ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Thursday, 29 July 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ስለ ሰንበት ወደ እሁድ መቀየር

ስለ አገልጉሎታችሁ ጌታ ይባርካችሁ።
ሰንበት ለምን ወደ እሁድ ተቀየረ ታሪኩና አመጣጡ ወንጌላዊያን አ/ክርስትያን ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላሉ?
Feb 27, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
Feb 27, 2011 ታርሟል

2 መልሶች

+2 ድምጾች
ሰንበት የሚለው ቃል ከእብራይስጡ Shabbat (שַׁבָּת) ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን ቀጥተኛ ትርጉሙም ከድካም ማረፍ ወይም ሥራን ማቆም (to cease or to desist from exertion) ማለት ነው።

ሰንበት እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ለእስራኤል ከሰጠው አሥርቱ ትእዛዛት ውስጥ አንዱ ነው።
Quote:
ኦሪት ዘጸአት 20
8 የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።
9 ስድስት ቀን ሥራ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ
10 ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ ሎሌህም፥ ገረድህም፥ ከብትህም፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ
11 እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንም፥ ያለባቸውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታልም።

የቃሉ ትርጉምና እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ሰንበት ከድካምና ከሥራ ሰዎችና እንስሳት የሚያርፉበት የእረፍት ቀን ነው። በተለይ ከሰንበት ጋር ተያይዞ የተጠቀሱት ሎሌዎች፣ የቤት ሠራተኞች፣ ባሪያዎችና ከብቶች በዚያን ጊዜ እጅግ አድካሚ ሥራ ይሠሩና ይለፉ የነበሩ ናቸው። ሰለዚህ ሰንበት በመጀመሪያ ደረጃ እግዚአብሔር ከሠራው ሥራ በሰባተኛው ቀን እንዳረፈ ሁሉ ከሥራና ከድካም ማረፍ ጋር የተያያዘ ነው። ለዚህ ነው ሰውን ብቻ ሳይሆን የአምልኮ ፕሮግራም ማድረግ የማይችሉትን ከብቶችንም የሰንበት ትእዛዝ የሚያጠቃልለው።

ከዚህ በተጨማሪ ሰንበት በእግዚአብሔርና በእስራኤል ሕዝብ መካከል የተደረገ የምልክት ቃል ኪዳን ነው። እንደማናቸውም የብሉይ ኪዳን ሕግ ሰንበትም በማያከብሩት ላይ መርገምና ፍርድ የሚያመጣም ትእዛዝ ነው።
Quote:
ኦሪት ዘጸአት 31
12 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው።
13 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው። እኔ የምቀድሳችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእኔና በእናንተ ዘንድ ለልጅ ልጃችሁ ምልክት ነውና ሰንበቶቼን ፈጽሞ ጠብቁ።
14 ስለዚህ ለእናንተ ቅዱስ ነውና ሰንበትን ጠብቁ የሚያረክሰውም ሰው ሁሉ ፈጽሞ ይገደል፥ ሥራንም በእርሱ የሠራ ሰው ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ።
15 ስድስት ቀን ሥራን ሥራ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የዕረፍት ሰንበት ነው በሰንበት ቀን የሚሠራ ሁሉ ፈጽሞ ይገደል
16 የእስራኤልም ልጆች ለልጅ ልጃቸው ለዘላለም ቃል ኪዳን በሰንበት ያርፉ ዘንድ ሰንበትን ይጠብቁ።
17 እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን ስለ ፈጠረ፥ በሰባተኛውም ቀን ከሥራው ስላረፈና ስለ ተነፈሰ፥ በእኔና በእስራኤል ልጆች ዘንድ የዘላለም ምልክት ነው

ብዙ ጊዜ ሰንበት ተብሎ በልማድ የሚታወቀው ሥራ የማይሠራበትንና የአምልኮ ፕሮግራሞች የሚካሄዱበትን ቀን ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ግን ሰንበት የሚባለው በእስራኤልና በእግዚአብሔር ብቻ የተገባን ቃል ኪዳን ነው። በዚያ ቀን "የአምልኮ ፕሮግራም የማይካፈል ይሙት" ሳይሆን ትእዛዙ የሚለው "በሰንበት ቀን የሚሠራ ሁሉ ፈጽሞ ይገደል" የሚል ፍርድና ቅጣት ያለው ነው። በብሉይ ኪዳንም ይሁን በአሁኑ ዘመን እስራኤላውያን ሰንበትን የሚጠብቁት ቅዳሜ ነው፡፡

