ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Sunday, 29 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

እግዚአብሔር በዘፍ 3፡14 የረገመው እባብን ነው ወይሰ ሰይጣንን ነው?

እግዚአብሔር በዘፍ 3፡14 የረገመው እባብን ነው ወይሰ ሰይጣንን ነው?
Jun 20, 2012 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

0 ድምጾች
Quote:
የዮሐንስ ራእይ
12፥9 ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።
20፥2 የቀደመውንም እባብ ዘንዶውን እርሱም ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለውን ያዘው፥

ከላይ የዮሃንስ ራእይ ግልጽ እንደሚያደርገው የቀደመው እባብ እርሱም ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለው ነው። በዘፍጥረት ላይም የተቀመጠው ዋናው ሃሳብ ሰውን ስለማሳትና ሰውን ከእግዚአብሔር መንገድ ስለማውጣት ነው። ይህ ደግሞ ዋናው የዲያብሎስ ስራ ነው እንጂ የእንስሳው እባብ አይደለም። እንስሳው እባብ የሰይጣን ምሳሌ ሆኖ በዘፍጥረት ቀረበ እንጂ እንስሳው እባብ ሰው ከእግዚአብሔር መንገድ እንዲወጣ ያሳተበት ታሪክ የለም። ከዘፍጥረት እስከ ራእይ ሰውን በማሳትና ሰው ከእግዚአብሔር መንገድ እንዲወጣ እንቅፋት በመሆን የሚታወቀው ዲያቢሎስ ነው። ስለዚህ እርግማኑም ቢሆን በዋናነት በእንስሳው እባብ ላይ ያነጣጠረ አይመስለኝም፤ ነገር ግን በሰይጣን ላይ እንጂ። አዎን ልክ ነው ሰይጣን እባብን ስለተጠቀመበት እባብም ተረግሟል (ቁጥር 14)። ሆኖም ዋናው እርግማን ያለው በቁጥር 15 ይመስለኛል ማለትም በሰውና በሰይጣን መካከል ያለው የዘላለም ጠላትነትና የሰው/የመሲሁ የሰይጣንን ራስ መቀጥቀጥ።
Jun 25, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...