ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 26 May 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

አንድ ሰው ትውልደላችሁ ተብለው እየተበቆ አንዳችው ቢሞቶ ትንቢቶ ትክክል አይደለም ማለት ነው?

Jun 28, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
ሰላም!
በዘመናችን አንዱ ትልቁ ችግር ቤተ ክርስቲያን አለቃና ምንዝር ያላት ድርጅት መሆኗ ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ ትንቢቶችም ሆነ ትምህርቶች ተለምዶና የሰውን ልምምድ መሰረት ወደማድረግ ከገቡ ከራርሟል፡፡ ይህ አሳዛኝ ክስተት ቢሆንም ማንም ግን ሃይ! የሚል የለም፡፡ ለምን ቢባል ከላይ አንድ ወንድም/እህት እንዳሉት ነው- መሪዎቻችን የማይመረመሩ እየሆኑብን መጥተዋል፡፡ መተለይማ ትንቢትን በተመለከተ?! በዚህ ጉዳይ ላይ ጨዋታ ማነሳት በህይወትህ ፈርደህ በእሳት እንደመጫወት ይቆጥሩታል- ቀንህን ትጠብቃለህ ማለት ነው! ቀን የረዝማል እንጂ አህያ የጅብ ናት ያለው ማን ነበር?! እንደዛው ማለት ነው - ምናልባት ቀን ቢረዝምም ውጉዝ መሆንህን መርሳት የለብህም፡፡
በዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን አንድ ማወቅ ያለባት ነገር አለ- ይኸውም ንም መሰላችሁ - ትንቢት ባይኖር እንኳን ቤተ ክርስቲያን መኖር የምትችል የክርስቶስ አካል መሆኗን መገንዘብ አለብን፡፡ ግን ታዲያ ትንቢት አያፈልግም ወይም የለም እንዳላልኩ ልብ በሉልኝ፡፡ ትንቢትን እንመርምር ማለት የመንፈስ ቅዱስ ተቃዋሚ ተደርጎ መቆጠር በተጀመረበት በዚህ ዘመን ቃላቶችን መምረጥ ያስፈልጋል መሰል፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም ከላይ መላሹ እንዳሉት 100 በ100 ማወቅ ያለብን የክርስቲያኖች ህይወት በትኒት ሊመራ ምንም ዓይነት መፅሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት የለውም፡፡ አንድም ስፍራ ላይ በሐዋሪያት ዘመን ነቢያት የሰውን ዕድል እየተናገሩ ያሳለፉበትና መድረኩን በጨው በርበሬ ጉዳይ የተቆጣጠሩበት ጊዜ ተፅፎ አላየንም፡፡ ምናልባት በአዋልድ መፃህፍት ውስጥ ይኖር ይሆን?
ትንቢት ማለት በእዚያብህር ቃል ሰዎችን ወደ እግዚያብህር ሃሳብ ማስገባት ነው እንጂ የቁሳዊ ኑሮ ተስፋ አይደለም

1 መልስ

+1 ድምጽ
Quote:
ኦሪት ዘዳግም
18፥22 ነቢዩ በእግዚአብሔር ስም በተናገረ ጊዜ የተናገረው ነገር ባይሆን ባይመጣም፥ ያ ነገር እግዚአብሔር ያልተናገረው ነው ነቢዩ በድፍረቱ ተናግሮታል እርሱን አትፍራው።

1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች
5፥20-21 ትንቢትን አትናቁ፤ ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ፤

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
14፥29 ነቢያትም ሁለት ወይም ሦስት ሆነው ይናገሩ ሌሎችም ይለዩአቸው (others should evaluate or judge what they said)

መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ያልተናገረውን ትንቢት ለመለየት የሚያስችል አንድ ቀላል መለያ ሰጥቶናል። አንድ ሰው አንድ ትንቢት ተናግሮ ያ ትንቢት ካልተፈጸመ ሌላ ምንም ነግሮችን መንፈሳዊ ማብራሪያና ረቂቅ ለማድረግ መሞከር የለብንም፤ ጉዳዩ አንድና አጭር ነው። ይህም 100 በ100 ይህ ትንቢት ከእግዚአብሔር አልነበረም! በቃ! ትንቢቱን ጋሽ እከሌ ይናገሩት ወይም ፓስተር እከሌ ምንም የሚለውጠው ነገር የለም። ትንቢቱን እግዚአብሔር አልተናገረውም።

እኛ በዚህ ዘመን ያለን ሰዎች እውነተኛና ጥራት ያለው ትንቢት ስለማናውቅና ስላልለመድን ትክክል ያልሆኑትን ትክክል ለማድረግ ብዙ ማብራሪያና መንፈሳዊ ካባ ለማልበስ እንጥራለን። ይህ ደግሞ በቤተክርስቲያን ብዙ የተሳሳቱና እግዚአብሔር ያልተናገራቸው ትንቢቶች እንዲበዙ በር ከፍቶአል።

