ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 27 July 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ዘፈን ማለት ምን ማለተ ነው…. አሁንስ ዘፈን ብለን የምንጠራው እርሱ ትክክለኛ ዘፈን ነውን?

Apr 25, 2014 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

2 መልሶች

0 ድምጾች
ወዳጃችን፤
ይህ መንፈሳዊ ጉዳዮችን መወያያ መድረክ ስለሆነና ጥያቄህን ማስተናገድ ስለማይችል
የዘፈን ጥያቄህን ይዘህ የዘፈን ባለሙያዎች ጋ እንድትሄድ እመክርሃለሁ።
Apr 28, 2014 ስም-አልባ የተመለሰ 1 ሪፖርት
0 ድምጾች
ወዳጄ ነገሩ እንዲህ ነው። ጉዳዩ ሁሉ የትርጉም ችግር ነው።

ለምሳሌ
ሮሜ 13፡13 "በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤
Quote:
ዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤"

1ኛ ጴጥሮስ 4፡3 "የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።"

እዚህ ጋር ዘፈን የሚለውን የአማርኛ ቃል በእንግሊዝኛ ትርጉሞች ላይ ተመልከታቸው።
KJV "rioting"; American Standard Version: "revelling"; Byington: "wild parties" በማለት አስቀምጠዋል።

በሌላ መልኩ ደግሞ
Quote:
በመዝሙር 150፡4 ላይ እግዚአብሔርን "በከበሮና በዘፈን አመስግኑት በአውታርና በእምቢልታ አመስግኑት።"

መዝሙር 149፡3 "ስሙን በዘፈን ያመስግኑ፥ በከበሮና በመሰንቆም ይዘምሩለት።"

ኤርምያስ 31፡4 "የእስራኤል ድንግል ሆይ፥ እንደ ገና እሠራሻለሁ አንቺም ትሠሪያለሽ እንደ ገናም ከበሮሽን አንሥተሽ ከዘፋኞች ጋር ወደ ዘፈን ትወጫለሽ።"

እነዚህኑ ጥቅሶች በሌሎች ትርጉሞች ላይ ስናያቸው፡
KJV: "dance"; ASV: "dance"; Todays English Version: "dancing" . . . .

ታዲያ ምን ተረዳን? መጽሐፍ ቅዱስ (በዘመኑ አጠራር ዘፈን ወይም ሙዚቃ) ኃጢአት ነው አይልም። የተለያዩ ትርጉሞች ላይ እንዳየነው ግን "ፈንጠዝያ"፣ "ከልክ ያለፈ ጭፈራ"፣ እንዲሁም አሁን በየከተማው እንደምናየው ያሉ የምሽት ጭፈራ ቦታዎች መገኘት ከሃጢአት እንደሚፈርጃቸው መረዳት ይቻላል።

በጥቅሉ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱሳችን "ዘፈን" ሲል ከዳንስና ጭፈራ ጋር የተያያዘ ሃሳብ አለው። ለዚህ ነው በመዝሙር መጽሐፍ ላይ ያየናቸው እግዚአብሔርን በዘፈን (ማለትም በሽብሸባ) ማመስገን እንደሚገባን የተጠቀሰው።

ጠያቂ "ዘፈን" ስትል ሙዚቃን ማለትህ እንደሆነ ግልጽ ነው። በዚህ ጉዳይ መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው ምንም ነገር የለም። ስለዚህ ፍርዱ እኛው ጋር ነው ያለው። ማንንም እንዲህ አድርግ አታድርግ ማለት አንችልም። አብዛኞቹ የዘመኑ ሙዚቃዎች ብልሹ ሥነ-ምግባርን የሚያበረታቱ በመሆናቸው፣ እኔ በበኩሌ ባንጠቀምባቸው እመርጣለሁ። አሁንም ውሳኔው ለራስ ነው። እንደ መስፈርት ግን የምናዳምጠውን ሙዚቃ "ኢየሱስ ቢሰማኝ ምን ይሰማው ይሆን" ብለን ብንለካው መልካም ይሆናል ብዬ አምናለሁ።


ሰላም
May 3, 2014 ስም-አልባ የተመለሰ
በጣም ነው ማመሰግነው ! ትክክለኛውን መልስ መልሰህልኛል . ጌታ ይባርክህ!!!!
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...