ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Monday, 25 January 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ግንቦት 11፣2011 አለም ያልፋል ብለው ብዙ ክርስቲያኖች ይናገራሉ።ማረጋገጫው ምንድነው?

Mar 15, 2011 ሌሎች ስም-አልባ የተጠየቀ

2 መልሶች

0 ድምጾች
እንደዚህ ያለው 100% ሊፈጸም የማይችል የውሸት ትንቢት ስለሆነ ምንም ማረጋገጫ የለውም።

መጽሐፍ ቅዱስ የዓለም ፍጻሜ መድረሱን የሚያመለክቱ ምልክቶች ብሎ የሰጣቸው አንዳንድ ነገሮች አሉ። እነዚያ ምልክቶች ናቸው የዓለም መጨረሻ መድረሱን የሚያስረዱ እንጂ የሰዎች የወራትና የዓመታት ቁጥር ለእግዚአብሔር ግድ የለውም። እ.አ.አ የ2000 ዘመን መለወጫ ከመድረሱም በፊት እንደዚሁ ሰዎች የውሸት ትንቢት ሲናገሩ ነበር። ያላስተዋሉት ግን 2000 ዓ/ም የሰዎች መቁጠሪያ እንጂ የእግዚአብሔር እንዳልሆነ ነው። ሰዎች ሲፈልጉ 2011 አይደለም 3011 ቢሉ የራሳቸው መቁጠሪያ ነው። እግዚአብሔር በእነርሱ ቁጥር አይቆጥርም፤ ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈውም የመጨረሻው ዘመን ፕሮግራም በሰዎች ቁጥር አይቀየርም።

የዓለም ፍጻሜ ከመድረሱ በፊት፤ በእስራኤል ቤተመቅደሱ መሠራት አለበት፣ ዓለምን የሚገዛው የክርስቶስ ተቃዋሚ መንገስ አለበት፣ ከዚያም አምላክ ነኝ ብሎ ራሱን በቤተመቅደሱ ማስገባት አለበት፣ ታላቁ የመከራ ዘመን የሚባለው መምጣት አለበት ወዘተ። እነዚህንና የመሳሰሉት ምልክቶች ናቸው የዓለም ፍጻሜን የሚጠቁሙ እንጂ፤ የሰዎች ዘመን መቁጠሪያ ካሌንደር አይደለም።
Mar 15, 2011 በምሕረቱ (1,510 ነጥቦች) የተመለሰ
ምንም ማረጋገጫ የሌለው ወሬ ነው፡፡
+1 ድምጽ
እንኳን እግዚአብሔር ሁላችንንም ለMay 22 በሰላም አደረሰን! :) ይህ የተሳሳተና ያልተፈጸመ ትንቢት ለወደፊት በእንደዚህ ባሉ ፈጽሞ ሊፈጸሙ በማይችሉ ትንቢቶች እንዳንረበሽ አስተምሮን ያለፈ ይመስለኛል።
May 22, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...