ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Wednesday, 23 May 2018
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

እየሱስ አምላክ ነው ወይ ? ከአብ ያንሳል ወይ

Nov 6, 2012 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

2 መልሶች

+1 ድምጽ
ጌታ እየሱስ 100% ሰው 100% አምላክ ነው። የህ ማለት ገማሽ ሰው ግማሽ አምልክ ማለት አይደላም የህ ማለት ሁለቱንም ሙሉ አደርግ የያዘ ማለት ነው።
አምላክ መሆኑን እርሱ ሲገልጽ

"ኢየሱስም አለው፦ አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ። አብን አሳየን ትላለህ?" ዮሃንስ 14፡9

አብ ደግሞ ከርሱ እደሚበልጥ እንዲህ ሲል የነግረናል

"እኔ እሄዳለሁ ወደ እናንተም እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ። የምትወዱኝስ ብትሆኑ ከእኔ አብ ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር።" ዮሃንስ 14፡28
ተባረኩ።
Nov 6, 2012 YaelD (8,180 ነጥቦች) የተመለሰ
አሞሃል?? ወይስ ሒሳብ አትችልም??
አምላክ ይርዳህ!!!!
ወገንተኛነት ይታይብሃል።
ኢየሱስ ራሱ አምላክ/እግዚአብሔር/ጌታ/ፈጣሪ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ (39ኙ ብሉይ ኪዳን እና 27ቱ አዲስ ኪዳን) ያስረዳል።

ኢየሱስ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው

የዮሐንስ ወንጌል 1
1 በመጀመሪያው ቃል (ኢየሱስ) ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር (አብ) ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር(ወልድ) ነበረ።
2 ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር(መንፈስ ቅዱስ) ዘንድ ነበረ።
3 ሁሉ በእርሱ ሆነ (ሁሉ በኢየሱስ ተፈጠረ)፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2
10 እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።

ከእግዚአብሔር አብ ክብርን እና ምስጋናን የተቀበለ ብቸኛ አምላክ።

ወደ ዕብራውያን 1፡
8 (እግዚአብሔር አብ ሲናገር) ስለ ልጁ ግን፦ አምላክ ሆይ (O GOD,)፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል (ዘላለማዊ ነህ) ፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው።
9 ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ (መንፈስ ቅዱስ፣ ኢሳይያስ 61፡1 ሉቃስ 4፡17-19) ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ (ማቴዎስ 17፡5)
10 ይላል። ደግሞ:- ጌታ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው፤ (አንተ ፈጣሪ አምላክ ነህ፤ አንተ ፈጠርካቸው)
11 እነርሱም ይጠፋሉ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፥
12 እንደ መጎናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ ይለወጡማል፤ አንተ ግን አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም ይላል።
2ኛ የጴጥሮስ መልእክት
1፥17 ከገናናው ክብር፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው የሚል ያ ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ምስጋናን ተቀብሎአልና።


ከኢየሱስ በቀር ሌላ የሚያድን የለም፤ አምላክም የለም

የሐዋርያት ሥራ 4
11 እናንተ ግንበኞች የናቃችሁት፥ የማዕዘን ራስ የሆነው ይህ ድንጋይ ነው።
12 መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።
ትንቢተ ኢሳይያስ 43:11-12
እኔ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም። ተናግሬአለሁ አድኜማለሁ አሳይቼማለሁ፥ በእናንተም ዘንድ ባዕድ አምላክ አልነበረም፤ ስለዚህ እናንተ <<ምስክሮቼ ናችሁ>>፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እኔም አምላክ ነኝ።
ትንቢተ ኢሳይያስ
43፥10 ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ፥ እናንተ፣ የመረጥሁትም ባሪያዬ <<ምስክሮቼ ናችሁ>> ይላል እግዚአብሔር ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም፤ ከእኔም በኋላ አይሆንም።
44፥8 አትፍሩ አትደንግጡም ከጥንቱ ጀምሬ አልነገርኋችሁምን? ወይስ አላሳየኋችሁምን? <<እናንተ ምስክሮቼ>> ናችሁ። ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? አምባ የለም ማንንም አላውቅም።
የዮሐንስ ራእይ 22፡
12 እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።
13 አልፋ እና ዖሜጋ፥ ፊተኛው እና ኋለኛው፥ መጀመሪያው እና መጨረሻው እኔ ነኝ።
14 ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው፣ በደጆችዋም ወደ ከተማይቱ እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው።
15 ... ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።
16 እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ።
የሐዋርያት ሥራ
1፥8 ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም፣ በይሁዳም ሁሉ፣ በሰማርያም፣ እስከ ምድር ዳርም ድረስ <<ምስክሮቼ ትሆናላችሁ>> አለ።

ኢየሱስ/እግዚአብሔር/ መልካም እረኛችን ነው

መዝሙረ ዳዊት 23 የዳዊት መዝሙር
1 እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።
2 በለመለመ መስክ ያሳድረኛል በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።
የዮሐንስ ወንጌል 10(ኢየሱስ ሲናገር)
11 መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል...
14-15 መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ፣ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ፤ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።

የኢየሱስ ቃል አያልፍም

ትንቢተ ኢሳይያስ 40 (ነቢዩ ኢሳይያስ ሲናገር)
8 ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፥ የአምላካችን (የእግዚአብሔር) ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።
የማቴዎስ ወንጌል (ኢየሱስ ሲናገር)
24፥35 ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም።
የማርቆስ ወንጌል 13፥31 ሰማይ እና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።
የሉቃስ ወንጌል 21፥33 ሰማይ እና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።

ኢየሱስ ብቻ እውነተኛ አምላክ / the true God/ ሲሆን ከሌሎቹ ሐሰተኛ አማልክት (ከጣዖታት) ልንጠበቅ ይገባል።

የይሁዳ መልእክት 1፡
4 ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ /Our God,ራእይ 22፡21/ በሴሰኝነት ይለውጣሉ ንጉሣችንን እና ጌታችንንም ብቻውን ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።
5 ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ፣ ጌታ (ኢየሱስ ክርስቶስ) ከግብፅ አገር ሕዝቡን አድኖ <<የማያምኑትን>> በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።
6 መኖሪያቸውንም የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት (ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ) በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቆአቸዋል።
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5 (ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስ ሲመክረን)
20 የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን። እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክ እና የዘላለም ሕይወት ነው።
21 ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠብቁ። /He is the true God and the eternal Life/

ኢየሱስ ኃያሉ/ኃይለኛው እግዚአብሔር ነው የዘላለም አባታችን ነው

ኃያል አምላክ

ትንቢተ ኢሳይያስ
9፥6 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት /mighty Godeternal Father/፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።
መጽሐፈ ነህምያ
9፥32 አሁንም አምላካችን ሆይ፥ ቃል ኪዳንን እና ምሕረትን የምትጠብቅ ታላቅ እና <<ኃያል የተፈራኸውም አምላክ>> ሆይ፥ ...
ትንቢተ ኢሳይያስ 10፥21 የያዕቆብም ቅሬታ ወደ ኃያል አምላክ ይመለሳሉ።
ትንቢተ ኤርምያስ
32፥18 ለብዙ ሺህ ምሕረት ታደርጋለህ፥ የአባቶችንም በደል ከእነርሱ በኋላ በልጆቻቸው ብብት ትመልሳለህ፤ ስምህ ታላቅ እና ኃያል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5
6 እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው/ከኃያሉ/ ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤
7 እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።

የዘላለም አባት

ወደ ዕብራውያን 2
14-15 እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ (አባት) ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።

በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ ኪዳን አንድ እውነት ያስተምረናል። ይኸውም እግዚአብሔር አብ ወይም እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እንደ ብሉይ ኪዳኑ ዘመን የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ... የያዕቆብ... የኤልያስ... አምላክ፣ የእስራኤል አምላክ... የሠራዊት አምላክ... ወዘተ እየተባለ በብዙዎች ስም (ፍጹማን ባልሆኑ ሰዎች ስም) መጠራቱ አሁን በአዲስ ኪዳን እንደ ቀረ ነው። በአዲስ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር አምላክ የማንም ሳይሆን የኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። በአዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉ አማኞችም በኪዳናቸው መሰረት መናገር እና መጸለይ ይገባቸዋል፤ እንጂ የአሮጌውን ኪዳን ስርዓት የሙጥኝ ማለት አይገባቸውም።
ማንም አምላክን ማስደሰት የቻለ የለም፤ ኢየሱስ ብቻ ግን አባቱን ፍጹም አስደሰተ። ማንም አምላክን ታዝዞ በመታዘዝ የፈጸመ አልተገኘም፤ የናዝሬቱ ኢየሱስ ግን ብቻውን አምላክን ፈጽሞ ታዘዘ። መታዘዝ የሚያስከፍለውን ዋጋ፣ ውርደት እና መከራ ሁሉ በትጋት እና በፈቃደኝነት ከፈለ። ኢየሱስ በእግዚአብሔርነቱ ክብር ከሚኖርበት ዝቅ ብሎ ሊመጣ ታዘዘ። እንደ ሰው፣ እንዲያውም ከሰውም ዝቅ ብሎ እንደ ባርያ ታዘዘ። (ፊልጵስዩስ 2፡9-11። መዝሙረ ዳዊት 22፡1-8።)
ኢየሱስ እግዚአብሔር አብን እና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን "አምላኬ አምላኬ" እስከሚል ድረስ ራሱን ባዶ አደረገ፤ ፈጽሞ ራሱን አሳልፎ ሰጠ። ከዚያም በኋላ አባቱ ኢየሱስን ሲያሞግሰው "አምላክ ሆይ፣ ዙፋንህ እኮ እስከ ዘላላም ድረስ ነው፤ አንተ በጣቶችህ ሰማይን ፈጥረሃል፤ ምድርንም መስርተሃል" ይለዋል። (ዕብራውያን 1፡8-12።)

