ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Friday, 4 December 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ጥምቀት በማን ስም መሆን አለበት?

1. ጥምቀት በማን ስም መሆን አለበት? 2. በአብ በወልድ በመንፈስ ስም የተጠመቀ አለ?
Dec 26, 2012 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

2 መልሶች

+1 ድምጽ
ለአጥማቂዎች የተሰጠው ትዕዛዝ "በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠምቃለሁ" ብለው እንዲያጠምቁ ነው።

ለተጠማቂው የተሰጠው ትዕዛዝ "በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምናለሁ" ወይም "ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አምናለሁ" ብሎ እንዲጠመቅ ነው።

ይህም የሚያሳየን ተጠማቂው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመኑ የዳነ መሆኑን፣
ከዳነ በኋላ ከክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ ጋር ለመተባበር በውሃ የሚጠመቅ (የሚቀበር) መሆኑን፣
በኢየሱስ ስላመነ መንፈስ ቅዱስ የተሰጠው መሆኑን፣ እና
በዚህ መንፈስ በኩል ወደ አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ህብረት /አንድነት/ የተቀላቀለ፣ የገባ መሆኑን በይፋ የሚያውጅ ነው።

ለአጥማቂዎች የተሰጠ ትዕዛዝ (ታላቁ ተልዕኮ)

የማቴዎስ ወንጌል 28
18 ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው። "ሥልጣን ሁሉ በሰማይ እና በምድር ተሰጠኝ።
19-20 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።

አስተውል "እየተጠመቃችሁ" አይልም። ምክንያቱም ትዕዛዙ የተሰጠው ለአጥማቂዎች ብቻ ነው። እንጂ ለተጠማቂዎች አይደለም። ስለዚህ በአዲስ ኪዳን የነበሩ አጥማቂዎች ሁሉ "በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠምቃለሁ" እያሉ እንዳጠመቁ ምንም ጥርጥር የለውም።


ለተጠማቂው የተሰጠ ትዕዛዝ (የእምነት ምስክርነት)

የሐዋርያት ሥራ 8
36 በመንገድም ሲሄዱ ወደ ውኃ ደረሱ። ጃንደረባውም፦ እነሆ ውኃ፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድር ነው? አለው።
37 ፊልጶስም፦ በፍጹም ልብህ ብታምን፥ ተፈቅዶአል አለው። ጃንደረባውም መልሶ፦ "ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ አምናለሁ" አለ። (የእምነት ምስክርነት ማለት ይህ ነው)
38 ሰረገላውም ይቆም ዘንድ አዘዘ፥ ፊልጶስና ጃንደረባው ሁለቱም ወደ ውኃ ወረዱ፥ አጠመቀውም።

የሐዋርያት ሥራ 2
37 ይህንም በሰሙ ጊዜ ልባቸው ተነካ፥ ጴጥሮስን እና ሌሎችንም ሐዋርያት፦ ወንድሞች ሆይ፥ ምን እናድርግ? አሉአቸው።
38 ጴጥሮስም አላቸው፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።

አስተውል "ተጠመቁ" ነው የሚለው። "አጥምቁ" አይልም። ምክኒያቱም ይህ ትዕዛዝ የተሰጠው ለአጥማቂዎች አይደለም። ለተጠማቂዎች ነው እንጂ።

በመጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ በአንድም ቦታ "በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አጥምቁ" የሚል አልተጻፈም።

ወደ ጥያቄው ስንመለስ 1. ጥምቀት በማን ስም መሆን አለበት?

አጥማቂ ከሆንህ "በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠምቃለሁ" ብለህ ማጥመቅ አለብህ። ተጠማቂ ከሆንህም "በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምናለሁ" ወይም "ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አምናለሁ" ብለህ አውጀህ ተጠመቅ። ማለትም በኢየሱስ ስም ተጠመቅ።

2. በአብ በወልድ በመንፈስ ስም የተጠመቀ አለ?

በአብ በወልድ በመንፈስ ስም ያጠመቀ አለ? ብትል ኖሮ መልሱ "አዎን ሁሉም የአዲስ ኪዳን አጥማቂዎች በአብ በወልድ በመንፈስ ስም አጥምቀዋል" የሚል ነው።

ተጨማሪ ጥቅሶችን አገናዝብ።

የማቴዎስ ወንጌል
3፥16 ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤

የማርቆስ ወንጌል
1፥9 በዚያ ወራትም ኢየሱስ ከገሊላ ናዝሬት መጥቶ ከዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ።

16፥16 ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።

የሉቃስ ወንጌል
3፥21 ሕዝቡም ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ ኢየሱስ ደግሞ ተጠመቀ። ሲጸልይም ሰማይ ተከፈተ፥

7፥30 ፈሪሳውያንና ሕግ አዋቂዎች ግን በእርሱ ስለ አልተጠመቁ የእግዚአብሔርን ምክር ከራሳቸው ጣሉ።

የዮሐንስ ወንጌል
11፥44 የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ፤ ፈቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበር። ኢየሱስም፦ ፍቱትና ይሂድ ተዉት አላቸው።

