ምናልባት የስሙን ትርጉም ፈልገህ ከሆነ፤ ጴንጤ ማለት በግሪክ ሃምሳ
(50
) ማለት ነው። ይህ ጴንጤ ወይም ሃምሳ የሚባለው ነገር የመጣው በበዓለ ሃምሳ ማለትም ፋሲካ ከተከበረ በኋላ በሃምሳኛ ቀኑ በሚከበረው በዓል ቀን በሃዋርያት ስራ 2 ላይ ከሆነው ነገር ጋ ተያይዞ ነው። በዚህ በዓለ ሃምሳ ቀን ወይም በዓለ ጴንጤ ቀን ወይም በ
pentecost ቀን ማለትም ከክርስቶስ ሞት በኋላ በሃምሳኛ ቀኑ
(ክርስቶስ በፋሲካ ስለሞተ ማለት ነው
) መንፈስ ቅዱስ በደቀመዛሙርቱ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የወረደበትና በልሳን የተናገሩበት ቀን ነው።
Quote:
የሐዋርያት ሥራ 2
1 በዓለ ኀምሳ (Pentecost) የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥
2 ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው።
3 እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው።
4 በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።
አማኞች እንግዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉበትና በልሳን የተናገሩበት ቀን በ
Pentecost ወይም በዓለ ሃምሳ ቀን ነው። ለዚህ ነው እንግዲህ በዚህም ዘመን በመንፈስ ቅዱስ ሙላትና በልሳን መናገር የሚያምኑና የሚቀበሉ አማኞች ጴንጤዎች ወይም
pentecostal ተብለው የሚጠሩት።