ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Thursday, 3 December 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

2ኛ የዮሐንስ መልእክት ላይ የተመረጠች እመቤት የሚለው ማንን ነው ?

Mar 14, 2011 መንፈሳዊ ቤኪ (230 ነጥቦች) የተጠየቀ
Mar 14, 2011 ቤኪ ታርሟል
2ኛ የዮሐንስ መልእክት ላይ የተመረጠች እመቤት የሚለው ማንን ነው ?
ከዚህ በላይ ምን ማረጋገጫ አለውና ነው የተመረጠች ያለው እመቤታችንን ነው ላለማለት ዙሪያውን መዞር ያስፈልጋል እንዴ ? ከቤተሰቦቻችን አንድ ሰው እህት ወይም እናት አይደለም ከእመቤታችን ሌላ ማን ነች የተመረች ሴት ? ቅናት ያደረበት ሰው ካልሆነ በስተቀር ይህንን መመለስ የሚያቅተው ማን ነው? አዎን የተመረጠእ ያለው የየሱስ እናት ማርያምን ነውወይም እመቤት የሚለው ቃል በዚያን ዘመን ለሮማውያን የገዥ መደቦች ወይም ልዕልቶችና የመኳንንት ወገኖች የሚሰጥ የማዕረግ ስም ነው። ካልን ከእመቤታቸችን ሌላ ማን ነች በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህንን ክብር ልታገኝ የምትችለው?
ቱቱዬ እባክሽ መጸሃፉን አንቢቢ መጀመሪያ ተብረኪ

2 መልሶች

+1 ድምጽ
2ኛው የዮሐንስ መልእክት የተጻፈው "ለተመረጠች እመቤትና ለልጆችዋ" ነው። በዚህ ክፍል የተመረጠች እመቤት ተብላ የተጠራችው ማን ናት በሚለው ላይ የተለያዩ ሃሳቦችና ግምቶች አሉ። አንዳንዶች ቤተክርስቲያን ናት፣ አንዳንዶች የኢየሱስ እናት ማርያም ናት ወዘተ ይላሉ። ከጽሑፉ መቶ በመቶ ይህች የተመረጠች እመቤት ማን እንደሆነች ማወቅ ቢከብድም፤ የሚሰጡትን ግምቶች ግን ትክክል ሊሆኑ የሚችሉ ወይም ሊሆኑ የማይችሉ ግምቶች እንደሆኑ ግን መገምገም ይቻላል።

በግሪኩ Εklektē የሚለው ማለትም "የተመረጠች" የሚለው ቃል የሚያሳየው ይህች እመቤት በጌታ የዳነችና የክርስቶስ መሆኗን ነው። በአዲስ ኪዳን በክርስቶስ የሆኑ ሁሉ የተመረጡ ናቸውና። በዚሁ በ2ኛ ዮሐንስ የመጨረሻው ቁጥር 13 ላይም እንዲሁ "የተመረጠች እህትሽ" የሚል ቃል አለ። ስለዚህ "የተመረጠች" የሚለው ቃል በክርስቶስ ስለ ዳነች እመቤት እንደሚናገር የበለጠ ግልጽ ያደርገዋል።

ይሄ በአማርኛው "እመቤት" የሚለው ቃል በግሪኩ Kuria የሚለው ሲሆን፤ ትርጓሜውም የሴት ጌታ ወይም የሴት መኳንንት ወዘተ ማለት ነው። ስለዚህም ነው "እመቤት" ተብሎ በትክክል የተተረጎመው። ይህ Kuria ወይም እመቤት የሚለው ቃል በዚያን ዘመን ለሮማውያን የገዥ መደቦች ወይም ልዕልቶችና የመኳንንት ወገኖች የሚሰጥ የማዕረግ ስም ነው።