ክርስቲያኖች ሰንበትን ይጠብቁ ዘንድ አልታዘዙም። በእርግጥ እስራኤላዊ ሆነው ወደ ጌታ እምነት የሚመጡ ሰንበትን መጠበቅ ይችላሉ አልተከለከሉም። ነገር ግን ሰንበት ለክርስቲያኖች የተሰጠ ትእዛዝ አይደለም። እስራኤላዊ ባልሆኑ አህዛብ ክርስቲያኖችም ዘንድ በአዲስ ኪዳን ሰንበት ሲጠበቅ ይሁን ሰንበትን እንዲጠብቁ ሲታዘዙ አናነብብም። ይህ ብቻ አይደለም፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያኖች ይጠብቁትና ያከብሩት ዘንድ የተሰጠ ምንም ዓይነት ቀን ወይም በዓል የለም። ክርስትና የቀኖችና የበዓላቶች አክብሮ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ የሆነ ሕይወት ነውና።
Quote:
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2
16 እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ።
17 እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፥ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው።

በአዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች በዚያን ዘመን የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን በሆነው እሁድ እሁድ ይሰበሰቡና ጌታን እያመለኩ የጌታን እራት ይካፈሉ እንደነበር ተጽፎአል፦
Quote:
የሐዋርያት ሥራ
20፥7 ከሳምንቱም በመጀመሪያ ቀን እንጀራ ለመቁረስ ተሰብስበን ሳለን፥ ጳውሎስ በነገው ሊሄድ ስላሰበ ከእነርሱ ጋር ይነጋገር ነበር፥ እስከ መንፈቀ ሌሊትም ነገሩን አስረዘመ።

ይህ የሳምንቱ መጀመሪያ የሆነው እሁድ ቀን ጌታ ኢየሱስ ከሙታን የተነሳበትም ቀን ሰለ ነበር አንዳንዴም የጌታ ቀን ተብሎ ይጠራል፦
Quote:
የሉቃስ ወንጌል 24
1 ነገር ግን ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ያዘጋጁትን ሽቱ ይዘው ከእነርሱም ጋር አንዳንዶቹ ወደ መቃብሩ እጅግ ማልደው መጡ።
2 ድንጋዩንም ከመቃብሩ ተንከባሎ አገኙት፥
3 ገብተውም የጌታን የኢየሱስን ሥጋ አላገኙም።
4 እነርሱም በዚህ ሲያመነቱ፥ እነሆ፥ ሁለት ሰዎች የሚያንጸባርቅ ልብስ ለብሰው ወደ እነርሱ ቀረቡ፤
5 ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ፥ እንዲህ አሉአቸው። ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።

የዮሐንስ ራእይ
1፥10 በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፥ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ትላቅ ድምፅ ሰማሁ፥

አዲስ ኪዳን የሚሰጠው ፍንጭ ክርስቲያኖች ጌታ ኢየሱስ በተነሳበት ቀን እሁድ እግዚአብሔርን እንደሚያመልኩና የጌታን እራት እየቆረሱ ሕብረት እንደሚያደርጉ ያመለክታል። ይሄንን ሲያደርጉ ግን ሰንበትን እያከበሩ አይደለም፡፡ ሰራተኞቻቸውንና ከብቶቻቸውን ወዘተ ቀኑን ሙሉ ከድካማቸው እያሳረፉና ሰው ቢተላለፈው ፍርድ ያለበትን በሕግ የተደነገገውን ሰንበትን እያከበሩ አይደለም።

በአዲስ ኪዳን የቀንና የምግብ እርኩስና ቅዱስ የለም! የምግብና የበዓላት ትእዛዛት ሁሉ በሕግ ውስጥ ካለ የሥርዓት ሸክምና ለጽድቅ የሚደረግ ልፋት ሊያሳርፈንና ወደ እረፍቱ ሊያስገባን የመጣው የክርስቶስ ጥላዎችና ምሳሌዎች ብቻ ናቸው።

