ይህን ለሚያነቡ ሁሉ የጌታ ሰላም ይሁን። አሜን!!!
"የእግዚ/ር ፈቃድ የሆነ ጋብቻ እንዴት ነው?" የሚል ጥያቄ በእህት ወይስ በወንድም ነው የቀረበው? ያም ሆነ ይህ መልሱ ለሁሉ ያው ነው።
አንድ ጥያቄ አለኝ። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለጋብቻ ብቻ ለምን ይሆን የምንፈልገው? ለምን እስከ ዛሬ ፈቃዱን አልጠየቅንም። ጌታ ከጋብቻ በላይ ነው ጌታ የሚፈለገው የሚገኘውም ከጋብቻ በፊት ነው። በወንድ ፍቅር በሴት ፍቅር በወርቅ አልማዝ በሹመት በሃብት የተነደፈ ልብ ትርኪ ምርኪ ስለ ሞላ ልብ እንደ መሰለው ነው የሚመላለሰው።
የእግዚአብሔር ፈቃዱን ለማወቅ እግዚአብሔር ሲናገር የምንሰማ መሆን አለብን ስምተን ደግሞ የምንለይ መሆን አለብን ግን ታድያ ድምፁን ሰምቶ ለመልየት እግዚአብሔር ባዶ ልብን ይፈልጋል። ባዶ ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው መጀምሪያ መሰረታዊ ለውጥ ለማድረግ ጥቅም የሚፈልግ ሳይሆን ባዶ ልብ የሆነ ይዘን ወደ ጌታ ፊእት ለመውደቅ እንወስን። ያኔ ጌታ ባል ያዘጋጅልሻል ያኔ ሚስት ይሰጥሃል።
ጌታ ይባርካቹህ
ወንድማቹህ