ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Saturday, 25 September 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ሃሌሉያ ማለት ምን ማለት ነው?

ሃሌሉያ የሚለውን ቃል ትርጉም ብትነግሩኝ? ትክክለኛ ትርጉሙ ምን ማለት ነው?
Feb 27, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

4 መልሶች

+1 ድምጽ
ሃሌሉያ ወይም (ሃሌ ሉያ) ከእብራይስጥ በቀጥታ ሳይተረጎም የተወሰደ ቃል ነው። ሃሌ ሉያ ወይም በእብራይስጥ הַלְּלוּיָהּ (Halleluya ) የሚለው ስንኝ በውስጡ ሁለት ቃላቶችን ይዟል። አንደኛው "ሃላል" ወይም הַלְּלוּ (halal) የሚለው ሲሆን ትርጓሜውም በደስታና በጩኸት ማመስገን ወይም ማወደስ፤ እንደ ሞኝ ወይም እንደ እብድ በመፈንጠዝ መኩራራት፣ መመካት፣ መጓደድ ወዘተ ማለት ነው። ሁለተኛው ቃል "ያህ" ወይም יָהּ (Yahh) የሚለው ሲሆን የያህዌ (YHWH) አጠር ያለ ፎርም ነው። ይሄ ያህዌ የሚለው ቃል ወይም አንዳንዴም ጄሆቫ የሚባለው ቃል በእብራይስጥ የእግዚአብሔር ስም ነው። በአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ይሄ ያህዌ የተባለው ቃል በአብዛኛው "እግዚአብሔር" ተብሎ ነው የተተረጎመው።

ሃሌ ሉያ የሚለው እንግዲህ "ሃላል" ማለትም በደስታና በጩኸት በፈንጠዝያ አመስግኑ፣ አወድሱ፣ ተጓደዱ፣ ተመኩ የሚለውን ቃል እና "ያህ" ወይም "ያህዌ" ማለትም እግዚአብሔር የሚለውን ቃል አብሮ የያዘ ስንኝ ነው። ሙሉ ትርጉሙም "ሰዎች ሆይ፣ እግዚአብሔርን በደስታና በጩኸት በፈንጠዝያ አመስግኑ/አወድሱ በእርሱም ተመኩ/ተጓደዱ" ወዘተ ማለት ነው። ይህ ስንኝ በአብዛኛው የሚገኘው በመዝሙረ ዳዊት ላይ ሲሆን፤ በቀጥታ እግዚአብሔርን የማመስገኛ ስንኝ ሳይሆን ይልቁኑም ሰዎች እግዚአብሔርን እንዲያወድሱ ሰዎችን ለምስጋና የመቀስቀሻ ቃል ነው።
Feb 27, 2011 iyesus (7,430 ነጥቦች) የተመለሰ
+1 ድምጽ
ሃሌሉያ ማለት እግዚአብሄርን አመስግኑት ነዉ፡፡
Mar 3, 2011 rati (180 ነጥቦች) የተመለሰ
0 ድምጾች
ክብርና ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁን ማለት ነው!!!

ጌታ ይባርካችሁ!!!!!!
Mar 3, 2011 ወስናቸው (430 ነጥቦች) የተመለሰ
0 ድምጾች
ሃሌሉያ ማለት ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን ማለት ነው
Apr 23, 2013 ወስናቸው (430 ነጥቦች) የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...