ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄና መልስ
Email this page to a friend Printer-friendly   Saturday, 23 September 2017
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

ለመላእክት ስግደት ይገባል ወይስ አይገባም አብራሩልኝ

ለመላእክት ስግደት ይገባል ወይስ አይገባም አብራሩልኝ
6 ዓመታት በፊት መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
ኦሪት ዘጸአት 20
1 እግዚአብሔርም ይህን ቃል ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ።
2 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ።
3 ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።
4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ።
5 አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ
6 ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና።
የዮሐንስ ራእይ
19፥10
ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና አለኝ።

22፥9
እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ።

6 መልሶች

0 ድምጾች
በፍሱም ለምላከት ሰግደት አይግባም ምክንያቱም የእግዝያብሃር ካል ሰናግር ገታ በመላእክት እንኩዋን እንዳማይተማመን ይናግራል በእዮብ ከፍል ላይ በለላ በኩል ደግሞ እ\ር ከነ በቀር በሰማይ ይሁን በምድር ለለላ አትሰግድ ይላል.ገታ ይባርካቹ
6 ዓመታት በፊት የክይዳን ልጅ (190 ነጥቦች) የተመለሰ
ለመሆኑ የት ቦታ ነው ጌታ በመላእክት እንኩዋን እንደማይተማመን ተናገረው የት ቦታ ነው?
ካላወቃችሁ ጠይቁ ተሳስታችሁ አታሳስቱ ከብዙ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የምትቀመጥብኝ አህያህ አይደለሁምን? በውኑ እንዲህ አደርግ ዘንድ ልማዴ ነበረን? አለችው። እርሱም፦ እንዲህ አላደረግሽብኝም አላት።እግዚአብሔርም የበለዓምን ዓይኖች ከፈተ የእግዚአብሔርን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ ሰገደም፥ በግምባሩም ወደቀ። ኦሪት ዘኍልቍ 22 ከዚህ የምንረዳው ለምላእክት ሰግደት እንደሚገባነው ስለዚህ እራሳችሁ ተሳስታችሁ የማያውኩትን(ህጻናትን) ባታሳስቱ መልካም ነው ። እንዲህ የሚል ተጥጽፍውልና
የማቴዎስ ወንጌል
18፥6 በእኔም ከሚያምኑ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ፥ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር መስጠም ይሻለው ነበር። ስለዚህ ዝም ብሎ በደፈናው መልስ መስጠት አያስፈልግም
ሰላም ቱቱ
መልስ የሰጠችው ልጅ እኮ መልስ ከሰጠች 7 ወራቶች ሆነዋል፤ እናም አሁን አንቺ የምትጽፊውን ላታነብበው ትችላለች። ስለዚህ ፈጥነሽ አትክሰሺ። ደግሞ ያ የጻፈውን ሰው ራሱኑ መናገር ነው እንጂ ያልጻፈውንም ጨምሮ "እናንተ" እያሉ በጅምላ ማጠቃለል ተገቢ አይመስለኝም። ልጅቱ ለጻፈችው ሌላ ሰው ምን አግብቶት ነው አብሮ የሚወቀሰው?

በዚህ ላይ ልጅቱ እኮ ኢዮብ መጽሃፍ ላይ እንደሆነ ገልጻለች፤ በደንብ አንብቢው የጻፈችውን። እኔ እንደሚመስለኝ የሚከተለውን ክፍል ማለቷ ሳይሆን አይቀርም፦
Quote:
መጽሐፈ ኢዮብ
4፥18 እነሆ፥ በባሪያዎቹ አይታመንም
መላእክቱንም ስንፍና ይከስሳቸዋል፤
ኽረ እንዲት ነው ብደንብ የሚነበበው፡ የሚለው እኮ "በባሪያዎቹ አይታመንም" እንጂ በመላእክቱ አይታመንም አይልም። እንደሚመስለኝ እያሉ ያልተጻፈውን ባናስተላልፍ መልካም ነው። ተባረኩ
ሰላም ለሁላችውም ይሁን ።
አንድ ነገር መጠየቅ ፈልጋለው ለመላእክት ስግደት አይገባም ቃልን
(ራእይ 19፡10)ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም። እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና አለኝ። እንዲእት በብሉ ኪዳን ያለው መላእክት ስግደት ተቀበለ ?
(ኢያሱ 5፡14-15) እርሱም። አይደለሁም፤ እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቼአለሁ አለ። ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና። ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድር ነው? አለው።
የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃ ኢያሱን። አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ አለው። ኢያሱም እንዲሁ አደረገ።

እስቲ እገሩኝ ከሁለቱ ማነው ያጠፋው ? ያጠፋውስ ተቀጣ?
ሐዋርያው ዮሐንስ ክልክል እንደሆነ አያቅም ነበር ? ተሳስቶ ከሆነ በራእይ 19፡10 እንዴት እያወቀ ደግሞ ይሰግድለታል ? በግድ ላምልክ እያለው ነው ? ካተፋ ደሞ አልዳነም ማለት ነው ? ድኛል ካልን ደሞ እኛም በንሰግድ አጥያት አይደለም ማለት ነው።
አትሳሳቱ ዮሐንስ ሕጉን በደብ ያቃል 1ኛ እስራኤላው ነው 2ኛ የጌታ ተማሪ ነበር 3ኛ መንፈስ ቅዱስን ተከብሎ በትምህርት ላይ በምንም ታምር አይሳሳትም ተሳሳተ ቃልን በወንጌሉም በመልክቱም በራእይ መጽሐፍም የጠጻፈውን እንዴት እንከበለዋለን ዛረ ሁሉም ከሱ በልጠው ነው መስገድ ይከለከላል ሚሉት?
+1 ድምጽ
በጥንት ዘመን ለሰዎችም ይሁን ለመላእክት ክብር በመስጠት መስገድ የተለመደ ነገር ነበር። ይሄ ግን አምልኮ ሳይሆን ልክ በአሁን ዘመን ትልቅ ሰው ወደ ቤት ሲገባ ሰዎች ለአክብሮት እንደሚቆሙት አይነት ነው።

የአምልኮ ስግደት ግን በአዲስ ኪዳን በግልጽ ተከልክሏል። የሚከተለቱን ሁለት ጥቅሶች አንብብ።
Quote:
የዮሐንስ ራእይ 22
8 ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ።
9 እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ።

የዮሐንስ ራእይ
19፥10 ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና አለኝ።

ልክ እንደ መልአኩ በተመሳሳይ ሁኔታ ሐዋርያው ጳውሎስና በርናባስም የክርስቶስን የመዳን ቃል ልስጥራን በተባለ ሥፍራ ሲሰብኩና በዚያም አንድ ሽባ ሲፈወስ ያዩ የልስጥራን ነዋሪዎች ለእነ ጳውሎስ ሊሰግዱላቸውና እነርሱን ሊያመልኳቸው ሲሞክሩ፤ እነ ጳውሎስ ልብሳቸውን ሳይቀር በመቅደድ ይሄንን ነገር በከፍተኛ ሁኔታ እንደተቃወሙት በሐዋርያት ሥራ ላይ እናነብባለን።

Quote:
የሐዋርያት ሥራ 14

8 በልስጥራንም እግሩ የሰለለ፥ ከእናቱም ማኅፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ፥ ከቶም ሄዶ የማያውቅ አንድ ሰው ተቀምጦ ነበር። 9 ይህም ሰው ጳውሎስ ሲናገር ይሰማ ነበር፤ እርሱም ትኵር ብሎ ተመለከተውና ይድን ዘንድ እምነት እንዳለው ባየ ጊዜ፥ 10 በታላቅ ድምፅ። ቀጥ ብለህ በእግርህ ቁም አለው። ብድግ ብሎም ተንሥቶ ይመላለስ ነበር። 11 ሕዝቡም ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በሊቃኦንያ ቋንቋ። አማልክት ሰዎችን መስለው ወደ እኛ ወርደዋል አሉ፤ 12 በርናባስንም ድያ አሉት፤ ጳውሎስንም እርሱ በመናገር ዋና ስለ ነበረ ሄርሜን አሉት። 13 በከተማውም ፊት ቤተ መቅደስ ያለው የድያ ካህን ኮርማዎችንና የአበባን አክሊሎች ወደ ደጃፍ አምጥቶ ከሕዝቡ ጋር ሆኖ ሊሠዋላቸው ወደደ። 14 ሐዋርያት በርናባስና ጳውሎስ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቡ መካከል እየጮኹ ሮጡ፥ 15 እንዲህም አሉ። እናንተ ሰዎች፥ ይህን ስለ ምን ታደርጋላችሁ? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፥ ከዚህም ከንቱ ነገር ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ዘወር ትሉ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን። 16 እርሱ ባለፉት ትውልዶች አሕዛብን ሁሉ በገዛ ራሳቸው ጐዳና ይሄዱ ዘንድ ተዋቸው። 17 ከዚህም ሁሉ ጋር መልካም ሥራ እየሠራ፥ ከሰማይ ዝናብን ፍሬ የሚሆንበትንም ወራት ሲሰጠን፥ ልባችንንም በመብልና በደስታ ሲሞላው ራሱን ያለ ምስክር አልተወም። 18 ይህንም ብለው እንዳይሠዉላቸው ሕዝቡን በጭንቅ አስተዉአቸው።
6 ዓመታት በፊት በቃሉ (2,230 ነጥቦች) የተመለሰ
6 ዓመታት በፊት የታረመ በቃሉ
1ኛ የሐዋርያት ሥራ 14
ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በሊቃኦንያ ቋንቋ። አማልክት ሰዎችን መስለው ወደ እኛ ወርደዋል አሉ፤ 12 በርናባስንም ድያ አሉት፤ ጳውሎስንም እርሱ በመናገር ዋና ስለ ነበረ ሄርሜን አሉት። 13

እዚ ምናየው የአምልኮት ስግደት ነው ለዚም ነው ያልተቀበሉት ።
በደንብ ቃነበብንው ግልጽ ነው .

