ ግን ትዳራቸው ከሌሎች ትዳሮች የሚለይበት ተብሎ የተጠቀሰ ነገር የለም። ስለዚህ ጸሃፊው በትዳር እንደኖሩ ከነገረን ግብረ ስጋ ግንኙነት እንደነበረ ያለምንም ልዩ ማብራሪያ ማወቅ እንችላለን። "ግብረ ስጋ ግንኙነት ያለው ትዳር ኖሩ" ብሎ የሚጽፍ ጸሃፊ የለምና። ይልቁኑ ትዳር እየኖሩ ግብረ ስጋ ግንኙነት ባያደርጉ ኖሮ ነው መጻፍ ያለበት። ይህ በትዳር ውስጥ የተለየ ነገር ነውና መጻፍ አለበት። ያለዚያ ግን ጸሃፊው ያላለውን በግድ እንዲል ማድረግ ነው። ማቴዎስ ዮሴፍ ማርያምን ሚስት አድርጎ እንደወሰዳት ሲናገር፤ ግብረ ስጋ ግንኙነትን የሚያጠቃልል ትዳር እንደኖሩ አንባቢያን እንደሚረዱ ለማቴዎስ ግልጽ ነበር። ለዚህም ነው አንድ ነገር ጸሃፊው ማሳሰብ የፈለገው። ይሄውም ምን እንኳን በትዳር ቢኖሩም ኢየሱስ እስኪወለድ ድረስ ግን ግብረ ስጋ ግንኙነት አለማድረጋቸውን ነው። ይሄንንም ዓረፍተ ነገር ማቴዎስ የጨመረው እኮ፤ ዮሴፍ ማርያምን ሚስቱ አድርጎ ወሰዳት ብሎ ሲጽፍ በትዳራቸው ውስጥ አንባብያን ግብረ ስጋ ግንኙነት እንዳለ እንደሚረዱ ስለተገነዘበ ነው።

ስለዚህ ሁለት ሰዎች በትዳር ኖሩ ወይም አንድ ሰው አንድን ሴት ሚስት አድርጎ ወሰዳት ወዘተ ብሎ አንድ ጸሃፊ ከጻፈ፤ ሌላ ማብራሪያ ካልጨመረለት በስተቀር፤ ይህ ትዳራቸው ግብረ ስጋ ግንኙነትን ያጠቃልላል ብለው አንባባያን እንደሚረዱ ለጸሃፊው ግልጽ ነው። ማንም ጸሃፊ "ግብረ ስጋ ግንኙነት ያለበት ትዳር" ብሎ የሚጽፍ የለምና።

ማርያም ለዘላለም ድንግል ናት ብለው የሚያምኑ ሰዎች እኮ እያሉ ያሉት፤ ዮሴፍና ማርያም የመሩት ትዳር "ግብረ ስጋ ግንኙነት ያለበት ትዳር" ነበር ብሎ እንዲጻፍላቸው ነው የሚፈልጉት። ይህ ካልሆነ፤ ዮሴፍና ማርያም ምንም እንኳን ባልና ሚስት ቢሆኑም፤ በቃ ቃሉ በግልጽ አልተነጋረም ወይም በቃ ድንግል ናት ማለት ነው የሚል ፈጽሞ እኮ የማያስኬድ ሎጂክ ነው የሚሉት ያለው። ቃሉማ ማርያምና ዮሴፍ በትዳር ኖሩ ወይም ባልና ሚስት ናቸው ብሎ ተናግሯል፤ ከዚህ በላይ አንድ ሴት ድንግል ሆና አለመኖሯ ሌላ ምን ማስረጃ አለ? ቃሉ ባልና ሚስት ናቸው ከማለት ሌላ ምን ይናገር? ኦ በነገራችን ላይ የዮሴፍና የማርያም ትዳር "ግብረ ስጋ ግንኙነትን የሚያጠቃልል ትዳር ነው" እንዲል ነው የፈለግነው?