ለምንድር ነው ሰው የራሱን ሃይማኖት ከመቀየር ይልቅ መጽሃፍ ቅዱሱ ቢቀየር የሚመኘው? መጽሓፉ ኢየሱስ ፈጣሪ አምላክ ነው ይላል። ደግሞም ኢየሱስ በኋለኛው ዘመን እኛን ለማዳን ሰው ሆነ ይለናል። ሰው በሆነ ጊዜም ጋጠ ወጥ እና አምላክ የለሽ /atheist/ አመጸኛ ወይም ከሃዲ አልነበረም። ይልቁንም አምላክ ያለው እና አምላክ ሁልጊዜም የተደሰተበት፣ አምላክ ያላዘነበት እንዲሁም አንዳች ነቀፋ ያላገኘበት ንጹሁ ሰው፣ በታሪክ ብቸኛው ሰው ኢየሱስ መሆኑን መጽሐፉ ይገልጣል። ያ ብቻም አይደለም ሰዎችም (ከሳሾቹም ሳይቀር)፣ ሰይጣን እና አጋንንቱም አንዳች ነቀፋ ሊያገኙበት አልቻሉም።

አምላክ

የማርቆስ ወንጌል 9፡
7 ደመናም መጥቶ ጋረዳቸው። ከደመናውም፦ የምወደው ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።

የሉቃስ ወንጌል 9፥
34 ይህንም ሲናገር ደመና መጣና ጋረዳቸው፤ ወደ ደመናውም ሲገቡ ሳሉ ፈሩ።
35 ከደመናውም፦ የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።
36 ድምፁም ከመጣ በኋላ ኢየሱስ ብቻውን ሆኖ ተገኘ። እነርሱም ዝም አሉ ካዩትም ነገር በዚያ ወራት ምንም ለማንም አላወሩም።

የማቴዎስ ወንጌል
3፥17 እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።
17፥5 እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው። እነሆም፥ ከደመናው፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።

2ኛ የጴጥሮስ መልእክት
1፥17 ከገናናው ክብር፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው የሚል ያ ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርን እና ምስጋናን ተቀብሎአልና።

ሰዎች

የሉቃስ ወንጌል 23፥
4 ጲላጦስም ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡ፦ በዚህ ሰው አንድ በደል ስንኳ አላገኘሁበትም አለ።
23፥14 ሕዝቡን ያጣምማል ብላችሁ ይህን ሰው ወደ እኔ አመጣችሁት፤ እነሆም፥ በፊታችሁ መርምሬ ከምትከስሱበት ነገር አንድ በደል ስንኳ በዚህ ሰው አላገኘሁበትም።
15 ሄሮድስም ደግሞ ምንም አላገኘም፤ ወደ እኛ መልሶታልና፤ እነሆም፥ ለሞት የሚያደርሰው ምንም አላደረገም።
23፥22 ሦስተኛም፦ ምን ነው? ያደረገውስ ክፋት ምንድር ነው? ለሞት የሚያደርሰው በደል አላገኘሁበትም።

የዮሐንስ ወንጌል
18፥38 ጲላጦስ፦ እውነት ምንድር ነው? አለው። ይህንም ብሎ ዳግመኛ ወደ አይሁድ ወጥቶ፦ እኔስ አንዲት በደል ስንኳ አላገኘሁበትም።
19፥6 ጲላጦስም፦ እነሆ ሰውዬው አላቸው። የካህናት አለቆችና ሎሌዎች ባዩትም ጊዜ፦ ስቀለው ስቀለው እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም፦ እኔስ አንዲት በደል ስንኳ አላገኘሁበትምና እናንተ ወስዳችሁ ስቀሉት አላቸው።

የማቴዎስ ወንጌል 27፥
3 በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፥ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ፦
4 ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ አለ። እነርሱ ግን፦ እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ አሉት።

አጋንንት

የማርቆስ ወንጌል 1፥24 እርሱም፦ የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደ ሆንህ አውቄአለሁ፥ የእግዚአብሔር ቅዱሱ ብሎ ጮኸ።
25 ኢየሱስም፦ ዝም በል ከእርሱም ውጣ ብሎ ገሠጸው።
የሉቃስ ወንጌል 4፥34 ተው፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደ ሆንህ አውቄሃለሁ፥ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱሱ አለ።
35 ኢየሱስም፦ ዝም በል ከእርሱም ውጣ ብሎ ገሠጸው።

ኢየሱስ እንዲህ ዓይነት ፍጹም ሰው ነው። ከሰዎችም ሁሉ ይለያል። ከነቢያት፣ ከፋላስፋዎችም ሁሉ ይበልጣል። ምክንያቱም እነዚያ ሁሉ ተንኮል አለባቸው ኢየሱስ ግን ተንኮል አልተገኘበትም። እነዚያ ሁሉ ሰውን ይጠሉ፣ ይሰድቡ፣ ወይም ይገድሉ፣ ወይም የራሳቸውን ትምህርት ያልተቀበለውን ሰው ያሳድዱ ነበር። በግድ የራሳቸው ተከታይ ያደርጉ ነበር። ኢየሱስ ግን ማንንም አልጠላም፤ ማንንም አልተሳደበም (ዮሐንስ 8፡15)፣ ማንንም አልዛተም፣ ማንንም አልገደለም። ያ ብቻ አይደለም እነዚያ ሁሉ ሰይፍና ጦር ይመዝዙ ነበር። ኢየሱስ ግን "ሰይፍ የሚያነሱ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉ" ብሎ አስተማረ። ኢየሱስ አንድም ሰይፍ ሳያነሳ አንድም ጦር ሳያስከትት ወይም ታጣቂዎችን ሳያሰልፍ፣ በፍቅሩ እና በውበቱ ብቻ እየማረከ (እያሸነፈ) ይኸው እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ ቢሊዮኖችን የራሱ አደረገ (እኔንም ጨምሮ ማለት ነው፤ ክብር ለእርሱ ይሁንለት፤ አሜን)

ፍጹም ሰው

የሐዋርያት ሥራ 2፡
22 የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች፣ በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤
23 እርሱንም፣ በእግዚአብሔር በተወሰነው አሳቡና በቀደመው እውቀቱ ተሰጥቶ በዓመፀኞች እጅ ሰቅላችሁ ገደላችሁት።
24 እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነሣው፥ ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና።

1ኛ የጴጥሮስ መልእክት
2፥23 ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራንም ሲቀበል አልዛተም፤ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ።

ይቀጥላል...
የቀጠለ...

1ኛ የዮሐንስ መልእክት
3፥5 እርሱም ኃጢአትን ሊያስወግድ እንደ ተገለጠ ታውቃላችሁ፥ በእርሱም ኃጢአት የለም።
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት
2፥22 እርሱም ኃጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም።

የሉቃስ ወንጌል
23፥15 ሄሮድስም ደግሞ (በኢየሱስ ላይ) ምንም አላገኘም፤ ወደ እኛ መልሶታልና፤ እነሆም፥ ለሞት የሚያደርሰው ምንም አላደረገም።
23፥41 ስለ አደረግነውም የሚገባንን እንቀበላለንና በእኛስ እውነተኛ ፍርድ ነው፤ ይህ (ኢየሱስ) ግን ምንም ክፋት አላደረገም ብሎ ገሠጸው።

ክርስቶስ ስለ ራሱ ፍጹምነት/ንጽህና/ ሲናገር

የዮሐንስ ወንጌል
8፥46 ከእናንተ ስለ ኃጢአት የሚወቅሰኝ ማን ነው? እውነት የምናገር ከሆንሁ እናንተ ስለ ምን አታምኑኝም? (ዛሬም ቢሆን ጌታ ኢየሱስ ሰዎችን እንዲህ ይጠይቃል)