1 አማልክት ሰዎችን መስለው ወደ እኛ ወርደዋል ይላሉ
2 በርናባስንም ድያ አሉት፤ ጳውሎስንም እርሱ በመናገር ዋና ስለ ነበረ ሄርሜን አሉት
ዲያስ እና ሄርሜን ግሪኮች ከሚያመልኳቸው አማልክት ነበሩ ። እነሱ ሰው መስለው ወረዱ ብለው ነው ። ክ12 አማልክት 2 ነበሩ

2ኛ የሐዋርያት ሥራ 10፤ 25-26
ጴጥሮስም በገባ ጊዜ ፤ተገናኝቶ ከእግሩ በታች ወደቀና ሰገደለት።
ጴጥሮስ ግን። ተነሣ፤ እኔ ራሴ ደግሞ ሰው ነኝ ብሎ አስነሣው።

3ኛ ራእይ 19፤10
ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና አለኝ።

ከላይ የምንጠቅሳቸው ጥቅሶች የክብር ስግደትን የሚከለክሉ አይደሉም ።

1ኛ ህዝቡ የአምልኮት ስግደት ሊስግድላቸው ስለነበር አልተቀበሉም ምክንያቱም ይህ ጣወት ማምለክ ነው

2ኛ ጴጥሮስ ትሁት ስለሆነ ከአንድ ባለስልጣን ስግደትን አልጠቀበለም ፤ቆርኔሌዎስም ጴጥሮስ የዕብራውያንን እምነት ሰለሚያሁቅ እና እሁነተኛውን አምላክን ይፈራ ስለነበር ጴጥሮስ በማክበር ልስግድለት ነበር

3ኛ ዮሐንስ ተሳስቶ ጌታ መስሎት የአምልኮ ስግደት ሊያከርብ ከነብር በትክክል መልአኩ ስግደቱን አልጠቀበለም እንደ በርናባስ እና ጳውሎስ
ለአምላክ እንጂ ለፍጡር አምልኮት አይገባም ።
ዮሓንስ ግን ማን እንደሆነ እያወቀ ከሰገደ ስግደት የአክብሮት እንደሚፈቀድ ነው ሚያሳየው
ዮሐንስ የብያይስጥ ነበር የብሉን ኪዳን ሕግ ብደብ ነው ሚያቀው ጌታም የሚወደው ደቀመዛሙርት ነበር ወንድልን መልክቶችን እና ራእይ የጻፈ ስሆን የውነተኛው አምላክ አማኝ ለጣወት አይሰግደም
ራእይ 22፤8
ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ።

ደግሞ ማን እንደሆነ እያወቀ ለሁለተኛ ጊዝ ሊስግድ ወደቀ መልአኩም ትውት ስለሆነ መልሶ ከለከለው ልክ ጴጥሮስ ቆርኔሌዎስን እንደከለከለ
ምን ትላላቱ ዮሓንስ አቲያስ ሰራ ለዛዉም ሁለቴ ስልዚ አልዳነም ማልት ነው ከዳነስ እኛ ለምድነው ማንድነው?

ትያቅ
ራእይ 19፤10 22፤8 ላይ ወይስ
ኢያሱ 5 ፤13-15 ላይ ያለው መልአክ ነው አቲያት የሰራው?

ስግደት ማምለቅ ብቻ ቢሆን ጌታ ራእይ 3፤9-10 ላይ ለሰው እንዲ ሰግዱ አያዝም ነበር ።
0 ድምጾች
በፍፁም እንደማይገባቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ተገልፆል፡፡ ምክንያቱም እሱ ቀናተኛ አምላክ ነውና፡፡ ዘፀ 20 እና ዘዳ 4 አንብበው፡፡
6 ዓመታት በፊት እንያት ፀጋዬ (2,060 ነጥቦች) የተመለሰ
የእግዚአብሔርም መልአክ ከወይኑ ቦታዎች መካከል በወዲያና በወዲህ ወገን ግንብ በነበረበት በጠባብ መንገድ ላይ ቆመ።አህያይቱም የእግዚአብሔርን መልአክ አይታ ወደ ቅጥሩ ተጠጋች፥ የበለዓምንም እግር ከቅጥሩ ጋር አጣበቀች እርሱም ደግሞ መታት።የእግዚአብሔርም መልአክ ወደ ፊት ሄደ፥ በቀኝና በግራ መተላለፊያ በሌለበት በጠባብ ስፍራ ቆመ። አህያይቱም የእግዚአብሔርን መልአክ አየች፥ ከበለዓምም በታች ተኛች በለዓምም እጅግ ተቈጣ፥ አህያይቱንም በበትሩ ደበደባት።እግዚአብሔርም የአህያይቱን አፍ ከፈተ፥ በለዓምንም። ሦስት ጊዜ የመታኸኝ ምን አድርጌብህ ነው? አለችው።በለዓምም አህያይቱን፦ ስላላገጥሽብኝ ነው በእጄስ ሰይፍ ቢኖር አሁን በገደልሁሽ ነበር አላት።አህያይቱም በለዓምን፦ ከብዙ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የምትቀመጥብኝ አህያህ አይደለሁምን? በውኑ እንዲህ አደርግ ዘንድ ልማዴ ነበረን? አለችው። እርሱም፦ እንዲህ አላደረግሽብኝም አላት።እግዚአብሔርም የበለዓምን ዓይኖች ከፈተ የእግዚአብሔርን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ ሰገደም፥ በግምባሩም ወደቀ። ኦሪት ዘኍልቍ 22 ከዚህ የምንረዳው ለምላእክት ሰግደት እንደሚገባነው ስለዚህ እራሳችሁ ተሳስታችሁ የማያውኩትን(ህጥጻናትን) ባታሳስቱ መልካም ነው ። እንዲህ የሚል ተጥጽፍውልና
የማቴዎስ ወንጌል
18፥6 በእኔም ከሚያምኑ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ፥ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር መስጠም ይሻለው ነበር።

የማርቆስ ወንጌል
9፥42 በእኔም ከሚያምኑት ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለው ነበር።

የሉቃስ ወንጌል
17፥2 ከእነዚህ ከታናናሾች አንዱን ከማሰናከል ይልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይጠቅመው ነበር።
ይህ ለናንተ እንዳይሆን ተጠንቀቁ።
ሰላም ወገኔ

አንደኛ በጥንት ዘመን፤ በእኛም አገር በሃይለ ስላሴም ዘመን ለተከበሩ ሰዎች መስገድ የተለመደ ነበር። ይሄ ማለት ግን የሚሰግዱት ሰዎች የሚሰገድለትን እያመለኩት ግን አይደለም። እያከበሩት እንጂ። በአሁኑ ዘመን ግን ሰዎች ለመላእክት የሚሰግዱት ለተከበረ ሰው እንደሚሰግዱት ሳይሆን አምልኮ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ስህተት ነው።

ከዚህ በተጨማሪ በለዓም የጻድቅ ሰው ምሳሌ ሊሆን አይችልም። በለዓም ማለት እግዚአብሔር አንተ ከላይ እንደጠቀስከው መላእክ ልኮ እስራኤላውያንን እንዳይረግም ቢከለክለውም፤ ይህንን ጥሶ ለገንዘብ ሲል እስራኤላውያንን ለመርገም የሞከረ ሰው ነው።

