ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄና መልስ
Email this page to a friend Printer-friendly   Saturday, 18 May 2013
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

ይሁዳን እንደክሐዲያን ለምን ይታያል

በክርስትና ሀይማኖት እንደ ምሰማው፡ይሁዳ እየሱስ ክርስቶስን አሳልፎ እንደ ሰጠውና እንደ ከዳው ተሁኖ ይነገራል እናም በኢትዮጵያ አንድን ሰው ከሀዲያንነቱ ወይም መጥፎነቱን ለመግጽ አይሁዳ ተብሎ ይሰደባል፡ ከዚህ አልፎ በብዛት በካቶሊኮች አመለካከት ይሁዳውያኖች ነው ያሰቀሉት(የሱስን) የሁዳውያንን ወይም ይሁዳን ይጠላሉ፡እኔ የምጠይቀው እየሱስ ወደዚህ ገለም ሲመጣ ሕዝቡን በደሙ ሊያድን ከሆነ በመሰቀልም ይሁን በሌላ መንገድ፡ ይሂን ነገር ነቢያትም ተምብተውታል፡ይሄ ነገር የእግዚያብሔር ትዛዝ የነቢያት ትንቢት ከሆነ ይሁዳ ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ ግዴታ ነው፡ታድያ ይሁዳም ሆነ አይሁዳውያን ለምን እንደ መጥፎ አድራጊወች ሁነው ይጠላሉ፡በክርስቲያን መጽሓፍ ቅዱስ ላይ የእግዚያብሔርን ቃል ትንቢት የፈጸመ ጻዳቃን ተብሎ ከመጻፍ አልፎ በመጥፎ ነገሮች ነው የሚነሳው፡
9 ወራቶች በፊት መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

2 መልሶች

+1 ድምጽ
ሰላም

ይሁዳን እና አይሁዳውያንን ለያይተንም ማየት ያለብን ይመስለኛል። ይሁዳ አንድ ግለሰብ ነው፤ አይሁዳውያን ደግሞ እስራኤላውያን ናቸው። በመሰረቱ ሰው መጥፎ ሲሆን "ይሄ ይሁዳ ነው" ነው እንጂ የሚባለው "አይሁዳዊ ነው" አይባልም። ይህ ብቻ አይደለም ኢየሱስም ራሱ አይሁዳዊ ወይም እስራኤላዊ ነበረ። ከዚህም በተጨማሪ 12ቱ ሃዋርያት እንዲሁም ጳውሎስ ሁሉ አይሁዳውያን ነበሩ። ስለዚህ አይሁዳውያንን መጥላት የሚባል ነገር ፈጽሞ መጽሃፍ ቅዱሳዊ አይደለም።

በእርግጥ የአስቆሮቶ ይሁዳ ኢየሱስን ለገንዘብ ሲል አሳልፎት እንደሰጠ በአዲስ ኪዳን ተጽፎአል። የአይሁዳውያን መሪዎችም እንዲሁ ኢየሱስን በሞት እንዲቀጣ ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጥተውታል። አንደኛ የአይሁድ ህዝብ ሁሉ አይደለም ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠው፤ በተለይ ደግሞ የካህናት አለቆች ናቸው። የተወሰኑ አይሁዳውያን ደግሞ ኢየሱስን እንደ ነብይ ያዩና ይከተለቱም ነበር። ስለዚህ ሁሉንም አይሁዳውያን በአንድ ላይ መጨፍለቅ ከእውነት የራቀ ነው።

ይህ ሁሉ ደግሞ አንተ እንዳልከው አስቀድሞ እግዚአብሔር በነብያቱ የተናገረው ነገር ስለሆነ ይሁዳንም ይሁን የአይሁድ መሪዎችን ከእኛ የተለዩ ልዩ ሰይጣኖች አድርገን መመልከት የለብንም። ኢየሱስ በእኛ በሁላችን ኃጢአት ምክንያት ሞተ እንጂ በእነርሱ ኃጢአት ብቻ አልሞተምና። በኢየሱስ ሞት እኛ ሁላችን ተካፋዮች ነንና።

በተለይ ደግሞ አይሁዶችን ማለትም እስራኤላውያንን እንዳንጠላና በእነርሱ ላይ የትዕቢትን ነገር እንዳንናገርና እንዳንመጻደቅ ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ ያስጠነቅቀናል (ሮሜ ምእራፍ 9 እስከ ምእራፍ 11)። ምንም እንኳን ለጊዜው የክርስቶስ ነገር ቢሸፈንባቸውም አሁንም እግዚአብሔር አልጣላቸውም፤ የገባላቸውንም ተስፋ አልተወውም።
Quote:
ወደ ሮሜ ሰዎች 11
18 ብትመካባቸው ግን ሥሩ አንተን ይሸከምሃል እንጂ ሥሩን የምትሸከም አንተ አይደለህም።
19 እንግዲህ፦ እኔ እንድገባ ቅርንጫፎች ተሰበሩ ትል ይሆናል።
20 መልካም፤ እነርሱ ከአለማመን የተነሣ ተሰበሩ አንተም ከእምነት የተነሣ ቆመሃል። ፍራ እንጂ የትዕቢትን ነገር አታስብ
21 እግዚአብሔር እንደ ተፈጠሩት ለነበሩት ቅርንጫፎች የራራላቸው ካልሆነ ለአንተ ደግሞ አይራራልህምና
9 ወራቶች በፊት ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
ከ 25 አመት በፊት ኢትዮጵያ በኖርኩበት ጊዜ በተለይ በጎንደር ዙሪያ ቤተ እስራኤሎቺን በዘረኝነት እና በሗላ ቀር አመለካከት ብዙ መጥፎ አባባሎችን ይሉን ነበር በተለይ ጎንደር ከተማ ውስጥ በምኖሮበት ጊዜ ማንነታቺን ደብቀን ነበር የኖርነው፡እኛ ብቻ አልነበርነም የተለየ ሐይማኖት የነበረን እስላምቺም የራሳቸው ሐይማኖት አላቸው ነገር ግን እነሱ ላይ እንዲህ ያለ ጫና አልነበረም፡ለምን ከእስራኤሎች ብቻ እንዲህ አይነት ዘረኝነት የነበረ ምክኒያቱስ ምንድን ነው፡
9 ወራቶች በፊት ስም-አልባ የተመለሰ
8 ወራቶች በፊት የታረመ ስም-አልባ

የተዛመዱ ጥያቄዎች

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2013 by iyesus.com
Terms of use | Contact us