ሆኖም አንዳንዶች ይህ Kuria ወይም Kyria የሚለውና በአማርኛ እመቤት ተብሎ የተተረጎመው ቃል የሴትዮዋ ስም ነው ብለውም ያምናሉ። የታሪክ አዋቂዎች ደግሞ ምንም እንኳን የግሪኩ ሰዋሰው (grammar) Kyria የሚለው ቃል ስም ሊሆን እንደሚችል ቢፈቅድም፤ መልእክቱ በተጻፈበት ዘመን ግን በዚህ ስም መጠራት የተለመደ እንዳይደለ ይናገራሉ። አልፎ አልፎ ይህንን እመቤት የሚለውን የመኳንንት ቤተሰብ የሚጠሩበትን ቃል፤ እንደ ስም ሲያገለግል ቢታይም፤ ያ ግን መሆን የጀመረው 2ኛ ዮሐንስ ከተጻፈበት ዘመን በኋላ ነው ይላሉ።

ስለዚህ ይህ Kuria ወይም እመቤት የሚለው ቃል የሚያመለክተው የተጻፈላት ሴትዮ የመኳንንት ቤተሰብ ሳትሆን አትቀርም የሚለው ግምት ከሁሉም የተሻለ ግምት ነው።

የኢየሱስ እናት ማርያም ናት?

አንዳንዶች በዚህ ክፍል "የተመረጠች እመቤት" ተብላ የተጠቀሰችው የኢየሱስ እናት ማርያም ናት ብለው የሚያምኑ አሉ። ሆኖም ይህ ሊሆን የማይችልበት አንዳንድ ተጨባጭ ማስረጃዎች አሉ።

አንደኛ መልእክቱ የተጻፈው እ.ኤ.አ ከ90 እስከ 100 ዓ/ም ውስጥ ነው። በሌላ አነጋገር፤ ኢየሱስ በሕይወት ቢኖር በዚያን ዘመን ከ90 እስከ 100 ዓመቱ ይሆን ነበር ማለት ነው። በዚያን ዘመን እንግዲህ ማርያም እድሜዋ ስንት ሊሆን እንደሚችል መገመት አይከብድም። ይህ መልእክት በተጻፈበት ዘመን ማርያም በሕይወት መኖርዋ እጅግ ያጠራጥራል፤ በሕይወትም ኖራ ቢሆን እድሜዋ ከ100 ዓመት በላይ ሆኖዋት እጅግ እጅግ አርጅታ ነው ሊሆን የሚችለው። ታዲያ ዮሐንስ ይህንን ከሃሰተኛ አስተማሪዎች የሚያስጠነቅቅ መልእክት ለዚህች እጅግ ላረጀችና ከ100 ዓመት በላይ ለሆናት ሴት ነው የጻፈው ብሎ ለማመን ይከብዳል።

በሁለተኛ ደረጃ መልእክቱ የሚያስጠነቅቀው በቁጥር 7 እንደተጻፈው "ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ" ከማያምኑ አሳቾች የተጻፈላት እመቤትና ልጆችዋ እንዲጠነቀቁ ነው። መቼም ለማርያም ኢየሱስ በሥጋ እንደመጣ ምንም ሊነግራት የሚያስፈልግ አይመስለኝም። ይሄ "ልጅ ለእናቷ ምጥ አስተማረች" እንደሚባለው ነው የሚሆነው። ኢየሱስ በሥጋ ነው የመጣው እንጂ፤ ያለ ሥጋ በመንፈስ አይደለም ብሎ ለማርያም ማስጠንቀቂያ መጻፍ ምንም ትርጉም አይሰጥም። እርሷ ከማንም ይልቅ ልጇ በሥጋ እንደመጣ ታውቃለችና።

ሶስተኛ በዮሐንስ ወንጌል 19፡26-27 ላይ ኢየሱስ በተሰቀለ ጊዜ፤ ጌታ እናቱን ማሪያምን ዮሐንስ ራሱ እንዲንከባከባት አደራ እንደሰጠው ተጽፎአል። ዮሐንስም "...ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።" ዮሐ 19፡27 ነው የሚለው። ማለትም ኢየሱስ ከተሰቀለ በኋላ ማርያም ትኖር የነበረው በዮሐንስ ቤት ነበር ወይም ከዮሐንስ ጋር ነበር። እንዲህ ከሆነ ደግሞ ዮሐንስ አብሮአት ለሚኖር ሴት ይህንን የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መጻፍ ባላስፈለገው።

እንግዲህ ከላይ የተጠቀሱት ተጨባጭ ማስረጃዎች የሚያመለክቱት፤ ይህ መልእክት የተጻፈው ለኢየሱስ እናት ለማርያም ሊሆን እንደማይችል ነው።

ቤተክርስቲያን ናት?