ያ ብቻ አይደለም፡ መራገሙ አልሳክላት ሲል ንጉሱን ባላቅ ለእስራኤላውያን ሴቶችን እንዲያቀርብና እንዲያመነዝሩና ለጣኦት እንዲሰዉ የመከረ በዚህም ምክንያት በአንድ ቀን ከእስራኤላውያን ከ20 ሺህ ሰዎች በላይ በእግዚአብሔር መቅሰፍት እንዲሞቱ ያደረገና በመጨረሻም በእነ ሙሴ ትዕዛዝ በእስራኤላውያን የተገደለ ሰው ነው።

በአዲስ ኪዳንም ቢሆን፤ እርሱ እስራኤላውያን እንዲሴስኑና ጣኦትን እንዲያመልኩ ያደረገበት ዘዴ "የበለዓም ትምህርት" በመባል የሚታወቅ የሰይጣን ዘዴ ነው።
Quote:
የዮሐንስ ራእይ
2፥14 ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ።

ስለዚህ ይህ በእግዚአብሔር ቃል የተጠላ ሰውን እንደ ምሳሌ አድርገህ ወስደህ እርሱ ያደረገውን እኛም እንዳድርግ ማለት መሳሳት ነው የሚሆነው።

ከዚያ ይልቅ ግን የክርስቶስ ሐዋርያ የሆነው የዮሐንስን ሕይወት ምሳሌ አድረገን ከእርሱ መማሩ ይበጃል። እርሱ በአዲስ ኪዳን ዘመን ለመልአኩ ሲሰግድ መልአኩ ከአንዴም ሁለቴ እንዳስጠነቀቀው በራእይ መጽሐፍ ተጽፎአልና።
Quote:
የዮሐንስ ራእይ 22
8 ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ።
9 እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ።

የዮሐንስ ራእይ
19፥10 ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና አለኝ።
ለመላእክት የሚሰግደው ሰው ለአክብሮት ነው እያለ እመሰከረ፡ እንዳንተ ያለው ሰው ግን እያመለክ ነው የምትሰግደው ይላል። እየሰገደ ያለው ሰው ስለራሱ መናገር ይችላል ። አንተ ግን ሰውየው ያላለው እያልክ በሃሰት ትመሰክራለ።
ለዚህ ነው ለዚያ ነው ማለት አያስፈልግም። አዲስ ኪዳን ላይ በግልጽ "እንዳታደርገው ተጠንቀቅ" ያላል። ደግሞ "ለእግዚአብሔር ስገድ" ይላል። ስለዚህ ለመላእክት ለመስገድ ምንም ምክንያትና ሰበብ አያስፈልግም። ቃሉ እንደሚለው እንዳናደርገው መጠንቀቅ ብቻ ነው የሚበጀን። አለቀ!
የእገዚያብሂር ሰላም ለሁላችንም ይሁን

መላእክት በክብር ቢስግዽላችው ችግሩ ምንድነዉ?
በመጀመሪያ ስግደት በሁለት ይከፈላል የአምለኮትና ያክብሮት የተባለውን እስማማብታለሁ። ከላይ ባልተግባባችሁበት ጉዳይ ዮሃንስ19፡10፣ "የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና አለኝ።" የሚለዉ የሚግባኝ አምልኮተና የአምልኮት ስግደት ለእግዚያብሔር ብች እንደሚገባ ነዉ። አለቀ። ሉቃ፣4 9-10 "ለ ገታ አምላክህ ስገድ እርሱን ብቻ አምልክ" አዎ እግዚያብሔርን ልንስግድለት እሱንም ብቻ ልናመልክ የግድ ነዉ። ሃዋርያት ና ካህናት በሃዋሪያዊነትና በከህነታችዉ በመላእክትም እንደሚክበሩ ማወቅ አለብን ። 1ቆሮ ም6-3 ቅዱስ ጵዉሎስ "በመላእክት እንኩዋን እንድንፈርድ አታቁመን?" ይላል። በዚህም ምክነያት ከላይ በዮሃንስ ራእይ መላእኩ ቅ/ዮሃንስን አትስገድልኝ ያለዉ በስልጣነ ክህነቱ ለቅ/ዮሃንስ ክብር እንደሚገባዉ የሚያመለክት ነዉ። በሌላ አነጋገር "ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ..." የሚለዉን ብቻ ይዘን ስግደት ለመላእክት አይገባም ብንል ቅ/ዮሃንስ ክሁሉም ደቀምዛሙርት አምላክ በይበልጥ ይወደዉ የነበረ ወንገልን መልእክታትን አንዲሁም ራእይን የጽፈ ለክርስቲያኖቸ በቅድስናዉ ታላቅ ተምሳለት የሆነ አባት ነዉ። በመሆኑም ቅ/ዮሃንስ አምላኩን ለይቶ የሚያዉቅ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ አባት ነዉ። ስለዚሀ ቅ/ዮሃንስ በስህተት ለመላእክ ሰገደ መላእኩም አረመዉ ማለት በራሱ መፈስ ቅዱስን ተሳሳተ ማለት አይሆንምን? ይልቁንስ ክርስትና መሰረቱዋ ትህትና ነዉና አምላካቸነ መድሃኒታችን ና ገታችን እየሱስ ክርስቶስ ያስተማራችዉን ትህትና እና አክብሮት ቅ/ዮሃንስ አሳየ እንጂ። እናም ባጭሩ አክብሮት የክርስቲያን ባህሪ ነዉ። ለመላእክት የአከበሮት ስግደት ቢደረግ ለእግዚያብሔር ደገሞ የአክብሮትም የአምልኮትም ስግደት ተገቢ ነዉ። በመሆኑም ነዉ ኢያሱ ለመላእኩ የ አክብሮትን ስግደት የሰገደዉ ኢያሱ 5 13-15 "እንዲህም ሆነ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ አይኑን አንሰቶ ተመለከተ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ በ እጁ የያዘ ሰዉ በፊቱ ቆሞ ነበር ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ ክእኝ ወገን ወይስ ክጤላቶቻቸን? ኣለዉ። እርሱም -አደለሁም እነ የእግዚያብሔር ሰራዊት አለቃ ሆኝ አሁን መጥቻለሁ አለ። ኢያሱም ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደና ገታየ ለባሪያው የሚነግረው ምንድነው? አለዉ..."እንደምናየዉ መላእኩ ያለው የኤግዚያብሔ ስራዊት አለቃ እንጂ እግዚያቢሐር ነኝ አላለም ኢያሱም ይህን ክ ስማ ቡሃላ የ አክብሮት ስግደትን ሰገደ። የአክብሮት ስግደት ለሚገባችው አክብረን ብንስግድላችዉ ትህትናን በመንፈስ ቅ ክተላበሱት የ ሃዋሪያት ና ቅዱሳን መንፈሳዊያንን ስነምግባር በመከተል እንጂ ፍጽም እና ብችኝ የሆነውን የመለኮት/የአምላክነት ስግድት አና አክብሮት የሚገባዉን እግዚአብሔርን ክብር ና አምላከነት ለ ማይገባችዉ ለመስጤት አደለም። በመሆኑም እንደ ቅ/ዮሃንስ ያሉ ሃዋሪያትን እጅግ አላዋቂ በሆነ አእምሮዋችን ያወቅን እየመሰለን ሥግደት ለማይገባዉ መላእክት ስገደ እያልን ለተዳፈርን ሁሉ ገታቸን እና መደሃኒታችን አስተዉሎቱን እና ምሕረቱነ ይሰጥልን።
ወንድሜ ክፍሉ ላይ የሌለ ነገር በግምት መናገሩ "ከተጻፈው ማለፍ" ይመስለኛል። መልአኩ ዮሃንስን እንዳይሰግድ ያስጠነቀቀው እኮ ለምን እንደሆነ በዛው በክፍሉ ላይ ተጽፏል። ከእኛ የሚጠበቀው በደንብ ማንበብ ብቻ ነው። ዮሃንስ ወንጌልን ስለጻፈና ሃዋርያ ስለሆነ ከመላእክት ስለሚበልጥ ነው ምናምን የሚል ነገር በዛ ክፍል አናገኝም። እስቲ በቅድሚያ ክፍሉን በሚገባ አንብበው፤ እንዲህ ስለሆነ እንዲያ ስለሆነ እያልክ ከመገመትህ በፊት። እንዲህ ይላል ክፍሉ ራሱ፦
Quote:
የዮሐንስ ራእይ 22
8 ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ።
9 እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ።

የዮሐንስ ራእይ
19፥10 ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና አለኝ።

መልአኩ ዮሃንስ እንዳይሰግድ ያስጠነቀቀበት ምክንያቱ፤ ሁለት ጊዜም የተጻፈው መላእኩም ይሁን ዮሃንስ ስግደት የማይገባቸው ባሪዎች ስለሆኑ ነው። ቃሉ ምን ይላል "ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ" ነው የሚለው። ስለዚህ መላእኩ የሚለው እኔም እንዳንተው ባሪያ ነኝና ስግደ አንተም እንደማይገባህ እኔንም አይገባኝም ማለቱ ነው። በመቀጠል ደግሞ ስግደት የሚገባው ማን እንደሆነ ራሱ መላእኩ ይናገራል እንዲህ በማለት "ለእግዚአብሔር ስገድ"!

