ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 26 May 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

የጊታ ደምድ እንዲት መስማት እችላሎሁኝ

የጊታ ደምድ እንዲት መስማት እችላሎሁኝ? ቃሉን እዲት ላጥናው/ ገታ ማወቅ በጣም ነው መፈልገው ምን ላድርግ?
Apr 19, 2011 መንፈሳዊ ሉሲ2011 (120 ነጥቦች) የተጠየቀ

2 መልሶች

0 ድምጾች
ጌታ በተለያዮ መንገዶች ይናገረናል ለምሳሌ በፀሎት መልስ፣ በሰዎች አማካይነት፣ በሚገጥሙን ነገሮች፣ ብቻ በተለያዩ መንገዶች ይናገረናል ችግሩ እኛ ስለማናስተውለው ነው፡፡ እዚህ ላይ ግን መጠንቀቅ ያለብን የሰይጣንም የእግዚሐብሔርም ነገር ስላለ ሁለቱን ለይተን እና አጣርተን መስማት አለብን፡፡
Apr 20, 2011 እንያት ፀጋዬ (2,060 ነጥቦች) የተመለሰ
0 ድምጾች
ሰላም ሉሲ

የጌታ ሰላም ይብዛልሽ!

በቅድሚያ እግዚአብሔር ሰዎችን በአዲስ ኪዳን ሰዎችን የሚመራው በትንቢት ሳይሆን በውስጣችን ባለው በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት እንደሆነ መገንዘብ ይኖርብናል። ቃሉም በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ እንጂ በትንቢት የሚመሩ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው አይልምና።
Quote:
ወደ ሮሜ ሰዎች 8
14 በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።
15 አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና።
16 የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።

ከላይ ባለው ክፍል እንደምንመለከተው፤ የእግዚአብሔር ልጆች የሚመሩት በውስጣቸው ባለው የልጅነት መንፈስ በሆነው በመንፈስ ቅዱስ ነው። ቁጥር 16 ላይ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ እንዴት እንደሚመራቸው ተጽፎአል። ይህም መንፈስ ቅዱስ ለመንፈሳቸው በመመስከር ነው።

ማለትም ትልቁ የመንፈስ ቅዱስ ምሪት በውስጣችን በሚሰጠን የእርሱ ምስክርነት ነው። አንድ ምሳሌ ልጠቀም። የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነሽና ድነትን እንዳገኘሽ እርግጠኛ ነሽ? መልስሽ አዎ ከሆነ፤ ታዲያ ይሄንን እውነት ማን ነገረሽ? የአንቺን መዳን ያወቅሽው በትንቢት ነው? ነብይ መጥቶ ሉሲ ከዛሬ ጀምሮ ድነሻል ስላለሽ ነው? አይመስለኝም። ታዲያ ይሄን የሚያል ትልቅ እውነት ማለትም አንቺ መዳንሽን ማን ነገረሽ?

መልሱ በውስጥሽ ያለው የመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት ነው።
Quote:
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5
10 በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክር አለው፤ በእግዚአብሔር የማያምን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል።

ስለዚህ ከሁሉ አስቀድመን መረዳት ያለብን፤ መንፈስ ቅዱስ በውስጣች ስለሚኖር የሚመራንም በውስጥ በሚሰጠን ምስክርነት ነው።

ሌላው አንዳንዴ እግዚአብሔር በትንቢት፣ በሕልምና በራእይ ወዘተ ሊናገረን ይቻላል። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር እንዲ ባለ ነገር የተናገረው የክርስቶስ ወንጌል ወይም የእግዚአብሔር መንግሥት አገልግሎትን በተመለከተ ወይም ከዚያ ጋር በተያያዘ ነው። እግዚአብሔር በዚህ ሁኔታ የተናገረባቸውን ክፍልች በሐዋርያት ሥራ ስናነብ ሁሉም ማለት ይቻላል እግዚአብሔር የተናገረው ከመንግስቱ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ነው እንጂ፤ የእያንዳንዱን አማኝ የግል ኑሮ፣ ትዳር፣ ሥራ ወዘተ ለመምራት አይደለም።

ሌላው እግዚአብሔር የሚመራን በእምነት ነው። ማለትም እምነታችን እያንዳንዱን የእግዚአብሔርን ፈቃድ አውቀን በማድረግ ችሎታችን ላይ ሳይሆን፤ ፈቃዱንም እንኳን ባናውቅ እግዚአብሔር ፈቃዱን እንድናደርግ በማናውቀውም መንገድ ቢሆን ይከለክለናል በሚል እምነት ነው። ስለዚህ የእግዚአብሔርን ድምጽ በመስማት ችሎታችንም ይሁን፤ ፈቃዱን ሰምተን በማደረግ ችሎታችን አንደገፍም። ነገር ግን ፈቃዱን ብናውቅም ባናውቅም እግዚአብሔር እርሱ በታላቅ ቸርነቱ ወደ ፈቃዱ ይመራናል፣ ይጠብቀናል በሚል በኛ ችሎታ ላይ ሳይሆን በእግዚአብሔር ችሎታ ላይ ባለ እምነታችን ነው የምንመራው።

የዮሴፍንና እንዲሁም የብዙዎችን የእግዚአብሔር ሰዎች ስንመለከት የእግዚአብሔርን ፈቃዱን ሁሉ በሕይወታቸው ተረድተውት አይደለም የኖሩት፤ ቁም ነገሩ ግን ቢገባቸውም ባይገባቸውም እግዚአብሔር በጥበቡ ፈቃዱን በእነርሱ አድርጎ አልፈዋል።