የዮሐንስ ወንጌል
8፥29 የላከኝም ከእኔ ጋር ነው፤ እኔ ደስ የሚያሰኘውን ዘወትር አደርጋለሁና አብ ብቻዬን አይተወኝም አላቸው።

የዮሐንስ ወንጌል 10፡
25 ኢየሱስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል፦ ነገርኋችሁ አታምኑምም። እኔ በአባቴ ስም የማደርገው ሥራ ይህ ስለ እኔ ይመሰክራል፤
26 እናንተ ግን እንደ ነገርኋችሁ ከበጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም።
27 በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤
28 እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም።
29 የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም።
30 እኔ እና አብ አንድ ነን።
31 አይሁድ ሊወግሩት ደግመው ድንጋይ አነሡ።
32 ኢየሱስ፦ ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ ስለ ማናቸው ሥራ ትወግሩኛላችሁ? ብሎ መለሰላቸው።
33 አይሁድም። ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም፤ ስለ ስድብ፤ አንተም ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው እንጂ ብለው መለሱለት።

በመጨረሻም ኢየሱስ ሰው በሆነ ጊዜ አምላክ የለሽ እና ሕገ ወጥ ሳይሆን አምላክ ያለው ፍጹም ሰው መሆኑን መጽሐፉ ያስረዳል። ደግሞም ኢየሱስ ሥጋ ከመልበሱ በፊት፣ ሥጋ ከለበሰም በኋላ የሁሉ ጌታ የሆነ ፈጣሪ አምላክ መሆኑን መጽሐፉ ይገልጣል። ስለዚህ የመጽሐፉ አማኝ ነኝ የሚል ሰው ሁሉ፣ ሙሉ መጽሐፉ የሚነግረውን ማመን አለበት እንጂ አንድ ጥቅስ ብቻ (ወይም ጥቂት ጥቅሶችን ብቻ) መርጦ ማመን እና ለሎቹን ጥቅሶች መሸሽ/መፍራት የለበትም።

የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የምታስተምረው የስብዕና ሥላሴ እና የመሎኮት አንድነት አስተምህሮም ቢሆን ራሱ ኢየሱስ ያስተማረው ሰማያዊ እውነት ነው እንጂ ቤተ ክርስቲያን የወለደችው ተረት አይደለም። (ሥላሴ ማለት በግዕዝ ሦስትነት ማለት ነው)። ታላቁ መምህር እና ገናናው ጌታ፣ ሁልጊዜ እውነትን ብቻ የሚያስተምር አባት ክርስቶስ ኢየሱስ በትዕዛዙ፣ በትምህርቱ እና በኑሮው የስብዕና ሦስትነትን የመሎኮት አንድነትን አስተምሯል።

(1) በትዕዛዙ

የማቴዎስ ወንጌል 28
19-20 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ (1) በወልድና (2) በመንፈስ ቅዱስ (3) ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።

(2) በትምህርቱ

የዮሐንስ ወንጌል
15፥26 ዳሩ ግን እኔ (1) ከአብ ዘንድ (2) የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ(3) በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል።
የዮሐንስ ወንጌል 8፡
16 የላከኝ አብ ከእኔ ጋር ነው እንጂ ብቻዬን አይደለሁምና እኔ ብፈርድ ፍርዴ እውነት ነው።
17 የሁለት ሰዎችም ምስክርነት እውነት እንደ ሆነ በሕጋችሁ ተጽፎአል።
18 ስለ ራሴ የምመሰክር እኔ ነኝ (1)፥ የላከኝም አብ (2) ስለ እኔ ይመሰክራል።

(3) በኑሮው

የማቴዎስ ወንጌል 3
16 ኢየሱስም(1) ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ (2) እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤
17 እነሆም፥ ድምፅ(3) ከሰማያት መጥቶ ፦በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።

እንዲሁም መጽሐፍ እግዚአብሔር አብ አባታችን መሆኑን (ልጆቹ መሆናችንን) ፣ እግዚአብሔር ወልድ ጌታችን መሆኑን (ባሪያዎቹ መሆናችንን)፣ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መሪያችን/አምላካችን/ መሆኑን (ተከታዮቹ መሆናችንን) ይገልጣል።

ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡
14 በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።
ወደ ገላትያ ሰዎች 1
3 ከእግዚአብሔር ከአባታችን፣ ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ሰላም ለእናንተ ይሁን። (አሜን።)

የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች ነን

የሉቃስ ወንጌል 12፥ (ኢየሱስ ሲናገር)
35 ወገባችሁ የታጠቀ መብራታችሁም የበራ ይሁን፤
36 እናንተም ጌታቸው መጥቶ ደጁን ሲያንኳኳ ወዲያው እንዲከፍቱለት ከሰርግ እስኪመለስ ድረስ የሚጠብቁ ሰዎችን ምሰሉ።
37 ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል ቀርቦም ያገለግላቸዋል።
38 ከሌሊቱም በሁለተኛው ወይም በሦስተኛው ክፍል መጥቶ እንዲሁ ቢያገኛቸው፥ እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው።

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1፥1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች የሆኑ ጳውሎስ እና ጢሞቴዎስ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳት እና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፤
2 ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ሰላም ለእናንተ ይሁን። (አሜን።)
መጽሐፈ ዕዝራ
5፥11 እንደዚህም ብለው መለሱልን፦ እኛ የሰማይና የምድር አምላክ ባሪያዎች ነን።
ትንቢተ ዳንኤል
3፥26 የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር ወደ ሚነድደው ወደ እሳቱ እቶን በር ቀርቦ፦ እናንተ የልዑል አምላክ ባሪያዎች፥ ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም፥ ኑ ውጡ ብሎ ተናገራቸው። ሲድራቅና ሚሳቅም አብደናጎም ከእሳቱ መካከል ወጡ።
የሐዋርያት ሥራ
16፥17 እርስዋ ጳውሎስን እና እኛን እየተከተለች። የመዳንን መንገድ የሚነግሩአችሁ እነዚህ ሰዎች የልዑል አምላክ ባሪያዎች ናቸው ብላ ትጮኽ ነበር።

የሉቃስ ወንጌል 17
6 ጌታም (ኢየሱስ) አለ፦ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል <<እምነት ቢኖራችሁ>> ይህን ሾላ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል ብትሉት፥ ይታዘዝላችሁ ነበር።
7 ከእናንተም የሚያርስ ወይም ከብትን የሚጠብቅ ባሪያ ያለው፥ ከእርሻ ሲመለስ፦ ወዲያው ቅረብና በማዕድ ተቀመጥ የሚለው ማን ነው?
8 የምበላውን እራቴን አሰናዳልኝ፥ እስክበላና እስክጠጣ ድረስ ታጥቀህ አገልግለኝ፥ በኋላም አንተ ብላና ጠጣ የሚለው አይደለምን?
9 ያንን ባሪያ ያዘዘውን ስላደረገ ያመሰግነዋልን?
10 እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፦ <<የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል>> በሉ።

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13
14 የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የእግዚአብሔርም ፍቅር፣ የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።
እግዚአብሐር አንድ ነው።

የማርቆስ ወንጌል 12፡29 ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፡- እስራኤል ሆይ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፥
30 አንተም በፍጹም ልብህ፣ በፍጹምም ነፍስህ፣ በፍጹምም አሳብህ፣ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።

ኦሪት ዘዳግም
6፥4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው

ወደ ዕብራውያን
3፥4 እያንዳንዱ ቤት በአንድ ሰው ተዘጋጅቶአልና፥ ሁሉን ያዘጋጀ ግን እግዚአብሔር ነው።

የማቴዎስ ወንጌል
23፥10 ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና። ሊቃውንት ተብላችሁ አትጠሩ።
የማቴዎስ ወንጌል23
8 እናንተ ግን፦ መምህር ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ (መንፈስ ቅዱስ) ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ።
9 አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም፦ አባት ብላችሁ አትጥሩ።
10 ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና፤ ሊቃውንት ተብላችሁ አትጠሩ፡

ትንቢተ ዘካርያስ
14፥9 እግዚአብሔርም (ወልድ) በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፤ በዚያ ቀን እግዚአብሔር አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል።

ትንቢተ ሚልክያስ
2፥10 ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን?

የያዕቆብ መልእክት
4፥12 ሕግን የሚሰጥ እና የሚፈርድ አንድ ነው፤ እርሱም ሊያድን ሊያጠፋም የሚችል ነው፤ በሌላው ግን የምትፈርድ አንተ ማን ነህ?

አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነው።

ትንቢተ ኢሳይያስ
6፥3 አንዱም ለአንዱ፦ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር።
ወደ ሮሜ ሰዎች10
9 ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤
10 ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና።
11 መጽሐፍ፦ በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላልና።
12 በአይሁዳዊ እና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው።

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
2፥8 ከዚችም ዓለም ገዦች አንዱ እንኳ ይህን ጥበብ አላወቀም፤ አውቀውስ ቢሆኑ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉትም ነበር።

ሁለት ጌታ የለም አንድ የነፍሳችን ጌታ አለ።

የሐዋርያት ሥራ 7፡
59 እስጢፋኖስም፦ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር።
60 ተንበርክኮም፦ ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። (ኃጢአታችንን ይቅር ማለት የሚችል አንድ ጌታ ብቻ አለ።)

የማቴዎስ ወንጌል 6፡ 24 ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔር እና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።

የይሁዳ መልእክት 1 ፡
3 ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።
4 ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ (ራዕይ 22፡21) በሴሰኝነት ይለውጣሉ። ንጉሣችንን እና ጌታችንንም ብቻውን ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።
5 ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ ጌታ (ኢየሱስ ክርስቶስ) ከግብፅ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።
6 መኖሪያቸውንም የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት (ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ) በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቆአቸዋል።

ታዲያ ወንድሜ ሆይ ማመን ያለብህ የቱን ነው? በመጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ጥቅሶች የተብራራውን እውነት? ወይስ የሰዎችን ትንተና? ልብ በል የሚሰጡት ትንታኔ ዋና አላማ ሁለት ነው። አንደኛ፣ ጥቅሶችን በመውሰድ የጥቅሶቹን መንፈሳዊ እውነት ከመናገር ይልቅ የዚህን አለም ጥበብ እና አመክንዮ/logic/ ማዕከል በማድረግ ክርክር ማንሳት ነው። ሁለተኛ አንዳች መልካም ነገርን ለማስጨበጥ ሳይሆን፣ ሰዎች ወደ ነፍሳቸው አዳኝ እንዲጠጉ እና እንዲጣበቁ የሚያደርግ ሳይሆን፣ ሰዎች ሁሉ በአዳኛቸው ላይ ያላቸው እምነት እንዲሸረሸር እና እምነታቸውን እንዲጥሉ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች (ለምሳሌ ዮሐንስ 1፡1) ስህተት እንደሆኑ ለማሳየት የታለመ ነው። አንድ እውነት ልንገርህ። የትኛውም ትምህርት ወደ ክርስቶስ የበለጠ የሚያጣብቅህ ካልሆነ ከእግዚአብሔር አይደለም።

አብን እንደምታከብረው ወልድንም እንድታከብረው አብ ራሱ ይፈልግብሃል።
ለምን? ምክኒያቱም የአብን የዘላለም ዕቅድ የፈጸመው፣ አንተን እና መሰሎችህን ከአብ ጋር ያስታረቀው ወልድ ነውና።

የዮሐንስ ወንጌል 5፡
22-23 ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ፥ (አብ) ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም። ወልድን የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም።
24 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ (ይህን) ቃሌን የሚሰማ፣ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።

ኢየሱስ እግዚአብሐር ነበረ።

(1)
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡
6 እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን (እኩል መሆኑን) መቀማት (መንጠቅ) እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥
7 ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥
8 በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።
9 በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤
10 ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥
11 መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።

(2)
የዮሐንስ ወንጌል1፥1 በመጀመሪያው ቃል ነበረ... ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።

(3)
ኦሪት ዘፍጥረት 1፡1 በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።
ወደ ዕብራውያን 1 ፡8 (እግዚአብሐር አብ )ስለ ልጁ ግን (ስለ እግዚአብሐር ወልድ እንዲህ ይላል)፦ አምላክ ሆይ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ ...ጌታ ሆይ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው
11 እነርሱም ይጠፋሉ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ
12 እንደ መጎናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ፤ ይለወጡማል፤ አንተ ግን አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።
ትንቢተ ኤርምያስ 51፡
15 ምድርን በኃይሉ የፈጠረ፥ ዓለሙን በጥበቡ የመሠረተ፥ ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው። ...
18 እነርሱም ምናምንቴና የቀልድ ሥራ ናቸው፤ በተጐበኙ ጊዜ ይጠፋሉ።
19 የያዕቆብ እድል ፈንታ እንደ እነዚህ አይደለም፥ እርሱ የሁሉ ፈጣሪ ነውና እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነው፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።

(4)
የታመነው ፈጣሪ (ታማኙ ፈጣሪያችን) የነፍሳችን ጌታ፣ ኢየሱስ ነው

1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፡19 ስለዚህ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራን የሚቀበሉ፥ መልካምን እያደረጉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ይስጡ።
የሐዋርያት ሥራ 7፡ 59 እስጢፋኖስም፦ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር።
60 ተንበርክኮም፦ ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ። ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር። (ከእኛ በላይ ክርስቲያን መሆኑ የተረጋገጠለት እስጢፋኖስ ነፍሱን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ይሰጣል።)
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 19፡ 4 እርሱም አንድ ቀን የሚያህል መንገድ በምድረ በዳ ሄደ፤ መጥቶም ከክትክታ ዛፍ በታች ተቀመጠና፦ ይበቃኛል አሁንም፥ አቤቱ እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ ብሎ እንዲሞት ለመነ።
ትንቢተ ሕዝቅኤል (አምላክ ሲናገር)
18፥4 እነሆ፥ ነፍሳት ሁሉ የእኔ ናቸው፤ የአባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች ደግሞ የልጅ ነፍስ የእኔ ናት።

(5)
ክርስቶስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነበረ። እርሱም የነጴጥሮስ አምላክ ነው።

ትንቢተ ኢሳይያስ 8፡13 መፈራታቸውንም አትፍሩ፣ አትደንግጡ። ነገር ግን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ቀድሱት። የሚያስፈራችሁና የሚያስደነግጣችሁም እርሱ ይሁን።
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡15 ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ፣ አትናወጡም። ዳሩ ግን ጌታን (የሠራዊት ጌታን) እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት።

(6) ነቢያት እንዲህ ይላሉ፦

መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 15፥2 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል...
መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 7፥8 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል...
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 17፥7 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል....
ትንቢተ ኢሳይያስ1፥24 የእስራኤል ኃያል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል... እያሉ ነቢያት ተናገሩ ዳሩ ግን፡-

እግዚአብሔር ራሱ እንዲህ ይላል፦

የማቴዎስ ወንጌል
5፥22 እኔ ግን እላችኋለሁ፥
5፥28 እኔ ግን እላችኋለሁ፥
5፥32 እኔ ግን እላችኋለሁ፥
5፥34 እኔ ግን እላችኋለሁ።
5፥39 እኔ ግን እላችኋለሁ፥
5፥44-45 እኔ ግን እላችኋለሁ፥

የማቴዎስ ወንጌል
8፥11 እላችኋለሁም፥
10፥15 እውነት እላችኋለሁ፥
11፥9 አዎን እላችኋለሁ፥
11፥22 ነገር ግን እላችኋለሁ፥
11፥24 ነገር ግን እላችኋለሁ፥
12፥6 ነገር ግን እላችኋለሁ፥
12፥31 ስለዚህ እላችኋለሁ፥
12፥36 እኔ እላችኋለሁ፥
ትንቢተ ሕዝቅኤል 13፥15 እኔ... እላችኋለሁ።

(7)
ነቢያት እንዲህ አሉ፦
መዝሙረ ዳዊት 23 ፡1 እግዚአብሔር እረኛዬ ነው።

እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦
የዮሐንስ ወንጌል 10 ፡11 መልካም እረኛ እኔ ነኝ።
14 መልካም እረኛ እኔ ነኝ።

(8)
ነቢያት እንዲህ አሉ፦ (ነብዩ ኢሳይያስ እና ሐዋርያው ጴጥሮስ ሲመሰክሩ)

ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡8 የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።

1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡ 24 ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር፣ ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል፤ አበባውም ይረግፋል፤
25 የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል።

እግዚአብሔር/ኢየሱስ/ እንዲህ አለ፦
የማቴዎስ ወንጌል 24፥35 ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም።
የማርቆስ ወንጌል 13፥31 ሰማይ እና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።
የሉቃስ ወንጌል 21፥33 ሰማይ እና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።

(9) የነጴጥሮስን አምላክ እናመልከዋለን

2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ የሆነ ስምዖን ጴጥሮስ፥ በአምላካችን እና በመድኃኒታችን /our God and Saviour/ በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኙ... ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።
ኦሪት ዘጸአት 20
1 እግዚአብሔርም ይህን ቃል ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ።
2 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ።
3 ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።
4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ።
5 አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛ እና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ
6 ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና።

ይቀጥላል...
..የቀጠለ

(1o) የነጳውሎስን ታላቅ አምላክ እናመልከዋለን

ወደ ቲቶ 2፡12-13 ይህም ጸጋ...የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን /our great God and Saviour/ ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ፣ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል።
14 መድኃኒታችንም /our Saviour/ ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።
15 ይህን በሙሉ ሥልጣን ተናገርና ምከር ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ።


(11) ምስጋና የተገባው እግዚአብሔር ብቻ ነው። ስለዚህ በዙፋኑ ፊት እንቆማለን፤ ፈጣሪያችንን እናመሰግናለን፤ የትኛውንም ፍጡር አናመሰግንም ምክኒያቱም አምላካችን ቀናተኛ አምላክ ነውና፤ ክብሩንም ለማንም አይሰጥምና።