ቃሉ እንግዲህ የሚያወራው መላእክትም ይሁኑ ሰዎች ስግደት የማይገባቸው የእግዚአብሔር ባሪያዎች ብቻ ናቸው። ስግደት የሚገባው ግን አምላክ አለ። ለእርሱ ስገድ!

ክፍሉ ራሱ ቃል በቃል ከሚናገረውና ከሚሰጠው ምክንያት ውጪ ግን የራሳችንን ግምት እየሰጠን "አይ ዮሃንስ ከመልአኩ ስለሚበልጥ ነው ወዘተ" ብንል ክፍሉ ላይ ያለውን እያነበብን ሳይሆን፤ ክፍሉ ላይ ያልተጻፈ ነገር እየጨመረን ነው ማለት ነው።

ቃሉ ደግሞ "ከተጻፈው አትለፍ" ብሎ ያስጠነቅቀናል 1ቆሮ 4፡6።
ወንድሜ ወይ ፡ እንዳሉት "ከእኛ የሚጠበቀው በደንብ ማንበብ ብቻ ነው።" እስማማለው፡ የጠቀሱት ጥቅስ ላይ "ለእግዚአብሔር ስገድ " የሚል እንጂ ለ"ኢየሱስ" ስገድ የሚል አልተጻፈም።

ለኢየሱስ ስግደት ይገባል የሚል ሰው ክፍሉ ላይ ያልተጻፈ ነገር እየጨመረን ነው ማለት ነው?
መላዕክተ ሠማይ
ሰላመ እግዚአብሄር ከእናንተ ጋር ይሁን
መላዕክት ምህረትንና ቁጣን ከእግዚአብሔር ወደ ምድር ልመናንና ፀሎትን ወደ እግዚአብሄር የሚያሳርጉ በእግዚአብሔር የተፈጠሩ ረቂቃን ፍጥረታት ናቸው፡፡ የመላዕክት ቁጥራቸው እልፍ ጊዜ እልፍ ነው፡፡ ኢዮ2÷53፣ ኤር 33÷22፣ ዳን 7÷10፣ ሄኖ10÷1፣ ራዕ5÷11
• መላዕክት በሚፈራቸው ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራሉ፣ ይብቋቸውማል፣ ከመከራም ሁሉ ያወጧቸዋል መዝ 3÷37፣ሐዋ5÷19-20፣ ዳን 6÷22፣ ዳን 10÷13፣ መዝ 90÷11-12
• መላዕክት አብሳሪያን ናቸው ዘፍ16÷11፣ ሉቃ1÷13፣ ሉቃ1÷19፣ሉቃ1÷30-31፣ ሉቃ2÷10-11፣
• መላእክት በጭቀት ጊዜ ይደርሳሉ ዘፍ16÷7-8፣ዘፍ21÷16-17፣ማቴ28÷5-6፣ ዩሃ20÷12-13
• መላዕክት ያፅናናሉ ይመክራሉ ዘፀ 23÷20፣ ዳን9÷21-22፣ ሀዋ 8÷26፣ ሃዋ27÷23፣ ዕብ1÷14
ወደዋናው ጉዳይ ስንገባ መጽኃፍ ቅዱስን ያልመረመሩና ይልተረዱ ሰዎች መላዕክት ፤ፃድቃን አያምልዱንም ጌታ ነው የሚያማልደን ይላሉ፡፡ መጽሃፍ ቅዱስ እንዲህ ይለናል
1ኛ) መዝ 105፡23 ‹‹ ያዳናቸውን እግዚአብሔርን ረሱ እንዳያፋቸው ቁጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሰፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ…›› የዚህ ጥቅስ ሙሉ ሀሳብ ያለው በዘፀ 32 ላይ ነው፡፡ ከምድረ ግብፅ እግዚአብሄር መናን ከሰማይ ውሃን ከአለት እያፈለቀ ማርና ወተት ወደምታፈልቀው ከነአን ይዟቸው በሙሴ መሪነት ወጣ፡፡ ፈርኦንን ከነሰራዊቱ በኤርትራ ባህር አሰጠመ፡፡ እነሆም ብዙ ተአምራት እያሳየ ሙሴ ጽላት የተቀበለበት ቦታ ደረሱ፡፡ ሙሴም ከእነርሱ 40 ቀንና 40 ሌሊት ተለየ፡፡ በዚህ ጊዜ ወርቅና ብራቸውን አቅልጠው በሰሩት በጥጃ ምስል ፊት ሰገዱ፡፡ ከፈርኦን እጅ ፈልቅቆ ያወጣቸውንና የኤርትራን ባህር ለሁለት ከፍሎ ያሻገራቸውን የእግዚአብሔርን መስዋዕት በጣኦት ፊት ሠው፡፡ ዘፀ 20፡12 ‹‹ ከእኔ በቀር ሌላ አማልዕከት አይሁኑህ›› ያለ አምላክ በዚህ ጊዜ ቁጣው በእስራኤላዊያን ላይ ነደደች፡፡ ያጠፋቸውም ዘንድ ማለ፡፡ ‹‹ … ግብፃዊያን በተራራ መካከል ሊገድላቸው ከምድርም ፊት ሊያጠፋቸው ለክፋት አወጣቸው ብለው ስለምን ይናገራሉ ከመዓትህ ተመለስ ለህዝብህም በክፋታቸው ላይ አለ….›› ዘፀ 32÷12 እያለ ሙሴ ስለ እስራኤላዊያን ይለምን በእግዚአብሔርም ፊት ያማልዳቸው ያስታርቃቸው እንደነበር ይናገራል፡፡ ከሙሴም ልመና የተነሳ እግዚአብሔርም በህዝቡ ላይ ሊያደርግ ካሰበው መዓት(ዘፀ 32÷14) ተመለሰ ይላል መጽሀፍ ቅዱስ፡፡ የሙሴን ስለእስራኤላዊያን በእግዚአብሔር ፊት የለመነው ልመና፣ ፀሎትና ምልጃ ልበ አምላክ ዳዊት በመዝ105÷23 ላይ መቆም ያለው፡፡
ስለዚህ በፊቱ ባይቆም ኖሮ የሚለው ቃል ሲተረጎም ስለእስራኤላዊያን በእግዚአብሄር ፊት ባይፀልይ፣ ባይለምን፣ ስለበደላቸው ባያማልዳቸው ኖሮ ለማለት እንጂ በእግዚአብሔር ፊት መጋተር ማለት አይደለም፡፡ መጽሀፍ ቅዱስ አንድስ እንኳ የእግዚአብሔርን ፊት ያየ የለም ብሏልና፡፡
2ኛ. ዘፍ 18÷22-23 ‹‹ አብርሃምም ግን በእግዚአብሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር ›› የሶዶምና የጎመራ ሀጢያት በከበደ ጊዜ ወንዶች ወንዶችን በግብር ማወቅ በጀመሩ ጊዜ እግዚአብሔር እጅግ ተፀፀተ፡፡ ሊያጠፋቸውም አለ፡፡ አብርሃም ግን ስለሶዶምና ጎመራ ሰዎች እግዚብሔርን ይለምን ነበሩ፡፡ 50 ጻድቃን ቢኖሩ አትምርምን 40 ቢኖሩ አትምርምን እያለ እግዚአብሔርን ይለምን ነበርና ‹‹ ቆሞ ነበር›› ተባለ፡፡ ትርጉሙም ያማልድ ያስታርቅ ነበር ለማለት ነው፡፡
3ኛ. ዳን 12÷1 ‹‹ በዚያን ዘመን ስለህዝብህ ልጆች የሚቆመው( የሚለምነው ለማለት ነው) ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሳል››
4ኛ. ሉቃ 1÷19 ‹‹ እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፡፡
5ኛ. መዝ 44 ‹‹ በወርቅ ተሸፋፍና ተጎናፅፋ ንግስቲቱ በቀኝህ ትቆማለች
ወደ ሌላው ጉዳይ ስንገባ ስግደት ይገባቸዋልን? ስግደት በሶስት ይከፈላል የአክብሮት ፣ የፀጋና የአምልኮት በመባል
1) የአምልኮት ስግደት ለሃያሉ እግዚአብሔር ብቻ የሚደረግ ሰግደት ነው፡፡
2) የአክብሮት ስግደት ለሰዎች በማክበር የምናደርገው እጅ መንሳት ነው ለምሳሌ ለመኳንንት የሚደረግ ስላምታ ስግደት ይባላል
3) የፀጋ ስግደት ደግሞ ፃድቃን / ቅዱሳን ከልኡል እግዚአብሔር ያገኙትን በረከትና ረድኤት ያድርብን ዘንድ የምንሰግደው ስግደት /እጅ መንሳት ነው/
1. መሳ 13÷15-28 ‹‹ …. በምድርም በግንባራቸው ታደፉ….›› ማኑኤልና ሚስቱ በፊታቸው ለነበረ የእግዚአብሔር መላዕክ የፀጋ ስግደት እንደሚገባው ተረድተው በፊቱ ተደፉ ሰገዱም፡፡
2. ዘፍ19÷1 ‹‹ ሁለቱም መላዕክት በመሸ ጊዜ ወደ ሶደም ገቡ ሎጥም በሶደም በር ተቀምጦ ነበር፡፡ ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሳ ፊቱንም ደፍቶ ወደምድር ሰገደ›› ለቅዱሳን መላዕክት ስግደት እንዲገባ ሎጥ ሰገደ፡፡ ብዙዎች ሰው መስለውት ነው የሰገደው የሚሉ አሉ፣ ታዲያ ለሰው ከሰገደ ለመላዕከት እንዴ አይሰግድ? ተሳስቶ ነው የሠገደው ሚሉም አሉ፡፡ በመፅሀፍ ቅዱስ የተሳሳተ ነገር እንዴት ይፃፋል?
3. ዘጸ22÷31 ‹‹ እግዚአብሔርም የበለግምን አይኖች ….. ሰገደም በግንባሩም ወደቀ››
4. ኢያ5÷14 ‹‹ እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ አለ፡፡ ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ስገደና ….›› የምመልኩትን ዛሬ ምረጡ እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን ያለው እያሱ እንኳን ሰግዷል የጸጋ ስግደትን፡፡
5. ዳን 8÷16-17 ‹‹ …. እርሱም ወደቆምሁለት ቀረበ በመጣም ጊዜ ፈርቼ በግምባሬ ተደፋሁ›› በብሉይ ኪዳን የፀጋ ስግደት ለፃድቃንና መላዕክት እንዲገባ በብዙ ቦታ ተፅፎ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ዘመናችን በክህደትና በዋዛ ፈዛዛ የተጠመደበት ጊዜ ነውና ወደ ሃዲስ ኪዳን ሔደን አንድ ሁለት ምሳሌ እንይ፡፡
1) ሐዋ 16÷25-31 ‹‹ ….. መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ…›› ታዲያ ለጳውሎስና ለሲላስ የሠገደው የወህኒ ቤቱ ጠባቂ ለመላእክት ቢሠግድ ምኑ ላይ ይሆን ስህተቱ?
2) ራዕ19÷9-11 ‹‹ ይህ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃል ነው አለኝ፡፡ ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ፡፡ እርሱም እንደታደርገው ተጠንቀቅ…››
3) ራዕ 22÷6-9 ‹‹ በመላአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ…››
እዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ላይ ብዙ ሰዎች ይሳሳታሉ፡ ዩሃንስ በእግዚአብሔር ፊት የተመረጠ ክብርንም ያገኘ ሆኖ በፍጥም ደሴት ቁጭ ብሎ የልኡል እግዚአብሔርን ክብር በላይ በሠማያት የተመለከተ ባለራዕይ ነው፡፡ እንግዲህ መጀመሪያ በራዕ19÷9-11 ሊሰግድለት ሲል ‹‹ ተጠንቀቅ እንዳታደርገው›› ካለው ለምን ለዚህ ሁሉ ክብር የታጨው ዩሃንስ ደግሞ ሰገደለት ስላልሰማ ነውን? ወይስ አለመታዘዝ? አይደለም መላዕኩ እኔ ከወንድሞች ጋር ባሪያ ነኝ ብሎ ራሱን ስለእግዚአብሔር ክብር አዋረደ እንጂ፡፡ ማር 10÷17 ‹‹ እርሱም በመንገድ ሲወጣ አንድ ሰው ወደ እርሱ ሮጦ ተነበረከከለትና ቸር መምህር ሆይ….› ብሎ ባለው ጊዜ ኢየሱስም ‹‹ስለምን ቸር ትለኛለህ ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም…›› በ1ኛ ቆሮ 3÷23 ላይ ደግሞ‹‹ ክርስቶስም እግዚአብሔር ነው›› ይለናል፡፡ እነዚህን ሁለት ጥቅሶች ያነሳሁት በማር10÷17 መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቸር፣ ሁሉን ቻይ ፣ አልፋና ኦሜጋ አምላክ እርሱ ብቻ ሆኖ ሳለ ስጋ ስለለበሠና ለኛ እራሱን ማዋረድን ሊያስተምረን ‹‹ ስለምን ቸር ትለኛለህ ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም…›› ያለው፡፡ ስለዚህ መልዐኩም ተው እኔም አገልጋይ ባሪያ ነኝ ያለው ራሱን ዝቅ ለማድረግ ነው፡፡
4. ራዕ3÷8-9 ‹‹ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ፡፡ ይህ የተፃፈው በእስያ ካሉ 7 አብያተ ክርስቲያናት ወደ አንዱ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነው፡፡ ስለዚህ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ወዳሉ ክርስቲያኖችና አጲስ ቆጶሳት ነው፡፡ ታዲያ ለክርስቲያኖች ከሰገደ ለመላእክት ቢሰግድ ችግሩ ምኑ ላይ ነው
?
ለኢየሱስ መስገድ ወይም እርሱን ማምለክ አይገባም ወዘተ ላሉት ሰው የሚከተለውን ያንብቡ
Quote:
የዮሐንስ ራእይ 5
8 መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።
9-10 መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ
11 አየሁም፥ በዙፋኑም በእንስሶቹም በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቍጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፥
12 በታላቅም ድምፅ፦
የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ
13 በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ። በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ
14 አራቱም እንስሶች። አሜን አሉ፥ ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱ።
"መላዕክተ ሠማይ" ብለው ስለ ሙሴ ለጻፉ ሰው