በአሁኑ ዘመን ከቤተክርስቲያን ጨርሶ እንዲጠፋ ሰይጣን ያደረገውና እጅግም የተሳካለት ነገር ቢኖር መተራረም የሚባል ነገር ነው። ከሐዋርያት ሁሉ ዋነኛ ሐዋርያ የነበረው ጴጥሮስ በእግዚአብሔር ተመርቶ ወደ አህዛብ ማለትም ወደ ቆርኔሊዎስ ቤት መግባቱን አይሁዳዊ ወንድሞች ሲሰሙ ነገሩ ሳይገባቸው የተሳሳተ ስለመሰላቸው ብቻ አፋጠጡት፡ ተከራከሩትም።
Quote:
የሐዋርያት ሥራ 11
1 ሐዋርያትና በይሁዳም የነበሩት ወንድሞች አሕዛብ ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ተቀበሉ ሰሙ።
2 ጴጥሮስም ወደ ኢየሩሳሌም በወጣ ጊዜ ከተገረዙት ወገን የሆኑት ሰዎች ከእርሱ ጋር ተከራክረው።
3 ወዳልተገረዙ ሰዎች ገብተህ ከእነርሱ ጋር በላህ አሉት።
4 ጴጥሮስ ግን ከመጀመሪያው ጀምሮ በተራ ገለጠላቸው እንዲህም አለ፦

ምንም እንኳን ሐዋርያ ቢሆንም፤ ከሐዋርያም ዋናው ሐዋርያ ቢሆንም ወንድሞች የተሳሳተ ስለመሰላቸው ብቻ ጴጥሮስን ማፋጠጥና መጠየቅ እንዲሁም ማረም ይችሉ ነበር። ምክንያቱም ሁላችንም እኩል ወንድሞች ነን የሚል አመለካከት ነበር እንጂ የነበራቸው በእኛ ዘመን እንዳለው እርሳቸው ፓስተር እኔ ደግሞ ምዕመን አፌን ይዤ ዝም ልበል የሚል የበላይና የበታች ግንኙነት አልነበረም የነበራቸው።

ሐዋርያው ጳውሎስም እንዲሁ አንድ ጊዜ ጴጥሮስ እንደ ወንጌል እውነት በቅንንነት እንዳልሄደ አይቶ ፊትለፊት እንደገሰጸው ይናገራል።
Quote:
ወደ ገላትያ ሰዎች 2
11 ነገር ግን ኬፋ (ጴጥሮስ) ወደ አንጾኪያ በመጣ ጊዜ ፊት ለፊት ተቃወምሁት፥ ይፈረድበት ዘንድ ይገባ ነበርና።
12 አንዳንድ ከያዕቆብ ዘንድ ሳይመጡ ከአሕዛብ ጋር አብሮ ይበላ ነበርና፤ በመጡ ጊዜ ግን ከተገረዙት ወገን ያሉትን ፈርቶ ያፈገፍግ ነበርና ከእነርሱ ተለየ።
13 የቀሩትም አይሁድ ደግሞ፥ በርናባስ ስንኳ በግብዝነታቸው እስከ ተሳበ ድረስ፥ ከእርሱ ጋር አብረው ግብዞች ሆኑ።
14 ነገር ግን እንደ ወንጌል እውነት በቅንነት እንዳልሄዱ ባየሁ ጊዜ በሁሉ ፊት ኬፋን። አንተ አይሁዳዊ ሳለህ በአይሁድ ኑሮ ያይደለ በአሕዛብ ኑሮ ብትኖር፥ አሕዛብ በአይሁድ ኑሮ ሊኖሩ እንዴት ግድ አልሃቸው? አልሁት።

ስለዚህ መተራረም እከሌ እከሌ ሳይል በመጀመሪያዪቱ ቤተክርስቲያን የተለመደ ነገር ነበር። ይህም ከብዙ ስህተት ጠብቆአቸዋል።
Quote:
የዮሐንስ ራእይ 2
1 በኤፌሶን ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። በቀኝ እጁ ሰባቱን ከዋክብት የያዘው በሰባቱም የወርቅ መቅረዞች መካከል የሚሄደው እንዲህ ይላል።
2 ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትህንም አውቃለሁ፤ ክፉዎችንም ልትታገሥ እንዳትችል፥ እንዲሁም ሳይሆኑ፦ ሐዋርያት ነን የሚሉቱን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ፤