ይሄ ለእኔ ልክ ኢየሱስ ተገረፈ ይላል እንጂ ቃሉ "ጅራፉ በጀርባው ላይ አረፈበት" አይልምና ጅራፉ በእርግጥ ጀርባው ላይ ማረፉን እርግጠኛ አይደለንም የሚል አይነት የልጆች ክርክር እንደሆነ አድርጌ ነው የማየው።
" ቃሉማ ማርያምና ዮሴፍ በትዳር ኖሩ ወይም ባልና ሚስት ናቸው ብሎ ተናግሯል" ብለው የጻፉት፡ ኸረ እባክዎትን እንዲህ አልተሳፈም። የርስሆ አስተሳሰብ ማራመድ ይችላሉ ቃሉማ እያሉ የርስሆትን አስተሳሰብ ለካሉ አይስጡ
"he took her as his wife" ማለት ሚስት አድርጎ ወሰዳት ማለት ነው። በሙሉ የእንግሊዝኛ ትርጉሞች እንደዛ ነው የሚሉት። እኔ የፈጠርኩት ነገር አይደለም። መጀመሪያም ሊያገባት ነው ያጫት ለሌላ አይደለም። በኋላም ሊተዋት ሲል መልአክ አትተዋት አለው ስለዚህ ሚስቱ አድርጎ ወሰዳት ይላል ቃሉ እኔ ሳልሆን።

እዚህ በመጫን ወደ 8 የሚሆኑ የእንግሊዝኛ ትርጉሞችን ያንብቡ።
በጣም ያሳዝናል አለማወቅ ነው
–1 ድምጽ
ሰላም

ዮሴፍ ማርያም የበኩር ልጇን ከውለደች በኋላ ግን አውቆአታል የምለው አነጋገር በመጽሃፍ ቅዱስ በፍጹም አይደግፈውም። ምክንያቱም መጽሃፍ ቅዱስ የሚለው የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም ነው እንጂ ከወለደች በዋላ አወቃት የሚል በጭራሽ አልተጻፈም።

የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም ማለት ሰዎች ጌታ ኢየሱስ የዮሴፍ ልጅ ነው አንዳይሉ ነው። አንድም ቦታ በቅዱስ ቃሉ ዮሴፍ አውቃት የሚል የለም። ቢያውቃት ሓጥያት ነው እያልኩ አይደለም፤ አወቃት የሚል ሳይጽፍ እንደተጻፈ አድርጌ ሃሰት ግን አልናገርም።

ማቴ 13-55 ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን?56 እኅቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን? እንኪያስ ይህን ሁሉ ከወዴት አገኘው? ተሰናከሉበትም። መጽሃፍ ቅዱስ የሚለው ኢየሱስን የጸራቢ ልጅ ነው የጸራቢውም ልጆች (የስጋ)ወንድሞቹ ናቸው የሚሉ ሁሉ አሁንም እንደቀደሞ ዘመን እየተሰናከሉበት እንደውነ ነው።

በዚህም ዘመን ጌታን በስጋ(ከእናት፤ አባት) ወንድም አለው የሚል ይህንን ቃል ቢያስተውል መልካም ነው ፦ ማቴ12-47" እነሆ፥ እናትህና ወንድሞችህ ሊነጋገሩህ ፈልገው በውጭ ቆመዋል አለው። እርሱ ግን ለነገረው መልሶ፦ እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው? አለው። እጁንም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘርግቶ፦ እነሆ እናቴና ወንድሞቼ፤
በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነውና አለ።"
መድሃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ የጌቶች ጌታ ፤ የንጉሶችም ንጉስ ነው።
6 ዓመታት በፊት ስም-አልባ የተመለሰ
5 ዓመታት በፊት የታረመ ስም-አልባ
ሰላም ወንድሜ የአንተ ሎጂክ ትንሽ ችግር አለው።

አንደኛ የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም ማለት፤ ያላወቃት የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ ብቻ ነው ማለት ነው። ይሄ ማለት ምን ማለት ነው? ከዚያ በኋላም ምንም እንዳላወቃት መናገር ቢፈልግ ኖሮ መጽሐፍ ቅዱስ እስከ ሕይወት ፍጻሜዋ አላወቃትም ወዘተ ይል ነበር። ስለዚህ በዮሴፍና በማርያም መካከል የግብረ ሥጋ ግንኙነት ያልተደረገው የበኩር ልጇን እስክትወልድ ደረስ ነው። ከዚያ በኋላስ? ለሚለው ጥያቄኮ መጽሐፍ ቅዱስ መልስ ሰጥቶአል። ይሄውም ዮሴፍና ማርያም እኮ እጮኛሞች ነበሩ ማለትም ለትዳር የሚተሳሰቡ ማለት ነው። ከዚያ ደግሞ ዮሴፍ ሊተዋት ሲል መልአኩ እጮንነቱን እንዳያቋርጥና እንዲወስዳት ነግሮት ወስዷታል። ሚስት እንድትሆነው ነው እንጂ እህት ወዘተ እንድትሆነው አይደለም የወሰዳት። ስለዚህ ሚስት እንድትሆነው ከወሰዳትና ካገባት ደግሞ ግብረ ስጋ ግንኙነት እንዳለ ምንም የሚያጠያይቅና የሚያወያይ ጉዳይ አይደለም።

የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም ከዚያ በኋላ ሚስት እንድትሆነው ወሰዳት! ይህ ግልጽ አባባል ነው።
Quote:
Matthew 1:24

NET ©
When Joseph awoke from sleep he did what the angel of the Lord 1 told him. He took his wife,
NIV ©
When Joseph woke up, he did what the angel of the Lord had commanded him and took Mary home as his wife.
NASB ©
And Joseph awoke from his sleep and did as the angel of the Lord commanded him, and took Mary as his wife,
NLT ©
When Joseph woke up, he did what the angel of the Lord commanded. He brought Mary home to be his wife,
MSG ©
Then Joseph woke up. He did exactly what God's angel commanded in the dream: He married Mary.
BBE ©
And Joseph did as the angel of the Lord had said to him, and took her as his wife;
NRSV ©
When Joseph awoke from sleep, he did as the angel of the Lord commanded him; he took her as his wife,
NKJV ©
Then Joseph, being aroused from sleep, did as the angel of the Lord commanded him and took to him his wife,

ሁለተኛ ደግሞ ስለ ወንድሞቹ ያልከው ነገር ብዙም የሚያስኬድ አይደለም። ምክንያቱም ወረድ ብለህ ብታነብበው ኢየሱስ ራሱ የመሰናከያ ምክንያታቸውን የተናገረው ስለሚያውቁት እንደ ነብይ አለማክበራቸውን ነው እንጂ በስጋ ወንድም እንዳለው በመናገራቸው አይደለም።
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል 13
54 ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ እስኪገረሙ ድረስ በምኩራባቸው ያስተምራቸው ነበር፤ እንዲህም አሉ። ይህን ጥበብና ተአምራት ይህ ከወዴት አገኘው?
55 ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን?
56 እኅቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን? እንኪያስ ይህን ሁሉ ከወዴት አገኘው? ተሰናከሉበትም።
57 ኢየሱስ ግን፦ ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤቱ በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው።
58 በአለማመናቸውም ምክንያት በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም።

ኢየሱስንና ቤተሰቡን ከልጅነት ጀምሮ በሚያውቋቸው በናዝሬት ሲመጣ የተሰናከሉበት የስጋ ወንድሞች እንዳሉት በመናገራቸው አይደለም። ኢየሱስም ያንን አይደለም ያለው። ነገር ግን ይሄ እዚህ የምናወቀው የእነከሌ ልጅ እንዴት ነብይ ነኝ ይላል? አናውቀውም እንዴ ብለው "አወኩሽ ናኩሽ" አይነት ነገር ነው የተሰናከሉበት እንጂ ወንድሞች እንዳሉት በመናገራቸው አይደለም።

ስለዚህ የመሰናከላቸው ምክንያት የስጋ ወንድሞች አሉት በማለታቸው ሳይሆን እርሱን፣ ወንድሞቹንና እህቶቹን እንዲሁም ቤተሰቦቹን ሁሉ ስለሚያውቁ ሊያከብሩትና ሊያምኑበት ስለከበዳቸው ነው። ኢየሱስም የመሰናከላቸውን ምክንያት ያብራራው እንደዚህ ነው።

የስጋ ወንድሞቹ ናቸው የሚሉ ሁሉ ይሰናከላሉ ትላለህ ነገር ግን ማርቆስ፣ ሉቃስና ማቴዎስ ራሳቸው ሲጽፉ እናቱና ወንድሞቹ ሊያነጋግሩት እንደፈለጉ ጽፈዋል። ዮሐንስ ደግሞ "7፥5 ወንድሞቹ ስንኳ አላመኑበትም ነበርና።" ብሏል። እንግዲህ እነዚህ ጸሐፊዎች ወንድሞቹ ብለው በስጋ ወንድሞች እንዳሉት በመጻፋቸው ተሰናከሉበት ማለት ነው። ዮሐንስ ወንድሞቹ ስንኳ አላመኑበትም ሲልና የስጋ ወንድሞች እንዳሉት ሲናገር ተሰናከለበት ማለት ነው?