መልሴን ምን ብዬ እንደምጀምር ግራ ነው የሚገባኝ። ምክንያቱም አንደኛ ጥያቄው ስለ ምልጃ አይደለም፤ እርሶ ግን ብዙ ነገር ስለ ሙሴ የጻፉት ስለ ምልጃ ነው። ሁለተኛ ጥያቄው ስለ ሰው ሳይሆን ስለ መላእክት ነው እርሶ ግን ስለ ሙሴ ነው የሚጽፉት።

አንድ ሰው በህይወት እያለ ለሌላው ሰው እንዲማልድና እንዲጸልይ እኮ አዲስ ኪዳንም ብዙ ቦታ ያሳስበናል። አንዱ ለሌላው መጽለይና መማለድ እኮ አዲስ ኪዳናዊ ትምህርት ነው። ማንም ይሄን የሚቃወም የለም። አሁንም በዚህ ዘመን አንዱ ክርስቲያን ለሌላው ይማልዳል ይጸልያል። እንዲያውም አዲስ ኪዳን ለሚጠሉንና ለሚያሳድዱንም ነው እንድንማልድና እንድንጸልይ የሚናገርው። ይሄንን የተቃወመ ሰው የለም እኮ።

ስለ ምልጃ ጉዳይ ጥያቄው ያለው በሁለት ነገሮች ላይ ነው። አንደኛ የሞቱ ቅዱሳን ያማልዳሉ ወይስ አያማልዱም የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ መላእክት ያማልዳሉ ወይስ አያማልዱም የሚል ነው። ስለዚህ ምልጃን በተመለከተ ትልቁ ጥያቄ ያለው በህይወት ስላሉ ሰዎች አይደለም። እዛ ላይ ማንም ጥያቄ የለውም። በህይወት የሌሉ ግን አሁን ያማልዳሉ ወይ? አሁን እነርሱ እንዲያማልዱን ወደ እነርሱ እንለምን ወይ? መላእክትስ እንዲያማልዱልን ወደ እነርሱ እንጸልይ ወይ የሚል ነው።

መጽሃፍ ቅዱስ የሞቱ ቅዱሳንም ይሁኑ መላእክት ሲያማልዱ ወይም ሰዎች እነርሱ እንዲያማልዱላቸው ወደ እነርሱ ጸሎትን ሲያቅርቡ አንድም ቦታ አይናገረም። ለማናቸውም ይህ አምድ ስለ ምልጃ ሳይሆን ለመላእክት ስለ መስገድ ነውና፤ ብዙ ርእሱ ባንወጣ መልካም ነው። ስለ መላእክት አማላጅነት ሌላ ቦታ ጥያቄ ተነስቶ ከዚህ በፊት ብዙ ውይይት ተደርጎበታል። ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።
Quote:
የዮሐንስ ራእይ 22
8 ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ።
9 እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ።

