ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Monday, 14 June 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ስነፍጥረት በስንት ቀን ተጠናቀቀ??

May 15, 2014 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

+1 ድምጽ
ብዙ እምነቶች ስነ-ፍጥረት በስድስት (የምናውቃቸው) ቀናት ውስጥ ተጠናቀቀ የሚለውን ሃሳብ መውሰድን ይመርጣሉ። አንዳንዶች ደግሞ ስድስቱ የፍጥረት ቀናት ረጅም ጊዜን ሊያመለክቱ ይችላሉ ብለው ያምናሉ። እውነታው ምንድነው?

የመጽሐፍ ቅዱስን ዘገባ ከንቱ ለማድረግ የሚራወጡ ሳይንቲስቶች ስልጣኔ የነበረባቸውን ዘመናት 20 ሺ እናም ከዚያ በላይ እንደነበረ ሲተርኩ ይሰማል። በተቃራኒው ደግሞ ለእውነት የቆሙ የመስኩ ባለሙያዎች ስልጣኔ ከአምስትና ስድስት ሺህ ዓመት እንደማይበልጥ ማስረጃዎች እንደሚጠቁሙ ይናገራሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ደግሞ የሰው ልጅ ታሪክ ስድስት ሺህ ዓመታት እድሜ እንዳለው እናነባለን (አስልተን ልንደርበስትም እንችላለን)

ስልጣኔ ከአምስትና ስድስት ሺህ ዓመት እንደማይበልጥ አጥንተው የነገሩን ባለሙያዎች ስለ ምድር ሲጠየቁ ግን ተመሳሳይ የማስያ ዘዴን ተጠቅመው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዓመታት እድሜ እንዳላት ይነግሩናል።

ይህንን ከግምት በማስገባት መጽሐፍ ቅዱስን እስቲ እንመርምር።

Quote:
መዝሙረ ዳዊት 90፥4 "ሺህ ዓመት በፊትህ እንዳለፈች እንደ ትናንት ቀን፥ እንደ ሌሊትም ትጋት ነውና።"
Quote:
2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፥8 "እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመትሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።"

በመሆኑም በነዚህ ጥቅሶች መሰረት አንድ ቀን በጌታ ዘንድ ብዙ ሺ ዓመታትን ሊያጠቃልል እንደሚችል መረዳት እንችላለን።

የፍጥረት ቀናትን ጠቅለል አድርጎ በዘፍጥረት 2፡4 ላይ ያለውን ቃል እንመልከት፡
Quote:
ኦሪት ዘፍጥረት 2፡4 "እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው።"

እዚህ ጥቅስ ላይም ስድስቱን የፍጥረት ቀናት እንደ አንድ ቀን ሲወስዳቸው እናነባለን።

ቀንና ሌሊትስ በአንደኛው ቀን መፈጠራቸው ምን ያሳየናል? - ዘፍጥረት 1፡5

በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ ከእውነተኛው ሳይንስ ጋር ይስማማል ብንል የተሳሳትን አይመስለኝም። - በጭፍን እምነት የተያዝን ካልሆንን በቀር።

እንደው የከረረ የሒሳብ ስሌት ውስጥ አንግባና ስነፍጥረት ብዙ ሚሊዮን ዓመታትን ፈጅቷል የሚለውን ሃሳብ መጽሐፍ ቅዱስ አይቃረንም።

ሰላም
May 16, 2014 ኦፍቲ (1,250 ነጥቦች) የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...