ሐዋርያው ጳውሎስም በገላትያ መልእክት ያዕቆብ የጌታ ወንድም እንደሆነ ጽፎአል፤ ታዲያ ጳውሎስ በኢየሱስ ተሰናከለ ማለት ነው? ይህ ሎጂክህ ጨርሶ የሚያስኬድ አይደለም።
Quote:
ወደ ገላትያ ሰዎች
1፥19 ነገር ግን ከጌታ ወንድም ከያዕቆብ በቀር ከሐዋርያት ሌላ አላየሁም።
ወንድሜ ሆይ፡
የሉቃስ ወንጌል 1፥80 "ሕፃኑም አደገ በመንፈስም ጠነከረ፥ ለእስራኤልም እስከ ታየበት ቀን ድረስ በምድረ በዳ ኖረ፡" ጌታ ለእስራኤል ከታየ በሃላ በምድረበዳ አልኖርምን እንዴ? "እስከ" የሚለው ቃል በእንተ ትርጉም ከወሰድነው፤ ጌታ ለእስራኤል ከታየ በሃላ ፈጽሞ በምድረበዳ አልኖረም እንደማለት ነው።

ለምን ያለተጻፈ እናነባለን? ወንድሜ "ስለዚህ ሚስት እንድትሆነው ከወሰዳትና ካገባት ደግሞ ግብረ ስጋ ግንኙነት እንዳለ ምንም የሚያጠያይቅና የሚያወያይ ጉዳይ አይደለም" በጠቀስካቸው የእንግሊዘኛ ጥቅሶች ለሚስትነት ጌታን ገና ሳትወልድ እንደወሳዳት ይሰረዳሉ፤ " ካገባት ደግሞ ግብረ ስጋ ግንኙነት እንዳለ ምንም የሚያጠያይቅና የሚያወያይ ጉዳይ አይደለም" ምን ማለትህ ነው? ወይስ ጌታ በድንግልና መወልዱን አታምንም? "መጽሐፍ ቅዱስ እስከ ሕይወት ፍጻሜዋ አላወቃትም ወዘተ ይል ነበር።" እንዲህ አንዲያ ይል ነበር ማለትና ፤ የአላለውን ብሎአል ብሎ ማወጅ፤ በፍጹም ትክክለኛ አካሄድ አይደለም ።

ቃሉ የሚለው አላወቃተም ነው፤ እንጅ አውቆአታል የሚል በፍጽም አልተጻፈም፤ በተጨማሪም ደግሞ የጌታ እናት አንዳንዶች እንደሚሉት ልጆች ቢኖራት ኖሮ ፤ ለምን በመስቀል ላይ ዩሃንስን ልጅ አድርጎ ለእርሱም እናት አድርጎ ሰጣት?
የማቴዎስ ወንጌል 13- 54 "ይህን ጥበብና ተአምራት ይህ ከወዴት አገኘው? 55 ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን? 56 እኅቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን? እንኪያስ ይህን ሁሉ ከወዴት አገኘው? ተሰናከሉበትም። "
"እንዴት ነብይ ነኝ ይላል"ሳይሆን ያሉት ይህን ጥበብና ተአምራት ይህ ከወዴት አገኘው? ቤተሰቹንስ የምናወቃቸው አይደሉምን ? የሚል ሃሳብ ነው ይለው። የእግዚሃብሄር ልጅነቱን ስላልተረዱ ነው የተሰናከሉብት። አሁንም የተሰናከሉበትን ሰዎች ምስክርነት ይዘው የሚሞግቱ ወገኖች አሉ። የተሰናከሉበት ሰዎች እኮ ወንድሞቹ ናቸው ያሉዋቸውን ከመዘርዘራቸው በፊት አባቱን ጸራቢ(ዬሴፍን) ነው ያደረጉት።

እኔስ የጌታ አባቱ አብ ነው ብዬ ስለማምን የተሰናከሉበትን ሰዎች ምስክርነት አልቀበልም።

ወንዴሜ እንዳንተ አባባል ወንድሞቹ ካላመኑበት ያዕቆብ ደግሞ የጌታ ወንድም ከወነ ። ያልመነበትን ጌታን ነበር ይሰብክ የነበረው ማለት ነው? እንዳንተ አባባል ያዕቆብ ጌታን ያምን ነበር ለማለት መጽሃፍ ቅዱስ በግልጽ ከያቆብ በስተቀር ወንድሞቹ አላመኑበትም ማለት አለበትን? ካልወነ እስከ ሕይወት ፍጻሜዋ አላወቃትም ትብሎ እንዲጽፍልህ ለምን ትጠብቃለ? በነገርችን ላይ የዬሴፍ ልጆች የሉትም አላልኩም። ዬሴፍ ልጆች የጌታ ወንድሞች ሊባሉ አይገባምም አልላኩም እኛ እንዃን ወንድሞቹ ተብለናልና።
ሰላም ወገኔ

