ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Monday, 25 January 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ዘጸአት 4.(24-26)ን ብታስረዱኝ.......ተባረኩልኝ

እንዲህም ሆነ፤ በመንገድ ላይ ባደረበት ስፍራ እግዚአብሔር ተገናኘው፥ ሊገድለውም ፈለገ።
25 ሲፓራም ሚስቱ ባልጩት ወሰደች፥ የልጅዋንም ሸለፈት ገረዘች፥ ወደ እግሩም ጣለችው። አንተ ለእኔ የደም ሙሽራ ነህ አለች።
26 ከእርሱም ፈቀቅ አለ። የዚያን ጊዜ። ስለ ግርዛቱ አንተ የደም ሙሽራ ነህ አለች

*የደም ሙሽራ ማለት ምን ማለት ነው?
*እግዚአብሔር ሙሴን ወደ ግብጽ ከላከው ቡሃላ በምንገድ ሳለ ለምን ሊገድለው ፈለገ?
Jan 12, 2013 ሌሎች ስም-አልባ የተጠየቀ
Jan 12, 2013 ታርሟል

1 መልስ

0 ድምጾች
Quote:
ዘጸአት 4፡24-26
24 እንዲህም ሆነ በመንገድ ላይ ባደረበት ስፍራ እግዚአብሔር ተገናኘው፥ ሊገድለውም ፈለገ።
25 ሲፓራም ሚስቱ ባልጩት ወሰደች፥ የልጅዋንም ሸለፈት ገረዘች፥ ወደ እግሩም ጣለችው። አንተ ለእኔ የደም ሙሽራ ነህ አለች።
26 ከእርሱም ፈቀቅ አለ። የዚያን ጊዜ። ስለ ግርዛቱ አንተ የደም ሙሽራ ነህ አለች።

ሰላም

ከክፍሉ የምንረዳው እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለዘሩ የቃል ኪዳን ምልክት ይሆን ዘንድ ያዘዘውን የግርዘት ስርዓት ሙሴ በልጁ ባለመፈጸሙ ማለትም ሙሴ ልጁን ባለመግረዙ ነው እግዚአብሔር ሊገድለው የፈለገው። እንደሚታወቀው የአብርሃም ዘር የሆነ ወንድ ሁሉ በ8 ቀኑ መገረዝ ነበረበት፤ ሙሴ ግን ይህንን በልጁ አላደረገም። ሚስቱ ይህ ነገር ስለገባት ነው ባሏ እንዳይሞት ፈጥና ልጇን የገረዘችው እናም በሚስቱ ድርጊት የተነሳ ሙሴን አዳነችው ማለት ነው። ስለዚህም በግርዘቱ ደም የተነሳ ሙሴን ስላዳነችው "የደም ሙሽራ" ብላ ጠራቸው። በደም ከሞት አዳንኩህ እንደገና አጨሁህ ወዘተ ማለት ነው ("ስለ ግርዛቱ አንተ የደም ሙሽራ ነህ አለች" ቁጥር 26)
Jan 12, 2013 ስም-አልባ የተመለሰ
በሚገባ ተመልሶልኛል ተባረኩልኝ.
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...