ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Wednesday, 25 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

በፍቅር የምቀርባቸው ወንዶች ሁሉ ልቤን ክፉኛ ሰብረዉ ይለዪኛል ምን ትመክሩኛላችሁ?

በጣም ጥሩ ልብ ያለኝ ሴት ነኝ ግን ለምን እንደሆነ አላዉቅም በወንዶች ተደጋጋሚ ክህደትና በደል ይደርሥብኛል።ጥሎብኝ ደግሞ ተጠራጣሪ አይደለሁም በጣም ሰው አምናለሁ።አሁን ግን እጅግ በጣም በደል ሲደጋገምብኝ ወንድ የሚባል ላለመቅረብ እስከመወሰን ደርሻለሁ።ምን ትመክሩኛላችሁ በአሁን ሰአት በጣም ብቸኝነትና ያለመፈለግ ስሜት እያሰቃየኝ ነዉ።ከቻላችሁ ወይ ምከሩኝ ወይ ፀልዩልኝ።ተባረኩ።
Jul 7, 2012 ሌሎች ስም-አልባ የተጠየቀ

2 መልሶች

0 ድምጾች
ሰላም እታችን

በቅድሚያ አይዞሽ እግዚአብሔር የልብን ስብራትም የሚጠግንና የሚፈውስ አምላክ ነውና እርሱ ስብራትሽን ይፈውሳል።

ሌላው የምመክረሽ ነገር ቢኖር፤ ሁሉ ነገር ከልክ ካለፈ ጥሩ አይደለም። ሁሉ ነገር ሚዛን ሲኖረው ጥሩ ነው። ስለዚህ ወንዶችን እንዲያው ሳይመረምሩ ልብን ሙሉ በሙሉ መስጠት ጉዳት ያመጣልና ለወደፊቱ ተጠንቀቂ። ዓይንን ከፍቶ መመርመር እንዲሁም ሰውየውን የሚያውቁ ሰዎች የሚሉትን ለመስማት ጆሮን መክፈት ጥሩ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ሁሉን ተጠራጣሪ መሆንም ጥሩ አይደለም። ስለዚህ በተቻለሽ መጠን ሚዛንን ለመጠበቅ ሞክሪ። ከሁሉም በላይ ደግሞ በሰው ላይ ሙሉ ለሙሉ ተስፋ አታድርጊ። ብዙ ጊዜ እኛ የምንጎዳው ከሰው ብዙ ስለምጠብቅም ነው። ከእግዚአብሔር እንጂ ከሰው ብዙም አትጠብቂ፤ አይከዳኝም ይሄስ አይተወኝም ወዘተ ብለሽ ብዙም በሰው አትታመኚ፤ ሌላው ቀርቶ ካገባሽም በኋላ ሙሉ ለሙሉ በሰው ተስፋ አታድርጊ። ሰው ወጣም ወረደም ሰው ነው። ቃሉን ሁሉ ጊዜ የሚጠብቅ እግዚአብሄር ብቻ ነው። ዛሬ ቢምልና ቢገዘት ነገ ደግሞ ሁኔታዎችና ስሜቶች ሲቀየሩ የሰው ነገርም ይቀየራልና ሁልጊዜ አይንሽ ወደ ጌታ ብቻ ይሁን።
Jul 17, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
ስለተሰጠኝ ጠቃሚ ምክር እና ማፅናኛ በጣም አመሰግናለሁ ወገኔ ጌታ ይባርክልኝ.
0 ድምጾች
ልብሽን ጠብቂ። የልብ ጥበቅው ስራ የተሰጠው ለባለ ልቡ ነው ስለዚህ ልብሽን ጠብቂ።
Jul 29, 2012 zk77 (680 ነጥቦች) የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...