ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Monday, 23 July 2018
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ባለቢቲ ኦን ላይን ሲክስ እናድርግ ትለኛለች ችግር አለው?

የጊታ ሰላምና ጸጋ ይብዛላቹ
እነ ባለትዳሪና የ አንድ ወንድ ልጅ አባት ነኝ እኒና ባለቢቲ ከተጋባን 2 አመት 6 ወር ሆኖናል አሁን እኒ በስራ ምክንያት ከ እኢትዮ ውች ነኝ እና ከባለበቲ ጋር በየጊዘው በ ፊስ ቡክና በ ኢሚል እንዲሁም በሲልክ እንገናኛለን በ ፊስ ቡክ ቻት ስናረግ ሁሊም አንድ ትያቂ ትጠይቀኛለች ብልትሂን አቁምና ፎቶ አንሳና ላክሊኝ እነ ደሞ ዪሂ ነገር ክርስትያናዊ ባህሪ አይደለም እሱን ለማቆም የማደርገው ልምምድ ነገ ወደ ሊላ ልምምድ ይከተኛል ያለሁበት ሃገር እንካን እንደዚህ ልምምድ ውስት ለገባ አይደለም የ ዝሙት መንፈስ በደኒብ ሚሰራበት ሃገር ነው እናም ወገኖች እንቢ ስላት ቻው እንካን አትለኝም ዝም ብላ ነው ምትወጣው እኒ ደሞ በጥም ሲለ ልጂና ስለ እሳ መስማትና ማውራት አፈልጋለው እሳ ግን ሁሊም ስለ ሲክስ ብቻ ነው እንድናወራ ምትፈልገው እና አሁን ውስጢ በተለያየ ጥያቂ ተሞልታል በነገራችን ላይ ባለቢቲ ይ 2 አመት ታላቂ ናት አሁን የኒ እድሚ 30 ነው ሊላው እነና ባለቢቲ ስንጋባ እሳ ድንግል አልነበርችም ለኒ ደሞ እሳ የመጀመሪያዪ ነች አሁን ውስጢ በጣም እየተቸነቀ ነው ስራውን ጥዪ አልመጣ ለ 2 አመት ፈርሚያለው አርፊ አልሰራ ውስጢ በስጋት ተሞልታል ወደ ሊላ ወንድ ልትሂድ ትችል ይሆን ደሞ አፈቅራታለው ማጥት አልፈሊግም ቃላን ተቀብየ በስሊክ ሲክስ እናድርግ እላለው ውስጢ ደሞ ይህ ራስን በራስ ማርካት ነው ዪሂ ደሞ በ አምላክህ ፊት ሓጢያት ነው ዪለኛል ቅዱሳን ምን ትላላቹ
Sep 19, 2012 መንፈሳዊ ዘላለም ታደሰ (140 ነጥቦች) የተጠየቀ
Sep 25, 2012 ተመልካች ታርሟል
ምን በፈጠረው ያድርጉ ወይስ አያድርጉ ???

1 መልስ

–1 ድምጽ
አንተ የሰጠሃት መልስ ሁሉ ጥሩ ነው እላለሁ። ሆኖም ሁለት ነገሮችን ብቻ እንደ ሃሳብ ላነሳልህ እወዳለሁ።

አንደኛ ምናልባት እርሷ ይህንን የፍትወት ነገር የምታነሳብህ፤ አንተ ወደ ሌላ ሴት ትሄዳለህ ብላ ፈርታ ቢሆንስ? ስለዚህ እርካታን ፈልገህ ወደ ሌላ ሴት ከምትሄድባት በኦንላይን አንተን ለማርካት ፈልጋ ቢሆንስ? ምናልባት በአንተ ላይ ያላት አለመተማመን ይህንን ፈጥሮባት ቢሆንስ? ልክ አንተ እርሷ ወደ ሌላ ወንድ ትሄዳለች ብለህ እንደምትፈራው፤ እርሷም አንተ ወደ ሌላ ሴት ይሄዳል ብላ ፈርታ ቢሆንስ? ምክንያቱም ወንድ ብቻውን ያለ ሚስት ሁለት ዓመታት ሙሉ ሲኖር በሌሎች ሴቶች ሊፈትን ይችላል ብላ ልትፈራ ትችላለች። ስለዚህም የፍትወት እርካታ ፈልገህ ወደ ሌላ ሴት እንዳትሄድ ይሆናል እርሷ ይህንን የምታደገው። ይህ ከሆነ ችግሯ በተቻለ መጠን በግልጽ ብትነጋገሩበትና አንተም ታማኝነትህን በተለያየ ሁኔታ ብታሳውቃት መልካም ነው። በተለይ እርሷን ብቻ አሁንም እንደምትወዳት እርግጠኛ እንድትሆን ፍቅርህን ግለጽላት። ሌላው ደግሞ ለምሳሌ ትርፍ ጊዜህን እርሷ ከምታውቃቸው ሰዎች ጋር እንደምታሳልፍ በማሳወቅ ወዘተ።

ሁለተኛ የምመክርህ ነገር ቢኖር ለወደፊት የሚሆን ነው። በፍጹም በፍጹም ለስራና ለገንዝብ ብለህ ወደፊት በፍጹም ትዳርህንና ቤተሰብህን ጥለህ ለዓመታት አትለይ። ይህ መጽሃፍ ቅዱስ በግልጽ የሚያስጠነቅቀን ጉዳይ ነው። ብዙዎች ገንዘብንና የሥራ እድገትን ወይም ትምህርትን ከትዳርና ከቤተሰብ በላይ እያደረጉ ለሰይጣን በር ይከፍታሉና ትዳርህንና ቤተሰብህን እንደ ቀላል ነገር አትቁጠር። እንደው እንደፈለጉ ጥለውት ሄደው ተመለስው ሲመጡ ቁጭ ብሎ የሚያገኙት ነገር አድርገህ ትዳርህን አቅልለህ አትይ። አንዳንዶች በዚህ ምክንያት ትዳራቸው ፈርሶ፤ ቤተሰባቸውም ተበትኗልና። ስለዚህ ወደፊት በዚህ ጉዳይ መጽሃፍ ቅዱስ የሚመክረውን ምክር በልብህ አኑር።
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
7፥5 ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ ደግሞ አብራችሁ ሁኑ
Sep 25, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2018 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...