መዝሙረ ዳዊት 18
1 አቤቱ ጕልበቴ ሆይ፥ እወድድሃለሁ...
3 ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፥ ከጠላቶቼም እድናለሁ።

1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1፡12 ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ ኃይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ። (ጳውሎስ በአጠገቡ በአካል ያላገኘውን ኢየሱስን፣ በስልክ፣ በኢሜል ወይም በዴብዳቤ ያላገኘውን ኢየሱስን በመንፈስ ሆኖ ያመሰግነዋል፤ ይህ አይነት ምስጋና አምልኮ በመባል ይታወቃል።)
እነሆ ዛሬም የጳውሎስን አምላክ ይኼውም የእኛን አምላክ ክርስቶስን እናመሰግነዋለን። ለምን? አዎን ምስጋና የተገባው እግዚአብሔር እርሱ ነውና። አምላኬ ሆይ አድርገህልኛልና ለዘላለም አመሰግንሃለሁ፤ አሜን።

ስግደት ለአምላክ በሰማይ ዙፋኑ ፊት

የዮሐንስ ራእይ 5፡ 8
መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶች እና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ (በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ወደቁ)

ጸሎት ወደ አምላክ ነው

የዮሐንስ ራእይ 5፡ 8
...መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶች እና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳንዳቸውም በገናን እና የቅዱሳን (የአማኞች) ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።

ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ።
ኦሪት ዘጸአት
15፥1 በዚያም ጊዜ ሙሴ እና የእስራኤል ልጆች ይህንን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ፥ እንዲህም ብለው ተናገሩ። በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ፈረሱን እና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ።

አምላኬ ሆይ ለአንተ እዘምራለሁ

መጽሐፈ መሣፍንት
5፥3 ነገሥታት ሆይ ስሙ፤
መኳንንት ሆይ አድምጡ፤
እኔ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፥
ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ።
መዝሙረ ዳዊት
104፥33 በሕይወቴ ሳለሁ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፥ ለአምላኬም በምኖርበት ዘመን ሁሉ እዘምራለሁ።

የዮሐንስ ራእይ 5፡ 9-10
...መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ፣ ከቋንቋም ሁሉ፣ ከወገንም ሁሉ፣ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥት እና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።

ሰማያዊ ዝማሬ እና መንፈሳዊ ቅኔ ለእግዚአብሔር ብቻ የተገባ ነው። በሰማይ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት የሚመለከው ራሱ እግዚአብሔር ብቻ ነው እንጂ ከእግዚአብሔር የተለየ ሌላ አካል አይደለም።

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፡ 17 ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ።
18 መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤
19 በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ፤
20 ሁልጊዜ ስለ ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንን (መንፈስ ቅዱስን) እና አባታችንን (አብን) ስለ ሁሉ አመስግኑ።
21 ለእያንዳንዳችሁ በክርስቶስ ፍርሃት የተገዛችሁ ሁኑ።

የሐዋርያት ሥራ 16፡
25 በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ (በዝማሬ) ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር
26 ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ የሁሉም እስራት ተፈታ።
27 የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ።
28 ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ። ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ ብሎ ጮኸ።
29 መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ፥ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ፤
30 ወደ ውጭም አውጥቶ። ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል? ኣላቸው።
31 እርሱም፦ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ (በእግዚአብሔር ወልድ) እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት።
32 ለእርሱና በቤቱም ላሉት ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ተናገሩአቸው።
33 በሌሊትም በዚያች ሰዓት ወስዶ ቍስላቸውን አጠበላቸው፥ ያን ጊዜውንም እርሱ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር (በጌታ በኢየሱስ ስም) ተጠመቀ፤
34 ወደ ቤቱም አውጥቶ ማዕድ አቀረበላቸው፥ በእግዚአብሔርም (ማለት በጌታ በኢየሱስ) ስላመነ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ሐሤት አደረገ። (ክርስቶስ እግዚአብሔር ሲሆን ሌላ ማንም ሰው ወይም ነቢይ እግዚአብሔር አይደለም አልነበረም አይሆንምም።)

መላእክት ሁሉ ፈጣሪያቸውን ኢየሱስን ያመልኩታል

የዮሐንስ ራእይ 5፡
11 አየሁም፥ በዙፋኑም፣ በእንስሶቹም፣ በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቍጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋት እና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፥
12 በታላቅም ድምፅ፦ የታረደው በግ ኃይል እና ባለ ጠግነት፣ ጥበብም፣ ብርታትም፣ ክብርም፣ ምስጋናም፣ በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ።

መላእክት ኢየሱስን እንዲያመልኩት አብ ይፈልጋል። ለምን? ምክኒያቱም አብ እና ኢየሱስ ፈጽሞ የማይነጣጠሉ አንድ ናቸው (የዮሐንስ ወንጌል 10፡31)

ወደ ዕብራውያን 1፡ 6 (እግዚአብሔር አብ) ደግሞም በኵርን (ኢየሱስን) ወደ ዓለም ሲያገባ፦ የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉም ለእርሱ ይስገዱ ይላል።

ፍጥረት ሁሉ ፈጣሪን ያመሰግናል።

የዮሐንስ ራእይ 5፡ 13
በሰማይ እና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፦ በረከት እና ክብር፣ ምስጋናም፣ ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም (ለኢየሱስ) ይሁን ሲሉ ሰማሁ።
14 አራቱም እንስሶች፦ አሜን አሉ፤ ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱ።

አየህ? ኢየሱስ ማለት ፍጥረት ሁሉ በዙፋኑ ፊት የሚያመልኩት አምላክ ነው። ልብ በል ፍጥረታት ሁሉ ሌላውን ፍጡር አያመልኩም አንድ ፈጣሪያቸውን ያመሰግናሉ እንጂ። በእግዚአብሐር ዙፋን ፊት አምልኮ የሚቀበል ሌላ ደባል አካል ወይም ፍጡር እንደ ሌለ እግዚአብሔር ብቻውን አምልኮ እንደሚቀበል መጽሐፍ ቅዱስ ያረጋግጣል። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡7 የምለውን ተመልከት፤ ጌታም በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጥህ።

እግዚአብሔር እና በጉ አይነጣጠሉም

የዮሐንስ ራእይ 22፡
1 በአደባባይዋም መካከል ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን (ነጠላ ቁጥር መሆኑን ልብ በል-ዙፋን) የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወትን ውኃ ወንዝ አሳየኝ።
2 በወንዙም ወዲያ እና ወዲህ በየወሩ እያፈራ አሥራ ሁለት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበረ፥ የዛፉም ቅጠሎች ለሕዝብ መፈወሻ ነበሩ።
3 ከእንግዲህም ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን (ነጠላ ቁጥር መሆኑን ልብ በል-ዙፋን) በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፥ ባሪያዎቹም ያመልኩታል፥ ፊቱንም ያያሉ፥
4 ስሙም በግምባሮቻቸው ይሆናል ።
5 ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፥ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃን እና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።

ነጠላ ቁጥር መሆኑን ልብ በል፣ ባሪያዎቻቸው ያመልኳቸዋል ሳይሆን ባሪያዎቹ ያመልኩታል ይላል። ማንን? እግዚአብሔርንና በጉን። ፊቶቻቸውን ያያሉ ሳይሆን ፊቱን ያያሉ ይላል። እንዲሁም ስሙም ይላል ስሞቻቸው አይልም፣ ...ያበራላቸዋል ይላል ያበሩላቸዋል አይልም።

መዝሙረ ዳዊት 2
1 አሕዛብ ለምን ያጕረመርማሉ? ወገኖችስ ለምን ከንቱን ይናገራሉ?
2 የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ።
3 ማሰርያቸውን እንበጥስ፥ ገመዳቸውንም ከእኛ እንጣል።
4 በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል።
(እግዚአብሔር የሳቀበት ሰው በከፍተኛ አደጋ ላይ ነው፤ ይህ ሰው አይለማም፤ አይበረክትም፤ የሚያድነውም የለም።)
5 በዚያን ጊዜ በቍጣው ይናገራቸዋል፥ በመዓቱም ያውካቸዋል።
6 እኔ ግን ንጉሤን (ኢየሱስን) ሾምሁ፤ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ።
7 ትእዛዙን እናገራለሁ እግዚአብሔር አለኝ፦ "አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለድሁህ።
8 ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ።
9 በብረት በትር ትጠብቃቸዋለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃዎች ትቀጠቅጣቸዋለህ።"
(የዮሐንስ ራእይ 2፡26-27)
10 አሁንም እናንት ነገሥታት፥ ልብ አድርጉ፤ እናንት የምድር ፈራጆችም፥ ተገሠጹ።
11 ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፥ በረዓድም ደስ ይበላችሁ።
12 ተግሣጹን ተቀበሉ፤ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ቍጣው ፈጥና ትነድዳለችና። በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው።

