ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Saturday, 25 September 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

በእርግጥ በዚህ ዘመንም እግዚአብሔር ይፈውሳል?

ሰላም ወገኖች

የእኔ ጥያቄ በዚህ ባለንበት ዘመንም እግዚአብሔር በእርግጥ ይፈውሳል ወይ? በአንዳንድ መንፈሳዊ ስብሰባዎች ላይስ የሚነገረቱን ፈውሶችና መገለጦች እውነተኝነታቸውን እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን? የሚል ነው።
Feb 27, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
እግዚአብሔር ይፈውሳል? በደንብ አድርጎ እግዚአብሔር ይፈውሳል በተለያየ ዘመናት የነበሩ አማኞች እግዚአብሔር ሲፈወሳቸዉ እንድነበር መፃህፈ ቅዱስ ያሳየናል ፈዉስ የልጆች እንጀራ ነዉ ይላል መፃህፍ ቅዱስ እየሱስ ክርስቶስ ትላንተናም ዛሬ እስክ ለዘላለም ያዉ ነዉ ትላንትም ፈወሶዋል ዘሬም ይፈወሳል ነገም ይፈዉሳል
ውድ ወንድሜ! "ፈዉስ የልጆች እንጀራ ነዉ ይላል መፃህፍ ቅዱስ" ላልከው የት ስፍራ እንደተጻፈ ልትግልጽልኝ ትችላለህን?

ጌታ ይባርክህ!
ውድ ወንድሜ! "ፈዉስ የልጆች እንጀራ ነዉ ይላል መፃህፍ ቅዱስ" ላልከው የት ስፍራ እንደተጻፈ ልትግልጽልኝ ትችላለህን?

ውድ ወዳጄ ይህን አባባል እኔም ጥያቄ ሆኖ ያውቃል ሆኖም ግን አንድ እግዚአብሄር ሰው ከዚህ ቃል የተነሳ እንድምንል ነግሮኝ እኔም ተስማምቼያለሁ ነገር ግን ቃል በቃል እንድዚህ የሚል ክፍል የለም።
የማቴዎስ ወንጌል 15
25 እርስዋ ግን መጥታ። ጌታ ሆይ፥ እርዳኝ እያለች ሰገደችለት።
26 እርሱ ግን መልሶ፦ የልጆችን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባም አለ።

በጌታ እህታችሁ ገኒ

1 መልስ

+2 ድምጾች
በብሉይም ይሁን በአዲስ ኪዳን ዘመን እግዚአብሔር ሰዎችን ከበሽታ እንደፈወሰ መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል። በተለይ ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎት ፈውስ ትልቅ ቦታ እንደነበረው መጽሐፍ ቅዱስ ያሳያል። ከኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ በኋላም እግዚአብሔር በክርስቶስ ተከታዮች አማካኝነት ሰዎችን ሲፈውስ በሐዋርያት ሥራ ላይ እናነባለን። ስለዚህ ባጠቃላይ እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በሽታን የሚፈውስ አምላክ ነው።
Quote:
ኦሪት ዘጸአት 15
26 እርሱም፦ አንተ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀህ ብትሰማ፥ በፊቱም የሚበጀውን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና አለ

ምንም እንኳን ዛሬም እግዚአብሔር ቢፈውስም፤ በዚያው መጠን ደግሞ በዚህ ባለንበት ዘመን ብዙ ያልተጣሩና ያልተረጋገጡ ፈውሶች በተለያዩ የእምነት ተከታዮች ስብሰባዎች ላይ ሲነገሩ ይሰማል። ሳይፈወሱ ተፈውሰሃል የተባሉና በኋላ ያዘኑና የተሰበሩ፤ በማያምኑ ዘንድ ምስክርነታቸው የተበላሸ ወዘተ ብዙ ሰዎች አሉ። ከዚህም ጋር በተያያዘ ብዙ ችግሮች በአሁኑ ዘመን ጎልተው እየታዩ ነው። በተለይ ደግሞ በአሁኑ ዘመን ሰዎች ተፈውሰዋል የሚባለው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፉት ለየት ባለ ሁኔታ በአብዛኞቹ ውስጣዊ በሽታዎች ስለሆኑ እውነትነታቸውን ለማረጋገጥ ይከብዳል። በእኛ ግምትም እንደነዚህ ያሉትን ፈውሶች ያለ ሐኪም ማስረጃ ለማረጋገጥ ያስቸግራል እንላለን።