ሰይጣን በአሁኑ ዘመን መተራረም የሚባል ነገርን በተለይ ከኢትዮጵያውያን አብያተ ክርስቲያናት ፈጽሞ ድራሹ እንዲጠፋ አድርጎአል። ስለዚህም ማንም የፈለገውን ቢያስተምር ወይም የፈለገውን ትንቢት ቢናገር ያንን ትንቢት መዝግቦ ትንቢቱ ተፈጽሞ እንደሆነና መጽሐፍ ቅዱስን የተመረኮዘ እንደሆነ መርምሮ ትንቢቱ ካልተፈጸመ ወይም ስህተት ከሆነ የተናገረውን ሰው የሚያርመው የለም። እንዲያውም ከማረም ይልቅ ዝም ማለት "አትፍረድ ይፈረድብሃል" የሚለው ጥቅስ ያለአግባቡ እየተጠቀሰና አለመተራረምና አፍን መዝጋት መንፈሳዊ እንደሆነ እንዲታይ ተደርጎአል። ይህ በእኔ አመለካከት በጥንቷ ቤተክርስቲያን ያልነበረ አዲስ ክስተት ነው።

አንድ ሰው ትንቢት ተናግሮ ባይፈጸም እርግጠኛ ነኝ አማኞች በጥንቷ ቤተክርስቲያን የተናገረውን ሰው እንደሚያፋጥጡት። እርሱም ተሳስቶ ከሆነ ንስሐ ይገባል አለዚያም ሌላ ምክንያት ካለ ያብራራል። ምንም ልዩ አፍን የመዝጋትና ቤተክርስቲያን ስትበላሽና መረን ስትሆን የማየት መንፈሳዊነት ወይም "ጸጋ" እንደ አሁኑ ዘመን ጥንት አልነበረም።

ስለዚህም በተለይ በኢትዮጵያው ባለቺው ቤተክርስቲያን ዘንድ መረን የለቀቀ የውሸት ትንቢት እጅጉን እንዲበዛና ብዙዎች እምነታቸውንና እግዚአብሔርን ራሱን እንዲጠራጠሩ እስኪሆኑ ድረስ ሆኗል።

አዲስ ኪዳን የሚያዘን ትንቢትን እንድንፈትንና ነብያቶች ትንቢትን ሲናገሩ ሌሎች እንዲለዩአቸው ማለትም እንዲመረምሮአቸው ነው። ለምን ይሄንን ይናገራል አዲስ ኪዳን? ምክንያቱም ትንቢት ባለበት ቦታ ሁሉ የተሳሳተ ትንቢትም ሊኖር ስለሚችል ነው።

እዚህ ላይ በእርግጥ ሁለት ነገሮችን መለየት ይኖርብናል። አንደኛ ሰው ንስሐ እንዲገባ የማስጠንቀቂያ ትንቢቶች እንዳሉ መርሳት የለብንም። ማለትም ልክ እንደ ዮናስ እግዚአብሔር ክፉ እንዲያደርግባቸው ሰዎችን ቢናገርና እነርሱ ግን ንስሐ ቢገቡ ክፉ የተናገረባቸው ትንቢት ሳይፈጸም ሊራራላቸው ይችላል። ነገር ግን ይህ ነገር አንተ ለጠየቅኸው አይሠራም። ምክንያቱም ልጅ መውለድ መልካም ትንቢት እንጂ ማስጠንቀቂያ አይደለም።

በሁለተኛ ደረጃ በጌታ የሚያምን ሰው ትንቢት ተናግሮ ያ ትንቢት ባይፈጸም ያ ሰው ሐሰተኛ ነብይ ነው ማለት ግን አይደለም። ከአፉ ቃል ጠብ የማይለው ታላቁ ነብይ ሳሙኤል እንኳን እግዚአብሔር ለንጉሥነት የመረጠው ቁመና ያለውን የዳዊትን ወንድም ኤልያብን መስሎት ተሳስቶ "በእውነት እግዚአብሔር የሚቀባው በፊቱ ነው" ብሎ ነበር 1ሳሙ 16፡6። ይህ የሳሙኤል መሳሳት ግን ሳሙኤልን ሐሰተኛ ነብይ አያደርገውም። ሐሰተኛ ነብይ ትንቢቱ ይፈጸምም አይፈጸምም ሰዎችን ከክርስቶስና ከወንጌሉ ለማራቅ ባለው ዓላማና በሕይወቱ ፍሬ ነው የሚታወቀው።

ስለዚህ የተናገረው ትንቢት ያልተፈጸመለትና የተሳሳተ ትንቢት የተናገረ ሁሉ ሐሰተኛ ነብይ አይደለም። ሆኖም ግን ከእግዚአብሔር ያልሆነ ትንቢት ሁሉ የሰዎችን እምነትና ሕይወት እጅጉን የሚጎዳና የሚያሰናክልም ሊሆን ስለሚችል ፈጽሞ ፈጽሞ መታረም አለበት። ዝም ተብሎ የሚታለፍ ግን አይደለም። በወንድማማች ፍቅር መተራረም በጣም አስፈላጊ ነው።