የዮሐንስ ራእይ
19፥10 ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና አለኝ።
እኛ እንደ አምላክ አይደለም ምንሰግድላቸው ። የአክብሮት ነው ጌታ እንደሚያዘን ራእይ 3፤9-10 እይገባቸዉም ካለን ጌታ ለምን ያዛል።
በራሱ ልጆች አይቀናም ከበር የሰጣቸው ራሱ ነውና ። መዝ 8፤4-5 ዘጸ 20፤12 ዘሌዋውያን 19፤32
1 ሳሙኤል 2፤30
ስለዚህም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በእውነት ቤትህ የአባትህም ቤት ለዘላለም በፊቴ እንዲኖር ተናግሬአለሁ፤ አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ አይሆንልኝም።
መዝ 68፤35
እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው፤ የእስራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል፤ እግዚአብሔርም ይመስገን።

መዝ 112
1 ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ትእዛዙንም እጅግ የሚወድድ ሰው ምስጉን ነው።

2 ዘሩ በምድር ላይ ኃያል ይሆናል፤ የቅኖች ትውልድ ትባረካለች።

3 ክብርና ባለጠግነት በቤቱ ነው፥ ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል።

4 ለቅኖች ብርሃን በጨለማ ወጣ፤ መሓሪና ይቅር ባይ ጻድቅም ነው።

5 ቸር ሰው ይራራል ያበድራልም፥ በፍርድም ነገሩን ይፈጽማል።

6 ለዘላለም አይናወጥም፤ የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል።

7 ከክፉ ነገር አይፈራም፤ በእግዚአብሔር ለመታመን ልቡ የጸና ነው።


(የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል።)
እቺ አንተ እንዳልከው ይሁን ለምን ሁለቴ ሊሰግድ አለ 1ኛ ራእይ 19፤10 ለእግዚአብሔር ብቻ እንደሚደባ እየነገረው ከደገና 22፤8-9 ላይ ይሴግዳል (በግድ ላምልክ እያለው ነው ?) ሐዋሪያው ዮሐንስ አይውቅም ዛሬ እኛ ከሱ በልጠን እናውቃለን ማለት ነው።
0 ድምጾች
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመላዕክት ለመስገድ ሲሞክሩ የተከለከሉ ሰዎች እኮ በገሐድ መላዕክትን አይተዋል።እኛ መላዕክትን ሳናይ ለመላዕክት ስለመስገድና አለመስገድ ምን አስጨነቀን?
5 ዓመታት በፊት ስም-አልባ የተመለሰ
እየተነጋገርን ያለነው ስለመጽሃፍ ቅዱስ facts ነው። ያቀረቡት ሎጂክ በጣም ደካማ ነው። ኢየሱስ ጌታ ስለወነ እንስግድለታለን፡ እንጂ ስለአየነው አይደለም።
ወንድሜ ሆይ
የመጽሐፍ ቅዱስን fact እኮ አስቀመጥኩልዎት።አሁንም ደግሜ እላለሁ በጻፍኩት simple logic ለመላዕክት መስገድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት እንደሌለው ገልጫለሁ።
አይ ለጌታ ኢየሱስ እሰግዳለሁ ለመላዕክትም በሌሉበት "የአክብሮት" ስግደት እሰግዳለሁ ካሉ የራስዎ ምርጫ ነው፡፡ለጌታ ኢየሱስ የምንሰግደው በእውነትና በመንፈስ ነው።በውሸትና በሥጋ አይደለም።የጌታ ሰላምና ጸጋ ይብዛልዎት።
ወንድሜ ሆይ፡
አሜን የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና ጸጋ ይብዛልኝ። የ"የአክብሮት" ስግደት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት እንደለውማ ብዙ መረጃ እዚው ቦታ ተጠቅሶአል (ዘፍ. 19፥1 መጽ ኢያሱ 5፥13 ዳን. 8፥15 ዜና መዋዕል ቀዳ 21፥16) እኔ እያልኩ ያለውት እነዚህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃዎች ማፈን ጌታን ከሚያምን ሰው አይጠበቅም ነው።
ጌታ ኢየሱስ የጌቶች ጌታ፤ የንጉሶች ንጉስ፤ አዳኝና እውነተኛ አምላክ ስለወነ እንደርሱ ያለ አምላክ የለም ብዬ እሰግድለታለው። የጌታ መላዕክት ሁሌ ከኔ ጋር ናቸው (መዝሙረ ዳዊት
91፥11 በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና። መዝሙረ ዳዊት 104፥4 መላእክቱን መንፈስ የሚያደርግ፥ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል።) የአክብሮት የምሰግደው የጌታ መላእክት ባሉበት ነው እንሱ መንፈስ ናቸው። ክብርን ለሚገባው ክብርን እንድሰጥ ስለታዘዝኩኝ፡ ክብርን ለሚገባው ሁሉ የሚገባውን ክብር እሰጣለው። ተባረኩ
0 ድምጾች
እስቲ የራሳችንን ሃሳብ ትተን መጻፍ ቅዱስ ምን ይላል ?

1) (ዘፍ. 19፥1) ሰዶምና ገሞራን በእሳት ለማቃጠል የተላኩት መላእክት ወደ ሎጥ ቤት በገቡ ጊዜ ሎጥ በግምባሩ ተደፍቶ ለመላእክቱ እንደሰገደ ተጽፏል፡፡

2) (መጽ ኢያሱ 5፥13) ኢያሱ በግምባሩ ተደፍቶ ለመልአኩ ሰግዶለታል፡፡ ‹‹የቆምክባት ሥፍራ የተቀደሰች መሬት ናትና ጫማህን ከእግርህ አውጣ›› አለው እንጂ አልከለከለውም (መጽ ኢያሱ 5፥13)፡፡

3) (ዜና መዋዕል ቀዳ 21፥16) የእሥራአል ንጉሥ የነበረው እግዚአብሔር ነብይ ዳዊት ከእሥራኤል ሽማግሌዎች ጋር ከመሬት ከፍ ብሎ ሰይፉን ዘርግቶ ለተገለጠላቸው ለእግዚአብሔር መልአክ ሰግደውለታል ፡፡

4) (ዳን. 8፥15) ነቢየ እግዚአብሔር ዳንኤል መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በአባል ወንዝ አጠገብ በተገለጠበት ጊዜ ለመልአኩ ለቅዱስ ገብርኤል ራሱን ዝቅ አድርጐ በግንባሩ ወድቆ ሰግዶለታል፡፡ በዚሁም ላይ የግርማውን አስፈሪነት እና አስደንጋጭነት ጠቅሷል፡፡

5) ራእ. 19፥10 እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ።

ማጠቃለያ፡ እዚህ ጋ ብቻ አራት ጥቀስ ለመላእከት ጌታ ለሰጣቸው ክብር የተነሳ እንደሚሰገድ ያስተምሩናል። አንድ ጥቅስ ይዘን አራቱን ለማፈን ባንሞክር መልካም ነው። ጠባረኩ።
5 ዓመታት በፊት ስም-አልባ የተመለሰ
5 ዓመታት በፊት የታረመ ስም-አልባ
በአዲስ ኪዳን እኮ ብዙ ነገር ተለውጧል። የብሉይ ኪዳን ብዙ መቶዎች የሚሆኑ ህጎች ለእስራኤል ተሰጥተዋል፤ እነዚያን ሁሉ የአዲስ ኪዳን አማኞች ያከብራሉ ማለት አይደለም። ብሉይ ኪዳን ደግሞ በሙሉ የተሰጠው ለኢትዮጵያዊያኖች ወይም ለሌሎች ሳይሆን ለእስራኤሎች ብቻ ነው። እኛ የዳንነውና የምንድነው በኢየሱስ የአዲስ ኪዳን ደም ነው። ስለዚህ የአዲስ ኪዳኑ ሁል ጊዜ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል። በክርስቶስ የዳኑ ሰዎች ለመላእክት ስግደትን እንዳያደርጉት ተጠንቀቅ የሚል ከሆነ ልንቀበለው ይገባል፤ እንጂ በብሉይ ኪዳን እኮ እከሌ አድርጎት ነበር ብለን የአዲስ ኪዳኑን መሻር አንችልም።

ሌላው በብሉይ ኪዳን ለሰዎችም መስገድ የተለመደ ነገር ነበር፤ አክብሮት የመስጠት ነው። በአዲስ ኪዳንና በእኛ ባለንበት ዘመን ሰዎችን ለማክበር አንሰግደም፤ የምንሰግደው ከአምልኮ ጋር በተያያዘ ነው። እናም አምልኮን የሚመለከት ነው። አምልኮ ደግሞ የሚገባው መልአኩም እንዳለው ለእግዚአብሔር ብቻ ነው።
የተክበሩ ወንድም

ክ አባባሎ እንደገባኝ ብሉይ በሃዲስ ተቀይሩዋል እያሉ ነዉን

ብሉይን በ እስራዐላዉያን በኩል የስጤዉ ራሱ እግዚያብሔር አደለም ?
ብሉይ በመሲሁ መምጣት ምፈጸምን አግኝ እንጂ ተስረዘ ማለት ነው?

