ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Sunday, 29 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

እግዚአብሄር አስቀድሞ የመረጣቸው ሲል ምን ለማለት ነው? በሮሜ 9፡ 12 ላይ ያለው ሀሳብ

Mar 20, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

3 መልሶች

+1 ድምጽ
ተመሳሳይ ሃሳብ በኤፌሶን ጥናት ላይ ተብራርቶአል። ጥናቱን እዚህ በመጫን ይመልከቱ
Mar 20, 2011 iyesus (7,430 ነጥቦች) የተመለሰ
–1 ድምጽ
እ/ር ሁሉን አዋቂ እንደመሆኑ መጠን ገና ሳንፈጠር ስለኛ ያውቃል ለዛ ነው፡፡
Apr 1, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ 1 ሪፖርት
+3 ድምጾች
እግዚአብሔር ሰዎችን ባላቸው ወይም በሚኖራቸው ብቃት ሳይሆን ሉአላዊ/ልኡል አምላክ ስለሆነ ለሚፈልገው ስራ የወደደውን የመምረጥ ሃይልም/መብትም አለው ለምሳሌ:-ወደ ሮሜ ሰዎች 9፥10-12
Quote:
10 ...ይህ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ርብቃ ደግሞ ከአንዱ ከአባታችን ከይስሐቅ በፀነሰች ጊዜ፥
11 ልጆቹ ገና ሳይወለዱ፥ በጎ ወይም ክፉ ምንም ሳያደርጉ፥ ከጠሪው እንጂ ከሥራ ሳይሆን በምርጫ የሚሆን የእግዚአብሔር አሳብ ይጸና ዘንድ
12 ለእርስዋ። ታላቁ ለታናሹ ይገዛል ተባለላት።
ቁጥር 11 ላይ እንደምናየው በጎ ወይም ክፉ ስላደረጉ ወይም ከተወለዱ በውሃላ ስለሚያደርጉ ሳይሆን የጠሪው እግዚአብሔር ውሳኔ ነው። ይህም ሃሳቡ/ስራው በሰዎች ችሎታ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በራሱ ሃይል እና ፍቃድ/ምርጫ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ያሳያል። በዚህም ከእኛ ምርጫ ውጭ የሆነ የእግዚአብሔርን ፍቃድ ምርጫ በግልጽ እናያለን።
Quote:
17 መጽሐፍ ፈርዖንን። ኃይሌን በአንተ አሳይ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ይነገር ዘንድ ለዚህ አስነሣሁህ ይላልና።
18 እንግዲህ የሚወደውን ይምረዋል፥ የሚወደውንም እልከኛ ያደርገዋል።
19 እንግዲህ ስለ ምን እስከ አሁን ድረስ ይነቅፋል? ፈቃዱንስ የሚቃወም ማን ነው? ትለኝ ይሆናል።
20 ነገር ግን፥ አንተ ሰው ሆይ፥ ለእግዚአብሔር የምትመልስ ማን ነህ? ሥራ ሠሪውን። ስለ ምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ ይለዋልን?
21 ወይም ሸክላ ሠሪ ከአንዱ ጭቃ ክፍል አንዱን ዕቃ ለክብር አንዱንም ለውርደት ሊሠራ በጭቃ ላይ ሥልጣን የለውምን?
ሮሜ ሰዎች 9፥17 ላይም እንደምናየው እግዚአብሔር ፈርዖንን ያስነሳው/ያነገሰው ክብሩን ሊገልጥበት ፈልጎ ሲሆን ፈርዖን ግን እግዚአብሔርን የማያውቅ በመሆኑ እግዚአብሔር እንደመርጠው እንኳ አያውቅም/አያምንምም።
*** ስለዚህ አስቀድሞ የመረጣቸው ሲል የ ሰዎቹን ችሎታን ቅድስናን...ወዘተ ያማከለ ሳይሆን በበጎ ፍቃዱ የጠራቸው ለማለት ነው። ይህም መብቱ መሆኑን ለማሳየት ሮሜ 9፥21 ላይም እንደምናየው ሸክላ ሠሪ ከአንዱ ጭቃ ክፍል አንዱን ዕቃ ለክብር አንዱንም ለውርደት ሊሠራ በጭቃ ላይ ሥልጣን የለውምን? ይላል መልሱም አለው!!! መሆኑ ግልጽ ነው።
አመሰግናለሁ!!!
አቤስ.
Jan 8, 2012 አቤስ (650 ነጥቦች) የተመለሰ
Jan 8, 2012 አቤስ ታርሟል
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...