በተለይ ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር እየተዘዋወሩ የሚያገለግሉ ሰዎች የትንቢታቸው ውጤትና ፍጻሜ ምን እንደሆነ ሊነገራቸው ይገባል። ይሄ እነርሱ እንዲታረሙና እንዲጠነቀቁ እጅግ ይረዳል። ለቤተክርስቲያን ጥበቃ ደግሞ እንደ እኔ እንደ እኔ በመድረክ አለማውያኖችም ጭምር እየሰሙ የተነገረና ያልተፈጸመ ትንቢት ሁሉ በመድረክ መታረም አለበት እላለሁ። ቢያንስ ቢያንስ ሰዎች ተናጋሪው ተሳሳቶ የተናገረው እንጂ እግዚአብሔር ጋር ችግር እንደሌለ እንዲያውቁና እምነታቸው እንዳይናጋ ይረዳል። እግዚአብሔር የሚጫወትባቸው እቃዎች እንዳልሁኑ ያውቃሉ። በሌላ በኩል ደግሞ መተራረም ባለበት ቤተክርስቲያን፤ ተዘዋዋሪ አገልጋዮችም ይሁኑ እዛው የሚኖሩ፤ ትንቢት ከመናገራቸው በፊት ከእግዚአብሔር መሆኑን በደንብ እንዲያረጋግጡ ይረዳቸዋል። ያለዚያ በግልጽ እንደሚታረሙ ስለሚያውቁ ጉባዬና ፕሮግራም ለማሞቅ ብቻ ዝም ብለው ፈጥነው ትንቢት አይናገሩም። ይሄን የምለው ሳይፈጸሙ የቀሩ ጉባዬ ማሞቂ ትንቢቶች ሰምቼ ስለማውቅ ነው።

በመጨረሻም በአዲስ ኪዳን የክርስቲያኖች ሕይወት በትንቢትና በነብያት እንዲመራ የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም!!! ይሄንን በጣም አጽንቼ መናገር እወዳለሁ! የትም ቦታ በአዲስ ኪዳን ነብያት የሰዎች የኑሮአቸውና የሕይወታቸው መሪዎች አልነበሩም! የነብያቱም አገልግሎት በአዲስ ኪዳን ጨርሶ ይሄ አልነበረም። በአሁኑ ዘመን በተለይ በኢትዮጵያ የሚታየው አይነት ጥንቆላ የሚመስልና ለሆነው ላልሆነው ነገር ሁሉ "ነብያትን" መፈለግ ጨርሶ እንዲህ ያለ ነገር በአዲስ ኪዳን አይገኝም መጽሐፍ ቅዱሳዊም አይደለም። የአዲስ ኪዳን አማኞች ራሳቸው የእግዚአብሔር መንፈስ ማደሪያዎች ናቸውና እንደ ብሉይ ኪዳን በሆነ ባልሆነው ነገር ነብይና ባለ ራእይን ይፈልጉ ዘንድ ፈጽሞ አይገባም። በአዲስ ኪዳንም እንዲህ ያለ "ጥንቆላን" የሚመስል አሠራር የለም። የሰዎች ጌታና የሕይወታቸው መሪ ራስ የተሰቀለው ጌታ ራሱ መሆኑ ቀርቶ "ነብያቶችና" "ባለ መገለጦች" እንዲሆኑ ይህ ጨርሶ ጨርሶ የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም፤ በአዲስ ኪዳንም አንድም ጊዜ አይገኝም።

በአዲስ ኪዲን ነብያት በቅድሚያ ከሐዋርያት ጋር አብረው የወንጌል ሰባኪዎችና አገልጋዮች ናቸው። ከብሉይ ኪዳንም ዘመን ጀምሮም የነብያት ዋና መገለጥ የክርስቶስ የማዳኑ ወንጌል ነው "የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና" ራእይ 19፡10።

ስለ ነብያት የበለጠ ለመረዳት እዚህ በመጫን ማንበብ ይቻላል።

በአዲስ ኪዳን አማኞችን እግዚአብሔር እንዴት እንደሚመራቸው አጭር ማብራሪያ እዚህ በመጫን ማንበብ ይቻላል።

ስለ ፈውስ ደግሞ እዚህ በመጫን ማንበብ ይቻላል።
Quote:
ኦሪት ዘዳግም
18፥22 ነቢዩ በእግዚአብሔር ስም በተናገረ ጊዜ የተናገረው ነገር ባይሆን ባይመጣም፥ ያ ነገር እግዚአብሔር ያልተናገረው ነው ነቢዩ በድፍረቱ ተናግሮታል እርሱን አትፍራው።
Jun 29, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Jun 29, 2011 ታርሟል
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...