በዚህ በ2ኛ ዮሐንስ ላይ የተጠቀሰችው የተመረጠች እመቤትና ልጆችዋ ማን እንደሆኑ ከሚሰጡት ግምቶች አንዱ ደግሞ ቤተክርስቲያን ናት የሚል ነው። ይህንን አመለካከት የሚደግፉ ሰዎች መልእክቱ ስለ ሴትዮዋ ልጆች ሲናገር የሚያወራው ስለ መንፈሳዊ ልጆቿ እንጂ፤ ሴትዮዋ በሥጋ ስለወለደቻቸው ልጆች እንዳልሆነ ይናገራሉ።

በእርግጥ እነዚህ የሴትዮዋ ልጆች መንፈሳዊ እንጂ በሥጋ የወለደቻቸው የሴትዮዋ ልጆች እንዳልሆኑ ይህንን መልእክት ከራሱ ከዮሐንስ 3ኛ መልእክት ጋር አነጻጽሮ ማየትም ይቻላል።
Quote:
2ኛ የዮሐንስ መልእክት
4 ትእዛዝን ከአብ እንደ ተቀበልን ከልጆችሽ በእውነት የሚሄዱ አንዳንዶችን ስለ አገኘኋቸው እጅግ ደስ ብሎኛል።

3ኛ የዮሐንስ መልእክት 1
4 ልጆቼ በእውነት እንዲሄዱ ከመስማት ይልቅ የሚበልጥ ደስታ የለኝም።

ከላይ እንደምንመለከተው በ3ኛው የዮሐንስ መልእክት ላይ ልጆቼ ብሎ የሚጠራቸው መንፈሳዊ ልጆችን እንጂ የራሱን የሥጋ ልጆች እንዳልሆነ ሁሉ፤ እንዲሁም በዚህ በ2ኛው የዮሐንስ መልእክት ላይም የሚያወራው ስለ መንፈሳዊ ልጆች ነው። ይህ ብቻ አይደለም ይሄን ልጆች የሚለውን ቃል ዮሐንስ በ1ኛ ዮሐንስ ላይም ብዙ ጊዜ ለመንፈሳዊ ልጆች ሲጠቀምበት እናያለን (1ኛ ዮሐንስ 2:1, 28; 3:1-2, 7, 10, 18; 4:4; 5:2, 21)

ሆኖም ጥያቄው ግን ያለው የሴትዮዋ ልጆች መንፈሳዊ ልጆች መሆናቸው ማለትም በክርስቶስ የዳኑ አማኞች መሆናቸው ሴትዮዋን ቤተክርስቲያን ያደርጋታል ወይ? የሚለው ላይ ነው። ቤተክርስቲያን ናት የሚለው አስተሳሰብ ምንም እንኳን ከተለመደው የፕሮቴስታንት እመለካከት ጋር የሚሄድ ቢሆንም፤ በዚህ ክፍል ግን ስለ ቤተክርስቲያን እንደማያወራ የሚያሳዩ አንዳንድ ምልክቶች አሉ።

አንደኛ ይሄ ከላይ ባየነውና "እመቤት" በሚባለው፤ በተለምዶ የሮማውያን የመኳንንት ሴቶች በሚጠሩበት ቃል ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ይጠራታል ብሎ ለመገመት እጅግ ይከብዳል። በመጽሐፍ ቅዱስም የትም ቦታ ቤተክርስቲያን በዚህ Kuria ወይም እመቤት በተባለው ቃል ተጠርታ አታውቅም። በተጨማሪም በዚህ በ2ኛ ዮሐንስ የመጨረሻ ቁጥር 13 ላይ "የተመረጠች እህትሽ" የሚል ቃልም አለ። እንደዚሁ ቤተክርስቲያን በመጽሐፍ ቅዱስ የትም ቦታ "እህት" ተብላ ተጠርታም አታውቅም። የአጥቢያ ቤተክርስቲያንም ብትሆን ማለት ነው። ከዚህም በላይ ዮሐንስ በ3ኛው መልእክቱ ላይ ከአንዴም ሁለቴ ቤተክርስቲያንን "ቤተክርስቲያን" ወይም በግሪኩ ekklesia እያለ ነው የጠራት። (3ኛ ዮሐንስ 9 እና 10)። ስለዚህ በ3ኛ ዮሐንስ እንደታየው ዮሐንስ ወደ ቤተክርስቲያን ሲጽፍ "ወደ ቤተ ክርስቲያን ጻፍሁ" እያለ ነው እንጂ አጥቢያ ቤተክርስቲያንን የሚጠራት፤ "እመቤት" እያለ አይደለም።

