ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Monday, 14 June 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ወንድምዎችና እህቶች

በመጀመሪያ እግዚያብሄር አንድ አምላክ በሶስት አካል ተሰይሟል፡ ይህም በአብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ሲሆኑ። በስልጣን አንዱን ከአንዱ ነጥሎ ማየት አይቻልም። እርግጥ ነው የእግዚያብሄር ቃል እደሚለው እየሱሰ የእግዚያብሄር ልጅ መሆኑን በመፅሀፍ ቅዱስ ተጽፋል። ይህን አምናለሁ ምክንያቱም መፅሃፍ ቅዱስ ትክክለኛ የእግዚያብሄር ቃል መሆኑን ሰለማምን ነው። ግን እየሱስ ለእግዚያብሄር ለአምላክህ ብቻ ስገድ ተብሏል ሲል ማንን ነው?እዚህ ላይ
ሉቃ 4>8/9 ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአል አለው። ሰው በእግዚአብሔር ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል ብሎ መለሰለት።
ዮሃ 10> 17 ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል።
ታዲያ ይህ ሆኖ ሳለ ሴይጣን እየሱስን በፈተነው ግዜና ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ ለአንተ እሰጠሀለሁ ባለው ግዚ እየሱስ ለአንድ አምላክህ ለእግዚያብሄር ብቻ ስገድ ተብሎ ተጽፉል ብሎ መልሷል
እየሱስ የእግዚያብሄር አንድ አካል እንደመሆኑ ለሰይጣን አንተ ለእኔ ብትስግድልኝ ይህን ሁሉ ለአንተ እሰጥህ ነበር ለምን አላለውም ወይም ይህ የምታየው ሁሉ እኔ የፈጠርኩትና የእኔ የእጅ ስራ ነው አላለውም ነበር

በሌላ በኩል በ1ኛ ቆሮ 15>27/28 ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቶአልና። ነገር ግን። ሁሉ ተገዝቶአል ሲል፥ ሁሉን ካስገዛለት በቀር መሆኑ ግልጥ ነው። ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል። ሲል ምን ለማለት ነው?በስልጣን የበላይነትና የበታችነን የሚያሳይ ይመስላል እባካችሁ አብራሩልኝ።
Jan 6, 2014 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

+1 ድምጽ
በዚህ ጉዳይ ብዙ ውይይት ከዚህ በፊት ስለተደረገበት ያንን ብታነብብ መልካም ነው። ለማንበብ እዚህ ተጫን
Jan 6, 2014 ስም-አልባ የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...