በ ብሉይ የነበረ በሃዲስም ያለ እግዚያበሔር የተለያየ አምልኮትን አሰተማረ ማለት ንዉ?

"ብሉይ ኪዳን ደግሞ በሙሉ የተሰጠው ለኢትዮጵያዊያኖች ወይም ለሌሎች ሳይሆን ለእስራኤሎች ብቻ ነው።"

ሰለዚህ ብሉይ አያስፈለገንም?
"ብሉይ ኪዳን ደግሞ በሙሉ የተሰጠው ለኢትዮጵያዊያኖች ወይም ለሌሎች ሳይሆን ለእስራኤሎች ብቻ ነው። " ይህ አስተሳሰብ እውነት ከወነ። ለወንጌል በዘመናት ሁሉ እለት እለት የምደክሙ ብሉይ ኪዳን ማጥናታቸውና ማስተማራቸው ከንቱ ነዋ። ኸረ ለምን አስፈላጊ ባልወነ ነገር ጊዜአቸውንና ጊዜያችንን ያጠፋሉ?

በየኢየሱስ ክርስቶስ መዳናችን የታመነ እውነት ነው፤ ለዚህም ነው የእንስሳት ደም የቀረው። ክብር ለሚገባው ክብር መስጠት በአዲስ ኪዳን ፈጽሞ አልቀርም። የማቴዎስ ወንጌል
5፥17 እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም።
ህግና ኪዳን ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው። እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር ያደረጋቸው ሁለት ኪዳኖች (ቃል ኪዳኖች) አሉ። የመጀመሪያው ቃል ኪዳን የተደረገው ከእግዚአብሔርና ከእስራኤል ጋር በሲና ተራራ ነው። የኪዳኑም እምብርት ህጉ ነው። በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያለ ሁሉ ወይም በዚያ ኪዳን መዳን የሚፈልግ ሁሉ፤ አንደኛ እስራኤላዊ መሆን አለበት ወይም ወደ ይሁዲነት የተለወጠ አህዛብ መሆን አለበት። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ህጉን መጠበቅ አለበት።

በዚያ ኪዳን ግን ሰው ሊድን ስላልቻለ፤ ማለትም ህጉን ጠብቆ እግዚአብሔር አዲስን ኪዳን ሰጠን። ይህም በክርስቶስ ደም የታሰረ ለሚያምኑ ሁሉ ሰዎች የሆነ ኪዳን ነው። እግዚአብሔር ታዲያ ህጉን አይደለም የሻረው፤ ህጉ አሁንም በብሉዩ ኪዳን ወደ እግዚአብሔር ለመድረስ ለሚፈልጉ ይሰራል። ህጉ ምንም ስህተት የለውማና።

ከብሉዩ ጎን ግን እግዚአብሔር አዲስን ቃል ኪዳን ከፍቶአል። በዚህ ኪዳን ህጉን ጠብቆ መገረዝ ወይም አለመገረዝ ሳይሆን፤ በክርስቶስ መሆን ነው ወሳኙ። የቃል ኪዳን እምብርት በአዲሱ ኪዳን ህጉ አይደለም ነገር ግን ክርስቶስ ነው።

ስለዚህ በብሉይ ኪዳን ያሉት ብዙ ህግጋት የሚሰሩት በብሉይ ቃል ኪዳን ውስጥ ላለ ሰው ነው። ስለ ሰንበት ቢሆን፣ ስለ የመቅደስ ስርዓት ቢሆን፤ ስለ መሬት በእስራኤል ነገዶች መካከል አከፋፈልና አጠቃቀም ቢሆን፤ ስለ ሌዋውያንና ካህናት ቢሆን ሁሉም የሚሰራው በእስራኤል አገርና በእስራኤል ህዝብ ዘንድ በብሉዩ ቃል ኪዳን ውስጥ ነው።

አሁን እኛ ግን የዳንነው በአዲሱ ኪዳን ነው። የዚያ ስርዓትና አስራር የተለየ ነው። ይሄን ብሉ ይሄን አትብሉ፤ በዚህ ቀን ስሩ በዚህ ቀን አትስሩ፤ መሬታችሁን እንዲህ እረሱት እንዲህ አትረሱት፣ ወዘተ በሚል ህግ አይደለም የምንመራው። ነገር ግን ከህግ ነጻ ወጥተን ለሞተልንና ለተሰቀለልን ለክርስቶስ ልንሆን ነው የተጣራነው።

ህግ አልተሻረም ኪዳን ግን ተለውጧል። ህጉ የሚሰራው በብሉይ ኪዳን ነው፤ በአዲሱ ግን ክርስቶስ ይሰራል።

ወደ ሮሜ ሰዎች 7
4 እንዲሁ፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንተ ደግሞ በክርስቶስ ሥጋ ለሕግ ተገድላችኋል፤ ለእግዚአብሔር ፍሬ እንድናፈራ፥ እናንተ ለሌላው፥ ከሙታን ለተነሣው፥ ለእርሱ ትሆኑ ዘንድ
6 አሁን ግን ለእርሱ ለታሰርንበት ስለ ሞትን፥ ከሕግ ተፈትተናል፥ ስለዚህም በአዲሱ በመንፈስ ኑሮ እንገዛለን እንጂ በአሮጌው በፊደል ኑሮ አይደለም

ወደ ሮሜ ሰዎች 6
14 ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና

ወደ ገላትያ ሰዎች 3
10 ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ በእርግማን በታች ናቸውና፤ በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ ጸንቶ የማይኖር የማያደርግም ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና።
13 በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን

ወደ ገላትያ ሰዎች 5
2 እነሆ፥ እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ። ብትገረዙ ክርስቶስ ምንም አይጠቅማችሁም።
3 ሕግንም ሁሉ እንዲፈጽም ግድ አለበት ብዬ ለሚገረዙት ሁሉ ለእያንዳንዶች ደግሜ እመሰክራለሁ።
4 በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል
አሁንስ ውይይታችን ሁሉ እየገረመኝ መጣ። እስቲ ለመላእክት መስገድ ህግ ወይም ኪዳን ነው ማን አለ? ጥያቄው ለመላእክት ስግደት ይገባል ወይስ አይገባም ነው።

እየተባለ ያለው ቢያንስ አራት ጥቀስ ለመላእከት ጌታ ከሰጣቸው ክብር የተነሳ እንደሚሰገድ ያስተምሩናል። አንድ ጥቅስ ይዘን አራቱን ለማፈን ባንሞክር መልካም ነው የተባለው እንጂ ህግ ነው ወይም ኪዳን ነው አልተባለም።

በነገራችን ላይ ኦሪት ዘጸአት 20ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ። 3 ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ። እናም ይህ ህግ የሚሰራው በብሉይ ኪዳን ዘመን ነበር አሁን አይሰራም የሚል ያለ ክርስቲያን ያለ አይምስለኝም፡፡ ብሉይ ኪዳን ስለተጻፈ አንቀበልም ልንል ነው እንዴ?

መደምደሚያ፦ ለመላእክት መስገድ መፍጹም የአምልኮ አይደለም የአክብሮት ነው። ይህ መህጻፍ ቅዱስ ላይ ብዙ ጊዜ የሰፈረን ጉዳይ በአንድ ጥቀስ ወይም ብሉይ ኪዳን ወስጥ ነው የሰፈረው በማለት ለማፈን መሞከር ትክክለኛ አስተምሮ አይደለም። ህግም ነው ደጎሞ ተብሎ እዚጋ ማንም አልጻፈም።

ኢየሱስ ጌታ ነው።
የተከበሩ ወንድማችን

"ስለዚህ በብሉይ ኪዳን ያሉት ብዙ ህግጋት የሚሰሩት በብሉይ ቃል ኪዳን ውስጥ ላለ ሰው ነው።" ብለዋል፡፡

ስለዚህ ክ ኦሪት ህግጋት ዋናዉ እና የመጀመሪያዉን ቦታ የሚይዘዉ አሰርቱ ህግጋት (ቃላት)የእግዚያብሐር መሪ ትእዛዛት(ህጎች)እግዚያብሐር ለሙስ በጽላት ላይ አስፍሮ እንደሰጤው መ/ቅ ይነግረናል(ዘጻአት 34፡28)። ታድያ በዚህ አባባልዎ ክቡር ወንድማችን በዚህ ዘመን የ ህግጋት (ትእዛዛት) መሪ እና በቀጥታ ክ እግዚአብሄር ዬተሰጡ የዘመነ ብሉይ ነዉና አንቀበለዉም?