(12) ለእያንዳንዱ ሰው ዋጋውን የሚሰጥ የሰማይ ጌታ

የዮሐንስ ራእይ 11፡
15 ሰባተኛው መልአክ ነፋ፤ በሰማይም፦ የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል
16 የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ሆኑ። በእግዚአብሔርም ፊት በዙፋኖቻቸው የተቀመጡ ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው
17 ለእግዚአብሔር እየሰገዱ እንዲህ አሉ። ያለህና የነበርህ ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ትልቁን ኃይልህን ስለ ያዝህ ስለ ነገሥህም እናመሰግንሃለን፤
18 አሕዛብም ተቈጡ፥ ቍጣህም መጣ፥ በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ። ለባሪያዎችህም፣ ለነቢያትና ለቅዱሳን፣ ስምህንም ለሚፈሩት፣ ለታናናሾችና ለታላላቆችም <<ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ>>፥ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ።
የዮሐንስ ራእይ 22፡
11 ዓመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፥ ርኵሱም ወደ ፊት ይርከስ፥ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፥ ቅዱሱም ወደፊት ይቀደስ አለ።
12 እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ <<ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን>> እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።
13 አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።
14 ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው፣ በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው።
15 ውሻዎችና አስማተኞች፣ ሴሰኛዎችም፣ ነፍሰ ገዳዮችም፣ ጣዖትንም የሚያመልኩት፣ ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።
16 እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። (የመላእክት ጌታ አንዱ እግዚአብሔር ነው) እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።
17 መንፈሱና ሙሽራይቱም፦ ና ይላሉ። የሚሰማም፦ ና ይበል። የተጠማም (ወደ ጌታ ኢየሱስ) ይምጣ፥ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይውሰድ።

በመቀጠልም ከሌላ ምንጭ በትዕምርተ ጥቅስ ጠቅሰህ "ወርቃማ እና የክርክርህ መሰረት" የሆነ ሕግ አስቀምጠሃል። እንዲህ ስትል፡-
የአንድ ዓረፍተ ነገር ባለቤትም ሆነ ተሳቢው ጠቃሽ አመልካች ካላቸው "ሁለቱም የታወቁ፣ አንድ ዓይነት እና ምንም ልዩነት የሌላቸው ናቸው፤ እንዲሁም አንዱ ሌላውን ሊተካው ይችላል።"

ለመሆኑ ይህን "ወርቃማ ሕግ" ያገኘኸው፤ ምንጩ ከየት ነው? ሟች እና አላፊ ከሆነው ከሰው ነው? ከዚህ አለም ጥበብ እና ጥበበኞች ነው? ወይስ ሰማይ እና ምድር ካለፉ በኋላም ከማያልፈው የክርስቶስ ቃል ነው? የጠቀስከውስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው? ወይስ ከሰው? ሁልጊዜስ እውነት ነው? የማይሻር እውነት ነው? ለመሆኑ አንተ እንዳልከው በዚህ ህግ፣ ሰዎች ሁሉ ይስማማሉን? ካልተስማሙስ "ወርቃማው" መሰረትህ በአንዴ ሊፈርስ ነው? በእርሱ ላይ የገነባኸው ያ ሁሉ ክርክርህስ በአንዴ ሊናድ ነውን? ለመሆኑ ይህ "መሰረታዊ" ሕግህ ማን የደነገገው ነው? የክርስቶስ ሕግ ነው ወይስ የሰዎች ሕግ? በዚህ ሕግ ተመስርተህ የምትናገረውስ ነገር ያዋጣሃልን? ቤትህስ በአለት ላይ የተመሰረተ ነውን ወይስ በአሸዋ ላይ? "አሕዛብ በአእምሮአቸው /በእውቀታቸው/ ከንቱነት እንደሚመላለሱ" ብትመላለስ ይሻልሃል ወይስ ጌታ ኢየሱስን በሚያከብረው በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ብትመላለስ ይሻልሃል? ምርጫው ያንተ ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክ እና ፍጹም ሰው ነው /perfect God and perfect Man/። ከአምላክነቱ አንጻር ስናየው ከአብ ጋር ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ፈጽሞ አንድ የሆነ እና ከቶ የማይነጣጠል እኩል ክብር እና ስልጣን ያለው ነው፤ አለም ሳይፈጠር በፊት ከአብ ጋር ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የነበረ፣ አምልኮንም የሚቀበል ፍጹም አምላክ ነው፤ የአማኞቹም ዘላለማዊ አባትና ኃያል አምላክ ነው፤ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ነው። ከሰውነቱ አንጻር ስናየው እርሱ የሰው ልጅ ሰው ነው። ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እኛን የመሰለ በንጹህ ኑሮ አብን ያስደሰተ፣ ራሱም በመንፈስ ቅዱስ የተደሰተ ፍጹም ሰው ነው፤ የአማኞችም ሊቀካህናት እና በኩር ወንድም ነው።

ወንድሜ ሆይ በየአመቱ የሚመጡ አዳዲስ የክህደት ወሬዎች እና ትምህርቶች ሊያስደንቁህ ወይም ሊማርኩህ አይገባም።

ትንቢተ ኤርምያስ 51፡
45 ሕዝቤ ሆይ፥ ከመካከልዋ ውጡ፤ እያንዳንዳችሁም ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ ራሳችሁን አድኑ።
46 በምድርም ከሚሰማ ወሬ የተነሣ አትፍሩ፤ ልባችሁም የዛለ አይሁን፤ በአንድ ዓመት ወሬ ይመጣል፥ ከዚያም በኋላ በሌላው ዓመት ወሬ፥ በምድርም ላይ ግፍ ይመጣል፥ አለቃም በአለቃ ላይ ይነሣል።
47 ስለዚህ፥ እነሆ የተቀረጹትን የባቢሎን ምስሎች የምቀጣበት ዘመን ይመጣል።

ይቀጥላል....
...የቀጠለ

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡
12-13 ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመን እና በማወቅ ወደ ሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደ ሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን (አማኞች) አገልግሎትን ለመሥራት እና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።
14 እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል፣ በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያ እና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥
15 ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን፣ በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤
16 ከእርሱም የተነሣ አካል ሁሉ እያንዳንዱ ክፍል በልክ እንደሚሠራ፥ በተሰጠለት በጅማት ሁሉ እየተጋጠመ እና እየተያያዘ፥ ራሱን በፍቅር ለማነጽ አካሉን ያሳድጋል።
17 እንግዲህ አሕዛብ ደግሞ በአእምሮአቸው ከንቱነት እንደሚመላለሱ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳትመላለሱ እላለሁ፣ በጌታም ሆኜ እመሰክራለሁ።

ይቀጥላል....
0 ድምጾች
ሰላም ሄኖክ

የኔ እምነት "ሰው ሁሉ ውሸተኛ ከሆነ እግዚአብሔር እውነተኛ ይሁን" የሚለውን የሮሜ 3፡4 ጥቅስ በመከተል የምደርስበት መደምደሚያ ምንም ይሁን ምን መጽሐፉ የሚለውን መቀበል ነው።

በዚህ መሰረት ላነሳሃቸው ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እሞክራለሁ

1. ክርስቲያን አንድ አምላክ ያመልካል ወይንስ ሁለት ?

መልሴ፡ አንድ አምላክን ያመልካል ነው።

ምክንያት፡
Quote:
ማቴዎስ 4፡10 "...ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአል..."።
ኢየሱስ እርሱን ጨምሮ ሁሉም ሰው ይህን ትዕዛዝ መታዘዝ እንዳለበት ገልጿል። ኢየሱስ ለሶስቱም ጥያቄዎች የመለሰውን መልስ ልብ ብለን እናንብብ።

ሀ. ሰይጣን 'እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል' ሲለው የኢየሱስ መልስ 'ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል' ነበር። ስለሌላው ሰው እየተናገረ ነበርን? ጥያቄው ሲቀርብ እርቦት ስለነበር ጥያቄውም መልሱም ስለ ኢየሱስ ነበር።

ለ. ሰይጣን 'ራስህን ወርውር፣ መላዕክቱን ስላንተ ያዛልና' የሚል ጥያቄ ሲያነሳ የኢየሱስ መልስ 'እግዚአብሔር አምላክህን አትፈታተን ተብሎ ተጽፏል' ነበር። የኢየሱስ መልስ ሰይጣን ኢየሱስን እንዳይፈታተን ወይስ ይህን በማድረግ ኢየሱስ እግዚአብሔር አምላክን እንዳይፈታተን?

