ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Sunday, 29 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ኢየሱስ እና ክርስቶስ ልዩነት አለው ካለውስ ምንድነው አስረዱኝ!!

Mar 16, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
ምንም ልዮነት የላቸውም የስም ልዮነት ካልሆነ በቀር፡፡

1 መልስ

+2 ድምጾች
ኢየሱስ የማርያም ልጅ የሆነው የኢየሱስ ስም ሲሆን ትርጓሜውም አዳኝ ማለት ነው። ክርስቶስ ግን የማዕረግ ስም ነው። ቃሉ የግሪክ ቃል ሲሆን በእብራይስጥ መሲሒ የሚባለው ቃል ነው፤ ትርጓሜውም የተቀባ ማለት ነው። እንግዲህ ክርስቶስ ወይም መሲሒ የሚባለው እግዚአብሔር ለእስራኤልና ለሰው ልጆች አዳኝ እልካለሁ ብሎ በብሉይ ኪዳን ተሰፋ የሰጠውና ወደ ምድር የሚልከው ነው። ኢየሱስ ሲወለድ ስሙን ኢየሱስ አሉት፤ ስለዚህም አገልግሎት እስከ ጀመረበት ጊዜ ድረስ የማርያም ወይም የዮሴፍ ልጅ ኢየሱስ እየተባለ ነው የሚጠራ የነበረው። በኋላ ግን አገልግሎት ከጀመረ በኋላና ተከታዮቹ እርሱ ያ በብሉይ ኪዳን እልክላችኋለሁ ብሎ እግዚአብሔር ቃል የገባው መሲሒ ወይም በግሪኩ ክርስቶስ እንደሆነ ካመኑ በኋላ ነው ክርስቶስ ወይም መሲሑ መባል የጀመረው።

ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ማለት ኢየሱስ ያ ከእግዚአብሔር የተላከው መሲሕ ወይም ክርስቶስ ነው ማለት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ስንል እንግዲህ ኢየሱስ እርሱ መሲሑ ነው ወይም ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው ማለታች ነው።

እምነታችንም የማርያም ልጅ ኢየሱስ፤ እርሱ ክርስቶስ ወይም መሲሑ እንደሆነ ነው።
Quote:
የማርቆስ ወንጌል 8
27 ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም በፊልጶስ ቂሣርያ ወዳሉ መንደሮች ወጡ በመንገድም። ሰዎች እኔ ማን እንደ ሆንሁ ይላሉ? ብሎ ደቀ መዛሙርቱን ጠየቃቸው።
28 እርሱም፦ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ከነቢያት አንዱ ብለው ነገሩት።
29 እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? ብሎ ጠየቃቸው። ጴጥሮስም፦ አንተ ክርስቶስ ነህ ብሎ መለሰለት።

Quote:
የማቴዎስ ወንጌል
16፥20 ያን ጊዜም እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ለማንም እንዳይነግሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው።
Quote:
የዮሐንስ ወንጌል
20፥31 ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።
Quote:
የሐዋርያት ሥራ
5፥42 ዕለት ዕለትም በመቅደስና በቤታቸው ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ማስተማርንና መስበክን አይተዉም ነበር።

ለዚህ ነው ስለመጨረሻው ዘመን ኢየሱስ ሲያስጠነቅቅ "እኔ ክርስቶስ ነኝ" እያሉ ብዙዎች ይመጣሉ ነው እንጂ ያለው "እኔ ኢየሱስ ነኝ" እያሉ አይደለም። ማለትም አሳሳቾቹ የሚሉት "እኔ ከእግዚአብሔር የተላክሁ መሲሑ ነኝ" ነው የሚሉት እንጂ "እኔ ከ2000 ዓመታት በፊት በምድር የነበርኩት የማርያም ልጅ ኢየሱስ ነኝ" አይሉም።
Quote:
የማቴዎስ ወንጌል
24፥5 ብዙዎች፦ እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።
Mar 16, 2011 በምሕረቱ (1,510 ነጥቦች) የተመለሰ
Mar 16, 2011 በምሕረቱ ታርሟል
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...