ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Wednesday, 23 May 2018
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ጴንጤ ለምን የይፋ ፆም የለውም?

Mar 11, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
Mar 11, 2011 iyesus ታርሟል
እኔ ጴንጤ ባልሆንም፤ ነገር ግን ለምን የይፋ ጾም የግድ ያስፈልግለዋል? ብዬ ጥያቄህን በጥያቄ ልመልስ። የቱ ጋ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ክርስቲያኖች በአመት በተወሰነ ጊዜ የሚደረግ የይፋ ጾም ያስፈልጋቸዋል የሚለው?

1 መልስ

0 ድምጾች
በመጀመሪያ ህብረት ይቀድማል ። ከአዋጅ [የይፋ] ፆም በፊት !! ለማን ነው ይፋ የሚሆነው?
Mar 11, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
ጾምን ለዩ (ቀድሱ)
ጉባኢውንም ጥሩ ስለሚል (ኢዪ ም.2)
በዚህ መሰረትም ክርስቲያኖች ከ ሃዋርያት ዘመን ጀምሮ ዓቢይ ጾምን ወስነው ሲጾሙት ኖረዋል። በካቶሊክም ቢሆን Lent ተብሎ እስካሁን ይጾሙታል።
እናንተ ይህን ጥያቒ በመጽሃፍ ቕዹስ ኣሳባችሁ የምታነሱት በዘመን መጨረሳ ሆዳም እንደሚበዛ ስለምታውቁ አጃቢ ያገናችሁ መስላችሁ ነው። ምክንያቱም ኣለም የሚወደውን ዪወዳልና።
ትላንት እንደ እንግዳ ደራሽ፡ እንደ ጎርፍ ፈሳሽ መጥታችሁ መጽሃፍ ቕዲስ ለማስተማር ሲዳዳችሁ በጣም ያስገርማል።
ኢሳያስ 58ን ምዕራፉን በሙሉ አንብበው። እውነተኛ ጾም የተቸገሩትን መርዳት፤ ከክፉ ሥራና ከክፉ ንግግር መራቅ ወዘተ ነው እንጂ ሃይማኖተኝነትና የሃይማኖት ሥርዓት መጠበቅ ብቻ ከንቱ ድካም ነው። የጾምና የሃይማኖትን ሥርዓት በመጠበቅስ ፈሪሳውያንን የሚያክል የለም። ቁም ነገሩ ግን ያ አይደለም። ጾም አላማ ያለው ነገር እንጂ እንዲያው አንድ የሆነ ወር በደረሰ ቁጥር ከማለፊያ ምግብ መቆጠብ፤ ክፉ ንግግርንና ክፉ ሥራን መቀጠል አይደለም። በመጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች የጾሙት፤ ጾምንም ያወጁት ለአንድ የተወሰነ ጉዳይ እግዚአብሔር ፊት ለመቅረብና ልመናቸውን ለማሰማት ነው እንጂ የአመቱ ወር ስለደረሰ አይደለም። አዲስ ኪዳን ልብን እንጂ ሥርዓትን አይፈልግም። የጾምና የቀኖች ቆጠራ የፈለገ ከፈሪሳውያን ጋር በብሉዩ ለመዳን መሞከር ይችላል። ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው እኛን የሃይማኖት ሥርዓት ባሪያዎችና አዲስ ፈሪሳውያን ለማድረግ አይደለም። ነገር ግን የፍቅርና ቅን ልብ ኖሮን መልካም ፍሬ እንድናፈራ እንጂ።

የማርቆስ ወንጌል 2
21 በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚጥፍ የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አዲሱ መጣፊያ አሮጌውን ይቦጭቀዋል፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል።
22 በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳል የወይኑም ጠጅ ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ያኖራሉ።

ትንቢተ ኢሳይያስ 58
3 ስለ ምን ጾምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለ ምን አዋረድን፥ አንተም አላወቅህም? ይላሉ። እነሆ፥ በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፥ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ።
4 እነሆ፥ ለጥልና ለክርክር ትጾማላችሁ በግፍ ጡጫም ትማታላችሁ ድምፃችሁንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ እንደምትጾሙት አትጾሙም።
5 እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነውን? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነውን? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ ያደርግ ዘንድ ማቅንና አመድንም በበታቹ ያነጥፍ ዘንድ ነውን? በውኑ ይህን ጾም፥ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተወደደ ቀን ትለዋለህን?
6 እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፥ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን?
7 እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፥ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፥ ከሥጋ ዘምድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2018 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...