የሐዋርያት ሥራ
2፥38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።

2፥41 ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ፥ በዚያም ቀን ሦስት ሺህ የሚያህል ነፍስ ተጨመሩ፤

8፥12 ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም እየሰበከላቸው ፊልጶስን ባመኑት ጊዜ፥ ወንዶችም ሴቶችም ተጠመቁ።

9፥18 ወዲያውም እንደ ቅርፊት ያለ ከዓይኑ ወደቀ፥ ያን ጊዜም ደግሞ አየ፤ ተነሥቶም ተጠመቀ፥

16፥15 እርስዋም ከቤተ ሰዎችዋ ጋር ከተጠመቀች በኋላ። በጌታ የማምን እንድሆን ከፈረዳችሁልኝ፥ ወደ ቤቴ ገብታችሁ ኑሩ ብላ ለመነችን፤ በግድም አለችን።

16፥33 በሌሊትም በዚያች ሰዓት ወስዶ ቍስላቸውን አጠበላቸው፥ ያን ጊዜውንም እርሱ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ተጠመቀ፤

18፥8 የምኵራብ አለቃ ቀርስጶስም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር በጌታ አመነ፥ ከቆሮንቶስ ሰዎችም ብዙ በሰሙ ጊዜ አምነው ተጠመቁ።

19፥3 እንኪያ በምን ተጠመቃችሁ? አላቸው። እርሱም፦ በዮሐንስ ጥምቀት አሉት።

19፥5 ይህንም በሰሙ ጊዜ በጌታ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ፤
22፥16 አሁንስ ለምን ትዘገያለህ? ተነሣና ስሙን እየጠራህ ተጠመቅ (የእምነት ምስክርነት ማለት ይህ ነው) ከኃጢአትህም ታጠብ።

ወደ ሮሜ ሰዎች
6፥3 ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን?

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
1፥13 ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቀለን? ወይስ በጳውሎስ ስም ተጠመቃችሁን?

1፥14-15 በስሜ እንደ ተጠመቃችሁ ማንም እንዳይል ከቀርስጶስና ከጋይዮስ በቀር ከእናንተ አንድን እንኳ ስላላጠመቅሁ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።

10፥2 ሁሉም ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ በደመናና በባሕር ተጠመቁ፤

ወደ ገላትያ ሰዎች
3፥27 ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።

(G.G.A.A የተወሰደ)
Dec 26, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
Dec 26, 2012 ታርሟል
G.G.A.A ምንድን ነው?
የጌታ ጸጋ ይብዛልህ
እኔም እንዳተው በዚህ በጥምቀት ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ መረዳት ነው ያለኝ የበለጠ በጣም ደስ ያለኝ ከዚህ በፊት በዚህ ጉዳይ ላይ ከምንከራከርባቸው ለየት ያለ ጥሩ መረዳት አግኝተሃልና ላባራታታህና የበለጠ ጌታ የቃሉን ትርጉም እንዲያበራልህ እንድትተጋ እመክርሃለሁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ተኵላዎች ይበዛሉና የእግዚአብሔርን መንጋ የምንጠብቅበት ትልቁ መንገድ ቃሉን በትክክል ማግኘት ነውና በርታ የጌታ ጸጋ ከመንፈስህ ጋር ይሁን። ከ.TB Abrha Ministry
0 ድምጾች
ሌሎች ተጨማሪ ጥቅሶች።


የሐዋርያት ሥራ
2፥38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ፤ አላቸው።
(አስተውል ጴጥሮስ "ተጠመቁ!" አለ እንጂ "አጥምቁ!" አላለም። ይህ ለተጠማቂዎች የተሰጠ ትዕዛዝ ነው።)

የሐዋርያት ሥራ
8፥16 በጌታ በኢየሱስ ስም ብቻ ተጠምቀው ነበር እንጂ ከእነርሱ በአንዱ ላይ ስንኳ ገና አልወረደም ነበርና።
(አስተውል "ተጠምቀው ነበር" ይላል እንጂ "አጥምቀው ነበር" አይልም። ይህም ተጠማቂዎችን የሚያመለክት ነው።)

የሐዋርያት ሥራ
10፥48 በኢየሱስ ክርስቶስ ስምም ይጠመቁ ዘንድ አዘዛቸው። ከዚህ በኋላ ጥቂት ቀን እንዲቀመጥ ለመኑት።
(አስተውል "ይጠመቁ ዘንድ አዘዛቸው" ይላል እንጂ "ያጠምቁ ዘንድ አዘዛቸው" አይልም። ይህ ለተጠማቂዎች የተሰጠ ትዕዛዝ ነው።)

የሐዋርያት ሥራ
19፥5 ይህንም በሰሙ ጊዜ በጌታ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ።
(አስተውል "ተጠመቁ" ይላል እንጂ "አጠመቁ" አይልም። ይህም ተጠማቂዎችን የሚያመለክት ነው።)

የጌታ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን።

(G.G.A.A)
Jan 9, 2013 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...