የሦስተኛው ጥያቄ መልስም እንዲሁ ስለኢየሱስ ነው የሚናገረው።
Quote:
ዮሐንስ 17፡3 "እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።"
ይላል። ይህንን ጥቅስ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች "ብቻህን እውነተኛ አምላክ የሆንህ . . ." በማለት ይገልጹታል። (በግሪክኛ "σὲ τὸν μόνον ἀληθινὸν θεὸν" == 'YOU THE ONLY TRUE GOD')። በዚህም ኢየሱስ ራሱ እውነተኛው አምላክ አንድ ብቻ እርሱም 'አባቱ' እንደሆነ ገልጾልናል።
Quote:
1 ቆሮንቶስ 8፡5-6፡ "መቼም ብዙ አማልክትና ብዙ ጌቶች አሉ፤ ነገር ግን በሰማይ ሆነ በምድርም ሆነ አማልክት የተባሉ ምንም ቢኖሩ፥ ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፥ ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።"
-- "አንድ አምላክ አብ አለን" የሚለው እና "ብዙ አማልክት ... አሉ" የሚለው አገላለጽ አንድ የሚነግረን ነገር አለው። ኢየሱስና ሃዋርያው ጳውሎስ እንደገለጹት እውነተኛው አምላክ አንድ ብቻ ሲሆን አማልክት የሚባሉ ሌሎች ደግሞ አሉ። ይህም እነዚህ አማልክት ወይ የሐሰት አማልክት ናቸው አሊያም የእውነተኛው አምላክ ነጸብራቅ ናቸው ወደሚል ምክንያታዊ መደምደሚያ ያደርሰናል።
Quote:
መዝሙር 8፡5፡- "ከመላእክት (በዕብራይስጥ 'ኤሎሂም' = አማልክት) እጅግ ጥቂት አሳነስኸው በክብርና በምስጋና ዘውድ ከለልኸው።"
የሚለውን ጥቅስ ሃዋርያው ጳውሎስ በዕብራውያን 2፡7 ላይ እነዚህ አማልክት "መላእክት" እንደሆኑ ይገልጻል። በነገራችን ላይ መላእክት በብሉይ ኪዳን መጽሓፍት ገጾች ውስጥ "እግዚአብሔር" / "ያህዌህ" ተብለውም ተጠተዋል። ለምሳሌ ዘጸአት 3፡1-5 ያለውን ብንመለከት ለሙሴ በቁጥቋጦው የተገለጠለት መልአክ ሲሆን 'እኔ የአብርሃም የይስሃቅ የያዕቆብ አምላክ ነኝ' ሲል እንሰማለን። እስጢፋኖስም ሙሴ ያየው "የጌታን መልአክ" እንደሆነ ተናግሯል (የሐዋርያት ሥራ 7፡30)። ዘፍጥረት 22፡11-12 ላይ ያለውን ብናነብ "የእግዚአብሔር መልአክ" አብርሃምን "አንድ ልጅህን ለእኔ አልከለከልህምና" ሲለው እንመለከታለን። በዘፍጥረት 18 ላይ ወደ አብርሃም ቤት የገቡት 3 "ሰዎች"ም እንዲሁ መላእክት እንደነበሩ ምዕራፍ 19 (ቁጥር 1 ላይ "ሁለቱም መላእክት ..." በማለት አስቀድሞ እንደጠቀሳቸው በመጠቆም) በግልጽ ያስቀምጣል። ሃዋርያው ጳውሎስም በተዘዋዋሪ መንገድም "መላእክት" እንደነበሩ ጠቅሷል። (ዕብራውያን 13፡1-2) ዘፍጥረት 18ን ከዮሐንስ 1፡18 ጋር ማወዳደርም ሊበቃን ይችላል።

ኢየሱስም በዮሐንስ 10፡34 ላይ "እኔ። አማልክት ናችሁ አልሁ ተብሎ በሕጋችሁ የተጻፈ አይደለምን?" በማለት በመዝሙር ላይ የተጠቀሱትን የእስራኤል ፈራጆች እግዚአብሔር "አማልክት" ብሎ እንደጠራቸው ተናግሯል።

ሃዋርያው ጳውሎስ በኤፈሶን 4፡6 ላይ፡ "ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሰራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።" በማለት የሁሉ አባት የሆነው አብ ብቻውን አምላክ እንደሆነ የሚናገሩትን እጅግ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች በሚስማማ መልክ ይገልጸዋል።

በዚህ ጉዳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ወገን ለማንም ግልጽ ነው። የትኛውም ንጹህ አእምሮ ያለው ግለሰብ መጽሐፉን በንጹህ ህሊና ቢያነብ የሚደርስበት መደምደሚያ ይህ እና ይህ ብቻ ነው።


2. ኢየሱስ አምላክ ነው ወይ? ይመለካልን?

መልሴ፡ አዎን ኢየሱስ አምላክ ነው፤ ነገር ግን አይመለክም።

ይህ ምን ማለት ነው? የሥላሴ አማኞች ብዙውን ጊዜ አላግባብ ከሚጠቅሷቸው ጥቅሶች አንዱ የሆነው ዮሐንስ 1፡1 ነው። ጥቅሱ በ1954 ትርጉም መሰረት እንዲህ ይነበባል፦
Quote:
"በመጀመሪያው ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሔር (ግሪክኛ፣ ቶን ቴኦን) ዘንድ ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር (ግሪክኛ፣ ቴኦስ) ነበረ።"
በዚህ ጥቅስ ላይ ቴኦስ (አምላክ) የሚለው የግሪክኛ ስም በሁለት መንገዶች ተቀምጧል። ከመጀመሪያው ስም በፊት ቶን የሚል የግሪክኛ ጠቃሽ አመልካች (article) ገብቷል፤ በመሆኑም በዚህ ቦታ ላይ ቴኦስ የሚለው ቃል ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ያመለክታል። ከሁለተኛው ስም በፊት ግን ምንም ዓይነት ጠቃሽ አመልካች አልገባል። እዚህ ቦታ ላይ ጠቃሽ አመልካች ያልገባው በስህተት ነውን?

የዮሐንስ ወንጌል የተጻፈው ኮይኔ ተብሎ በሚጠራው ተራው ህዝብ በሚግባባበት ግሪክኛ ነበር፤ ይህ ዓይነቱ ግሪክኛ የጠቃሽ አመልካችን አጠቃቀም በተመለከተ ግልጽ የሆነ የሰዋስው ሥርዓት አለው። የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር የሆኑት አርኪባልድ ሮበርትሰ እንደተናገሩት የአንድ ዓረፍተ ነገር ባለቤትም ሆነ ተሳቢው ጠቃሽ አመልካች ካላቸው "ሁለቱም የታወቁ፣ አንድ ዓይነትና ምንም ልዩነት የሌላቸው ናቸው፤ እንዲሁም አንዱ ሌላውን ሊተካው ይችላል።" ለምሳሌ ማቴዎስ 13፡38 "እርሻውም (ግሪክኛ፣ ሆ አግሮስ) ዓለም (በግሪክኛ፣ ሆ ኮስሞስ) ነው" ይላል። ከሰዋሰው ህግ አንጻር ይህን ዓረፍተ ነገር "ይህ ዓለም ዕርሻው ነው" ብሎ ማስቀመጥም ይቻላል።

ይሁንና በዮሐንስ 1፡1 ላይ እንደምናገኘው የአንድ ዓረፍተ ነገር ባለቤት ጠቃሽ አመልካች ኖሮት ተሳቢው ጠቃሽ አመልካች ባይኖረውስ? ጀምስ አለን ሂዩት የተባሉ አንድ ምሁር ይህንን ጥቅስ እንደ ምሳሌ በመውሰድ እንደሚከተለው ብለዋል፦"እንዲህ ባለው ዓረፍተ ነገር ውስጥ ባለቤቱና ተሳቢው አንድ ዓይነት፣ እኩል እንዲሁም ምንም ልዩነት የሌላቸው አይደሉም።"

ሂዩት ሃሳባቸውን በምሳሌ ለማስረዳት "አምላክ ብርሃን ነው" የሚለውን 1ዮሐንስ 1፡5ን ይጠቅሳሉ። እዚህ ጥቅስ ላይ "አምላክ" በግሪክኛ ሆ ቴኦስ ሲሆን ጠቃሽ አመልካች አለው። ይሁን እንጂ "ብርሃን" በግሪክኛ ፎስ የሚለው ቃል ጠቃሽ አመልካች አልገባለትም። ሂዩት እንዳሉት "ምንጊዜም ቢሆን አንድ ሰው፣ አምላክ ብርሃን እንደሆነ መናገር ይችላል፤ ብርሃን አምላክ እንደሆነ ግን መናገር የሚቻለው ሁልጊዜ አይደለም።" ሌላ ምሳሌ "አምላክ (ሆ ቴኦስ) መንፈስ ነው" ዮሐንስ 4፡24፣ "አምላክ (ሆ ቴኦስ) ፍቅር ነው" 1 ዮሐንስ 4፡16። በሁለቱም ጥቅሶች ላይ የዓረፍተ ነገሩ ባለቤት ጠቃሽ አመልካች ያለው ሲሆን "መንፈስ" እና "ፍቅር" የሚሉት ተሳቢዎች ግን ጠቃሽ አመልካች አልገባላቸውም። ስለዚህ የዓረፍተ ነገሮቹ ባለቤትና ተሳቢዎች እርስ በርስ ሊተካኩ አይችሉም። እነዚህ ጥቅሶች "መንፈስ አምላክ ነው" ወይም "ፍቅር አምላክ ነው" ተብለው ሊቀመጡ አይችሉም። ይችላሉ እንዴ?