የክርስቶስ የሆኑትስ እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ እነርሱም ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብና እርሱን ለማግኘት ከሚደረግ የሥርዓት ጥረትና ድካም እርሱን አግኝተው አርፈዋል። ወደ እግዚአብሔር ሰንበትም ገብተዋል።
Quote:
ወደ ዕብራውያን 4
9 እንግዲያስ የሰንበት ዕረፍት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ቀርቶላቸዋል።
10 ወደ ዕረፍቱ የገባ፥ እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ፥ እርሱ ደግሞ ከሥራው አርፎአልና።

ስለዚህ ክርስቲያኖች ምንም እንኳን ታሪካዊ አመጣጡ ለብዙ የታሪክ ተመራማሪዎችም እንኳን ግልጽ ባልሆነ እሁድ እሁድ የመሰብሰብና እግዚአብሔርን የማምለክ ልምድ ቢኖራቸውም፤ ይሄን ግን እንደ ሰንበት መውሰድ ወይም ይባስ ብሎ ሰንበት ከቅዳሜ ወደ እሁድ እንደተቀየረ ማሰብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የለውም። እሁድ የክርስቲያኖች ሰንበት አይደለም። የብሉይ ኪዳኑን ሰንበትን የመጠበቅ ትእዛዝ ለአዲስ ኪዳን አማኞች አልተሰጠም።

ማንም ግን ሰንበትን ማክበር ቢፈልግ፤ ሰንበት ሕግ ነውና ሕጉ ደግሞ ያለ መርገም አልመጣምና በሰምበት ምንም አይነት ሥራ ቢሠራ ራሱን ከሕግና ከእርግማን በታች እያደረገ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ከሕግና ከእርግማን በታች ሳንሆን ከጸጋ በታች ሆነን በነጻነት እንድንኖር ከሕግ እርግማን ሊያመጣን መጣ እንጂ እንደገና ለሥርዓትና ለበዓላት ባርነት አልጠራንም።
Quote:
ወደ ገላትያ ሰዎች 3
10 ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ በእርግማን በታች ናቸውና፤ በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ ጸንቶ የማይኖር የማያደርግም ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና
11 ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎአልና ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው።
12 ሕግም ከእምነት አይደለም ነገር ግን፤ የሚያደርገው ይኖርበታል ተብሎአል።
13 በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን
Feb 27, 2011 iyesus (7,430 ነጥቦች) የተመለሰ
Feb 27, 2011 iyesus ታርሟል
ሰንበት ቅዳሜ ነው ማቴዎስ 5፤18ን ስናነብ 'እኔ ህግንና ነብያትን ልሽር አልመጣሁም' ይላል ሰንበት ደግሞ ከህግጋቱ አንዱ ነው። ወገኖች አትሳቱ የእሁድ ሰንበትነት መጽሃፍ ቅዱሳዊ አይደለም ነገር ግን የሮም ቤ/ያን እንደለወጠች 'ዘ ኮንቨርትስ ካቴኪዝም ኦፍ ካቶሊክ ዶክትሪን''ገጽ 50ን ያንብቡ። መጽሃፍ ቅዱስ ደግሞ አንዴም እሁድ ሰንበት ነው አይልም። ይልቅ እየሱስ በሰንበት ቀን ቤተ መቅደስ ይገባ ነበር።ሉቃስ 4፤16 ሃዋርያትም የዚሁ ዓይነት ልምድ ነበራቸው የኝኣ ልምድስ?
0 ድምጾች
ሰላም የክርስቶስ ሰላም የብዛልችሁ።
ሰንበት ማልት ሰባተኛ ቀን ሰሆን፣ አምላካቸን ያረፋበት ቀን የቱ እንደሆነ አይታወቅም፤
ግን አይሁዶችህ ቀን መቁተር ሲጀመሩ ቅዳሜን 7ቀን ሆናል፤ መሆን ያለብት ከሰባት አንዱ ቀን ነው በእርግጥ የቱ ቀን እንደ ሆነ ስለ ማይታወቅ፤ በ አድስ ኪዳን 1/7 እሁድ የሆነበት ምክንያት ጌታችን እየሱስ ሞትን ድል የነሳበት የ "ትንሳኤ" ዉ ቀን ለማክበር ነው። የህን በማደረግ አሁንም ሰንበት እየተጠበቀ ነው። ከተሳሳትሁ አርሙኝ፡፡
አመሰግናለሁ።
Mar 3, 2011 YaelD (8,160 ነጥቦች) የተመለሰ
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...