በመጨረሻም፤ በአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ሲል አማኞቹን እንጂ ሌላ ነገር አይደለም። ታዲያ የሴትዮዋ ልጆች አማኞቹ ራሳቸው ቤተክርስቲያን ከሆኑ፤ እርሷ ደግሞ ራሷም ቤተክርስቲያን ከሆነች እንዴት ብሎ ነው ዮሐንስ ለሴትዮና ለልጆችዋ የሚጽፈው? ዮሐንስ አንዳንዴ ለእርሷ ብቻ "አሁንም፥ እመቤት ሆይ" ቁ. 5 እያለ ሲጽፍ አንዳንዴ ደግሞ ለእርሷንና ለልጆቿ ነው የሚጽፈው። ሁለቱም ቤተክርስቲያን መሆናቸው፤ ምንም ትርጉም አይሰጥም። የትም ቦታ ደግሞ በአዲስ ኪዳን መሪዎች ብቻቸውን ቤተክርስቲያን ተብለው ሲጠሩ አናይም።

ከላይ የተዘረዘሩት ተጨባጭ መረጃዎች የሚያመለክቱት፤ ይህች ሴት ቤተክርስቲያን ወይም አጥቢያ ቤተክርስቲያን ልትሆን እንደማትችል ነው።

የቤተክርስቲያ አገልጋይ?

ከሁሉም ግምቶች ሊሆን የሚችለው የተጠቀሰችው ሴት በእርግጥም ይህ እመቤት የሚለው የመኳንንት ማዕረግ የነበራትና ምናልባትም በቤቷ የክርስቲያኖች ህብረት ታስተናግድ የነበረች ሴት ናት። ልጆችዋ የሚለውም በዚህ ህብረት የሚገለገሉትንና በአገልግሎቷም ወደ ጌታ የመጡትን አማኞች ነው። በአዲስ ኪዳን የተለያዩ የሴት አገልጋዮች ተጠቅሰዋል። ቤተክርስቲያን ከተጀመረች እስከ 100ና 200 ዓመታት ድረስ የቤተክርስቲያን ሕብረቶች የሚካሄዱት በቤት ውስጥ ነበር። ታዲያ የተለያዩ ሰዎች ለዚያ ቤታቸውን ከፈተው ያገለግሉ እንደነበር በአዲስ ኪዳን ተጠቅሷል። የሴቶችም አገልጋዮች እንዲሁ በአዲስ ኪዳን በተለያየ ሥፍራ ተጠቅሰዋል።
Quote:
ወደ ሮሜ ሰዎች 16
1 በክንክራኦስ ባለች ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የምትሆን እኅታችንን ፌቤንን አደራ ብያችኋለሁ፤
2 ለቅዱሳን እንደሚገባ በጌታ ተቀበሉአት፥ እርስዋ ለብዙዎች ለእኔም ለራሴ ደጋፊ ነበረችና፥ ከእናንተም በምትፈልገው በማናቸውም ነገር እርዱአት።
Quote:
ወደ ሮሜ ሰዎች 16
3 በክርስቶስ ኢየሱስ አብረውኝ ለሚሠሩ ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤
4 እነርሱም ስለ ነፍሴ ነፍሳቸውን ለሞት አቀረቡ፥ የአሕዛብም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የሚያመሰግኑአቸው ናቸው እንጂ እኔ ብቻ አይደለሁም፤
5 በቤታቸውም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከእስያ ለክርስቶስ በኵራት ለሆነው ለምወደው ለአጤኔጦን ሰላምታ አቅርቡልኝ።
Quote:
ወደ ሮሜ ሰዎች 16
7 በሐዋርያት መካከል ስመ ጥሩዎች ለሆኑ፥ ደግሞም ክርስቶስን በማመን ለቀደሙኝ፥ አብረውኝም ለታሰሩ ለዘመዶቼ ለአንዲራኒቆንና ለዩልያን ሰላምታ አቅርቡልኝ።