ፈውስንም ይሁን ሌሎች ትንቢቶችና መገለጦችን በተመለከተ፣ የኢየሱስ ተከታዮች ነን የምንል ሁሉ እውነትንና እውነትን ብቻ መውደድ ይኖርብናል እንላለን። ከእውነተኛ ፈውስ ያነሰ፤ እንዲያው በክርስቲያን ስብሰባዎች ላይ በስሜት ብቻ የሚነገር ምስክርነት እግዚአብሔርን የማያስደስትና በመጨረሻም የሰዎችን እምነት የሚጎዳ ነው። ስለዚህ እንደ እኛ አስተያየት ከሆነ፤ በተለይ ውስጣዊ ከሆኑ በሽታዎች ተፈውሻለሁ የሚል ሰው በመድረክ ወጥቶ ከመመስከሩ በፊት፤ የሚከተሉት መስፈርቶችን ቢያሟላ ይመረጣል እንላለን፦
  • በእውነት ተፈወስኩ የሚለው በሽታ ነበረበት ወይ? ለዚህም ከሐኪም የተረጋገጠ ማስረጃ አለው? ይህን የምንለው ብዙ ስዎች በራሳቸው ግምት ያለ ምንም የሐኪም ማስረጃ ጉበት አለበኝ፤ ደም ብዛት አለበኝ ወዘተ ስለሚሉ ነው። ታዲያ እንደዚህ አይነት ሰዎች በአንድ ጉባዬ ላይ በስሜት ተነስተው ከጉበት በሽታ እግዚአብሔር ፈወሰኝ ቢሉ፤ ቀድሞውንም የሌለባቸውን በሽታ እንደተፈወሱ ማቅረብ ሊሆን ይችላል።
  • ከውስጣዊ በሽታ ተፈወስኩ የሚለው ሰው ይህን ፈውሱን ወደ ሐኪም ሄዶ ማረጋገጣና ማስረጃ ይዞ፤ ፈውሱን በማስረጃ ቢያረጋግጥ ይመረጣል። ብዙ ሰዎች በጉባዬ ላይ፣ ከኤድስም እንኳን እንደተፈወሱ ይመሰክራሉ፤ እንደዚህም አይነት መገለጥ የሚናገሩ ሰባኪዎችም አሉ። እግዚአብሔር እንኳን ከኤድስ መፈወስ ይቅርና ከሙታምን የሚያስነሳ አምላክ ነው። ሆኖም እንዲህ ያለውን የውስጥ ሕመም፤ ታማሚውም እንኳን መፈወሱን በእርግጠኛነት ማወቅ አይችልም። በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው የሐኪም ምርመራ ውጤት ሲመጣ ብቻ ነው።
በቤተክርስቲያን የሚነገሩ ትንቢቶችንና መገለጦችን በተመለከተም እንደዚሁ ለዚሁ ጉዳይ በተመደቡ ወገኖች ትንቢቶቹና መገለጦቹ መፈጸማቸውን ወይም አለመፈጸማቸውን ተከታትሎ ማጣራትና ውጤቱን ይፋ ማድረግ ይገባል እንላለን።
Quote:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14
29 ነቢያትም ሁለት ወይም ሦስት ሆነው ይናገሩ ሌሎችም ይለዩአቸው

በዚህ ክፍል "ሌሎችም ይለዩአቸው" ተብሎ የተተረጎመው ቃል፤ ሰዎቹ የሚናገሩትን ሌሎች በጥንቃቄ ይመርምሩ/ይፈትኑ/ይመዝኑ ወይም በእንግዚኛው others should evaluate/weigh carefully/pass judgment what is said ማለት ነው።

እንዲህ አይነቱ ትንቢቶችንና መገለጦችን የማጣራትና ውጤቶችንም ይፋ የማድረግ አሠራር፤ ገለባውን ከፍሬው እንድንለይና፣ እግዚአብሔርን በእውነትና በእውነት ብቻ እንድናከብረው፤ ለዓለም የምንሰጠውም ምስክርነት በፈተና የሚያልፍና የማያሳፍር እንዲሆን ይረዳል። ከዚህ በተጨማሪ፤ አገልጋዮችም ቶሎ እንዲታረሙና ሳያጣሩ ትንቢትን ወይም መገለጥን እንዳይናገሩ ለጥንቃቄ ያግዛል። እውነትና ውሸቱን መመርመርና፣ መተራረም በሐዋርያት ሥራ ላይ ባለች የጥንቷ ቤተክርስቲያንም የተለመደ ተግባር ነው። እንደ ጴጥሮስ ያሉ ዋና ሐዋርያት እንኩዋን ሳይቀሩ ያለ አግባብ ሲሄዱ በሌሎች ይታረሙና ይመረመሩ ነበር። መመርመርንና መተራረምን ከናካቴው አውጥታ የጣለች ቤተክርስቲያን ግን፤ ለብዙ ስህትቶችና ስሜታዊና እውነት ያልሆኑ ፈውሶችና መገለጦች ራሱዋን ማጋለጡዋ አይቀርም።

በመጨረሻም፤ ፈውስ ወይም ተዓምር የእምነትን ወይም የትምህርትን ትክክለኛነት የሚያረጋግጥ እንዳልሆነ መረዳት አለበን። እውነተኛው የእግዚአብሔር መንፈስ መሆኑና አለመሆኑን የምናውቀው፤ መንፈሱ የተሰቀለውን ክርስቶስን ማእከላዊ ያደረገ መልእክትንና ወንጌልን አብሮ ሲያበስርና፤ የመንፈስ ፍሬ በሰዎች ሕይወት ሲታዩ ነው። እነዚህ ሁለቱን፤ ማለትም የተሰቀለውን ኢየሱስን ማወጅ/ማስተማርና የመንፈስን ፍሬ ማፍራት ሰይጣንና ሥጋ ሊሠሩዋቸው የማይችሉት፤ የመንፈስ ቅዱስ ዋና ሥራዎች ናቸውና።
Quote:
1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ
3፥15 ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።

የዮሐንስ ወንጌል
4፥23 ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤
4፥24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።
Feb 27, 2011 በምሕረቱ (1,510 ነጥቦች) የተመለሰ
Feb 27, 2011 በምሕረቱ ታርሟል
ጥያቄው ግልስ ባይሆንም ምን አይንት ፈውስ ያስብላል?
የስጋ፣የመንፈስ፣የነፍስ....ያስጋን ከሆነ ጥያቄው መልሱ አንድ ነው ይሔውም
አዎ ነው.የብዙ ስዎቸ መፈወስ ጥያቄ ቢሆንብህም የአግዚአብሄርን ፈዋሸነት
ከስዎቸ መፈወስ ጋር ፈጽሞ አታያይዝው እሱን በጌታነቱ በአምክነቱ አንዳመንከው ሁሉ ፈዋሸ አምላክ እንደሆነ እመነው.

ተባረከ.
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...