በቅድሚያ አንተ የጠከስከው ሉቃስ 1፡80 የሚያወራው ስለ መጥምቁ ዮሐንስ እንጂ ስለ ጌታ ኢየሱስ አይደለም። ከላይ ጅምረህ አንብበው።
Quote:
የሉቃስ ወንጌል 1
57 የኤልሳቤጥም የመውለጃዋ ጊዜ ደረሰ፥ ወንድ ልጅም ወለደች
58 ጎረቤቶችዋም ዘመዶችዋም ጌታ ምሕረቱን እንዳገነነላት ሰምተው ከእርስዋ ጋር ደስ አላቸው።
59 በስምንተኛውም ቀን ሕፃኑን ሊገርዙት መጡ፥ በአባቱም ስም ዘካርያስ ሊሉት ወደዱ
60 እናቱ ግን መልሳ። አይሆንም፥ ዮሐንስ ይባል እንጂ አለች።
61 እነርሱም፦ ከወገንሽ ማንም በዚህ ስም የተጠራ የለም አሉአት።
62 አባቱንም ማን ሊባል እንዲወድ ጠቀሱት።
63 ብራናም ለምኖ። ስሙ ዮሐንስ ነው ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ።
64 ያንጊዜም አፉ ተከፈተ መላሱም ተፈታ እግዚአብሔርንም እየባረከ ተናገረ።
65 ለጎረቤቶቻቸውም ሁሉ ፍርሃት ሆነ፤ ይህም ሁሉ ነገር በይሁዳ በተራራማው አገር ሁሉ ተወራ፤
66 የሰሙትም ሁሉ። እንኪያ ይህ ሕፃን ምን ይሆን? እያሉ በልባቸው አኖሩት፤ የጌታ እጅ ከእርሱ ጋር ነበረችና።
67 አባቱ ዘካርያስም መንፈስ ቅዱስ ሞላበትና ትንቢት ተናገረ እንዲህም አለ፦
68 የእስራኤል ጌታ አምላክ ይባረክ፥ ጐብኝቶ ለሕዝቡ ቤዛ አድርጎአልና፤
69-70 ከጥንት ጀምሮ በነበሩት በቅዱሳን ነቢያት አፍ እንደ ተናገረ፥ በብላቴናው በዳዊት ቤት የመዳን ቀንድን አስነስቶልናል፤
71 ማዳኑም ከወደረኞቻችንና ከሚጠሉን ሁሉ እጅ ነው፤
72-73 እንደዚህ ለአባቶቻችን ምሕረት አደረገ፤ ለአባታችን ለአብርሃምም የማለውን መሐላውን ቅዱሱን ኪዳን አሰበ፤
74-75 በእርሱም ከጠላቶቻችን እጅ ድነን በዘመናችን ሁሉ ያለ ፍርሃት በቅድስናና በጽድቅ በፊቱ እንድናገለግለው ሰጠን።
76 ደግሞም አንተ ሕፃን ሆይ፥ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፥ መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሄዳለህና
77 እንደዚህም የኃጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ፤
78 ይህም ከላይ የመጣ ብርሃን በጐበኘበት በአምላካችን ምሕረትና ርኅራኄ ምክንያት ነው፤
79 ብርሃኑም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ ያቀናል።
80 ሕፃኑም አደገ በመንፈስም ጠነከረ፥ ለእስራኤልም እስከ ታየበት ቀን ድረስ በምድረ በዳ ኖረ።

ኢየሱስ ወንድምና እህት አልነበረውም የሚለው ሃሳብ በመጀመሪያዎቹ አማኞች ዘንድ የማይታወቅ ጉዳይ ነበር። ለዚህም ጳውሎስና ወንጌላቱ ይመሰክራሉ። ኢየሱስ ወንድም አልነበረውም ማርያምም ለዘላለም ድንግል ናት የሚለው ሃሳብ በመጀመሪያ የመጣው ከክርስቶስ ልደት በኋላ ከ400 ዓመታት በኋላ Jerome በሚባል ሰው ነው።

ኢየሱስ ከድንግል እንደተወለደ እኮ ምንም አጠያያቂ አይደለም። ይህ በቀጥታ በቃሉ የሚገኝ ነገር ነው። እንደዚህም ደግሞ ኢየሱስ ወንድሞች እንደነበሩት የናዝሬት ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ ወንጌል ጸሃፊዎችና ጳውሎስም ጭምር ይመሰክራሉ። አንተ ግን ይሄንን ምስክር ልትቀበል አልወደድክም።

