ወንድማችን ወይም እህታችን ጌታ ይባርክህ
(ሽ
)
ቶሎ ቁጣና ስድብ የሚቀናቸውን በተቻለን መጠን ይህን ደግመው እንዳያደርጉ አሳስበናቸዋል። እናም ደግመው አያደርጉም የሚል እምነት አለን። ሆኖም በጣም የሚያስቸግሩ ካሉ ግን፡ እነርሱን ማገድም ይቻላል፤ ነገር ግን በጣም ከአቅም በላይ ካልሆነ በስተቀር ሰዎችን የማገድ ፍላጎቱ የለንም።
በሌላ መልኩ ግን እንደዚህ ቶሎ የሚቆጡ ሰዎች ከሌሎች ሰዎች በሚያገኙት የእርምት አስተያየት ራሳቸውን ለማየትና ለመገምገም ይረዳቸዋል ብለን እናምናለን። ፊት ለፊት ብዙዎች አይተው ያልተናገሩዋቸውን ድካማቸውን፤ እዚህ ግን እንዲያርሙ ከሌሎች አስተያየት የማግኘት እድሉ ስላላቸው፤ ይህ ይጠቅማቸዋል እንላለን።
እንግዲህ በዚህ መድረክ የምንሳተፍ የተለያየ እምነትና ባህርይ ያለን ስለሆነን፤ በታቸለ መጠን ብዙዎችን ለማስተናገድና እርስ በርስም ለመተራረም እንሞክር እንላለን።
በጣም ይረብሻል የምትሉትን አስተያየት ወይም ጥያቄ ግን
ይህን ፎርም በመጠቀም ብትልኩልን፤ አመዛዝነን ልንሰርዘው እንችላለን።
የጌታ ጸጋ ይብዛልህ
(ሽ
)