ስለዚህ በ2ኛ ዮሐንስ ቁጥር 1 ላይና በቁጥር 13 ላይ የተጠቀሱት ሴቶች፤ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ናቸው የሚለው ግምት ከሁሉም ግምቶች የተሻለና ሊሆን የሚችል ግምት ነው።
Mar 18, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
0 ድምጾች
የተመረጠች እመቤት ሲል ብዙ የተመረጡ እመቤቶች ወደ ልባችን ይመጣሉ እናም የተመረጠችው
እመቤት ማን እንደ ሆነች ለመለየት ግራ ያጋባናል፣ ምክንያቱ ማርያም እመቤታችን በመባል ስትጠራ
ከልጅነታችን ጀምረን አድገናል፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል “የተመረጠችው የእኅትሽ ልጆች
ሰላምታ ያቀርቡልሻል” ብሎ በምጨረሻው ቁጥር ላይ ያስቀምጣል፣ ይህ ቃል ደግሞ የተመረጠችው
እሷ ብቻ ሳትሆን እንደ እሷ ከአንድ አባትና እናት የተወለደችው እህቷም ጭምር ናት፣ ነገር ግን
መፅሐፍ ቅዱስ የተመረጠች እመቤትና ልጆችዋ ማን እንደሆኑ በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን በግልጽ
አስቀምጧል፣
ለምሳሌ በሉይ ኪዳን ያሉ የተመረጡ እመቤቶችን እንመልከት ሄዋን ከብዙ አጥንቶች መካከል
የተመረጠች አጥንት ነች፣ ሳራ ከሌሎቹ ሚስቶቹ ሁሉ የተመረጠች እመቤት ነች፣ ርብቃ በታዛዥነቷ
የተመረጠች እመቤት ነች፣ ራሄል ከልያና ከባሪያዎቹ ሁሉ የተመረጠች እመቤት ነች፣ ትዕማር
በጥበብዋና አስተውላ በማድረጓ የተመረጠች እመቤት ነች፣ ሩት፤ ሃና…ወዘት፣ ሁሉ ልዘረዝር
አልችልም፣ ነገር ግን ወደ አዲስ ኪዳን የተመረጡ እመቤቶች ስንመጣ በአንደኛ ደረጃ የምናገኛት
ማርያም የኢየሱስ እናት ከሴቶች ሁሉ የተመረች እመቤት ናት ፤ ከአስሩ ቆነጃጅት ጋር የሌለች
ከሙሽራው ጋር አብራ የመጣችዋ ሙሽሪት የተመረጠች እመቤት ናት፤ የበጉ ሚስት ከሰባቱ ቤተ
ክርስቲያን ድል የነሳች የተመረጠች እመቤት ናት፣ እርሷ አብራው መጣች አስሩ ግን ርቀው ጠበቁ
ስለዚህም ከአስሩ ይልቅ ኣርሷ ለእርሱ ተሻላለች የተመረጠች ነች፣
ብዙ ልንል እንችላለን ሁሉን ግን ተመራጭ ያደረጋቸው የየራሳቸው የሆነ ባሕሪ አላቸው፣ ጌታ
የመረጣት እመቤት ግን አንድ ናት፣ እርሷም ራሰዋን ያዘጋጀችው እመቤት ነች፣
ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት
14
“7 የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን ሐሤትም እናድርግ
ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ። 8 ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ
እንድትጐናጸፍ ተሰጥቶአታል። ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ጽድቅ ሥራ ነውና።፣”
ራዕይ.19፦7-8
ሁሉ እመቤቶች በዚህች እመቤት ይዋጣሉ፣ ማለት ሁሉ እመቤቶች ላይ የተገለጠው የተለያየ ባሕሪ
በዚች እመቤት ላይ በሙላት ተንጸባርቆ ይታያል፣ አንተ ወይም አንቺ የተመረጥሽ እመቤት ልትሆኑ
ትችላላችሁ፣ ነገር ግን ራስዋን ያዘጋጀችው እመቤት ላይ የተገለጠው ማንነት ሊገለጥብን ይገባል፣ ይች
የተመረጠች እመቤት ልጅ ብቻ ሳይሆን ልጆች አሏት ይህ ደግሞ የሚያሳየው በአምሳልዋ የመውለድ