ዮሴፍማ እንደ አባቱ መታየቱ ምንም የእምነት ችግር አያመጣም ወንጌላቱንም ብታነብብ ኢየሱስ እግዚአብሔር የእኔ አባት ብቻ ነው አልነበረም የሚለው። ነገር ግን ደቀመዛሙርቱንም ቢሆን በሰማይ ያለ አባታችሁ ነበር የሚላቸው። ምንም እንኳን እነርሱ በስጋ አባት ቢኖራቸውም። ስለዚህ ከስጋም የተወለደ ሰውን አባቱ እግዚአብሔር ነው ማለት ይቻላል። ጉዳዩ እርሱ ላይ አይደለም። ኢየሱስም የትም ቦታ እኔ ከስጋ ያልተወልድኩ የአብ ልጅ ነኝ እያለ አይደለም የሰበከው። ነገር ግን መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ ነበር የሚለው። ስለዚህ ብዙዎችም ያመኑት እርሱ የስጋ አባት የለውም ብለው አልነበረም። ነገር ግን እግዚአብሔር የላከው መሲህ ነው ብለው ነበር የተቀበሉት።

ኢየሱስም ስለ ናዝሬት ሰዎች ችግር የተናገረው "የእግዚአሔር ልጅ እንደሆንክ አላመኑም" አይደለም ያለው። ነገር ግን "ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤቱ በቀር ሳይከበር አይቀርም" ነበር ያላቸው። ማለትም እንደ ነብይ ወይም እንደ እግዚአብሔር መልእክተኛ አልተቀበሉኝም ነው ያለው።

እንደ ዮሴፍ ልጅ ሰዎች ኢየሱስን ማየታቸው ብቻውን ችግር የለውም። እንዲያውም የማቴዎስ ወንጌልን ብታነብብ የኢየሱስ የዘር ሃረጉን ማቴዎስ የሚዘረዝረው በዮሴፍ በኩል ነው። ታዲያ ማቴዎስ ተሰናከለ ማለት ነው?
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል 1
1 የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ
2 አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤
...
15 ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛርም ማታንን ወለደ፤ ማታንም ያዕቆብን ወለደ፤
16 ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ

ይህ ብቻ አይደለም ማርያም ራሷ የ12 ዓመት በሆነው ጊዜ በኢየሩሳሌም ጠፍቶባቸው ሲፈልጉትና ሲያገኙት የተናገረችው ምን ብላ ነው? "አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበር" አይደለም ያለቸው? (ሉቃ 2፡48) እና ማርያም ዮሴፍ አባቱ እንደሆነ አድርጋ መናገሯ ተሰናከለች ማለት ነው? አይደለም።

ስለ ያዕቆብ ያልከው ነገር ደግሞ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ ያደርገዋል። ወንድሞቹ ከማርያም በስተቀር ያዕቆብን ጨምሮ ወንጌላቱ ላይ በእርሱ እንዳመኑ ሳይሆን ይልቅስ ወንድሞቹና ዘመዶቹ በኢየሱስ እንዳላመኑ ነው የሚናገረው። ሆኖም ከትንሳኤ በኋላ ግን ኢየሱስ ከታያቸው ሰዎች አንዱ ያዕቆብ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል። ከዚያ በኋላ ነው ያዕቆብን እንደ አማኝና አንደ አገልጋይ በመጽሐፍ ቅዱስ የምንመለከተው። ስለዚህም ነው ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ አዋቂዎች ያዕቆብ በኢየሱስ ያመነው ከትንሳኤ በኋላ ነው ብለው የሚያምኑት።
Quote:
የዮሐንስ ወንጌል
7፥5 ወንድሞቹ ስንኳ አላመኑበትም ነበርና።

የማርቆስ ወንጌል
3፥21 ዘመዶቹም ሰምተው፦ አበደ ብለዋልና ሊይዙት ወጡ።

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15
3 እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ። መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥
4 መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥
5 ለኬፋም ታየ በኋላም ለአሥራ ሁለቱ፤
6 ከዚያም በኋላ ከአምስት መቶ ለሚበዙ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ፤ ከእነርሱም የሚበዙቱ እስከ አሁን አሉ አንዳንዶች ግን አንቀላፍተዋል፤
7 ከዚያም በኋላ ለያዕቆብ ኋላም ለሐዋርያት ሁሉ ታየ፤

ወደ ገላትያ ሰዎች
1፥19 ነገር ግን ከጌታ ወንድም ከያዕቆብ በቀር ከሐዋርያት ሌላ አላየሁም።

ሌላው በናዝሬት ቤተሰቦቹን የሚያውቁት የአገሩ ሰዎች ከጠቀሷቸው የኢየሱስ ወንድሞች ውስጥ ያዕቆብና ይሁዳ ይገኙበታል።
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል
13፥55 ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን?

