ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Sunday, 29 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

እውነት ነው ወይ ታቦቱ በንጉስ ሰለሞን ጊዜ ወደ ኢትዮጵ መጥዋል የሚባለው

(ጥያቄ ምልክት አልሰራ ስላለኝ ነው)
እውነት ነው ወይ ታቦቱ በንጉስ ሰለሞን ጊዜ ወደ ኢትዮጵ መጥዋል የሚባለው፣ መጽሐፍ ቅዱስ መረጃስ አለን እንዴ፣ የተሰጠውስ ለእስራኤለውን አልነበረም ወይ፣ መጣ ከተባለስ በኃላ በኢዮሲያስ ጊዜ በእስራኤል አልታየም ወይ፣የታቦቱ መጠሪያስ ቃል ኪዳን ታቦት አልነበረም ወይ ለምን ታቦተ ጽዮን ለምን ተባለ
Mar 16, 2011 መንፈሳዊ ዝናቡ (180 ነጥቦች) የተጠየቀ

3 መልሶች

0 ድምጾች
በታሪክ ደረጃ እንጂ በዚህ ጉዳይ ላይ በጽሁፍ የተፃፈ መረጃ የለም፡፡
Mar 31, 2011 እንያት ፀጋዬ (2,060 ነጥቦች) የተመለሰ
ለበለተ መረጃ ገድል ወይስ ገደል የሚለውን መፀሐፍ ያንብቡ
+1 ድምጽ
ጥያቄውን ራስዎ መልሰውታል እኮ። 2ዜና 35፡1፡4 የቃል ክዳኑ ታቦት በኢየሩሳሌም እንደነበረ እናነባለን።ሰለዚህ ታቦቱ በሰለሞን ጊዜ ወደኢትዮጵያ መጣ የሚለው ነገር ሰዎች የፈጠሩት እንደሆነ መረዳት አያስቸግርም።ለያውስ ታቦት በአዲስ ኪዳን ዘመስ ምንም ጥቅም የለውም።
እግዚአብሔር እንዲህ ብሏልና ።እነሆ ከእሥራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል ...ሕጌን በልቦናቸው አኖራለሁ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፡(ኤር 31፡31-33)
Feb 1, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
+1 ድምጽ
ሰላም

በመጸሃፍ ቅዱስ ስለታቦቱ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ምንም መረጃ የለም፡፡ ነገር ግን በተለያዩ ታሪካዊ መረጃወች እንደተጠቆመው ወደ ኢትዩጵያ ለመምጣቱ ጥናቶች ከማሳየታቸውም ባሻገር እኛጋ ነው ያለው የሚል ሃገር ፈጽሞ አልተገኝም። ኢትዮጵያ ውስጥም ከዚህ ጽላት መምጣት ጋር ተያይዞ ህገ ኦሪት እምነት መሆን የጀመረበትም ግዜ እንደነበር ታሪክዊ መረጃውች ያሳያሉ።

ንግስተ ሳባ ወደ እይሩሳሌም ወደሚገኝው የንጉስ ዳዊት ልጅ ንጉስ ሶሎሞን ለምን እና እንዴት እንደሄደች ከ መ/ቅ ያቁታል እና በ መ/ቅ ስላልሰፈረውና በታሪክ ግን ስለሚጠቀሰው የሙሴ ጽላት በ ንግስት ሳባ ልጅ ከ እስራኤል መምጣት የማውቀውን እነሆኝ።

ንግስተ ሳባ በንግስና የነበረችበት ዘመን ከክል በፊት ክ1ሺ13 ጀምሮ ለቀጣዮ 30 አመታት ነበር። ንግስናውን ያገኝችው የ አባትዋን እግር ተክታ ነበር። መጠርያ ስምዋ አዜብ/ማክዳ እንደንበርና ሳባ የሚለው ስያሜ የሳባውያን ንግስት እንደማለት ነው።የኢትዮጵያ ግዛት በዛ ዘመን በምስራቅ እስከ ማዳጋስካር እንደነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ። በዚሁ ዘመን በ እየሩሳሌም የነገሰው ንጉስ ሶሎሞን ነበር። ታምሪን የሚባል ኢትዮጵያዊ ንጋዴ ከ ኢየሩሳሌም ኢትዮጵያ በመመላለስ ይነግድ ነበር። እሱም በንጉስ ሶሎሞን ቤተመንግስት ያየውን ስረአቶች ና የ ንጉሱንም ጥበብ ለንግስቲቱ ነገራት። በጥበቡም እጅግ ትገረም ነበር። ይሄንን ጥበቡንም ለመማር ፈልጋ በታምሪን አማካኝነት የተጀመረው ግንኙንት ቀስ በቀስ ስጦታወችን በመለዋወጥ ተቀይሮ በመጨረሻም ስጦታውችን አስጭና በታምሪን መሪነት ወደ ኢየሩሳለም ሄደች።