ለምሳሌ እንደ ጳውሎስን በአዲስ ኪዳን ስንመለከት ወደ አንድ አገር ወንጌልን ለመስበክ የሚነሱት በመጀመሪያ ሙሉ ለሙሉ ምሪት ጠብቀውና አግኝተው ሳይሆን በእምነት ነው የሚወጡት። ብንስት ጌታ ይመልሰናል እኛ ግን በቅንነት ወደ መሰለን አገር ሄደን ወንጌል እንሰብካለን በሚል ነው የሚወጡት። ብዙ ጊዜም ትክክል ነበሩ፤ ሆኖም አንዳንዴ ወደ አንድ አገር ወንጌልን ለመስበክ ሲነሱ መንፈስ ቅዱስ ግን ሲከለክላቸው እናያለን።
Quote:
የሐዋርያት ሥራ
16፥6 በእስያም ቃሉን እንዳይናገሩ መንፈስ ቅዱስ ስለ ከለከላቸው በፍርግያና በገላትያ አገር አለፉ፤
16፥7 በሚስያም አንጻር በደረሱ ጊዜ ወደ ቢታንያ ይሄዱ ዘድን ሞከሩ፥ የኢየሱስ መንፈስም አልፈቀደላቸውም

ስለዚህ እነ ጳውሎስም ቢሆኑ በሁሉ ጉዳይ የእግዚአብሔርን ፈቃድና ምሪት አውቀው አይደለም የሚሄዱት የነበረው፤ ነገር ግን በእምነት ነበር። የእግዚአብሔርን ፈቃድ በማወቅ ላይ በተመሰረተ የራሳቸው ችሎታ ሳይሆን ፈቃዱን ቢስቱ እንኳን ወደ ፈቃዱ ሊያስገባ በሚችል በእግዚአብሔር ችሎታ ላይ በተመሠረተ እምነት ነበር የሚመሩት።

ስለዚህ በሁሉ ጉዳይ ፈቃዱን ለማወቅ መጨነቅ የለብንም። በቅንነት በቃሉ የተገለጠውን ፈቃዱን እያደረግንና ሕይወታችንን እንደቃሉ እየመራን እንኖራለን። እርሱም ፈቃዱን አወቅነውም አላወቅነውም ወደ ፈቃዱ ግን ያስገባናል። ቁምነገሩ ያለው ፈቃዱን ማወቁ ላይ ሳይሆን ፈቃዱ በሕይወታችን መፈጸሙ ላይ ነው። ለዚያ ደግሞ ብዙ ጊዜ የእኛ እውቀት አያስፈልግም። እግዚአብሔር ብዙውን ፈቃዱን ሳያማክረንም በሕይወታችን ሊፈጽም የሚችል አምላክ ነውና።

በዘመናችን ብዙዎች ቃሉን ካለማወቅና በእግዚአብሔር ቸርነትና ችሎታ ላይ እምነት ከማጣት የተነሳ በመጽሐፍ ቅዱስ በፈጹም በሌለ ሁኔታ፤ ለዕለት ተለት ኑሮአቸው ነብያትና ትንቢትን ሲፈልጉ ይታያል። ሕይወታቸውም በትንቢት ሱስ የተያዘ እስኪመስል ድረስ አይናቸውን ከእግዚአብሔር ቸርነትና ችሎታ አንስተው በትንቢቶች ላይ አድርገዋል። በሚያሳዝን ሁኔታ የሐሰተኛ ትንቢቶችና ነብያቶች ሱሰኞችና ባሪያዎች ሆነዋል። ይህ ጨርሶ የጌታ ፈቃድ አይደለም። የእግዚአብሔር ልጆች በውስጣቸው ባለ በእግዚአብሔር መንፈስና በቸርነቱ ባለ እምነታቸው እንዲመሩ እንጂ ጥንቆላን በሚመስል መልኩ የሐሰት ትንቢቶችና ነብያቶች ባሪያዎች እንዲሆኑ በፍጹም መጽሐፍ ቅዱስ አያስተምርም።

የማጠቃለያ ምክር
ውስጥሽ የማይረብሽሽንና ሕሊናሽም የማይወቅስሽን ነገሮች ልዩ ምሪት ሳትጠብቂ አድርጊ፤ እግዚአብሔር ልዩ ምሪት የሚያስፈልግሽ ከሆነ እርሱ ራሱ በሚገባሽ መንገድ ይናገርሻል ስለዚህ ብዙ አትጨነቂ። በምታልፊበት መንገድ ሁሉ ፈቃዱ ቢገባሽም ባይገባሽም አምላክሽ ወደ ቀና መንገድ እንደሚመራሽና ሊያስተካክልሽ እንደሚችል በእርሱ ችሎታ እምነሽ በእምነት ተመላለሺ። የሚከብደሽና ከአቅምሽ በላይ የሚሆን ነገር ሲመጣ እንደ ሐና ከልብሽ ወደ አምላክሽ ጩሂ እርሱ ይሰማሻል።

የጌታ ሰላም ይብዛልሽ!
Apr 21, 2011 በምሕረቱ (1,510 ነጥቦች) የተመለሰ
Apr 21, 2011 በምሕረቱ ታርሟል
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...