የይሁዳን መልእክት ስታነብብ ደግሞ ይሄንኑ ነው የሚያረጋግጠው።
Quote:
የይሁዳ መልእክት
1፥1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ፥ በእግዚአብሔር አብ ተወደው ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ፤

ስለዚህ እግዚአብሔር በአዲስ ኪዳን የመረጣቸውና የተጠቀመባቸው ሰዎች በአብዛኞቹ በገዳምና ሰው በማይደርስበት ስፍራ ራሳቸውን ለይተው በፍጹም ጽድቅና ልዩ ቅድስና የኖሩ ሰዎች አልነበሩም። ይልቁኑ እንደ እኔና እንዳንተ ያሉ ዓሳ አጥማጆች፣ እንደ ማርያም ያሉ የ15 እና የ16 ዓመት የሚሆኑ ደናግል ህጻናት የመሳሰሉትን ነው (በዚያን ጊዜ የሚታጩት በዚህ ዓመት ስለነበር)። እንደ ፈሪሳውያንማ ሃጢአት እንዳይነካቸው ራሳቸውን የለዩትን ጭራሽ ሲገስጻቸው ነበር። ስለዚህ እንደ እኔና እንደ አንተ ያሉትን ኖርማል ሰዎችን እንደ ማርያምና እንደ ጴጥሮስ ያሉትን ልዩ ፍጥረታት ወይም ልዩ ከሰማይ የወረዱ ጻድቃን ባናረጋቸው መልካም ነው። ማርያም አግብታ በትዳር እንደማንም ሰው የሆኖረች ባለ ትዳር ሴት ናት። ገና የ15 እና የ16 ዓመት በሆናት ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን በድንግልናዋ እንድትወልድ ተጠቀመባት ማለት እንዲያው ከዚያ በኋላ ልዩ መላእክት ሆና ትዳርዋን ችላ ብላ መነነች ማለት አይደለም። ቢያንስ ቢያንስ ኢየሱስ የ12 ዓመት እስኪሆነው ድረስ ከዮሴፍ ጋር በትዳር አብራ ነበረች። አዲስ ኪዳን እኮ ሊያስተላልፍ የሚፈልገው መልእክት እግዚአብሔር ልዩ የገዳምና የቤተመቅደስ ጻድቃንን ሳይሆን በእንደ እኛ ባሉ ሃጢአተኞች፣ ቀራጮች፣ አሳ አጥማጆችና፣ ደናግል ህጻናት ወዘተ ይሰራል ይጠቀማል የሚል ነው። ስለዚህ እነዚህ እግዚአብሔር የተጠቀመባቸውን ሰዎች ልዩ መላእክት ባናደርጋቸውና ክንፍ ባናበቅልባቸው መልካም ነው።
እይ አንተ ጴንጤ ነህ ስለዚህ በ ምንም መንገድ ከ ኦርቶዶክስ ጋር መነጋገራ አትችልም እናንተ የ ትንቢቱ መፈጸሚያ ናችሁ ለምን ብትል በሁአለኛው ዘመን በ ጌታ ስም የሚመጡ አሉ ብሉአልና ሌላው ደሞ የ100 አመት ታሪክ ይዘህ ይማታውቀዉን አታውራ ስሜታዊ አትሁን ካቶሊክ እና ተዋህዶ(ቀደምቶቹ)የሚአስተምሩት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና የኖረች ብጺት መሆኑአን ነው እንጂ እንደ እናንት አይደለም እባካችሁ ክብሩአ የሚቀነስ መስሉአችሁ የማይገባ ቃል አትናገሩ ለ ተጨማሪ ማብራሪያ አምደ ሃይማኖት የሚል ምእጽሃፍ አንብቡ ስለ ሁሉ ታገኛላችሁ ደሞ እኛና እናንተ ያለን ልዩነት በ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብቻ አይደለም በጣም በሚያስገርም እና በ ሚያስደንቅ ብዙ ነገር ነው እንጂ ብቻ አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይነቃም ይባላል እግዚአብሄር ማስተዋሉን ይስጣችሁ አሜን!!!
0 ድምጾች
የተሰጡት መልሶች ሳነብ አንድ ነገር አስታወሰኝ።

A couple of years ago in Dallas, I met an African American young boy.

He said to me "What's up brother..."
I said to him "My mom never been in America."
He said. " .. to be your brother, do you think we have to have the same mother ..?" ... he said to me at last ".. are you ignorant or illiterate ?