ንጉሱም ለርስዋ እና ለ አጃቢወችዋ ልዮ አቀባበል አረገላቸው። ከግብዣው ቡሃላ ንጉስ ሰለሞን እርስዋ ወዳለችበት ዙፋን አመራ። "ጥበብህን እና ስራህን ሃገሬ ሆኜ ከሰማሁት እጅግ ይበልጣል " አለችው። የ እንግድነት ግዜዋን ጨርሳ ስትመለስ ጸንሳ ስለነበር "ልጅህ መሆኑን የምትረዳበት ምልክት ስጠኝ " በማለት የጣቱን ቀለበት ተቀብላ ወደ ሃገርዋ አመራች።

ንግስተ ሳባም ክነ አጃቢውችዋ ወደ አገርዋ ስትመለስ የ ኤርትራን ባህር ተሻግራ በሃማሴን አውራጃ ማይበላ ከተባለው ስፍራ ስትደርስ ወንድ ልጅ ወለደች።(በዘመኑ ትራንስፖርት እንደዛሬው እንዳልንበረ ልብ ይብሉ) ምኒሊክ ተወልደ ማለት ነው። አድጎም 20 አመት ሲሞላው "አባቴ ማን ነው ?" ብሎ ሲጠይቃት ነገረችው አባቱን ለማየትም ወደ እየሩሳሌም አቀና።

አባቱም ባየው ግዜ ተደሰተ ባረከውም በዛም ሶስት አመት ህገ ኦሪትን እና የመንግስት አስተዳደርን ቤእብራይስጥ ቁዋንቅዋ ሲያጠና ቆየ። ጨርሶ ሲመለስም ክ12ቱ ነገደ እስራዔል 12 ሺህ የ እብራዊ የበኩር ወንድ ለጆች(ክ እያንዳንዱ እንድ ሺህ )ማለት ነው ከተማሩትም ካህናት እንዲሁም ከ መሳፍንቱ ልጆች 22 አድርጎ ቅባአ ሜሮን በሊቀ ካህናት አስቀብቶ ልብሰ ምንግስት አሰፍቶ ከ ክርስቶስ ልደት በፊት በ 982 ወደ ኢትዮጵያ ሸኝዉ። ሚኒሊክና ሰወቹ ሲመጡ አዛሪያስ በሚባለው ሊቀ ካህን አማካኝነት በ እግዚያብሄር እጆች ተቀርጾ ለሙሴ የተሰጠው እውንተኛ ጽላት ወደኢትዮጵያ አብሮ መጣ። (በዚህ ጉዳይ ላይ አባቱ ፈቅዶለት ይዞ እንደመጣ እና ደብቆ እንዳመጣውም የጻፉ አሉ) ክዚያም ንግስተ ሳባ ተቀብላው ሚኒሊክን አነገሰችው። ንግስተ ሳባ በ ኢትዮጵያ ለመንገስዋ መ/ቅ እና ታሪክ ደግሞ ብልህ ንግስት እንደነበረች ያሳያል። በዘመኑም የሃገሪቱን ገጽታ የቀየረና የንግስናውን ዘር ከ እየሩሳሌሙ ጥበበኛ ንጉስ ጋር በማስተሳሰር ብዙሃኑ ህዝብ በጣኦት ማምልክን ትቶ በኦሪት ህግ እንዲመራ የሆነበት ታሪካዊ ሂደት ነበር።

ክላይ ላሳይ እንደሞከርኩት እና በብዙ የታሪክ ተመራማሪወች እንደተጠቀሰው የሙሴ ጽላት በሃገራችን ለመገኝቱ ብዙ ከመባሉም ባሻገር የትኛውም የአለማችን ሃገራት እኛጋ ነው ያለው ብለው አላሉም። የታሪክ ዱካን በመከተል ከእስራኤል ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣቱ የጻፉ እነ Hancock, Graham እና ሌሎቹም የሚያሳዩት ኢትዮጵያን ሃገራችንን ነው። መረጃወቹን ያገኝሁት "የ ኢትዮጵያ የ 5 ሺ አመት ታሪክ ክኖህ እስክ ኢሃዴግ" በ ፍሰሃ ያዜ ካሳ 2003 ነው። በኔ እምነት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ልያነበው የሚገባው የ ታሪክ መጽሃፍ ነው።
Feb 3, 2012 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...