እነዚሀን ህግጋት የስራልን እግዚያብሔር ዱሮም እሱ አሁንም እሱ ነው። ንጉስ ዳዊትም እግዚያበሐር ዘላለማዊና የማይለወጥ አልፋና ኦማጋ መሁኑን ሲነግረን መዘ/ዳ 101፡25 "አብቱ አንተ ከጥንት ምድርን መሰረትክ ስማያትም ዬጀህ ስራ ናቸዉ እነርሱ ይጤፋሉ አንተ ግን ትኖራልሀ " 26 "አንተ ግን ያዉ አንተ ነህ" ይላል። አሜን!

ሌላዉ "ህግ አልተሻረም ኪዳን ግን ተለውጧል። ህጉ የሚሰራው በብሉይ ኪዳን ነው፤ በአዲሱ ግን ክርስቶስ ይሰራል።" ብለዋል ክቡር ወንድሜ
እራሱ ገታ መድሃንያለም ክርስቶስ እንዲሀ ይላል ማት 5፡17" እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም።
18 እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፥ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ።
19 እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል፤ የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢሆን እርሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል።" በመንግስተ ስማያት ክሁሉ ታናሽ እንድንባል አይሁን አሜን!
ስለዚህ ክቡር ወንድሜ በመጅመሪያ ጥያቀየ
ብሉይን በ እስራዐላዉያን በኩል የስጤዉ ራሱ እግዚያብሔር አደለም ?
ብሉይ በመሲሁ መምጣት ምፈጸምን አግኝ እንጂ ተስረዘ ማለት ነው?
ክሁነ ታድያ

በ ብሉይ የነበረ በሃዲስም ያለ እግዚያበሔር የተለያየ አምልኮትን አሰተማረ ማለት ንዉ?

ነበሩ ቀጥተኝ መልስ ቢኖር አሪፍ ነበር

ለዉድ ግዘዎ ምስጋና ይድረስዎ
ስለ ሁለቱ ኪዳኖች መሠረታዊ መረዳት ለማግኘት እዚህ በመጫን ያንብቡ።
የጤየኮትን ጥያቄወች በቀጥታ ስላልመልሱ አመስግናለሁ። ለመሆኑ በቤ/ክ ወይም በግሎ ስግደትን የሚያረጉት መቼ ነው?
0 ድምጾች
በቅድሚያ ስግደትን ስንመለከት ለፈጣሪና ለፍጡር የሚቀርብ ብለን በሁለት ከፍለን ልናየው ያስፈልጋል።ይህውም ለፈጣሪ የሚቀርበው የአምልኮት ስግደት ሲሆን ለፍጡር የሚቀርበው ድግሞ የአክብሮት ስግደት ነው።

የክብር ስግደት
ዜና መዋዕል ቀዳማዊ።29፤20
ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ። አምላካችሁን እግዚአብሔርን ባርኩ አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባታቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ባረኩ፥ ራሳቸውንም አዘንብለው ለእግዚአብሔርና ለንጉሡ ሰገዱ።

ለእግዚአብሔርና ለንጉሡ ሰገዱ።
ለእግዚአብሔር የሰገድው የአምልኮት ነው

ለንጉሡ የአክብሮት ነው ።

እግዚአብሔርም የበለዓምን ዓይኖች ከፈተ፤ የእግዚአብሔርን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ፤ ሰገደም፥ በግምባሩም ወደቀ።
ኦሪት ዘኁልቁ 22፤31
ኢያሱ 5፤ 13-15

ራእይ 19፤10 ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም። እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና አለኝ።
ራእይ 22፤8-9
ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ።
እርሱም። እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ።

ራእይ 19፤10 ዮሐንስ የሰገደው የአክብሮት ነው መልአኩም ደግሞ እይገባም አለው ስለሚከለከል ሳይሆን ራሱን ዝቅ በማድረግ ነው።
ዮሐንስ ስግደት እንደሚፈቀድ ስለሚያቅ ነው እንጂ መልአኩን ለማምለቅ አይደለም
ምቅንያቱም ተሳስቶ ብዎን ኖሮ ከንደገና አይሰግድም ነበር ራአይ 22፤8-9

ጥያቄ
ራአይ ላይ ያለው ወይስ እያሱ ላይ ያለው መላአክ ነው አጢያጠኛ ?
ራእይ ላይ ያለው ስግደት አልተቀበለም እያሱ ላይ ያለው ተቀበለ።
ስግደት ክልክል ነው የሚሉ ከዉተት አንዱን አጢያጠኛ ነው ማለታቸው ነው።

ጌታችን ለሚዎዳቸው ስገዱ ስል እንሱ ከ ሐዋርያው እና ከጌታችን በልጠው አትስገዱ ይላሉ።

የጌታ ትዛዝ
ራእይ 3፤9
እነሆ፥ አይሁድ ሳይሆኑ። አይሁድ ነን ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ እነሆ፥ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።
4 ዓመታት በፊት ስም-አልባ የተመለሰ
እሺ አሁን የተባለውን ሁሉ ተመለከትኩ ከግራም ከቀኝም። ለመሆኑ ለመላእክት ስግደት እይገባ የምትሉ ሰወች ለ እግዚያብሄር የምትስግዱት እንዴትና መቼ ነው? በቤ/ክናችሁ ለ እግዚያብሄር አብ የምትስግዱበት የ አምልኮ ስረአትስ አላችሁን?
እስቲ የራሳችንን ሃሳብ ትተን መጻፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቃል የማይጠብቁ ሊሰግዱ ግድ ነው እነርሱ ከመላእክት ብቻ ሳይሆን ከህግ በታችም ጭምር ናቸው እንጂ!


1) (ዘፍ. 19፥1) ሰዶምና ገሞራን በእሳት ለማቃጠል የተላኩት መላእክት ወደ ሎጥ ቤት በገቡ ጊዜ ሎጥ በግምባሩ ተደፍቶ ለመላእክቱ እንደሰገደ ተጽፏል፡፡

2) (መጽ ኢያሱ 5፥13) ኢያሱ በግምባሩ ተደፍቶ ለመልአኩ ሰግዶለታል፡፡ ‹‹የቆምክባት ሥፍራ የተቀደሰች መሬት ናትና ጫማህን ከእግርህ አውጣ›› አለው እንጂ አልከለከለውም (መጽ ኢያሱ 5፥13)፡፡

3) (ዜና መዋዕል ቀዳ 21፥16) የእሥራአል ንጉሥ የነበረው እግዚአብሔር ነብይ ዳዊት ከእሥራኤል ሽማግሌዎች ጋር ከመሬት ከፍ ብሎ ሰይፉን ዘርግቶ ለተገለጠላቸው ለእግዚአብሔር መልአክ ሰግደውለታል ፡፡

4) (ዳን. 8፥15) ነቢየ እግዚአብሔር ዳንኤል መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በአባል ወንዝ አጠገብ በተገለጠበት ጊዜ ለመልአኩ ለቅዱስ ገብርኤል ራሱን ዝቅ አድርጐ በግንባሩ ወድቆ ሰግዶለታል፡፡ በዚሁም ላይ የግርማውን አስፈሪነት እና አስደንጋጭነት ጠቅሷል፡፡

5) ራእ. 19፥10 እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ
እኔ በጣም የሚገርመኝ ቢኖር በተጻፈና ባልተጻፈ ነገር ላይ ሁለቱንም አንድ አድርገን መወያየታችን ነው።
አረ ለመሆኑ የቱጋራ ነው ለመላእክት፤ ለሰው፤ ባጭሩ ለፍጥረታት ሁሉ ስገዱ የሚለው ያለው? የክብር ስግደት የፍርሃት ስግደት ያምልኮ ስግደት እያልን የምንከፋፍለው ባንፈላሰፍ ምን አለበት ከተጻፈው ባናልፍ ከፈጣሪያችን ጋራ በቃሉ ብንስማማ አይሻልም እንዲ ብሎን ስላለ፤ የሉቃስ ወንጌል 4፥8 ኢየሱስም መልሶ፦ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአል አለው። ከዚ በሃላ ማንም ሰው ለፈለገው ሊሰግድ ይችላል እኮ፤ ግን በሰገደ ሳይሆን ቃሉ ባለን ነው የምንመራው እራሱን ተማምኖ የተናገረው አምላክ እራሱ ይጠየቅበት ለእርሱ ካልሆነ ለሌላ ለማንም አልሰግድም።

የተዛመዱ ጥያቄዎች

0 መልሶች
3 ዓመታት በፊት መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
1 መልስ
3 ዓመታት በፊት መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
0 መልሶች
3 ዓመታት በፊት መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2017 by iyesus.com
Terms of use | Contact us