( ትርጉም፦ ከጥቂት አመታት በፊት አንድ ጥቁር አሜሪካዊ በዳላስ ከተማ አግኝቶኝ እንዲህ አንለኝ - ሰላም ወንድሜ ፤ እኔ ደግሞ እናቴ አሜሪካ መጥታ ስለማታውቅ ወንድምህ ልወን አልችለም አልኩት፤ ጥቁር አሜርካዊውም ..ወንድምህ ለመባል አንድ እናት ሊኖረን ያስፈልጋልን? ...በመጨርሻም ወይ ማስተዋል አትፈልግም ወይም ምንም የማታውቅ ነህ አለኝ።

አሁን ግን ወንድምና ፤ እህት ለመሆን ከአንድ ማህጸን መውጣት አለበት ቤዬ የማስበውን ያላዋቂ አስተሳሰቤ አውጥቼ ጥያለው።

መጽሃፍ ቅዱስ የጌታን እናት ከጌታ ሌላ ወልዳለች፤- ዮሴፍ አወቃት፤ጸነሰች፤ ወለደች ሳይል የጌታ ወንድሞች የሚለውን ብቻ በመያዝ ከጌታ እናት የተወለዱ ናቸው የሚሉትን። ጥቁር አሜርካዊው ቢሰማ ምናልባትም እንዲ ይል ይሆናል "...to be his(Jesus') brother, do you think they have to have the same mother? ... He may say to them at last ".. are you ignorant or illiterate ?

stay blessed
5 ዓመታት በፊት ስም-አልባ የተመለሰ
5 ዓመታት በፊት የታረመ ስም-አልባ
Now you show your self how ignorant you are of the word of God. If you live in Dallas then I am sure of you can read so open the word of God read it for your self stop "_" others. It is a challenge to you personally you don't even need to buy the book it is on iyesus.com download Iota and read, read, and read some more. The beauty of Iota is it has አማርኛ, KJV and it has Strong which you can read in the language it is originated to do word study so you have no excuse to stay in darkness about the true word of God.
stay blessed my prayer is you read the word of God ከ አሉ ወጥተ እኔም አወቅሁት ቃሉ ያለውን እውነቱን እድትል ነው። May the God open your eyes and heart to see HIM face to face, may the secret of the cross of Christ Jesus be revile to you. So you may know the truth.
How are you to judge on my faith?

My eyes are opened and they can see clear enough the light & the love of the Lord who is Son of God. I can't argue with a person start by insulting others.

My heart is full of the light of Jesus Christ the True Lord of Lords. I don't have any darkness and I don't have any shame to satisfy about the true Word of God. እኔስ የተሰቀለውን ብቻ እሰብካለሁ።የጌታ ኢየሱስን የስጋ ወንድሞችና እህቶች አላውቅም፤ የማውቀው ወንድሞቹና እህቶቹ በሰማይ ያሉ የአባቱን ፈቃድና ትእዛዝ የሚያደርጉትን ብቻ ነው። (ማቴ12፤50). You have the right to believe what ever you think, but I assure you the Word of God doesn't support your claim. Because it never said the Mother of Jesus Christ has other children. I assure you one thing if you are a believer of Jesus Christ the True One, you can be her son too.

Jesus Christ Lords of Lord, Kings of King.
I am sure if you read vs. 50 you can as well read the whole chapter. It was not me who said it that he has sibling, But the bible it self so if you have to pick and chose what you believe that is on you. But don't compare the word with a brother who called you thinking you are from the mother land you share his straggle. I did not insulted you if you feel that way I am sorry but it is as if you ignore the Holy word of God and put as if it is the same as "brother" that you are call by. IF you are try to say Christ has no brothers or sisters while he was on earth. That is dead wrong. He did and the proof is in Mathew ch12 but that does not take away for HIS divinity. If you think may be that will lower Him down no it does not as HIS birth in manger and death on the cross did not this will not and never has lower WHO HE IS.
መጽሃፍ ቅዱስ ላይ፡ - የጌታ እናት ሌላ ልጅ ወልዳለች የሚል አልተሳፈም።

የጌታ እናት ሌላ ልጅ ወልዳለች የሚል በመጽሃፍ ቅዱስ ላይ አልተሳፈም!!!
0 ድምጾች
መጽሃፍ ቅዱስ ላይ፡ - የጌታ እናት ሌላ ልጅ ወልዳለች የሚል አልተጻፈም።
4 ዓመታት በፊት ስም-አልባ የተመለሰ

የተዛመዱ ጥያቄዎች

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2017 by iyesus.com
Terms of use | Contact us