በኮይኔ ግሪክኛ የሰዋስው ህግ መሰረት ተሳቢው ጠቃሽ አመልካች ሳይኖረው ከተቀመጠ፣ የዓረፍተ ነገሩ ባለቤት የተሳቢው ባህርይ አለው ማለት ነው። በዚህ መሰረት "አምላክ ፍቅራዊ ነው" ወይም "ፍቅር የአምላክ ባህሪይ ነው" ማለት እንችላለን። በተመሳሳይም "አምላክ መንፈሳዊ ነው" ወይም "አምላክ መንፈሳዊ ባህርይ አለው" ማለት ይቻላል።

እንደ እውነቱ ከሆነ ይህ ዓይነቱ ማብራሪያ ለሥላሴ አማኝ የሚጥም አይደለም። ዮሐንስ 1፡1 በከፊል " ቃል (ኢየሱስ) በአምላክ (ቶን ቴኦን = እግዚአብሔር) ዘንድ ነበረ፣ ቃልም አምላክ (ቴኦስ = አምላክ) ነበር" ተብሎ በትክክል ሊተረጎም ይችላል። ይህም ቃል መለኮታዊ ባህርይ አለው የሚለውን ሃሳብ የሚያስረግጥ ነው። የሥላሴ እምነት የ"ክርስትና" ዋነኛ መሰረታዊ ትምህርት እንደመሆኑ መጠን የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች (አብዛኞቹ የሥላሴ አማኞች ናቸው) እንደ ዮሐንስ 1፡1 የመሳሰሉ ጥቅሶችን የእምነታቸው ተጽዕኖ እንዲያርፍባቸው አድርገዋል። ይህም እውነትን ከልባቸው የሚፈልጉ ሰዎች ከፍተኛ ጥረት ማድረግ እንዲጠበቅባቸው አድርጓል። በትንሹ ግን አዮታን ተጠቅመው ጥቂት ምርምር ማድረግ ይበቃ ይሆናል። አዮታ 3588 የሚለውን ስትሮንግ ቁጥር ለጠቃሽ አመልካቾች ያስቀምጣል። ይህም ቢያንስ በዮሐንስ 1፡1 ሁለት ቦታ ላይ የተጠቀሱት በአማርኛችን "እግዚአብሔር" (ቴኦስ፣ በ2316 ስትሮንግ ቁጥር የተጠቀሰው ቃል) የሚሉት ቃላት ልዩነት እንዳላቸው መገንዘብ እንችላለን ማለት ነው።

በምሳሌ ለማስረዳት ያህል ልክ እንደ ኮይነ ግሪክኛ ሁሉ አማርኛችንም በተወሰነ መልኩ ተመሳሳይ ነገር ይጠቀማል። ለምሳሌ ጠቃሽ አመልካች የገባለት አንድ ቃል "ሰውየው" ቢሆን ጠቃሽ አመልካች ያልገባለት ደግሞ "ሰው" ይሆናል። በዚህ መሰረት "አበበ ከሰውየው ጋር ነበር፣ አበበም ሰው ነበር" ብንል በትክክል አበበ ሰውየው እንዳልነበረ እንረዳለን። የዮሐንስ 1፡1 ሰዋሰዋዊ ስሜትም ይህ ነበር።

በዚህ መሠረት ኢየሱስ "አምላክ" ተብሎ ሊጠራ እንደሚችል ከዚህ ጥቅስና ከሌሎች ጥቅሶች (ኢሳይያስ 9፡6፡ "ኃያል አምላክ . . . ተብሎ ይጠራል") በግልጽ ማየት ይቻላል። ኢየሱስ ክርስቶስ "ብቻውን እውነተኛ አምላክ" የሆነው አብ እንደሆነ ከገለጸልን (ዮሐንስ 17፡3)፣ ታዲያ ኢየሱስ ምን ዓይነት አምላክ ነው? ሃዋርያው ጳውሎስ በቆላስይስ 1፡15 ላይ ኢየሱስ "የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው" በማለት ይገልጸዋል። በዕብራውያን 1፡3 ላይም ኢየሱስ የእግዚአብሔር "የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ" እንደሆነ ገልጾልናል። በመሆኑም ኢየሱስን የእውነተኛው አምላክ ትክክለኛ ነጸብራቅ ነው ብንል የተሳሳትን አይመስለኝም።


3. ኢየሱስ ፍጡር ነውን?

ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ወቅት ወደ ምድር ከመጣቱ በፊት በሰማይ ይኖር እንደነበር ገልጿል። (ዮሐንስ 3፡13፤ 8፡23) በመሆኑም የኢየሱስ ህይወት የጀመረው ከማርያም ሲወለድ አይደለም። ቆላስይስ 1፡15 ላይ "የፍጥረት ሁሉ በኩር" (በግሪክኛ "πρωτότοκος πάσης κτίσεως" = FIRSTBORN OF-ALL CREATION) እንደሆነ ይገልጻል። "በኩር" ምን ማለት ነው? እስቲ አዮታን ተጠቅመን ቃሉን በመፈለግ መጽሐፍ ቅዱስ ቃሉን የሚጠቀምበትን መንገድ በቀላሉ መረዳት እንችላለን። ("የፈርኦን በኩር"፣ "የእስራኤል በኩር"፣ "የእንስሳት በኩር" ...) በቀላል አገላልጽ ኢየሱስ በእግዚአብሔር የፍጥረት ቤተሰብ ውስጥ አንጋፋ መሆኑን እንገነዘባለን። በተጨማሪም ራዕይ 3፡14 "በእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው" (በግሪክኛ "ἡ ἀρχὴ τῆς κτίσεως τοῦ θεοῦ" = THE BEGINNING OF-THE CREATION OF-THE GOD) በማለት ኢየሱስ ራሱን ሲገልጽ እናነባለን። አሁንም "መጀመሪያ" (በግሪክኛ ἀρχὴ አርክሄ) የሚለውን ቃል እንዲሁ እንመርምር። ("የጥበብ መጀመሪያ"፣ "የምልክቶች መጀመሪያ" - ዮሐንስ 2፡11፣ "የምጥ ጣር መጀመሪያ" - ማቴ 24፡8 ...)። አብዛኞቹ የሃይማኖት ምሁራን እንደሚስማሙበት ምሳሌ 8 ላይ በጥበብ አስመስሎ የሚናገረው ስለ ኢየሱስ ነው ብንል (1 ቆሮንቶስ 1፡24፡ "...የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው") ቁጥር 22 "እግዚአብሔር የመንገዱ መጀመሪያ አደረገኝ፣ በቀድሞ ሥራው መጀመሪያ" የሚለው ሃሳብ ከቆላስይስ 1፡15 እና ራዕይ 3፡14 ጋር ይስማማል።
Quote:
የዮሐንስ ወንጌል 5፥26 "አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና።"
የክርስቶስ ህይወት ምንጭ አብ እንደሆነ ይገልጻል። "ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣቸዋል" (ዮሐንስ 5፡21)። እግዚአብሔር ፍጥረታትን በሙሉ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል እንደፈጠረ የሚናገሩት ብዙ ጥቅሶች ነገሩን ግልጽ ያደርጉታል። 1 ቆሮንቶስ 8፡5-6 አብን የነገር ሁሉ ምንጭ አድርጎ ሲገልጸው ("ከእርሱ" በግሪክኛ "ἐξ" = OUT / FROM) ስለ ክርስቶስ ደግሞ "በእርሱ በኩል" (በግሪክኛ "δι’" = THROUGHT) ሁሉ ነገር እንደተፈጠረ ይነግረናል። ዮሐንስ 1፡3 "ሁሉ በእርሱ ("δι’" = "በእርሱ በኩል") ሆነ" የሚለውንም እናስታውስ።

ከዚህ አንጻር ጌታ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመሪያ መሆኑንና እግዚአብሔር ፍጥረትን ሁሉ በእርሱ በኩል እንደፈጠረ መጽሐፉ የሚነግረንን ማመን ምንኛ መልካም ነው! ዕብራውያን 1፡1-2 የሁለቱን ግንኙነት ሲገልጽ "እግዚአብሔር ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ" በማለት አስቀምጦታል።

በመሆኑም ሊመለክ የሚገባው አምላክ አንዱ እግዚአብሔር አብ ብቻ ነው። ጸሎት የአምልኮ ክፍል ነው፤ መጸለይ የሚገባንም በኢየሱስ ስም ነው (ዮሐንስ 14፡13-14) ፣ ይህ ማለትም ኢየሱስን እንለምናለን ማለት አይደለም (ዮሐንስ 16፡23)፤ ከዚያ ይልቅ ልክ ሃዋርያት እንዳደረጉት በክርስቶስ ስም ብቸኛውን እውነተኛ አምላክ አብን / እግዚአብሔርን እንለምናለን እንጂ። - የሐዋርያት ሥራ 4፡24-30


ሰላም።
Aug 12, 2013 ኦፍቲ (1,230 ነጥቦች) የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2018 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...