የማፍራት ብቃትዋን ነው፣ ደግሞም ማርያም ብቻ እንዳልሆነች ነው፣ ትልቁ የማፍራትዋ ቁልፍ ግን
ይች የተመረጠች እመቤት ባል ያላት መሆንዋ ነው፣ ባልዋ በጉ የናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፣ ባልዋ
በእርሱዋ እርሱዋም በባልዋ የምትኖር ነች፣ ይህ ትዳር ከሰጋዊ ትዳር ጋር ምንም መገናኘት የለውም፣
ይህ አይነቱ ማፍራትና መብዛት ነው፣ በዘፍጥረት. 1፦27-28 የምናገኘው፣
“26፤ እግዚአብሔርም አለ። ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር
ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ
ይግዙ።27፤ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤
ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።28፤ እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው። ብዙ፥
ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች
በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው፣”
ዘፍ.1፦26-28
ይህ መብዛትና ማፍራት በስጋ አልነበረም ምክንያቱም አዳም ሚስቱ ገና ከእርሱ አልወጣችም ነበርና
ነው፣ ይህን ሚስጥር በዚህ መጽሐፍ ባለስቀምጠውም ይህ ማፍራት ግን በውስጣችን ካለው እውነት
ጋር በመጋባት የሚወለድ ዘር የሚበዛ ፍሬ ነው፣ ዘፍጥረት 1፦27 ላይ ያለው ሰው ወንድም ሴትም
ነበር፣ አሁንም አንቺም ሆንክ አንተ ወንድም ሴትም ናችሁ፣ የበለጠ ሰለዚህ ሚስጥር ለመረዳት
(ዘፍጥረት በሸመገለው አይን) የሚለውን ቁጥር አንድ መፅሐፌን ያንብቡ፣
ይህች እመቤት በጌታ የተመረጠች ነች፣ ለምን እንደ መረጣት ለዋወቅ ከፈለግን ከላይ የዘረዘርኳቸውን
እመቤቶች አመራረጥ በመመልከት መገንዘብ እንዝላለን፣ ልጆችዋንም ለማወቅ እመቤቶቹን መመልከት
ብቻ በቂ ነው፣ ማርያም ጸጋን ስላገኘት በዘመንዋ የተመረጠች እመቤት ነች፣
ሁሉ ተጠርቷል ሁሉ ግን አልተመረጠም፣ ይህ ማለት ያልተመረጡት ሕይወትን ያጣሉ ማለት
አይደለም፣ ነገር ግን በመንፈሳዊ ትዳር ውስጥ የሚገኘው በረከት ይጎድላሉ፣ የመጀመሪያውን ትንሳኤ
ርስታችውን ያጣሉ፣ እንደ አስቴር የንጉሱ አልክሊል አይደረግላቸውም ነገር ግብ በንጉሱ ቤት ለዘላለም
ይኖራሉ፣
እነዚህ ያልተመረጡት በምደረ በዳ እንደ ቀሩት እንደ ሙሴና የእስራኤል ሕዝብ ናቸው፣ በእረፍት ወደ
ሚገኘው ደስታ በረከት አልገቡም፣ ነገር ግን በፋሲካው በግ በጌታ ኢየሱስ ግን ሁሉ እስራኤል የገባውም
ሆነ ያልገባው መላካሙም ሆነ ክፉው ሳያደርግ በደሙ ድኗል፣ ደሕንነትን ባለመመረጥ ምክንያት
አይጠፋም፣ አለመመረጥ ግን ብዙ በረከትንና ክብርን ያጎድላል፣
ከላይ ከተዘረዘሩት እመቤቶች ጋር የነበሩ ያልተመረጡ እመቤቶችን ያለተመረጡበትን ምክንያት
እናግኝ፣ ይህ በማድረግ የእኛም መመረጥ እንዲፀና መልካም ትምህርትንና ምክርን እንቀበል፣
ከሊዮን ኢማኒኤል(የተመረጠች እመቤት )ከሚለው የተወሰደ
Feb 3, 2012 ናኒ (460 ነጥቦች) የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...